*_ዘካተል ፊጥር እና አፈጻጸሙ_*
*የመጨረሻው ክፍል*
√ *_ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ ተምኖ መክፈል_*
ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ መክፈል አይፈቀድም። ምክንያቱም በኢብኑ አባስ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥር የተደነገገበትን አላማ ሲገልፁ ‹‹ለምስኪኖች መብል …›› በማለታቸው ጋር የተያያዘ ነው፡፡
አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዲህ ብለዋል:-
“የአላህ መልዕክተኛ በነበሩበት ዘመን ዘካተል ፊጥር የምናወጣው ከምግብ አንድ ሷዕ ነበር” ብለዋል።
ዘካተል ፊጥርን ከተገደበለት ጊዜ ማስቀደም ወይም ማቆየት እንደማይቻል ሁሉ የአወጣጡን አይነትም መቀየር አይቻልም። ዒባዳ ሁልጊዜ በአላህ የሚደነገግ እንጂ በአስተያየት ምንፈፅመው አይደለም። ማንኛዉም ሙስሊም ዒባዳው እንዳይበላሽበት ሊጠነቀቅ ይገባዋል። በገንዘብ መተመን በቀደምት ሰለፎች አልተፈፀመም። ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃዉንት በገንዘብ ማዉጣትን ይቃወማሉ። አል-ኢማም ማሊክ፣ አል-ኢማም አሻፊዒይ እና አል-ኢማም አህመድ ይህ መዝሀባቸው ነው። ስለዚህም በተባለው መልኩ በእህል ያወጣ ሰው በሁሉም ስምምነት ትክክለኛ ዒባዳ ፈፅሟል።
√ *_ዘካተል ፊጥርን ወደ ሌላ ቦታ መላክ_*
በመሰረቱ እያንዳንዱ ሙስሊም በጾመበት ቦታ ዘካተል ፊጥርን ማዉጣቱ ቢሆንም የሚገባው ነገር ግን ምግብ የሚቀበል ሚስኪን ሰው የሌለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች በቤተሰቦቻቸዉ ወይም ጓደኞቻቸው አማካኝነት ችግረኞች ወዳሉበት ቦታ መላክ ይችላሉ።
በጥቅሉ ማንኛዉም ሰው ዒባዳውን በዒልም ላይ የተመሰረተ በማድረግ ኢስላምን በሚገባ ለመተግበር መሞከር ይገባዋል።
*ተፈፀመ*
**تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال**
✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ*
👇
የመጀመሪያውን የቻናሉን ሊንክ ለመፈለግ (ሰርች) ለማድረግ ስለሚያሰቸግር በዚህ ቀይሬዋለሁ። ስለዚህ ከቀድሞው ሊንክ ጋር አያይዛችሁ ያስተላለፋችሁ ወንድሞች እና እህቶች በዚህኛው መቀየሩን ከምስጋና ጋር ለማስታወስ እወዳለሁ።
ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!
t.me/tahaahmed9