ዝምተኛው የግጥም ቤተ-መጽሐፍ


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


አላማችን፦ ግጥም የተራቡ ነፍሶችን ከግጥም ባህር ምንጭ ማጠጣት

በዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI
የሁሉም ሰው ሀሳብ የሚንሸራሸርበት መድረክ
የሚያስቁ
የሚያስተምሩ
የሚያነቃቁ
ሀሳቦች መንሸራሸሪያ መድረክ

Related channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በቃላችን መሰረት አሸናፊዎች የሚለዩት በ reaction ብዛት ስለሆን የዚህ ዙር የውድድር አሸናፊዎች
:
:
:
1:-ተወዳዳሪ ፩------------- ሞረሽ
2:-ተወዳዳሪ ፲፪------------ቤተል

ይሆናሉ ማለት ነው።ሞረሽ እና ቤተል በውስጥ መስመር አናግሩኝ🙏
ከዚህ ሰአት ጀምሮ እኒህ ሁለት ድንቅ ገጣሚያን በቤታችን ሀሳባቸውን በነፃነት እያጋሩን አብረውን የሚዘልቁ ይሆናል።
በቤታችን ውስጥ ድንቅ ድንቅ ገጣሚያን እንዳላችሁ ለመገንዘብ ችያለሁ ሁላችሁም ክብር ይስጥልን🙏
በቀጣይ ለየት ባለ የውድድር መድረክ የምንገናኝ ይሆናል። ከዚህ ጋር በተየያዘም በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ስለ ስነፅሁፍ የምንወያይበት አለፍ ሲልም ታዋቂ እንግዶችን የምንጋብዝበት ነፃ መድረክ በቲክታክ ወይም በቴሌግራም ግሩፓችን የምናዘጋጅ ይሆናል።
✍ስለ አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን🙏


✍ ዝምተኛው ፀሀፊ


ሰላም ቤተሰቦች ውድድሩ በዚህ መልኩ ተጠናቋል ከደቂቃዎች በሗላ አሸናፊዎችን የምናሳውቅ ይሆናል ።


ሰላም ቤተሰቦች, እንዴት አላችሁ? ውድድሩ ሊያበቃ 32 ሰአታቶች ብቻ ይቀራሉ ። በእነዚህ ሰአታቶች አሸናፊዎችን ለመለየት ድጋፋችሁ አይለየን እንላለን።


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ፲፭
ልንገርሽ እማ

ፍቅር መፈቃቀር ቢሆንም ውበቱ
ለኔ ግን ማፍቀሬ ልዩ ነው በእውነቱ
አንቺን በማፍቀሬ እጅግ ታድያለሁ
ስላንቺ ለመሰብ ከቶ መች ደክማለሁ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ልንገርሽ እማ......

ዝም ብትይ ድንገት.....ምላሽን ባትሰጪኝ
ማውራት አልፈልግም....ብለሽ ብትቆጪኝ
ከቶ መች ሊጨልም....ፍቅሬ ላንቺ ያለኝ
እንደውም ልንገርሽ.....እንደዛ ስትይ
ጨመረብኝ ፍቅሬ....ከምችለው በላይ
በፊት ከነበረው....ተመንጥቆ ወደላይ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

አወይ አንቺ ፍጥረት......ምን አስነክተሺኝ????
ከልብሽ አዳራሽ.....በጠረባ ጣልሺኝ
አላቅም ምንድነው ስቦ የሚያመጣኝ
አንቺን አንቺን ብቻ እያለ የሚያማታኝ
መኳረፍ ሲመጣ ፍቅሬ ጫፍ ላይ ወጥቶ
የበፊቱን ነገር ወደ ሁዋላ ትቶ
ይመኛል ለመቅዘፍ የልብሽን ባህር
ተከፍቶለት ገብቶ ለመሰጠም እስከዳር

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ልንገርሽ እማ.......

እንደው ባታፈቅሪኝ ......እኔስ መች ተዋለው
የልቤን ብርሀን......እንዴት አጠፋለው
ሳት ብሎሽ ድንገት.... ቃላጥን ሳትመርጪ
ወይም አስተውለሽ....ደፍረሽ ብትቆጪ
አልወድህም የሚል....የሚዋጋ መርፌ
ቢሰማው ቢደማ.....ይሄ ሞኙ ልቤ

ይኸዉልሽ እማ....... ልጠላሽ አልችልም
አንቺን መጥላት ልቤ...ችሎታው አይደለም
ሲፈጠርም ገና አንቺን እንዳይጠላ......
ቂምን እንዳያዝል ፍቅሩም እንዳይላላ.....
ተደርጎ ተፈጥሯል.....ሀቅ ነው በእውነቱ
አልቀይረው እኔ......ድካም ነው በከንቱ

