``ዮሐንስ መደብር``
ከኢትዮጵያ ተሰርቆ ወደ ውጪ ሀገር ተወስዶ ከሊቃውንት ዐይን ለዘመናት ተደብቆ የቈየው፥ የነቅዩስ ጳጳስ በነበረው ቅዱስ ዮሐንስ በዓረብኛ ቋንቋ የተደረሰው፥ ድንቅ መንፈሳዊ የታሪክ፣ የምርምር፣ የጥበብ፣ የፍልስፍና መጽሐፍ የሆነው ``ዮሐንስ መደብር`` የተሰኘው መጽሐፍ በሚደንቅ የአተረጓጐም ስልት ተተርጒሞ፥ ለአንባብያን እንዲመች ተደርጎ፥ ጎን ለጎን በግእዝና በአማርኛ ሆኖ ተጽፎ የሕትመት ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
ይህ ``ዮሐንስ መደብር`` የተሰኘው የነቅዩስ ጳጳስ የዮሐንስ መጽሐፍ ዐረብኛንና ግእዝን አቀላጥፎ ይችል በነበረው፥ ዲያቆን ቅብርያል በሚባል ግብጻዊ ዲያቆን በ16ኛው መ.ክ.ዘ የሰራዊት አለቃ በነበረው አትናቴዎስና በእቴጌ ማርያም-ሥና ትእዛዝ በ፲፭፻፺፬ (1594) ዓ.ም በዐፄ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት ከልሳነ ዐረቢ ወደ ልሳነ ግእዝ ተተርጕሟል። ተሰርቆ ወደ ውጪ ሀገር እስከ ተወሰደበት ዘመን ድረስም ብዙ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ይማሩበትና ያስተምሩበት የነበረ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የተለያዩ ሀገራት ሐያልነትን ከመተረክ አልፎ የሐበሾች/ኢትዮጵያውያን አኵሪ የጀግንነት ታሪክን በሰፊው የሚያትት ድንቅ መጽሐፍ ነው።
የ``ዮሐንስ መደብር`` ይዘት በጥቂቱ፦
●በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው ያልተሟሉትን አሟልቶ ይዟል።
●ከአዳም ጀምሮ እስከ እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ያለው፥ ለ6200 ዓመታት የዘለቀው፥ የስድስት ሺህ ዓመታት ታሪክን አጠቃሎ ይዟል።
●በዓለም ላይ የነገሡት የተለያዩ ሀገራት ኀያላን ነገሥታት ሙሉ ታሪካቸውን ይተርካል።
●በዓለም ላይ የተነሡትን መናፍቃን ታሪካቸውንና ምንፍቅናቸውን ተርኮ መልስ ይሰጣል።
●ከአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ እስከ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ የተነሡትን ቅዱሳን ሊቃውንትን በመዘርዘር ሙሉ ታሪካቸውን ያስቀምጣል።
የዮሐንስ መደብር ጥቅሙ፦
●የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀትዎን ሙሉ ያደርጋል።
●ዓለም ዐቀፍ ታሪክን እንዲያውቁ ያደርጋል።
●መናፍቃን ለሚያነሧቸው የምንፍቅና ትምህርቶች መልሳቸውን እንዲያውቁ ያስችላል።
●የእግዚአብሔር ሀልዎትና መግቦት፣ አንድነትና ሦስትነት፥ በጥቅሉ ምሥጢረ ሥላሴን በጕልህ እንዲያውቁ ይረዳል።
●ነገረ ማርያም፣ ነገረ ቅዱሳንንና ነገረ መስቀልን በአግባቡ እንዲገነዘቡ ያደርጋል።
●የኢትዮጵያ ጥንታዊ ዓለም ዓቀፋዊ መሪነትንና ኀያልነትን እንዲያውቁ ያደርጋል።
●የተለያዩ ነገድ አሰፋፈርና አቀማመጥን ለይተው እንዲያውቁ ያግዛል።
●ስለ ሥነ ፈለክ፣ ስለ ዑደተ ፀሓይ ወወርሕ፣ ስለ ምሕዋረ ከዋክብትና ስለ ዐበይት አፍላጋት... ሰፊ ዕውቀትን ያስጨብጣል።
●የግእዝ ቋንቋ ክህሎትዎን ያዳብራል።
የመጽሐፉ ተርጓሚና አሳታሚ፦
መጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ
በድሬዳዋ ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የቅኔና የመጽሐፍ ትርጓሜ መምህር፥ የድሬዳዋ ሊቃውንት ጉባኤ ዋና ጸሓፊ
👇ለሚያደርጉልኝ ድጋፍ ከወዲሁ ልባዊ መንፈሳዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ መጽሐፉ ታትሞ ገበያ ላይ እንዲውል እስፖንሰር ለመሆንና ለማገዝ፥ አልያም ቀድሞ ተመዝግቦ መጽሐፉን ለመግዛት የሚከተለውን ሊንክ ጠቅ አድርገው ቢገቡ ያገኙናል።👇
https://t.me/yohanis_medebir