Forward from: Ministry of Education Ethiopia
በተቀናጀ የተግባር ተኮር የትምህርት ብርሃን ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
----------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ እያካሄደ ካለው የሪፎርም ስራ ውስጥ የተቀናጀ የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህርት መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ አኤች ዲ) ገልጸዋል፡፡
በሀገራችን የመጻፍ፣ የማንበብና የማስላት ችሎታ ያላቸውን ጎልማሶች ለመለየት የሚያስችል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጀ የትምህርት ብርሃን ፈተና ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በፈተናውም ውጤት ያመጡ ጎልማሶች የ3ኛ ክፍል ያጠናቀቁበት አቻ ሰርተፊኬት ይዘጋጅላቸዋል ነው ያሉት፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትምህርት ዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ ሪፎርሞች ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ምክክር እያካሄደ ነው፡፡