Forward from: SameN
My Pencil and My chronicle.....
ሁላችንም አውቶቡሱን ከበን ተቀምጠናል ግማሹ ስለጉዞው ያወጋል ገሚሱ የወጣውን ተራራ በተመስጦ እያየ ይቆዝማል። ድካሙ የበረታበትም አውቶቡሷን እንደ ቤርጎ ተጠቅሞ ወገቡን ያሳረፈም አለ። ከዚህ በኋላ እንኳን ተመልሰን እኚህን ተራሮች ስለማንወጣቸው ፈገግታዬ ጨምሯል። ሰላም ሲሉኝ ራሱ ተነስቼ ለማቀፍም ይዳዳኛል። ልክ ዘመቻ ሄዶ ከሞት አምልጦ እንደመጣ ወታደር ደስታዬ ወደር አልነበረውም።
ራሃባችንንም ለጊዜው ለማስታገስ አካባቢው ያፈራውን ሸንኮራ አገዳና ቆሎ መቀማመስም ተያያዝነው። በጣም የሚጣፍጥ ምግብ ማለት ርቦህ ምትበላው ምግብ ነው ይል ነበር አንድ ወዳጄ። ህዝቡ ግን ቸር ነው ኤልሳ ቆሎ ተሰልፈን ግማሹን ከ70-80 ብር አውጥተን የምንገዛውን እዚህ በ25 ብር ብቻ በውሃ ጆግ ሙሉ ያሸክሙሃል። ሂሳብም ሲቀበሉ እንኳን እንደማፈርም ያረጋቸዋል በቦታው ያሉትን ጌጣጌጦችም እንደፍላጎቶቻችን ገዝተን ወደ አውቶቡሱ ለመግባት ተነሳን። ግና ለመመለስ ስንሰናዳ አንዳች ነገር ተሰማኝ ቅርም አለኝ ሰው እንዴት ጨክኖ ይህን የመሰለ መልከዓምድር ትቶ ወደ ሁካታው አለም ይመለሳል። ብቻ ተዉት 'ወዳጅ ያዝናል እንጂ አብሮ አይሞትም' ይባላልና።
ጉዞ ወደ ደ.ብርሃን መልስ ጀመረናል ሹፌሩ እንዴት ያለ ጎበዝ ቢጤ ነው። አውቶቡሷን የሚሾፍራት ሳይሆን የሚያባራት ነው ሚመስል እንደውም ቄራ አካባቢ ሞተረኛ ሆኖ ማቀውም መሰለኝ። ለዚህም ይመስላል ከተሳፋሪ አንዷ እንስት ወራጅ አለ ብላ ወርዳ የተመለሰችው።
ደ.ብርሃን ደረስን ከከተሜ ጋር ተቀላቀልን ለምሳም ተሰናዳን። አ.አ ጥሩ የሚባል ቦታ ተመግበናል ግና እንዲህ ያለ ንፁህ ምግብ እውነቱን ለመናገር እናታችን ጋር የበላን ነን። ለዚህ ምስክራችን አበላላችን መመገቢያ ሳሕኑን ካላጠብን ብለን ሙግትም ገጥመን ነበር። አ.አ እንደለመደብን ሁለት ሊትር ውሃ ለማዘዝ ስንሰናዳ አንድ ወዳጄ እጄን ጎትቶ እስቲ የተፈጥሮውን እየው አለኝ። እግዜር ውሃን ሲፈጥር እዚህ አካባቢ ነበር እንዴ ያስብላል። የጀበና ቡና እዛው ጋር ወጣ ብለን ጠጣን። ልጅቷም ጥሩ ቡና ከጥሩ ፈገግታ ጋር ቸረችን። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ወደ አ.አ የመልስ ጉዞውን ጀመርን። ለጥቂት ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ ብዙም ሳይቆይ የኋላው ደጀን ለቤት ይዞት የመጣውን እርጎ ጎንጨት አለ መሰል አለኝ የሚለውን ሙዚቃ ያንቆረቁር ጀመር። ያው የድምፅ ነገር እንዳለ ነው። እኛ የ90ዎቹ ነን መሰል ወደ ልጅነትም መለስ ቀለስ ይባላል። ቆይ እኛ የስንተኞቹ እንደሆንን የማናውቀውስ ምን ብለን እንዝፈን ብቻ ይቺ የደ.ብርሃን እርጎ ስንሄድም ስንመለስም ለውጥ አላት ልዩነት ፈጣሪ ነች።
ጉዞውንም መጨረሳችንን ለማብሰር ይመስላል 'እዚህ ጋር ወራጅ' አለ የሚል ድምፅ ሹፌሩን አስቆመው ያው ለደ.ብርሃን ቀረብ ያለ አካባቢ መሰለኝ።።።
እኔም መውረጃዬ ስለሆነ በሌላ ጉዳይ እስክንገናኝ ደህና ቆዩልኝ ሹፌሩንም በሰላም ያሳድርህ በሉልኝ። በዚህ አጭር የበውቀቱ ስዩም ግጥም ልሰናበት .....
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፣ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፣ ከመሞት ምን ሊገኝ?
......>...... ተፈፀመ.....