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ልንገርሽ እማ

ለኔም ይገርመኛል.....ስትርቂኝ ያመኛል
አንዳች ነገር ውስጤን.....ይሰረስረኛል
እንጃ ምን ልበልሽ....ሽንፈቴ በዛና
አልፈልግም ስትይ....ፍቅሬ ገነነና
እንደገና መውደድ....አሁንም አብልጦ
ቅኔውን ለመዝረፍ....ሁሉንም ገላልጦ
እንደገና ማፍቀር.....አንቺን አንቺን ማለት
ብታኮርፊም እንኳን....እጎንሽ መቀመጥ
እንደገና እንደ አዲሰ......ፍቅርሽን ማለምለም
የሚታየኝ ይህ ነው....አንቺን ብቻ ማቅለም


እንታረቅ🥹🥹

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

✍ ብሩክ ተፈራ


አነሆ ውድድሩ ከተጀመረ አምስት ቀን አስቆጥሯል። ተወዳዳሪዎችም ድጋፍ መሰብሰባችሁን ተመልካቾችም ድጋፍ መስጠታችሁን አትዘንጉ።

መልካም ቀን🙏


ዝምተኛው ቤት
ተወዴዳሪ ፲፬

ሴት ልጅ ናት


ቆንጆ ናት ድንቅ ውበት አምላኳ ያደላት
ለትዳር አስቦ ወንድ ሁላ የተመኛት
ስስት ናት ለእናቷ ስስት ናት ላባቷ
ቤት ያበራ ነበር ስትስቅ ፍካቷ
ያ ለፍቅር ያሰባት ያጫት ለትዳር
ሴት አያውቅም መሰል አልሰጣትም ክብር
ያለው መሰል እናት ምጥን ያስጎበኛት
የለው መሰል እህት ወንድሟ የሚሆናት
አያውቅም መሰለኝ ሴትን በህይወቱ
አላስተማሩትም ክብርን አባቱ
በር ዘግቶ መታት ፊቷን አበላሻት
ለሰው እንዳትነግር በሀይል አሰፈራራት
ደሞ ይባስ ብሎ ሳይበቃው ማቁሰሉ
ዋሸበት በሞቷ አኮራው መግደሉ
አለም ስለሰጠው እውቅና በዘፈን
እውነትም ገደላት አለበሳት ከፈን
ብዬ ልፈርድብ ልቤ ይነሳሳል
ስለ እውነቱ ከቶ ማን ያውቃል
መግደልስ ሀጥያት ነው
ማንም የማይወደው
ከ10ቱ ትዕዛዛት 1ዱ አትግደል ነው
ፈጣሪ የፈጠረው ፍጡር አትንጠቀው
ይብቃን ማልቀስ ይብቃን ፍርድ ማጓድል
በዚ ይቁምልን የሴት ልጅን በደል
ፈጣሪሆይ እርዳኝ እንዳላይ ስቃይ
እኔም ከፍጥረቱ ሴት ልጅ ነኝ አገልጋይ
የቤቱ ድምቀት እንደሻማ ቀልጣ ምትበራ
ሴት ልጅ ናትና ሀገር ምታስጠራ
አቤቱ ማረን ከዚ ሴጣን ስራ
ሳናውቅ ነውና ምህረትህን አብዛልን አደራ።


@HasuCEO12

ሀሱ ፍልቅልቋ😂😂😂😂😂


N.B👉ውድድሩ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ👌


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፲፫
ልብ ደክሟል
ነበረች ለመባል አንድ እርምጃ
ኖረች ለመባል አንድ ወደ ሗላ
ተረት አልባ ሞት አናት ላይ
ጥላ ገለ ፀሀይ ስታይ
አቤት አይዞሗ ማማሩ
እንባ ማበሱ ሀዘን መጠውለጉ


በሳቋ ያደረቀቻቸው የህዝብ ሁሉ እንባ
ከሷ ተጣመዱ ከደጇ ስትገባ
በጆሮዎቿ የገደለችው ብሶት
ይበቅላታል በእጥፍ ፈገግታዎን ጥሶት


ልብ ደክሟል
ነጠላ ሊደፍ ድንኳንም ሊጣልላት
እሷም እንደ ሰርግ ወግ ደረሳት
ይሰማታል መሰል ከአፈር አዋደዳት
የገደላት እንባ ሙሾ ወረደላት

