የመጽሐፍት ማዕድ /menu books 📚


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣቹ ዩቲብ ቻናላችን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 👉👉👉 https://youtu.be/Jl8O2VzYRJM
👉👉👉👉👉 https://youtu.be/MXnbplyjW2Y

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን በሀገር ዉስጥም በዉጭ ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጲያዊያን በሙሉ በዓሉ የሠላም የጤና ይሁንላችሁ።


ጅብ እና ተኩላ ቀበሮን ማስገደል ስለፈለጉ ለአንበሳ ሄደው 'ቀበሮ እኮ አሪፍ ጫማ መስራት ትችላለች። እርሰዎ እንዲህ በባዶ እግርዎ እየሄዱ እንዴት ዝም ትላለች?' ብለው አሳበቁ።
አንበሳም ተናዶ ቀበሮን ማፈላለግ ጀመረ። በመጨረሻም ተገኘችና አንበሳ ፊት ቀረበች።

አንበሳም ' እንዲህ በባዶ እግሬ ስሄድ እያየሺ ጫማ መስራት እየቻልሺ ለምን ዝም አልሺ?' በማለት አፋጠጣት።

ቀበሮም 'መስራትስ እችል ነበር ነገር ግን ጥሬ እቃው አይገኝም ብዬ ነው' ስትል መለሰች።

አንበሳም 'ለመሆኑ ጥሬ እቃው ከየት ነው የሚገኘው?' በማለት ጠየቃት። ቀበሮም ከጅብ ቆዳና ከተኩላ ጅማት ስትል መለሰች።

አንዳንድ በደለኞች የበደላቸውን ልክ አያውቁትም። ግፍ የትም ቢሆን ተከትሎህ ይመጣል ከሞት በኋላም።

'የተንኮል ጉድጓድ ስትቆፍር አታርቀው ምክንያቱም ቀድሞ ማን እንደሚገባበት አታውቅም!?'





#መፅሐፍት #የመጻሕፍትማ #መልዕክት #ቤተመፅሐፍት


ከእለታት በአንዱ ቀን የተወሰኑ እንቁራሪቶች ተሰባስው ለምን ተራራ የመውጣት ውድድር አናደርግም በማለት ይወያያሉ ።

በዚህም ሀሳብ ተስማምተው ቀጠሮ ይዘው ይለያያሉ ።

በቀጠሮው ቀን ተገናኝተው ተራራውን የመውጣት ውድድር ይጀመራል። ቢሆንም የተራራው ግርጌ ሆነው የሚመለከቱት ሌሎች እንቁራሪቶች ተራራውን የሚወጡትን አረ ይቅርባችሁ የማይሆን ነገር አትሞክሩ ፤ ሞኞች ፤ አረ ይሄ ለእናንተ አይሆንም ፤ እንቁራሪት ከመቼ ወዲህ ተራራ መውጣት ጀመረች እያሉ ሲያሾፉባቸውና ሲተቿቸው ብዙዎቹ ሞራላቸው እየተነካ ወደ ኋላ አፈገፈጉ ግማሾቹም የትም ሳይደርሱ ተመለሱ ።

ከነሱ መሀል ግን አንዲት እንቁራሪት ተራራውን ወጥታ ጨረሰች። ሁሉም ተገርመው ነገሩን ሲያጣሩ እንቁራሪቷ ደንቆሮ ነበረች ።

ምንም ነገር ስናደርግ ሰዎች ሊተቹን ይችላሉ። አትችሉም ብለው ደካማ ሊያደርጉን ይሞክራሉ ነገር ግን ጆሮአችንን አንስጣቸው።

ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር ለመስራት ስንነሳ እንቅፋት አያጣንም ። ቢሆንም ተስፋ አንቁረጥ የመልካም ስራ መንገዱ ረጅም ነው። እንቅፋት አያጣውም እና እንታገስ። #ሼር




