. 💗▬▬ஜ۩ገምሃልያ۩ஜ▬▬💗
💘አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ💘
▬====🧣ተከታታይ ታሪክ🧣====▬
#ክፍል_7
...🖊ሁሉም ሰው ወጥቶ ቤተክርስቲያኑ ፀጥ ካለ በኃላ እኔና ታዲ ማውራት ጀመርን። በምን እንደተነሳ ትዝ ባይለኝም ብቻ በመሃል እድሜዬን ጠየቀኝ ከወር በኃላ 22 አመቴን እንደምይዝ ነገርኩትና የሱንም እድሜ ጠየቅኩት እሱም 29 አመት እንደሞላው ነገረኝ፡ ድንገት ፍቅረኛ አለህ አልኩት ዞር ብሎ አየኝና ምን ያረግልሻል ብሎ ጠየቀኝ አይ እንዲው ለማወቅ ነው አልኩት ምንም አያደርግልሽም እሱን ማወቅ አለኝ ተናደድኩ ማንም ወንድ እንዲ ተንጠባርሮብኝ አያውቅም በጣም ሲበዛ ኩራተኛ ነው እልህ አስያዘኝ እኔማ ካላዝረከረኩት ፅናት አይደለሁም ብዬ በልቤ ዛትኩ። ቆይ ምን ችግር አለው ብትነግረኝ ምን ከባድ ነገር አይደል የጠየቅኩህ አልኩት ቆጣ ብዬ፡፡ ፅናት! አለኝ ጠንከር ባለ አነጋገር ምንም አያደርግልሽም አልኩሽ አይደል ሲነገርሽ ስሚ ችክ አትበይ አለኝ ይበልጥ አበሳጨኝ ግን ምንም አማራጭ ስላልነበረኝ ዝም አልኩት እሱም ትንሽ ሲያሰላስል ከቆየ በኃላ አየሽ ፅናት አንቺ ገና ልጅነት አለብሽ አሁን ባወራናቸው ጥቂት ወሬዎች ውስጥ እንኳን ማየት እንደቻልኩት ለነገሮች መቸኮል እምትወጅ ይመስለኛል ሁሉም ነገር አንቺ በምትፈልጊው መንገድ እንዲሄድ ትፈልጊያለሽ ህይወት ግን እንደዛ አይደለችም ህይወት ትመራሻለች እንጂ አንቺ አትመሪያትም ወዲያው ጠይቀሽ ወዲያው መልስ እንዲሰጥሽ ትፈልጊያለህ ከተዋወቅሽው 24 ሰአት እንኳን ያልሞላሽን ሰው ስለፍቅር ታሪኩ መጠየቅ ለኔ አግባብ ነው ብዬ አላስብም ሁሉም ነገር በትክክለኛው ግዜ እና ባታ እንደሚሆን አምናለው። ትክክል የሆነ ነገር እንኳን አለግዜውና ቦታው ትክክል አይደለም አንዳንዴ ተረጋግተን ማሰብ ይኖርብናል በችኮላ እሚደረጉ ነገሮች ብዥታ ይበዛባቸዋል ምንነታቸውን ሳናውቅ እናልፋቸዋለን ነገር ግን ረጋ ማለት ስንጀምር ሁሉም ነገር ጥርት ብሎ ይታየናል አንቺም ረጋ ማለትን ልመጅ አለኝ። በርግጥ ውስጤ ያለውን ነገር ነበር የነገረኝ ሁሌም ለነገሮች እንደምቸኩል አስባለው እውነቱን ስለነገረኝ ግን መናደድ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላወቅኩም እሺ አመሰግናለው ብቻ ብዬው ዝም አልኩ ዛሬ እንደምወደው ልነግረው እያሰብኩ ነበር ግን አሁን ከነገረኝ ነገር ጋር ፈፅሞ የማይሄደ ነገር እንደሆነገባኝ አይደለም ለዚ ለተራ ጥያቄ እንኳን ትክክለኛውን ግዜ ጠብቂ የሚል አይነት ሰው ሆነብኝ።
ምን እንደማወራው ግራ ቢገባኝ ዝም ብዬው ተቀመጥኩ እሱም አያወራም ዝም... ለረጅም ግዜ ዝም ተባብለን ከተቀመጥን በኃላ ደስስስ...! አይልም አለኝ ከልቡ ደስ እንዳለው ያሳብቅበታል ምን ደስ እንዳለው ግን ስላልገባኝ ምኑ ብዬ ጠየቅኩት። ይበልጥ እየተደሰተ ፀጥታው!፣ ሰላሙ!፣ ዝምታው ደስ አይልም አለኝ። በልቤ እኔ አንተን ላገኝ ብዬ በሌሊት ተሯሩጬ መጥቼ ዝምታው ደስ አይልም ትለኛለህ እንዴ አልኩ ለይስሙላህ ፈገግ እያልኩ እእእ አው ደስ ይላል ሰላም አለው አልኩት ውስጤ እየተቃጠለ ስለሱ ለማወቅ በጣርኩ ቁጥር ይበልጥ የሚሸሸኝ መስሎ ተሰማኝ የውስጡን ለማንም የማያሳይ ድፍን የሆነ ልብ ያለው ድብቅ ሰው መሆኑ ይበልጥ ምን አይነት ሰው እንደሆነ ለማወቅ አጓጓኝ ምንም የማይጨበጥ ነበልባል ሆነብኝ። ታድኤል ምን አይነት ሰው ነው ብለህ ታስባለህ ብዬ ጠየቅኩት ዳግም ዝምታውን ለመስበር። የሰው ባህሪይ የሚታይ እንጂ የሚነገር አይደለም ብሎ መለሰልኝ እንዴት? ብዬ ደግሜ ጠየቅኩት። የአንድ ሰው ማንነት እንደየሰዉ አተረጓጎም ይለያያል ለምሳሌ እኔ አንቺን የማይበት መንገድና ሌላ ሰው አንቺን የሚያይበት መንገድ ፈፅሞ ይለያያል... እሚያወራውን ሳላስጨርሰው እኔን እንዴት ነው እምታየኝ ብዬ ጠየቅኩት። አላውቅም ግን ገና ያልበሰልሽ ችኩል ህፃን ልጅ ትመስይኛለሽ አለኝ ፊቴ ወዲያው ተቀያየረ እኔ እሱን ወድጄው እንደሞኝ ብሆን ጭራሽ ህፃን አደረገኝ። ተናደድኩና አኩርፌሃለው እንዳታናግረኝ አልኩት እንደህፃን ከንፈሬን እየዘረገፍኩ። ምንም አላለኝም ዝም አለ።
