Tikvah World


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


@tikvah_tena
@tikvahpharma
@tikvah_vacancy
@tikvah2024

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


#DV2025

የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ 2025 አሸናፊዎች ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ለዲቪ  2025 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov/ESC/ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።

Via
@tikvah2024 | @tikvah_sales


#ሆሣዕና

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓ/ም ሆሣዕና በዓል አስመልክተው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ የዛሬው የሆሣዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙት እና የሚከተሉት ህዝብ በተለይ አእሩግ እና ሕጻናት " ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም ሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም " በማለት ጌታችንን መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል መሆኑን አስረድተዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ሰሙነ ህማማትንም  አስመልክተው ለመላው ምዕመናን አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ፦

" ሰሙነ ሕማማትን እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አስጀምሮ እንዲያስፈጽመን ለብርሃነ ትንሳዔው እንዲያበቃን እግዚአብሔር አምላካችንን እንለምነዋለን።

ሰሙነ ሕማማትን ሁላችንም በየአካባቢያችን ባለው ቤተክርስቲያን ተገኝተን ሰሞነ ሕማማትን ፣ ስግደቱን ፣ ጸሎቱን፣ ልመናውን በሕብረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችን እንጸልያለን።

በጸሎታችን ደግሞ ያለውን ችግር ሁሉ እንዲያስወግድልን ፦
- #ሰላሙን፣
- #ፍቅሩን፣
- #አንድነቱን እንዲሰጠን የሁላችንም ጸሎትና ምኞት ነውና እግዚአብሔር አምላካችን ከዚያ ያድርሰን ሰሙነ ሕማማቱን በሰላም ያስፈጽመን። "

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia




#Update: በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ  ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ሥራ ነገ ይጀመራል ተባለ

በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎችን በተቀናጀ መንገድ የመመለሱ ሥራ ነገ እንደሚጀመር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቋል።

በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራው የመንግሥት ልዑክ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር በመወያየት በተመላሾች መለየት እና መመለስ ላይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመሆኑም ሪያድ እና ጂዳ አካባቢ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ወደ ሀገር ቤት የመመለሱ ስራ ነገ አርብ ሚያዚያ 04 ቀን 2016ዓ.ም እንደሚጀመር አቅጣጫ ተቀምጦ ዝግጅቱ መጠናቀቁም ነው የተገለፀው።

@tikvah2024 | @tikvah_vacancy


#አውሮፓ

የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።

የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?

➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።

➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው  ይላል።

➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።

➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ℹ ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?

#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።

#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።

#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።

#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።

#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።

#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvah2024


ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዘማሪው ወደ መንፈሳዊው ህይወት ሳይገባ በፊት ለረጅም ዓመታት ዘፋኝ የነበረ ሲሆን በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ነበሩት።

ሙሉቀን መለሰ የዘፈንን ህይወት እርግፍ አድርጎ ከተወ እና ዘማሪ ከሆነ በኃላ የተለያዩ የመዝሙር ስራዎችን ለወንጌል አማኞች አቅርቧል።

ዘማሪው ከሀገር ወጥቶ አሜሪካ መኖር ከጀመረ ረጅም ዓመታት ያለፈው ሲሆን በዛው ባለበት ሀገር አሜሪካ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ከዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ስራዎች አንዱ ፦

ኢትዮጵያ !

" ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ።

አድገዋል አውቀዋል ያልሻቸው #ልጆችሽ፤
ሁሉም እሾህ ሆነው እየወጉ #አደሙሽ፤
የአንድነት ማሰሪያው መቀነት ይኑርሽ ይኑርሽ፤
እግዚአብሔር ነይ ይላል ወደእሱ ተመለሽ።

#ጦርነት #ረሃብ #ስደት ደርሶብሻል፤
ችግር በየፈርጁ ተፈራርቆብሻል፤
በመከራሽ ብዛት የአፍረት ማቅ ለብሰሻል፤
የሚታደግ አዳኝ ኃያል ብሩት አጥተሻል።

ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ። "


@tikvah2024 | @tikvah_vacancy


#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

ከ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የበዓሉ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ በአዲስ አበባ ከተማ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው  አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤ/መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል  አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ  አቧሬ ሴቶች አደባባይ  ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎባ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር  ወደ ብሔራዊ ቴአትር  ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ

... ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

መላው ህብረተሰቡ / አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvah2024 | @tikvah_vacancy


የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው።

ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ በመሆኑም የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ይከበራል።

ነገ ማክሰኞ የረመዷን #የመጨረሻው ሰላሳኛ ቀን ይሆናል።

@tikvah2024 | @tikvah_vacancy


ጅማሪ የተቋማዊ ልማትና ሥራ አመራር ባለሙያ
#chemical_industry_corporation
#business
#Muger
ዲግሪ በማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግ፣ በቢዝነስ አስተዳደር፣ በድርጅታዊ ልማት፣ በለውጥ አስተዳደር ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ች
Quanitity Required: 1
Minimum Years Of Experience: #0_years
Deadline: April 10, 2024
How To Apply: አመልካቾች ዋናውን የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ግሎባል አከባቢ በሚገኘው ጋራድ ሕንጻ በሰው ሀብት ሥራ አመራርና ኮሙኒኬሽን ቡድን እና በታጠቅ በሰው ሀብት ሥራ አመራርና ፋሲሊቲ ሰርቪስ ቡድን ቢሮ በአካል በመገኘት መመዝገብ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ በ+25111279015 /+251114404791 /+25111761951 ይደውሉ።

@tikvah_tena | @tikvah_vacancy


#AddisAbaba

ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት ጓደኛቸውን ሁለቱም ኩላሊቶቹ ከጥቅም ውጪ የሆኑ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የነበሩ 10 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው " አዲስ ሰፈር " አካባቢ መሆኑን አሳውቋል።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3- B21705 አ.አ " የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪን በመጠቀም ገንዘቡን ሲሰበስቡ የቆዩት " የኩላሊት ታማሚ ነው " ያሉትን ጓደኛቸውን መኪና ውስጥ በማስተኛት ነው።

በተያዙበት ወቅት ከ5 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እጃቸው ላይ መገኘቱን ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ የድጋፍ ጥያቄዎች ሲቀርቡ የሚስተዋል መሆኑን ገልጾ ነገር ግን ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት #የማታለል ተግባርም የሚፈፅሙ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝቦ ድጋፍ ሲያደርግ ከህክምናው ጋር የተያያዙ አግባብነት ያላቸውን #ሰነዶች በማየትና ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ሲል አሳስቧል።

@tikvah2024


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 / 2016 ዓ/ም ለሊት ችግር በገጠመው ጊዜ " የህዝብን ገንዘብ ያለአግባብ  ወስደው እስካሁን #አልመለሱልኝም " ያላቸው ግለሰቦች በተለያዩ ሚዲያዎች ፎቷቸውን እያሰራጨ ይገኛል።

ከሚዲያዎች በተጨማሪ በየባንኩ ቅርንጫፎች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም በር ላይ ለህዝብ በሚታይ መልኩ " ገንዘቡን አልመለሱም " ያላቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ በትልልቅ ባነር በማሰራት ለጥፏል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ " ብር ተመላሽ አድርገን እስካሁን ፎቷችን በሚዲያዎች እንዲሰራጭ እየሆነ ነው " ያሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ባንኩ ገንዘብ የመለሱትንም በፎቶግራፍ ማውጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

" የወሰድነውን ብር ተመላሽ አድርገን ሳለ ባንኩ ብር ካልመለሱት ጋር አደባልቆ ፎቶፍራፋችንን ማሰራጨቱ ተገቢ አይደለም በመሆኑንም ህዝብ በሚያውቀው መንገድ መመለሳችንን ሊያሳውቅ ይገባል " ብለዋል።

@tikvah2024


" በቦምብ ጥቃቱ 31 ተማሪዎች ተጎድተዋል " - ፖሊስ

ዛሬ በፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ዳሞት  መሰናዶ ቁጥር 1 ት/ቤት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በ31 ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የፍኖተ ሰላም ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለጸ።

በት/ቤቱ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት 6 ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

የቦምብ ጥቃቱ (ቦምቡ የተጣለው) ጥዋት 2፡30 ሰዓት ተማሪዎች በፈተና ላይ እንዳሉ መፈፀሙን የገለጸው ፖሊስ ፤ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው 6ቱ ተማሪዎች ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር ተፅፎላቸዋል ህክምና ላይ ናቸው ብሏል።

