❤️‍🔥❀✞ ምክረ አበው ✞❀❤️‍🔥


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


❀✞ማኅተብ የማሰር ጥቅሙ❀✞
❤️‍🔥[ክፍል - 3]❤️‍🔥

ማተብ ማሠር በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ዘንድ ለብዙ ጊዜ ጸንቶ ለመኖር የቻለው ጥቅሙ የጐላ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ለአንድ ሀገር አንድ ሰን ደቅ ዓላማ ለአንድ መሥሪያ ቤትም አንድ ዓይነት የጽሑፍ ምልክት ወይም አርማ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በአንድ ሃይማኖት ጥላ ሥር ላለ ሕዝብም አንድ ዓይነት ምልክት በማስፈለጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባሎችም በዚሁ ምልክት ሲጠቀሙ ቆይተዋል፤ አሁንም በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። ይህ ምልክት በሀገራችን በሃይማኖት አንድነት የሌላቸው ሁሉ በአንድነት ሊፈጽሙት የማይገባቸውን ከመፈጸም እንዲድኑ ከማድረጉ በላይ አንድ መንገደኛ ሰው ሞቶ በተገኘ ጊዜ ክርስቲያንነቱ በዚሁ ምልክት አመልካችነት ተረጋግጦ አስፈላጊው ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎለት በዐፀደ ቤተ ክርስቲያን እንዲቀበር በማድረግ ሲያገለግል ቆይቷል።

በጊዜያችን ግን ሃይማኖት በልብ ነው ምልክትም አያስፈልገውም በማለት በዚህ ምልክት የማይጠቀሙ ሰዎች እየበረከቱ ሄደዋል። የሚሰጡትም ምክንያት ጽዳት ያጐላል የሚል ነው፤ ጽዳት የማጉደሉ ሁኔታ ግን እንዳያያዙ ነው፤ የሚፈለገው ምልክትነቱ ነው እንጂ አንዳንዶቹ እንደሚያደርጉት የዐሥራ አምስት ክታብ ወይም ግሥንግሥ መሰብሰቢያ ማድረግ አይደለም።

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና ሥርዓት(በአእምሮ ማንደፍሮ የተዘጋጀ)

wwu>w.ethiopianorthodox.org


❀✞ በቤ/ክ በኩል ያለው መልክ ❀✞
❤️‍🔥[ክፍል ~ ፪]

ከሣቴ ብርሃን ሰላማ በአራተኛው መቶ ዓመት ወደ ሀገራችን መጥቶ የክ ርስትና ትምህርት ፋናን ሲተክል ያመነ የተጠመቀውን ካላመነው ለመለየት ከግንባሩ ላይ በመብጣት መስቀልኛ ምልክት ያደርግ ነበር ይባላል። ግን የመብጣቱና ደም የማፍሰሱ ዘዴ በሕዝቡ ዘንድ ሙሉ በሙሉ ስለአልተደገፈ ከጊዜ በኋላ እንደቀረ ይነገራል ። አሁንም ሳይቀር ሰሜናውያን ከግንባራቸው ላይ ምልክት የሚታይባቸው ከዚሁ ሲያያዝ መጥቶ ነው ይባላል ።

ምንም እንኳን መቼ እንደተጀመረ ከስንተኛውም መቶ ዓመት ጀምሮ እንደምትሠራበት በቂ መረጃ ባይገኝም ቤተ ክርስቲያናችን የማተብ ማሠርን ልማድ በደንብ ታከብራለች ፤ በቤተ ክርስቲያናችን ሥነ ሥርዓት መሠረት አንድ ሕፃን ወይም አንድ ሰው ሲጠመቅ ሦስት የተለያየ ቀለም ያላቸው ፈትሎች ከአንድ ላይ ተገምደው ለዚሁ የተወሰነው ጸሎት ተደርሶባቸው ለተጠማቂው ይታሠሩለታል ፤ ክሩም ነጭ ቀይና ሰማያዊ ሲሆን ፤ ነጩ ሐዲስ ሕግን/ ወንጌልን/ እጠብቃለሁ፤ ቀዩ በክርስቶስ ፍጹም ድኅነት እንደማገኝ አምናለሁ፤ ሰማያዊውም ሰማያዊ ሕግን በመጠበቅ ሰማያዊ ሕይወትን ተስፋ አደርጋለሁ ማለት እንደሆነ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ያትታሉ።
ስለዚህም ቤተ ክርስቲያና ችን ይህን ምልክት በአንገቱ ላይ በማድረግ አባልነቱን ታጸናለታለች ።


ይቀጥላል ...