የተወሰኑ ደቂቃዎች በዝምታ ታለፋ ከአሁን አሁን ይቅርታ ይለኛል ብዬ ስጠብቅ እሱ ግን ዝም ብሎ ዛፎቹን እያየ ይመሰጣል አልፎ አልፎ ዞር ብሎ ፈገግ እያለ ያየኝና ይመለሳል ይበልጥ አበሸቀኝ ይቅርታ እንኳን አትለኝም! ብዬ ተቆጣሁት። እንዴ እንዳታናግረኝ ብለሽኝ አልነበር አሁን አለኝ እሺ ይኀው አናግረኝ ይቅርታ በለኝ አልኩት ውስጤ እያረረ እንደመለሳለስ እያለ እሺ ይቅርታ እኔ አንቺን ህፃን ልልሽ ፈልጌ አይደለም ግን አንዳንዴ እምታደርጊያቸው ነገሮች ብስለት ይጎላቸዋል ለዛ ነው እንደዛ ያልኩሽ ካሳዘንኩሽ ይቅርታ! አለኝ። ልቤ ራራለት እሺ ከዚህ በኃላ እንደዛ እንዳትለኝ እኔም በሳል ሆኜ አሳይሃለው አልኩት ተስማማን። እጁ ላይ በነጠላ የተሸፈነውን ወርቃማ ሰአት ገለጥ አድርጎ እያየው ሰአቱ ሄደ እንሂድ መሰለኝ አለኝ። በናትህ ትንሽ እንቆይና እንሄዳለን አልኩት የምንለያይበት ሰአት መድረሱ እያስከፋኝ። አይ ዛሬ ምሳ ሰአት ግብዣ ስላለብኝ እንነሳ 05፡00 ሰአት ሆኗል አለኝ። ውስጤ ተቃጠለ ማነች ምሳ እምትጋብዘው በጣም ተብሰለሰልኩ። ማነች እምትጋብዝህ አልኩት ሳቅ እያለ ሴት መሆኗን በምን አወቅሽ አለኝ አይ በእሁድ እለት ምሳ ብዙ ግዜ ከፍቅረኛ ጋር ስለሆነ ብዬ ነው አልኩት ከት ብሎ እየሳቀ እሁድ የቤተሰብ ቀን ነው ቤተሰቦቼ ጋር ነው እምጋበዘው አለኝ። ውስጤ ደስ አለው ፍቅረኛ ይኑረው አይኑረው ባላውቅም ቢያንስ የዛሬ ግብዣው ከቤተሰቡ ጋር እንደሆነ አውቂያለው። ብቻህን ነው ምትኖረው ማለት ነው እነሱን ለማየት እምትሄደው አልኩት። ሳቁ ያደከመው ይመስል በረጅሙ እየተነፈሰ አው ብቻዬን ነው ምኖረው ሜክሲኮ አከባቢ አለኝና አረ በቃ እንነሳ ባይሆን ሌላ ግዜ ተገናኝተን እንጨዋወታለን አሁን እንሂድ አለኝ ተነስቶ እጁን እየዘረጋልኝ እኔም እሺ አልኩና የዘረጋልኝ እጁን ጨብጬ ስቤው ተነሳው። ፈጠን ፈጠን እያልን ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ከወጣን በኃላ መንገዳችን ለየቅል ስለነበር መሰነባበት ጀመርን። ዛሬ ስላገኘሁህ በጣም ደስ ብሎኛል አልኩት እኔም ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል አለኝ ቻው ልንባባል ስንተቃቀፍ አንገቴ ስር ሳመኝ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ በቃ አትጥፋ እሺ ደውልልኝ ሲመችህ እንገናኛለን አልኩትና ዞርኩ እሱም እሺ ደውላለው አንቺም አትጥፊ ደውይ አለኝ ጀርባዬን እንደሰጠሁት እሺ አልኩትና በፍጥነት መራመድ ጀመርኩ እንደጅል ሰው ጥርሴ ዝም ብሎ ይገለፍጣል ታዲ አንገቴን የሳመኝን ቦታ በእጄ ዳበስኩት ይበልጥ ስወደው ይበልጥ ፍቅሩ በልቢ ሲስፋፋ ተሰማኝ። እየሄድኩ አረ...አምላኬ እንደው ምን እዳ ውስጥ ነው የከተትከኝ አልኩ እስከዛሬ ድረስ ለማንም ወንድ እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም...
#ይቀጥላል...
❥..................🍃⚘🍃...................❥
🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣🌹,,,,,
••●◉Join us
ለመቀላቀል 👉
@princabeni