#መፅሐፍት #የመጻሕፍትማ #መልዕክት #ቤተመፅሐፍት


## Déjà vu: አወዛጋቢው ስሜት

# ክፍል ሁለት: ፍልስፍናዊ እይታ

ሳይንስ አንዳንድ ተጨባጭ ማብራሪያዎችን ሲያቀርብ፣ ፈላስፋዎች ስለ déjà vu ይበልጥ ጥልቅ እና ሚስጥራዊ በሆኑት ጉዳዮች ለረጅም ጊዜ ሲደነቁ ቆይተዋል።

✓ Déjà vu ስለ ጊዜ ተፈጥሮ ጥያቄዎችን ያስነሳል። በአሁኑ ጊዜ ላይ ቆመን ያለፈው ጊዜ ስሜት ከተሰማን፤ ይህ እኛ እንደምናስበው ጊዜ ወደፊት ብቻ የሚጓዝ መስመራዊ ተፈጥሮ እንደሌለው ይጠቁማል ተብሎ ይታመናል። አንዳንድ ፈላስፎች déjà vu በበርካታ ልኬቶች ከአንድ በላይ የሆኑ እውነታዎች(Alternative Realities) ወይም የጊዜ አዙሪት(Cyclic Time) እንዳለ ሊጠቁም እንደሚችል ገምተዋል።

✓ Déjà vu የአመለካከት ግንዛቤያችንንም ይፈታተናል። ልምዶቻችንን እንዴት እንደምንተረጉም déjà vu ምን ይነግረናል? የምናየው፣ የምንሰማው፣ የምናስታውሰው ሙሉ እና ትክክለኛ የእውነታ ነጸብራቅ ነው? የራሳችንን ልምድ እና የንቃተ ህሊና ተፈጥሮን እንድንጠራጠር የሚያደርግ ክስተት ነው።

✓ አንዳንዶች déjà vuን ጠለቅ ያለ ግንኙነት ምልክት አድርገውም ይመለከቱታል። ይህም እኛ በተለምዶ ከምናውቀው የበለጠ ትልቅ እና ሚስጥራዊ የሆነ ነገር አካል ልንሆን እንደምንችል ረቂቅ ፍንጭ ነው። በቀላሉ ልንረዳው ከምንችለው በላይ የሆነ እውነታ ሊኖር እንደሚችል እና ከዛ ሚስጥራዊ እውነታ ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ሊኖረን እንደሚችል እንድናሰላስል የሚያደርገን ልምድ ነው።

• ታላላቅ ፈላስፎች ስለ Déjà vu ምን ይላሉ?

የ déjà vu ቀጥተኛ ማጣቀሻዎች በብዙ አንጋፋ ፈላስፋዎች ስራ ውስጥ ባይገኝም፣ መሠረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦቹን የሚነኩት እነሆ፡

✓ ፕላቶ፡ የእሱ የቅጾች ፅንሰ-ሀሳብ(Concept of Forms) 'አሁን ያለን ልምዶቻችን በተወሰነ መልኩ ፍጹም ከሆነ ሃይል ጋር የተቆራኙ ናቸው' ከሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ጋር Déjà vu ቁርኝት አለው። ይህም déjà vu ያለፈውን ነገር የማወቅ እንግዳ ስሜት ሊሰጠን ይችላል ከሚለው ፅንሰ-ሀሳብ ጋር ነው፤ ምንም እንኳን ያ ትውስታ ተፈጥሮ የማያውቅ ቢሆንም።

✓ ሄንሪ በርግሰን፡- እኚህ ፈረንሳዊ ፈላስፋ ስለ ጊዜ እና የማስታወስ ባህሪ በሰፊው ያብራሩ ሲሆን ፍልስፍናቸው በ déjà vu ውስጥ ከምናገኘው ነገር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ያለፈውን እና የአሁንን መስተጋብር አጉልቶ ያሳያል።

በማጠቃለያው

Déjà vu ሳይንስ እና ፍልስፍናን የሚያገናኝ አስደናቂ ክስተት ነው። ሳይንስ በአንጎል አሠራሮች ውስጥ ማብራሪያዎችን ሲፈልግ፣ ፍልስፍና በጊዜ፣ በእውነታ፣ በምናገኘው ግንዛቤ ላይ የዚህን ተሞክሮ አንድምታ እንድናጤነው ይሞግተናል። የ Déjà vu አወዛጋቢ ስሜት ተመርምሮ እና ተጠንቶ ያላለቀ በመሆኑ አሁንም ለተለያዩ ማብራሪያዎች ክፍት ነው።

ይህ አስገራሚ ተፈጥሮ በእያንዳንዳችን ውስጥ የሚገኝ ነውና ለፈላስፎች እና ሳይንቲስቶች የሚተው ነገር አይደለም። ሁላችንም የራሳችንን ማብራሪያ እንፈልግ፣ እንጠይቅ፣ እንመርምር...

