✨✨ለሰዉ የማትናገሪዉ ተዓምር ተደርጎልሽ ያዉቃል..የሆነ የማታብራሪዉ..ልትናገሪዉ የሚያቅትሽ አይነት..ምናልባት ፍቅሩ ገዝፎብሽ ብታወሪዉ እንኳን በቃ እንዳልገባቸዉ እንዳልተረዱሽ እርግጠኛ የምትሆኚበት አይነት..እነሱ መረዳት ስለሚጎላቸዉ ምናምን ሳይሆን በቃ ስለማትችይ ...ልክ እንደ ባለበገናዉ ቅዱስ ዳዊት "እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑ!ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ"ማለት ሲያምርሽስ ራስሽን አግኝተሽዉ ታዉቂያለሽ...ያለሽበት የጠፋሽበት የተደበቅሽበት መጥቶ ከነጉድፍሽ እቅፍፍፍ ሲያደርግሽስ ተሰምቶሽ ያዉቃል...ቤቱን ቀና ብለሽ ለማየት አፍረሽ አፍረሽ ድንገት የመቅደሱ ዉስጥ አቁሞሽ ስታይዉስ..ደግመሽ ደጋግመሽ በመዉደቅሽ ቆሽሸሽ ሳለ ነጭ አልብሶ ከመቅደሱ አቁሞሽ በእጣን መዓዛ ሲሞላሽስ...ከጥጋቱ ተንበርክከሽ ያለቀሽበት ያ መድኃኔዓለም በሳቅ ሲሞላሽስ..አበቃልኝ እኮ ብለሽ ተስፋ ቆርጠሽ ሳለ ከባዶ ላይ መኖርሽን ቀጥሎ እዉነተኛ ተስፋ መሆኑን ሲያሳይሽስ..ዝብርቅርቅ ያልሽዋን አንቺን የሰላም ወደብ እርሱ እፎይታ ሲሆንሽስ...በቃ ብዙ እንደዛ ያለ ያልነገርኩሽን :የማልችለዉን:የማይገባኝን...ሁሉ አደረገልኝ..ድጋሚ ከተበታተንኩበት ሰበሰበኝና ሰራኝ..እንደገና እድል ሰጠኝኮ..🤍
አለችኝ...
https://t.me/yeesua_queen
አለችኝ...
https://t.me/yeesua_queen