የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ለዓለም ፍጻሜ እየተዘጋጁ መሆኑ ተገለጸ።
120 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ያላቸው አሜሪካዊ፥ በሀዋይ ደሴት ውስጥ በክፉ ቀን የሚጠለሉባቸው ቅንጡ ቤቶችን በመገንባት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።
መጠለያው ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦች ይመረትበታል፤ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ የውሃ ዋና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችንም ያሟላል ተብሏል።
የክፉ ጊዜ መጠለያው 30 መኝታ ቤቶችና 30 መታጠቢያ ቤቶች ይኖሩታል የተባለ ሲሆን፥ ህንጻዎቹን እርስ በርስ የሚያስተሳስሩ ተገጣጣሚ ድልድዮች ይኖሩታል።