❀✞ የማኅተብ ማሠር ልማድ✞❀
❤️‍🔥[ክፍል ~ 1]❤️‍🔥

የማኅተብ አንደኛው ፍቺ ምልክት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቡራኬ ማለት ነው፤ ሥርወ ግሡም « አተበ » አመለከተ፤ ባረከ የሚለው የግዕዝ ቃል ነው። ምልክት ሁልጊዜ አንዱን ነገር ከሌላው ለመለየት የሚያስችለው በመሆኑ ዓለም ይጠቀምበታል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በአራተኛው ምዕራፍ ስለ አብርሃም ሲናገር «ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ» ብሏል ። ወላጆችም መንታ ሲወልዱ የትኛው ቀድሞ እንደተገኘ ለማስታወስ ምልክት ያደርጋሉ። ለምሳሌ በአሪቱ ፋሬስና ዛራ ሲወለዱ አዋላጅዋ ቀድሞ በተወለደው አውራ ጣት ላይ ክር አሥራበት እንደነበረ ይነገራል።

❤️‍🔥❀✞ ታሪካዊ አመጣጡ ❀✞❤️‍🔥

የኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ማኅተብ ማሠር ልማድ የመጣው ለረዢም ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን ሞግዚት ሆና ከቆየችው ከእስክንድርያ ቤተ ክርስ ስቲያን ነው። በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቴዎዶስዮስ ዘመን በሀገሩ የነበረው ዐላዊ ንጉሥ በመሆኑ የክርስትናን አስተማሪዎች እያሠረ ያስደበድብ ነበር ።

ስለዚህም ቴዎዶስዮስ ካልሆነ ሰው ጋር ተጋፍጦ ከመቀሰፍና ሥራን ከማቋረጥ ዘወር ብሎ መዓቱን ማሳለፍ ይሻላል በማለት ሲሸሽ አንድ ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ የሚባል ለክርስትና ትምህርት ቀናተኛ የሆነ ሐዋርያ በሽሽግ ያስተምር ነበር ።

ይህንም የተቀደሰ ሥራውን ለማሰናከልና ለማቋረጥ የሚሹ አንዳንድ ቦዘንተኞች በስብሰባው ላይ እየተገኙ ያስተማራቸውን ያስቱበት ያሻክሩበት ስለነበር የርሱ የሆኑትን ለይቶ ለማወቅ ሲል በአንገታቸው ላይ አድርገው ለምልክትነት እንዲጠቀመብት ማኅተብ አሠረላቸው። ያሠረላቸውም ማኅተብ ሦስት ዓይነት ሆኖ በአንድ ላይ የተገመደ ሲሆን ጥቁር ፤ ቀይ፤ ቢጫ ነበር ። ይኸውም ጥቁሩ መከራ ዕቀበላለሁ፣ ቀዩ ደሜን አፈሳለሁ፣ ቢጫው ትንሣኤ ሙታንን ተስፋ አደርጋለሁ የሚል እንደነበረ ይነገራል ። ያዕቆብ ዘእልበረዳኢም ያስተምር የነበረበት ዘመን አምስተኛው መቶ ዓመት እንደነበረ ይገመታል።

(ሃይማኖተ አበው፣ ድርሳነ ያዕቆብ ።)


❤️‍🔥 አርምሞ ❤️‍🔥

አርምሞ (ዝምታ) መንፈሳዊ ሰው ካሉት ድንቅ ችሎታዎች መካከል አንዱ ነው:: ይህ ደግሞ የልብ፣ የነርቭ፣ የአሳብ፣ የስሜት፣ የጠባይና የሰውነት አርምሞን ያጠቃልላል:: የዝምተኛ ሰው ልብ ምንም ዓይነት ምክንያት ቢገጥሙትም ፈጽሞ አይታወከም:: ችግሮቹ ምንም ዓይነት ነገር ቢያደርሰብትም ዝምታውን አያጣውም:: ነቢዩ ዳዊት ይህን አስመልክቶ ሲናገር:- ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማማናለሁ።» (መዝ 26:3) ብሏል::

