የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
ነሐሴ 29/ 2013 ዓ.ም በመደበኛው ፕሮግራም በመጀመሪያ ድግሪ ካስመረቃቸው አዲስ ምሩቃን መካከል በአጠቃላይ ውጤታቸው (CGPA) ብልጫ ውጤት ይዘው የተመረቁትን በመምህርነት ሙያ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 29/ 2013 ዓ.ም በመደበኛው ፕሮግራም በመጀመሪያ ድግሪ ለተመረቃችሁና በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት ሙያ ተቀጥራችሁ ማገልገል ለምትፈልጉ፤
- ለወንድ ምሩቃን ከተመረቃችሁበት ኮሌጅ ብልጫ ውጤት በማምጣት ከኮሌጅ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የሜዳሊያ ተሸላሚ የነበራችሁ፣
-ለሴት ምሩቃን ከተመረቃችሁበት ት/ክፍል ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ በብልጫ ውጤት የተመረቃችሁ፡፡
በዩኒቨርሲቲው የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት የት/ት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በአካል በመቅረብ
ከ 01/02/2014 እስከ 05/02/2014 ዓ.ም ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን
የቅጥር ፈተናው በቀን
08/02/2014 እና በቀን 09/02/2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑንም ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ የቅጥር ፈተናው ከሰለጠናችሁብት ሙያ ጋር የሚያያዝ፣ አጠቃላይ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሁም የሥነ-ምግባር ጉዳዮችን ያካትታል፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
"OUR REWARD IS STUDENT'S HAPPINESS!!!"
Join Us!
https://t.me/wkusuhttps://www.facebook.com/WKUStudentUnion