ለአ.አ.ሣ.ቴ.ዩ ማህበረሰብ በሙሉ
የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ዩኒቨርሲቲያችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ በበጎ አድራጎት እና ሙያዊ ስራዎች ዘርፍ የተለያዩ እንቀስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት በበጎ አድራጎት ዙሪያ እየተከናወኑ ከሚገኙት ስራዎች አንዱ በአገራችን የተከሰተውን የደም እጥረት ደም በመለገስ መርዳት ነው፡፡ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማይተላለፍ መልኩ ለማከናወን ይቻል ዘንድ ስራው የተሰጠው ኮሚቴ በኢትዮጵያ የደም ባንክ ድረ-ገፅ በመመዝገብ ሰራተኞቻችን በሚኖሩበት ቦታ ሆነው ደም እንዲለግሱ ታስቧል፡፡
ስለዚህ በመመዝገቢያው የድረ-ገፅ አድራሻ፤
https://bloodbank.moh.gov.et/#/በመመዝገብ የግል ዳታችሁን ከሞላችሁ በኋላ ልገሳውን የምትሰጡበትን ቦታ በመምረጥ ደም እንድትለግሱ በትህትና እየጠየቅን የደም ልገሳውን ተግባር ካከናወናችሁ በኋላ ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ሙሉ ስማችሁንና ደም የለገሳችሁበትን የቦታ አድራሻ እንድታሳውቁን እንጠይቃለን፡፡
1. ዶ/ር አስራት ሙላቱ (+251911538342) Email: asrat.mulatu@aastu.edu.et
2. ዶ/ር ተረፈ ጌታቸው (+251983915354) Email: terefe.getachew@aastu.edu.et
የእኔ በጤና መኖር ለሁላችንም በጤና መኖር ጉልህ ሚና አለው!
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