እንዲህ ዓይነቱ አርምሞ ከእምነት የሚመነጭ አርምሞ ነው:: አንድ ሰው ውስጣዊ ሰላሙን ሲያጣ በዐይኖቹ ፊት የሚመለከታቸው ነገሮች ሁሉ የታወኩ ይሆኑበታል፤ቀላሉም ነገር ውስብስብ ይሆንበታል፡፡

ይህ ውስብስብነት የሚመጣው ግን ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ነው:: ልብ ከተረጋጋ ነርቮቹም ይረጋጋሉ፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ የሰው ቁጣ ገንፍሎ አይወጣም፤ ይልቁንም ችግሩን በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ያቃልለዋል::

የሰው አዕምሮ አንድ ችግርን ማቃለል ከተሳነው ነርቮቻችን ለማገዝ በመካከል ጣልቃ ይገባሉ:: የተነሣሱት ነርቮች የመፍትሔ እጦትን ሊያሳውቁ ይችላሉ፣ ነርቮቹ ይበልጥ እየታወኩ በመጡ ቁጥር ደግሞ ይበልጥ ይነሣሳሉ፡፡ የተረጋጋ ልብ እና ነርቭ ያለው ሰው የአሳብና የድርጊት ዝምታን ገንዘቡ ማድረግ ይችላል:: አሳቦቹ ምንም ዓይነት ሁከት የሌለባቸውና የተመጣጠኑ ይሆናሉ፡፡ ስለሆነም ድርጊቱን የሚፈጽመው ከቁጣ ወይም ከጭንቀት በራቀ መንገድ በአርምሞና በትክክለኛነት ነው፡፡

ሰው ውስጣዊውን ሰላም እንዲያገኝ የሚረዳው ውጪያዊው ሰላም ነው:: ይህም በውስጡ ምንም ዓይነት የሚያውክ ሁኔታ የሌለበት ሰላማዊ አካባቢን ይፈጥራል:: ምክንያቱ ይህ በመሆኑም መነኰሳት ከሁከት፤ ከሰዎች ጫጫታ ወይም ከሚያውክ ወሬና ግጭት ርቀው በምድረ በዳ ውስጥ በሰላም ይኖራሉ፡፡ እነርሱ እንደዚህ ያለውን አርምሞ ተላምደውታል::

የመለየትና የብቸኝነት ሕይወት በአጠቃላይ አርምሞን ያመጣል:: የዚህ ምክንያቱም ስሜቶቻችን ሁሉ ስለሚረጋጉ ነው:: ቅዱሳን አባቶቻችን ስሜቶች የአሳቦች መንገድ ናቸው ይላሉ:: የምታዩት፤ የምትሰሙትና የምትዳስሱት ነገር ሁሉ አሳብ ይሰጣችኋል፡፡ ስሜቶቻችሁ ወሬ ከመሰብሰብ ተለይተው በእረፍት ላይ ከሆኑ አሳቦችን ከማሰብ እፎይ ትላላችሁ:: ፀጥ ያለ ቦታ የስሜትን መረጋጋት ያግዛል ይህ ደግሞ ወደ አሳቦች፥ ወደ ልብና ወደ ነርቭ መረጋጋት ያመራል::

ብዙ ሰዎች ጫጫታ ካለበት ስፍራ ርቀው የሚሄዱት የአዕምሮ ሰላምን ለመፈለግ ነው:: ባላቸው ብርታት ሁሉ አርምሞን ለማግኘት በፍቅር የሚፈልጉት ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ያለ ሁከትና ያለ ጫጫታ መኖር የማይችሉ ሰዎችም አሉ:: አርምሞ ለእነርሱ አሰልቺ ነገር ነው::

╭══•|❀.........♡...........❀|: ══╮
             አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
╰══•|❀.........♡...........❀|: ══╯