✍arsema


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፲፪
❤️❤️_ፍቅር ያዘኝ እንዴ _💖💝

የማላውቀው ስሜት እየተሰማኝ ነው
ከልቤ ላይ ይሆን ወይም በአምሮዬ
ምክንያቱ ምንድነው።🤔
በጡቶቼ መሀል አለ ድብቅ ስሜት
እሱን ምገልፅበት አጣውለት ቃላት😟
አንድ ሰው እንዳለ ልቤም ይነግረኛል
በግልፅም ባላውቅም ስሜቱ ታውቆኛል።😊
ሳየው ገና ልጁን ልቤ ከሁለት ተከፎሎ
ልዋጥሽ ይለኛል😮
ቆንጆ ልጅ አግኝቶ ይጫወትብኛል።
ወደ አንዲት ክፍል ያመላልሰኛል 🏠
ሳላየው ከዋልኩ ልጁ ይናፍቀኛል።🥹
እስኪ ልንገራቹ ስሙኝ እማ አንዴ
ስሜቱን ሳላውቀው ፍቅር ያዘኝ እንዴ።🤔
የማስበው እሱ የሚታየኝ እሱ
አንዴ ይምጣ እንጂ አልለይም ከሱ።🙅‍♀️
በእጆቹ እጆቼን አጥብቆ ሲይዛቸው👫
አይኖቹ አይኔን አለቅም ሲላቸው
በከንፈሩ ጉንጮቼን ደጋግም ሲስማቸው💋
አፌ እና አንደበቴ ሚናገሩት ጠፍቷቸው።
ሲርበተበቱ ሳይ ፍቅሬ እየጨመረ😍
በድንገት አንድ ሰው ልቤ እሱ ጋር ቀረ።😔

✍betel


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፲፩
ማነው ተጠያቂ
--------------------

ማነው ተጠያቂው
አሁን ላለንበት
በማን ላይ ልደንፋ
ማንን ልውቀስበት

ላልቅስ ልነፋረቅ

አታልቅሺ አትበሉኝ
እንዳይልሽም ቅር
መደብደብሽን ዋጥ
መጠላትሽን ፍቅር
አትበሉኝ

ለምን አላለቅስም
እንዴት አይለኝም ቅር
ሴት ልጅ ተበድላ
ተገፍታ ስትቀር

ለምን አልከፋ
ለምን ልቤ አይዘን
ፍትህን ሳላገኝ
ጠባሳዬ ሰይድን

እንዴትስ አልተክዝ
እንዴት አልጨነቅ
ፈራጅ ዳኛ ጠፍቶ
ሁሌ ስንሳቀቅ

ምንም ማድረግ ባልችል
አቅሙ ባይኖረኝ
ተጠያቂም ባይኖር
ፍርድንም ባላገኝ
ተውኝ በቃ ላልቅስ
ድንገት ከቀለለኝ ።
==========
......✍ 𝔂𝓮𝓻𝓸𝓼𝓮𝓷


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፲
@  ያንችን ትርጉም ፍለጋ

  ያቺ እርጉዝ ጨረቃ
         በሰማይ ማማ የተንጠለጠለች
እያነከሰች መታ
   ለኔ እንዲህ ስትል ተናገረች
  " ስማኝ ወዳጄ አድምጠኝ አንዴ
ብዙ ጉድ ይዟል ይህ ራብተኛዉ ሆዴ             

ያቺ  ልጅ ያቺ ሸጊቱ
                  ያቺ አማላይቱ
ምን አስባ እንደሆነ እንጃ
      ዉበታችንን አደረገችው ከንቱ
እሷ ጨረቃ ሆና
      ጨረቃ መሆን ዛሬ ለኔ ቀረ
አባታችን ፀሐይ ዘንድሮ ከሰረ
ዉበቷን(ያንቺን) ተጎናጽፋ
   ተዉባ ተገኘች እቺ ብኩን ምድር
ጨረቃ የምል ጠፋ
ስሟን ደገሙት እንዴ ዳዊት የምድር ሕዝብ የሰዉ ክምር"
እንድህ እያለች
  ጨረቃ ተንሰቀሰቀች
እርር... ብላ አለቀሰች
   አላባበልኳት
          ቱ...ፍ  በይ አላልኳት

ወደ ላይ አየዉ ወዳረጀዉ ሰማይ
ስያንኮራፋ አገኘሁት የሸበተዉን ፀሐይ
               .....  .......   በዙፋኑ ላይ
.... ጠየኩት ቀርበ  ስላንቺ ጉዳይ
ከሰመመኑ ነቅቶ እንድህ ስል መለሰ
..............  እንድህ ተናገረ
በኮልታፋዉ አፍ ምናምን ቃላትን  እየሰባበረ
ስማኝ አንተ ልጅ
       .......    አንተ ጉደኛ
እንደት ብትታደል ነዉ የሆንከው
     ....  የዛች ልጅ ጓደኛ
በመንበረ ሆኜ ምድርን ሳይ
እሷ ኮ ነች ደምቃ የምትታይ
የአይኗ ብርሀን ምድርን አካሎ ደመናን በጥሶ
እስከ ሱራፈል ሱባኤ እስከ አምላክ ፀባኦት
ይታያል ሰማይን ጥሶ
....................
    እንድህ አለ እንድህ አወራ
  ቦታዉን እንዳትነጥቂ እጅጉን ፈራ