15 ተማሪዎች ደግሞ በፍኖተ ሰላም ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ሲሆን 10 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

አደጋውን ተከትሎ አንድ ተጠርጣሪ #ተማሪ መያዙን ፤ እጁና እግሩ ላይም መቁሰሉን ያሳወቀው ፖሊስ ሌሎች በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvah2024


#ኢትዮጵያ

የኢዴፌሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሠረት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲተገበር የሚያደርግ አዋጅ አፅድቋል።

አዋጁ የቤት አከራይ ከ2 ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ እንደማይችልም ያስገድዳል።

አዋጁ ምን ይላል ?

➡ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን የተመለከተው የአዋጁ አንቀጽ የመኖሪያ ቤት አከራዮች በዘፈቀድ የኪራይ ዋጋ እንዳይጨምሩ ይከለክላል።

➡ አከራይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ መሠረት በማድረግ ነው።

➡ በአዋጁ መሠረት የሚደረገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ አመት የፀና ይሆናል።

➡ የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በዚህ አዋጅ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። ይህም አስገዳጅ ድንጋጌ ነው።

➡ አከራዮች ከሁለት ወር የቤቱ ኪራይ በላይ ቅድመ ክፍያ መጠየቅ #አይችሉም።

➡ የቤት ኪራይ ክፍያዎች በባንክ ወይም በሌላ ሕጋዊ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ መፈፀም አለባቸው። አከራይ እና ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያ ሰነዶችን አደራጅተው የመያዝ ግዴታ አለባቸው።

➡ ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በጽሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት። ሁለቱም ወገኖች የቤት ኪራይ ውሉ በተፈረመ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ውሉን አቅርበው እንዲረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። አዋጁን ተከትሎ የሚደረግ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም።

NB. በአዋጁ መሠረት ተቆጣጣሪ አካል ማለት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን እና ዋጋን እንዲቆጣጠር በክልሎች ወይም በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች የሚሰየም አካል ነው፡፡ #HoPR #ቢቢሲ

@tikvahethiopia




#ጊምቦ

" እንዲህ ያለዉን አረመኔ ህግ የሚለቀዉ ከሆነ መተማመኛችን ምንድን ነዉ ? " - የአካባቢዉ ነዋሪዎች

" ማስረጃ አሰባስቤ ለፍርድ ቤት ባቀርብም የቀረበዉ ማስረጃ በቂ ሆኖ  አለመገኘቱን ተከትሎ ከ3 ወራት እስር በኋላ ሊለቀቅ ችሏል " -  ፖሊስ

ከዛሬ 3 ወራት በፊት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በተፈጠረ የእርሻ መሬትን የተመለከተ አለመግባባት አቶ ታሪኩ ኃይሌ የተባለ ግለሰብ የገዛ አባቱን በመጀመሪያ በዱላ በመምታት በኋላም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በገጀራ ቆራርጦ በመግደል መጠርጠሩን ተከትሎ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ይውላል።

የጊምቦ ወረዳ ፓሊስ ምርመራ ሲደረግ ከቆየ በኃላ ግለሰቡ ከወራት እስር በኋላ ተለቋል። ይህ ጉዳይም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ግርምትን እና ድንጋጤን የፈጠረ ሆኗል።

የግለሰቡን ከእስር መለቀቅ ያዩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተለይም የምስክርነት ቃላቸዉን የሰጡ ግለሰቦች በሁኔታው መደናገጣቸውንና ከመግለጽ ባለፈ " ፖሊስ ምን እየሰራ ነው ? " ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

" እንዲህ ያለዉ ነብሰገዳይ በዚህ ሁኔታ ከተለቀቀ በፖሊስና በህግ አካላት ያለን መተማመን ይቀንሳል " የሚሉት የአካባቢዉ  ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ ጉዳዩን ሲከታተሉት መቆየታቸውን በማንሳት ግለሰቡ በማስረጃ እጥረት ፍ/ቤት #ሊለቀዉ መቻሉን አንስተዋል።

