✨የልደቴን ቀን በተለየ የጠበኩት እርሱ እንዲፅፍልኝ ነበር፨ድንገት ነበር መደብዘዝ የጀመረዉ...ቀስ በቀስ ነዉ አለመፈለጉን የጋተኝ...እንዳልሄድም እንዳልቆምም አድርጎ ከተወኝ በኋላ እንዲፈልገኝ እንዲያወራኝ ሰበብ ስጠብቅ በዚህ መኃል የልደቴ ቀን ደረሰ...እንዲያወራኝ ሰበብ ያገኘ ስለመሰለኝ በጉጉት ስጠብቀዉ ነበር...ከተፃፉልኝ ብዙ መዉደዶች መሃል ፈለኩት አልነበረም፨እንደማይረሳዉ አዉቃለሁ...ምን እንደተሰማኝ ታዉቂያለሽ...አስቦበት እንድተወዉ እየገፋኝ መሆኑን:የአለመፈለግ ገፁን ሲያሳየኝ እንዳልተረዳሁት:እኔን በማግኘቱ ዕድለኛነቱን እንዳልተረከልኝ ሰላም የነበርን ጊዜ ስለምወደዉ ስለቀኔ አከባበር ብዙ እንዳልተጨቃጨቅን ጣቶቹ ለእኔ መፃፍ ሲከብዳቸዉ ልቤን ዝቅ አደረገብኝ ...ዝም ነበር ያልኩት ዝምም...በዝምታ ሲገፋኝ በዝምታ ሔድኩለት፨
✍𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮
https://t.me/yeesua_queen
✍𝓮𝓶𝓾𝔂𝓮𝓮
https://t.me/yeesua_queen