❤️‍🔥 በሰው ድካም መፍረድ ❤️‍🔥

❤️‍🔥እንደማይገባ ❤️‍🔥

አባ ርስላዎስ(ብላርዮን) ከገዳም በቤቱ ሳለ አባ እስያስን ጎበኘው ሲበላም አገኘው፤ ውኃና ጨው ወስዶ በድስቱ ላይ አደረገ፡፡ መነኩሴውም በገባ ጊዜ ድስቱን (ፋጋውን) ወስዶ በሰሌኑ ስር ሸሸገው፡፡

"መነኩሴውም ምን ትበላለህ?" አለው፡፡ አባቴ ይቅር በለኝ ሰሌን ልቆርጥ ሄጄ በዚህ ፀሐይ ቃጠሎ ገብቻለሁና ከውኃው ጥማት የተነሳ መኮሬታውን (ዳቤውን) መዋጥ አልቻልኩም ጕረሮየ ደርቋልና ምግቤን እበላ ዘንድ ከውኃው ላይ ጨው ጨመርኩ ይቅር እንድትለኝ እለምንሃለሁ አለው፡፡ አረጋዊውም መነኩሴውን እዩ እሳያስን በገዳም ወጥን ሲበላ አለ፡፡ ወጥን ለመብላት ከፈለግክ ወደ ግብፅ ከተማ ሃድ አለው፡፡ (ማቴ. ፭)

የቆጵሮስ ኤጲስ ቆጶስ ኤጲፋንዮስ ወደ አባ ብላርዮን ገዳማዊ ላከ እየለመነ እንዲህ አለው፡፡ እርስ በእርሳችን እንተያይ አስቀድመን ከሥጋችን ሳንለይ(ሳንሞት በፊት እንገናኝ) አለው። እሱም ልመናውን ስምቶ መጣ ሲገናኙም ደስ ተሰኘ፡፡
ለማዕድም በተቀመጡ ጊዜ የቆቅ ሥጋ አቀረቡላቸውና ኤጲስ ቆጶሱ ለአባ ብላርዮን ሰጠው፡፡ መነኩሴውም ኤጲፋንዮስ ሆይ ይቅር በለኝ ይህን ቆብ ከተቀበልኩ (ከመነኮስኩ) ጀምሮ ይህን ሥጋ አልበላሁምና ኤጲፋንዮስም አለው እኔም ከመነኮስኩ ጀምሮ በልቦናየ ቂምንና ሐሜት ሌሎችንም ኃጢአቶች እንዲያድሩ አልወደድኩም (አላሳደርኩም) አለው፡፡ መነኩሴውም አባቴ ይቅር በለኝ ያንተ ተጋድሎ ከእኔ ተጋድሎ ይበልጣልና አለ፡፡


╭══•|❀.........♡...........❀|: ══╮
               መጽሐፈ ገነት
╰══•|❀.........♡.........❀|: ══╯








ስለ ዝሙት




ስለ ዝሙት


ይህንን link 👆 ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ share አድርጓቸው።




ሰላም እንዴት አላችሁ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱሳን አበው ወቅዱሳት እማት ምክሮች(Sᴘʀɪᴛᴜᴀʟ Ғᴀᴛʜᴇʀs , Aᴅᴠɪᴄᴇs) ተከታታዮች በዚህ channel ቀንን የሚያበሩ፤ መንፈስን የሚያድሱ፣ ተስፋን የሚያለመልሙ፤ ሕሊናን ወደ ሰማይ የሚሰቅሉ ... የቅዱሳን አባቶቻችንን እና የቅዱሳት እናቶቻችንን ምክሮች የምንለቅ ሲሆን፤ ከዚህ ሥር ባለው channel ደግሞ ዓለም ላይ የሚነገሩ ምርጥ ምርጥ አስተማሪ የሆኑ አባባሎችን የምንለቅበት ይሆናል። በመሆኑም ይህንን channel በመቀላቀል እንዲሁም ይህ link መላው ኦርቶዶክሳውያን ጋር እንዲደርስ share በማድረግ ሃይማኖታዊ ግዴታችንን እንወጣ።

👇👇👇

https://t.me/Quote_of_the_Day_Every_Night

እናመሰግናለን 🙏❤


ስለ እምነት


ስለ ተስፋ

16 last posts shown.

63

subscribers
Channel statistics