~ Déjà vu: አወዛጋቢው ስሜት




#መፅሐፍት #የመጻሕፍትማ #መልዕክት #ቤተመፅሐፍት


## Déjà vu፡ አወዛጋቢው ስሜት በቀዳማዊ

# ክፍል አንድ: ሳይንሳዊ ማብራሪያ

ያ የተለመደ አወዛጋቢ ስሜት; "እዚህ ቦታ ነበርኩ፣ ይህንን አድርጌው አውቃለሁ"ብላችሁ እንድታስቡ የሚያደርጋችሁ ስሜት–ምንም እንኳን እዛ ቦታ ላይ ቀድሞ እንዳልነበራችሁ እና ሁኔታውንም አልፋችሁበት እንደማታውቁ ብታውቁም–ያ ስሜት déjà vu ነው። የተለመደ ተሞክሮ ነው፤ ነገር ግን ከአእምሯችን በጣም ግራ የሚያጋቡ ነገሮች አንዱ ሆኖ ቆይቷል። ይህ ስሜት የአዕምሮ ሽወዳ ብቻ ነው ወይስ ሌላ ሊሆን ይችላል? በዚህ ክፍል የ déjà vu ን ሳይንሳዊ ትንታኔ በአጭሩ እንዳስሳለን።

ከስርወ ቃሉ ስንነሳ "Déjà vu" የፈረንሳይኛ ቋንቋ ቃል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጓሜውም 'አስቀድሞ ታይቷል' ወይም 'ታይቶ የሚያውቅ' ማለት ነው። ከሳይንስ አንፃር déjà vu በአጠቃላይ እንደ የተሳሳተ ትውስታ ክስተት ይቆጠራል።

✓ ከዋናዎቹ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎች አንዱ; déjà vu የሚከሰተው አዕምሯችን መረጃን በሚያስተናግድበት ጊዜ በሚፈጠር ትንሽ መዘግየት ወይም መረጃን የማብላላት እክል ሲኖር ነው የሚል ነው። በመሰረቱ አዕምሯችን መረጃን ሲያስተናግድ በቅድሚያ; መረጃው ወደ ንቃተ ህሊናችን ይገባል (አሁን እያጋጠመን ያለው)፤ በመቀጠል; ወደ ንቃተ ህሊናችን የገባውን አዲሱን መረጃ ከዚህ ቀደም ከነበሩ የመረጃ ማህደሮች(ከዚህ ቀደም ያጋጠሙን) ውስጥ አዕምሯችን ይመዘግባል። የሂደቱ ሁለቱ ደረጃዎች በጣም ተቀራርበው(ከሞላ ጎደል በተመሳሳይ ሰዓት ስለሚከሰቱ አዕምሯችን አዲሱን መረጃ እንደ ትውስታዎች ሊገነዘበው ይችላል። አዕምሮ አሁን ያለን ልምድ ያለፈ ትውስታ አድርጎ በስህተት የሚመዘግብበት ዋነኛ ምክንያት አዲሱን መረጃ በመቀበል እና ያለፈውን በማስታወስ መካከል በሚፈጠር የማይክሮ ሰከንዶች መዘግየት ነው።

✓ ሁለተኛው ዋነኛ ሳይንሳዊ ማብራሪያ; የልምዶች መመሳሰል ሲሆን፤ አዲሱ መረጃ ከዚህ ቀደም አዕምሯችን ውስጥ ካለው መረጃ ጋር ጥቂት መመሳሰል ሲኖረውና ቀድሞ አዕምሯችን የመዘገበውን መረጃ በትክክል ለማስታወስ ሲቸገር አዲሱን መረጃ እንደ ትውስታ ሊቆጥረው ይችላል። ይህም " ይህንን ነገር ከዚህ ቀደም አውቀዋለሁ" የሚል ስሜትን ይፈጥራል።

