ነገ ሰኔ 14 - የፀሀይ ግርዶሽ‼️⬇️
ውድ የ ቻናል ቤተሰቦች
ሠኔ 14 ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽን ልናይ በጣም ጥቂት ሰአቶች ቀርተውናል። ግርዶሹ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል እንደየቦታው ከ60% እስከ 80% ፀሐይ በጨረቃ ተሸፍና ከፊል ግርዶሹን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአማካይ ከጠዋቱ [12:50-3:15 ]ድረስ በኢትዮጵያ የሚታይ ይሆናል።
-በተለይ የግርዶሹ ዋናው መስመር የሚያቋርጥባቸው 97% ፀሐይ ተሸፍና የእሳት ቀለበት ሠርታ በብቸኝነት የሚያይዋት እድለኞች የሀገሪቱ ቦታዎች ውስጥ፦ ቶንጎ፣ ቦምባሲ፣ መንዲ፣ እንጅባራ፣ ግሽዐባይ፣ ጢስዐባይ፣ ሞጣ፣ ጋይንት፣ ዳሞት፣ ቡሬ፣ አገው፣ ግምጃ ቤት፣ ንፋስ መውጫ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ላሊበላ ይጠቀሳሉ።
-በተለይ 97% በሙሉ ፀሐይ በጨረቃ ተሸፍና አብረቅራቂ እሳታማ ቀለበት “ring of fire” ሠርታ በነዚያ አስደናቂ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በላይ በሰማይ ከጠዋቱ 1:59 ላይ ከመታየቷ በተጨማሪ ፕላኔት ሜርኩሪና ቬነስም አብርተው በቀን ጠዋት ላይ ይታያሉ። ይልቁኑ የግርዶሹ መስመር ንጉሥ ላሊበላ የሠራውን የፈለገ ዮርዳኖስን መስመር በቀጥታ አቋርጦ ማለፉ የላሊበላውን በተለይ አጓጊና አስደማሚ ያደርገዋል።
‼️ማሳሰቢያ፦ ፀሐይ በጊዜው የምትረጨው ጨረር ዐይናችሁን ሊያሳውርና eclipse blindness ስለሚያስከትልባችሁ eclipse viewer ከሌላችሁ ወደ ሰማይ ፀሐይን ለማየት እንዳትሞክሩ። ክስተቱን በጊዜው በቪዲዮ የምትቀርጹ ጋዜጠኞችም የካሜራችሁ ሌንስ እንዳይቃጠል ካሜራችሁ ላይ solar filter ተጠቀሙ።
መረጃውን ለሌሎች ሼር ሼር ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ።
@OFFICAL_HEAVINA