የማህበረሰቡ ጥያቄ ልክ ቢሆንም የፖሊስ ስራ ከቅድመ መከላከል ባለፈ ወንጀል ሲፈጸም ማስረጃ አጠናቅሮ ፍርድ ቤቱ ማቅረብ ላይ እንደሚገታ የሚገልጹት ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ " አሁን ላይ የሁኔታውን ውስብስብና አሳሳቢ መሆን ተከትሎ የክልሉ ፍትህ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ፕሮሰስ ላይ መሆኑን ከክልል ቢሮ መረጃ ደርሶኛል። ለዚህም ስራ ፖሊስ አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል " ሲሉ ጠቁመዋል።

የማህበረሰቡን ቅሬታ በተመለከተም ፥ " ህግ ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚንቀሳቀስ መሆኑ የግድ በመሆኑ የህግ ሂደቱን በትእግስት መጠበቅ ይገባል " ብለዋል።

ፖሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ጥረት ላይ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።


#Ethiopia

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን በጋራ ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የዲቪደንድ (የትርፍ ድርሻ) ታክስን ጨምሮ የተለያዩ የግብር ዓይነቶችን እንዲከፍሉ ወስኗል።

በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት የሕንፃውን ሱቆች በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ላይ ለሚገኙበት ከተማ ወይም የአካባቢ አስተዳደር የኪራይ ገቢ ግብር ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል።

ሚኒስቴሩ በአክሲዮን ማኅበራት ባለቤትነት ሥር የሚገኙና የሚተዳደሩ የንግድ ማዕከላት ላይ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የጥናቱ ግኝትም ፣ አክሲዮን ማኅበራቱ በሕግ የተጣለባቸውን ግብር በተገቢው መንገድ እየተወጡ አለመሆናቸው ያረጋገጠ ነው ተብሏል።

ገቢዎች ሚኒስቴር በጥናት የደረሰባቸውን ግኝቶች መሠረት በማድረግ ሊወሰዱ ይገባል ያላቸውን የማስተካከያ ዕርምጃዎች የተመለከተ ምክረ ሐሳብ ለመንግሥት አቅርቦ በቅርቡ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል።

በዚህም መሠረት ፥ በአክሲዮን ተደራጅተው የተገነቡና በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎች ባለቤት አክሲዮን ማኅበሩ በመሆኑ፣ የንግድ ማዕከሉን የሚመለከቱ የግብር ግዴታዎች ላይ ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ተወስኗል።

በመሆኑም በንግድ ማዕከልነት በሚያገለግለው ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በማከራየት የሚገኘው ገቢ ላይ በግብር አዋጁ መሠረት የሚጣለውን የኪራይ ገቢ ግብር እንደ ከዚህ ቀደሙ በከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰበሰብ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ ባካሄደው ጥናት አክሲዮን ማኅበራቱ በሚያስተዳድሯቸው የንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ኪራይ ተመን ፦
- ከወቅታዊ ገበያው በእጅጉ አነስተኛ መሆኑ፣
- በርከት ያሉ ማኅበራትም በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በርካሽ ዋጋ ለማኅበሩ አባላት እንዳከራዩ ፣
- ሌሎች በርከት ያሉ አክሲዮን ማኅበራት ደግሞ የባለቤትነት ማስተላለፍ ሥርዓቶችን ሳይከተሉ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እንደ አክሲዮን ድርሻ ለማኅበሩ አባላት አከፋፍለው መገኘታቸው ተመላክቷል።

በመሆኑም ፣ ከ2016 ዓ.ም. የግብር መክፈያ ወቅት ጀምሮ በንግድ ማዕከላቱ ውስጥ የሚገኙ ሱቆች የኪራይ ተመን በገበያ ዋጋ ተሰልቶ የኪራይ ገቢ ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

@tikvah_tena | @tikvahpharma | @tikvah_vacancy


ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለድኅረ ምረቃ ሬዚደንሲ ፕሮግራም የተመደቡ ተማሪዎች አቀባበል አድርጓል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ወስደው ያለፋና በጤና ሚኒስቴር የተመደቡ 58 ተማሪዎችን ተቀብሏል።

ተማሪዎቹ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሔንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቆይታ ይኖራቸዋል።

@tikvah_tena | @tikvahpharma | @tikvah_vacancy

17 last posts shown.

301

subscribers
Channel statistics