በ Déjà vu ዙሪያ ለረዥም ዘመናት ጥቂት የማይባሉ ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምሮች የተካሄዱ ሲሆን እነዚህ ከላይ ያሉት ሁለት ማብራሪያዎች በሳይንሱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኙ ናቸው። ምርምሮቹ አሁንም አላበቁም፤ በተለይም በ Neuro Science ዘርፍ የሚሰሩ ልሂቃን አሁንም Déjà vu ን የበለጠ ለመረዳት እየታተሩ ነው።

Déjà vu ብዙውን ጊዜ የተለመደ፣ ተፈጥሯዊ፣ እና ጤናማ የሆነ ተሞክሮ ሲሆን ከምንም አይነት የጤና እክል አይቆጠርም።

ይህ የሳይንሱ ዓለም የሰጠው ማብራሪያ ነው። የፍልስፍናው ዘርፍም Déjà vu ን ለየት ካለ አቅጣጫ እና ጠለቅ ካለ ትርጓሜ ጋር ያያይዘዋል።

ፍልስፍና ስለ Déjà vu ምን ይላል? በቀጣይ ክፍል...

~ Déjà vu: አወዛጋቢው ስሜት


💢💢ከርእስ ውጪ 💢💢


ቲክ ቶክ ከነገ በስቲያ ከአሜሪካ ሊሰናበት ይችላል
***

ቲክ ቶክ ከነገ በስቲያ (እሁድ) ከአሜሪካ ሊሰናበት እንደሚችል ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ አሊያም አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ የተዘጋጀውን ሕግ ደግፏል፡፡

ስለ እግዱ አተገባበር ዝርዝር መረጃዎች አለመውጣታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ቲክ ቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን እ.አ.አ ጥር 19 ቀን 2025 (እሑድ) እንዲሆን ቀነ ገደብ ተቆርጦ ነበር፡፡

ባይት ዳንስ በተባለው ካምፓኒ የሚተዳደረው መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ ከ170 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡

የካምፓኒው ባለቤት ዣንግ ይሚንግ ከቻይና ዜግነቱ ጋር ተያይዞ ቲክ ቶክ የአሜሪካ መንግሥት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው በሚል ሲያሟግት ቆይቷል፡፡


‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ
አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››

ካህሊል ጂብራን


አንዳንድ ሰዎች አሉ ከቤት መውጣት የማይወዱ፤ ሲወጡም ማንንም ሳያገኙ ስራቸውን ሰርተው የሚመለሱ። አንድ ወይም ሁለት የቅርብ ጓደኞች አላቸው። ከእኩያቸው ጋር ኮንታክት የሌላቸው ስልካቸውን ሁል ጊዜ Silent ወይም Forward የሚደርጉ።

በዚህም ስሜታቸውን ላማጋራት እራሳቸውን ያልሰጡ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ ባጠቃላይ ሶሻል ሚዲያን ከፍተው ከግማሽ በላይ ቀናቸውን ማንንም ሳያናግሩ በዝምታ እየተከታተሉ እርካታ የሚያገኙ ናቸው። እነሱ መፅሐፍት፣ ሙዚቃ፣ ክረምትና መገለልን የሚወዱ፤ የተረጋጉ፣ ሁሌም ፈገግ የሚሉና በimagination ማለትም በምናባቸው አለማቸውን የሰሩ፤ ማንንም የማይጎዱ ሌሎች እንዲጎዷቸውም የሚይፈቅዱ እውነተኛ ሰዎች ናቸው።

Rajneesh Osho said this to real people፦

‹‹አንዳድ ጊዜ ብዙም ማህበራዊ መስተጋብር የሌላቸው ከሰው መሃል ወጥተው ዳር የሚይዙ ሰዎች ማኀበራዊ ኑሮን የሚጠሉ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ የውሸት ድራማን ድድብናና አስመሳይነትን መቋቋም ስለሚከብዳቸው ነው››
ድጋፋችዉን የማዉቀዉ ላይክ👍 ስታረጉ ነዉ


#መፅሐፍት #የመጻሕፍትማ #መልዕክት #ቤተመፅሐፍት


🌠 አስትሮኖሚ 🌠
ሙሉ ጨረቃ ወጥታለች

ጨረቃ ሙሉ ሆና በምትወጣበት ማታ ብዙዎች ላይ የርህራሄ እና የማስተዋል ስሜታቸው ላይ የመጨመር ነገር ይፈጠራል።። ከጉዳት ጋር የተዛመዱ ስሜቶችን ለመላቀቅ የሚያስችል ጊዜም የመሆን አጋጣሚ አለው።

የሙሉ ጨረቃ የስበት ኃይል በፕላኔታችን የውሃ አካላት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን የስበት ሀይሏም ሙሉ ስለሚሆን ውቅያኖሶችና ሀይቆች እንዲወጠሩ በማድረግ ከወትሮው ከፍ ያለ ከፍተኛ ማዕበል ውስጥ ይከታቸዋል። በተመሳሳይ የስበት ኃይል በሰውነታችን ውስጥ ያለው ውሃ ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል። 60% የሚሆነውን የአካላዊ ውህደታችን ውሀ በመሆኑ ሙሉ ጨረቃዋ በምትፈጥረው ትልቅ ግራቪቲ ምክኒያት የስሜት ለውጥ ሊከሰትብን ይችላል።

የጨረቃ የስበት ኃይል እና የብርሃን ኮዶች ከሰውነታችን ፈሳሾች እና የ energy ፊልዶቻችን ጋር ሲገናኙ ስሜታችንን ሊያነቃቃ ይችላል፣ ይህም የበለጠ ስሜታዊነት እንዲሰማን ያደርገናል። ለዚህ ነው ብዙ ሰዎች ሙሉ ጨረቃ በምትወጣባቸው ምሽቶች ላይ የበለጠ ስሜታዊነት፣ ርህራሄ ወይም ምንነቱ የማይታወቅ የናፍቆትና የትዝታ ስሜት የሚሰማቸው። ያ ስሜት የተፈጠረባቸው ሙሉ ጨረቃ ስለወጣች እንደሆነ ግን ልብ ላይሉት ይችላሉ።

ይህ ከፍ ያለ ስሜታዊ ሁኔታ ወደ መጨናነቅ ስሜት፣ የስሜት መለዋወጥ እና ግልጽ ህልሞች ወይም ቅዠቶችም ሊያስከትልም ይችላል። እንደ የምግብ መፈጨት ችግር፣ መጠነኛ ራስ ምታት፣ ምናምንም ሊያስከትል ይችላል።

ምንም እንኳን እነዚህ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ሙሉ ጨረቃ የምትወጣበት ማታ ታላቅ የእውቀት እና የሳይኪክ ግንዛቤያችንን የምንጨምርበት ጊዜ ነው።
የኢነርጂ ስሜታቸውን የተዋሀዱ ሰዎች ከስሜታቸው እና ከደመ ነፍሶቻቸው ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ከውስጥ ጥበባቸው ጋር የበለጠ ሊጣጣሙ የሚችሉበትም ጊዜ ነው።


❤🙏🌟#ለቻናሉ_አባላት 🙏❤🙏🌟

የመፅሃፍት-ማዕድ ከተመሠረተ ጀምሮ የአባላት ቁጥሩ እየጨመረ አሁን ላይ 260 አባላት ቁጥር ላይ ደርሷል። ይሄ በራሱ ቻናሉ ምን ያህል ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱን ስለሚጠቁም ለወዳጅነታችን ተስፋ ሰጪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።


👉ስለዚህ አባላቱ በመፃፍ፣ የተፖሰቱ ፅሁፎች ላይ ኮመንት በመስጠት፣ ላይክ እና ሼር በማድረጉ ላይ ያለን ተሳትፎ እንዲያድግ ምን ይደረግ ትላላችሁ❓

👉ወዳጆቼ የሄ ቻናል የሁሉም አባላት ስለሆነ የሁላችንንም ተሳትፎ የሚሻ ስለሆነ ሃሳብ አስተያየታችሁን በቀናነት በማቅረብ ቻናላችንን:-
👉በተሳትፎ የዳበረ፣
👉አስተማሪና ተመራጭ ቻናል ለማድረግ በጋራ እንጣር እላለሁ!!
_//___
ለምትሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እናመሰግናለን🙏🙏


በህይወት የምንኖረው ለምንድነው?
ለዚህ ጥያቄ ብዙ መልሶች ሊሰጡ ይችላሉ። እኔ ግን ከደራሲ አለማየሁ ገላጋይ 'ሐሰተኛው በእምነት ስም' ከተሰኘው መጽሐፍ ላይ ካነበብኩት ላካፍላችሁ።
ሰው በዳቦ ብቻ የማይኖር ፍጡር ነው።የጥበብ፣ የመመራመርና የእምነት ፍላጎቶቹ በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ እስከመሆን ደርሰዋል።ሩሲያዊው ደራሲ ፍዮዴር ዴስተየቭስኪ "...The secret of man's being is not to live"ያለው ለዚህ ነው።"but to have something to live for"የሰው ልጅ መኖርን ብቻ በሌጣው አይሻም።የሚኖርለት የህይወት ፍቺ ይፈልጋል፥ እንዲያ ካልሆነ በህይወት ከመኖር ይልቅ እራሱን በራሱ ቢያጠፋ ይመርጣል ይላል ዶስተዮቭስኪ።እውነታን ብቻ አይደለም የምናብ ቅንብርንም እንሻለን።ከልበ ሰፊዎች የተገኘ ምናብ መሠረታዊ ፍላጎታችን እስከመሆን ደርሷል።ሙዚቃ... ድርሰት....ቴአትር...ዳንኪራ... ስብከት...ስዕል...የጥበብ ፍቅር ከራሱ ከሰው ልጅ ክብር እየላቀ የመጣበት ጊዜ ነው።
ፈላስፋው Nietzsche ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ እህቱ ኤልሳቤት ትደርሳለች።
" ምን ሆንክ?"
"ፈረንሳይ ውስጥ የጎዳና ላይ አመጽ ተነስቷል"
"እና"
"እሳት እየተቀጣጠለ ነው አሉ"
"እና የምታውቀው ሰው እዛ አለ? በእርግጥ የሰው ልጅ ላይ የሞት አደጋ ሲያጋጥም ባያውቁትም ሀዘን መሰማቱ አይቀርም ግን.."
"መች ለሰው ሆነና፥ሉቭ ውስጥ እሳቱ ከተዳረሰ እነዛ የምወዳቸው ስዕሎች ሁሉ መውደማቸው አይደል?" ሲል ለቅሶውን ቀጠለ።እንዲህ ሲሆን ቆይቷል፥ ወደፊትም እንዲሁ ይቀጥላል።የሰው ልጅ በገዛ እጁ ሥራ ዋጋው እያነሰ መሄዱ ዘልአለማዊ እውነት ነው።


ካላገባህ የዘር ፈሳሽህን ያዝ አድርገው።

ወንድ ልጅ የዘር ፈሳሹን ውስጡ ላይ ለረዥም ጊዜ በማመቅ እና energy ራሱ ጋር በማቆየት ንቃት ህሊናውንና እና መንፈሳዊ ግንዛቤውን ለማሳደግ ሊጠቀምበት ይችላል። የዘር ፈሳሽን አምቆ ለረዥም ጊዜ ማቆየት የህይወት ሃይልንና ቅድስናን በማሳደግ ኃይላችንን ለተሻለ አላማ እንድንጠቀም ይረዳናል።

epictetus የተባለ ፈላስፋ በአንድ ወቅት ወሲብን በተመለከተ ሲጠየቅ
"ወሲብ ማለት ወንዱ ፈሳሽን ከመራቢያው እስኪያወጣ ድረስ የሚደረግ የ አካላት ፍትጊያ ነው" ያለው ስለ semen retention ጥቅም ሲያብራራ ነበረ።

የዘር ፈሳሽ ባዮሎጂያዊ ፈሳሽ ብቻ አይደለም። የአንድ ሰው የሕይወት energy ነው።የመፍጠሪያ እና የመንፈሳዊ ማንነት ምሳሌም ነው። በሄርሜቲክ እና ታኦኢስት ወጎች መሰረት የወሲብ ጉልበት የሰው ልጅ ካላቸው ታላቅ ሃይሎች ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው ነው።

የወሲብ ጉልበት ለመራባት እንደሚያገለግለው ሁሉ ለመንፈሳዊ ከፍታም ሊያገለግል ይችላል።

የዘር ፈሳሽን የማቆየት ልምምድ ጠቃሚ ነው።አንድ ሰው ጉልበቱን ወደ ሳክሪያል ቻክራ እና ወደ ልብ ቻክራ ልኮ እንዲያጠራቅምና ለሌላ ነገር እንዲመነዝረው ይረዳዋል።

ልጄ ሆይ የማህፀኔ ልጅ ሆይ የስዕለቴ ልጅ ሆይ ጉልበትህን በሴት አትጨርስ::
መፅሐፈ ምሳሌ 31:2-3


ፕላኔታችን ላይ በየቦታው እየነደደ ያለው እሳት; የሰው ልጅ ከቁስ አካል ጋር ካደረገው ውስጣዊ ቁርኝት ይላቀቅ ዘንድ የሚያግዝ የመንጻት ነበልባል ነው።

ብዙዎችን ከስግብግብነትና ከቅዠት እያወጣቸው ታላቅ እውነታን እንዲፈልጉ እየገፋፋቸው ይገኛል።


እውነተኛ ሳይንስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል።

(የሕይወት ፪ እይታዎች በዶክተር መልሳቸው መስፍን)

ሳይንስ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው መልካም የእውቀት ዘርፍ ነው፡፡በሳይንስ ስለተፈጥሮ የበለጠ ለማወቅ ተችሏል።ሰው በትምህርት ፤ በጤና ፤ በቴክኖሎጂና በሌሎችም በርካታ መስኮች ከፍተኛ እድገት እንዲያመጣ አስችሏል።

በየቀኑ የምንገለገልባቸው እቃዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ናቸው፡፡የሰው ኢኮኖሚያዊ ፣ ማኅበራዊ ፣ ስነ ልቦናዊ ኑሮው እንዲዳብርና እንዲሻሻል ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔርና እርሱ ስለ ፈጠረው ዓለም ይነግረናል፡፡ሳይንስ ደግሞ የእግዚአብሔር ስለሆነው ዓለም መረጃ ይሰጠናል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የሳይንስ መጽሐፍ አይደለም፡፡ስለዚህ ስለ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ ዝርዝር ነገር ለማንበብ አንጠብቅም፡፡ሞሊኪውል፣ ዲ.ኤን.ኤ የሚሉ የሳይንስ ቴኪኒካዊ ቃላት የሉትም።ሆኖም እግዚአብሔር ለሰው ሊያስታውቅ የፈለገው እውነት ተጽፎአል ፣ በየጊዜውም በሳይንስ እየተረጋገጠ ነው፡፡

ለምሳሌ ፦ ከ500 ዓመታት በፊት መሬት ጠፍጣፋ እንደሆነች ይታመን ነበር፡፡ከዛሬ 2700 ዓመታት በፊት በመንፈስ ቅዱስ ተነድቶ ነቢዩ ኢሳይይስ …በምድር ክበብ ላይ ... (ኢሳ 40፡22) በማለት ተናግሮአል።እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማምለክ ከሚቀርብ መሥዋዕት ጋር በተያያዘ ሕይወት ያለው በደም ውስጥ መሆኑ ተገልጾአል (ዘሌ 17፡11)።ከጤና ጋር በተያያዘም የኳራንቲንን አስፈላጊነት በዘሌ 13፡45-46! 14፡8-9፤ 15፡131 ፤25-27 እንመለከታለን፡፡

እነዚህ ነገሮች በሳይንስ ትክክል እንደሆኑ ስለሚታወቅ እውነተኛ ሳይንስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይስማማል ማለት ነው።እንዲያውም እኮ ዘመናዊው ሳይንስ የተጀመረው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከት በነበራቸው ሰዎች መሆኑ አይዘነጋም።


♦️ዝንጀሮዎች ከበቆሎ ማሳው ውስጥ ሲያባርራቸው የነበረው ገበሬ መሞቱን ሲሰሙ በደስታ ፈነጠዙ።

♦️በሚቀጥለው ዓመት ግን ምንም በቆሎ አልነበረም። ምግባቸውን የሚያበቅልላቸው ያ ጠላታቸው አድርገው ያሰቡት ገበሬ መሆኑን ያወቁት በዚህ ጊዜ ነው።

🤔ሰዎች የሥራዎቻችሁን ዋጋ ዛሬ ላይረዱ ይችላሉ፣ ነገር ግን እናንተ በማትኖሩበት ጊዜ የእናንተን አስፈላጊነት ይገነዘባሉ!

መልካም ቀን ይሁንላችሁ ..❤🙏

#መፅሐፍት #የመጻሕፍትማ #መልዕክት #ቤተመፅሐፍት


💥💥"መቀየር በማትችለው ነገር ላይ ወደኋላ ተመልሶ መቆዘም #ነገህን ያበላሻል። ነገ የተሻለ እንደሚሆን #ማመን አለብህ። ነገ ይሻላል ብለህ ካመንህ ደግሞ ዛሬ ላይ መከራን መሸከም ትችላለህ። #በሕይወትህ ውስጥ የሚመጡ መስናክሎችን እየሰባበርህ ወደፊት ለመጓዝ ሞክር እንጅ በእነሱ ተሰብረህ አንድ ቦታ ላይ ሽባ ሆነህ አትቁም። ብዙ #ጊዜ #የሕይወት ታላላቅ ትምህርቶችን የምንማረው በከባድና በመጥፎ ጊዜያቶች #ውስጥ በፅናት ጎዳና ላይ ተራምደን ስናልፍ ነው። በሕይወታችን ውስጥ #የፅናትን ያህል ጉልህ ድርሻ የሚወስድ ምንም ነገር የለም። ህልማችን እውን ለማድረግ ሕይወት የምትሰነዝርብንን ፈተና ሁሉ በፅናት መቋቋም ግድ ይለናል።".......




#አርምሞ
#ጥበብ #ጥበብ #ግንኙነት #ዓለም #ፍልስፍና #አብርሃምሊንከን #መፅሐፍት
#የመጻሕፍትማ


ሄዳችሁ የማታውቁትን ቦታ እንደምታውቁት አይነት፣ አርጋችሁ የማታውቁትን ነገር አድርጋችሁ እንደምታውቁ ወይም አጋጥሟችሁ የማያውቅን ነገር ቀድሞ ገጥሟችሁ እንደነበር አይነት ያለ ግር የሚል ስሜት ተሰምቷችሁ ያውቃል?

እሱ Dèjà vù ተብሎ ይጠራል። ለዘመናት የሳይንስ ልሂቃንን ያመራመረ እና ፈላስፎችን ያስገረም የተለመደ ተፈጥሯዊ ተሞክሮ ነው።



#አርምሞ
#ጥበብ #ጥበብ #ግንኙነት #ዓለም #ፍልስፍና #አብርሃምሊንከን #መፅሐፍት
#የመጻሕፍትማ


Forward from: 4-3-3 World News
#alert

በዛሬው ዕለት ብቻ ከ7 ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰምቷል።

እንዲሁም ባለፉት 7 ቀናት ደግሞ ከ39 በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበረ ተገልጿል።

@Ethionews433 @Ethionews433


Forward from: 4-3-3 World News
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በውስጥ መስመር የተላከ

"ጂንካ ሰአቱ 1:16 አከባቢ"

@Ethionews433 @Ethionews433


ምን አልባት አስትሮይድ ሊሆን ይችላል ?

ይህ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ እሳታዊ አካል ከየት አካባቢ ሆናቹ ተመለከታቹት በኮሜንት መስጫ ሳጥን ውስጥ አሳውቁን ?https://t.me/sabawitube

20 last posts shown.