እዉነት አለዉ ቃላቸዉ አልተሳሳቱም
........ ስላንቺ ግን ብዙም አልገለፁም
  ስለዚህ እኔ....
በሀሳብ አለም ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በወረቀት ላይ ሀሳቤን ልወልድ እጅግ ተዳክሜ

ስንኝ ቋጥሬ አንችን ለመሳል በግጥም
ከሆሄያት ገበታ ፍደላትን ብመርጥም
አንችን ልገልጹ ግን በፍጹም አልቻሉም
..... እነዚህ አንካሳ ቃላት
              ጎባጣ ፍደላት ሆኑኝ ምናምንቴ
ስላንቺ ለመጻፍ አድስ ፍደላት አስፈለጉኝ
............  ኧረ ምን ተሻለ በሞቴ
ስለዚህ ረገምኳቸዉ እነዚህን ውዳቂዎች
                           እነዚህን አላቂዎች
ጓዛቸዉን ጠቅልለው በረሃ ይሰደዱ
... ይፈናቀሉ ከሆሄያት ገበታ
ማረፍያ አተዉ ዳስ ይለምኑ ተሰልፈዉ በተርታ
አ ቡ ጊ ዳ.. እድሜዉ ይጠር
    ...................  ይዉጣ ወደ ጎዳና
ለዘር የምሆን የስምሽ ፍደል ይቅር
                            ...... ይጻፍ በብራና
......የኔ ፀሐይ የኔ የቀን ጀምበር
ስላንቺ ብዙ አለኝ ብዙ የምነገር
..  አንቺ ፀሐይ ነሽ የብርሃን ጮራ
አምላክ እንደታየበት እንደ ቅዱስ ተራራ
..
ፊንድቅድቅ ስትይ ስትሽኮረምሚ
ስትስቂ አይቶሽ ማን ይተርፋል ከአላፊ ከአግዳሚ
የጥርሶችሽ ጸዳል የፊትሽ ፊካት
ወጌሻ ያልቻለውን ያክማል የልብን ስብራት
..........የአራዊት ጩኼት
  የወፎች ዝማሬ ባንቺ ሳቅ ተዋጠ
ከቢራቢሮ ቀለም ከአበቦች መአዛ
   ................  ያንቺ እጅጉን በለጠ
...................................
......
   ..........
          .......... አንቺ ማለት
               ፀሐይ ነሽ
                        ጨረቃ ነሽ
                                   አለም ነሽ


.............✍ Daviopia 📝


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፱

ያደናገረን.... ያመሳቀለን ....እንደው የኛ እጣ
ከየት ጠፍቶ ነው ....ከየት የወጣ
ብቅ.. እልም...
ደሞ እያረገን ...ባሳብ ስልምልም
እስከመች ይሆን ...የምንከራርም



ያገናኘን... ያስተያየን.... ድልድይ ግንቡ
አለያየን... ከፍቶ ልቡ
ስንተያይ ሳንጣገብ... በፍቅር ወጀብ
አለያየን... ሊያስብል አጀብ
የከረመ... ድብቅ ፍቅር ተንተርሰን
ባሳብ ታየን ...ጉድጓድ ምሰን




ለመደበቅ... ለመታመቅ ...እንዳይለየን ያለም ድንበር
ወይ እንዳንወድቅ... ክንፍ ዝሎ ካፋፍ ስንበር
ተጋርጦብን... ያገር ቋጥኝ የኛ ነገር እድል ከንቱ
በሁለት ቃል... ሲጠፋብን የፍቅራችን ስር እትብቱ
ሲሰለስል... አይበጠስ ወይ ዘልቆ አይደርስ
እኔም አለሁ... እሱም አለ ካሳባችን ሳንዳረስ



ለምን ይሆን.. መልስ የለንም እንጃ
እንደው በትዝታ ...መቸ ዳሶት ፍርጃ
አለ ያልነው... የለም... የሰራነው ፈርሶ
የሄድንበት... መንገድ ባቧራ ተምሶ
ሳቃችንም ሙቷል.. ትዝታው ተወርሶ




አቤት የኔ ነገር ...አቤት የሱ አቤቱታ
መንገዳችን... አደናግሮን ሲሆን መንታ
ይሄው አለን...
እያለቅን ...እያነስን ...እየራድን ...ሁነን በድን
ለጭንቅ እንጂ.. ላሳብ እንጂ... መች ወደድን
ብቻ ...
ናፍቆታችን... ሲበረታ
ፍቅራችንም.... ጠፍቶት አቻ
ያሳየናል... እልፍ ፅልመት
መለያየት ወይ መታየት

✍jessi


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፰

የህልሜ ንግስት

የዛኔ ሳገኛት አይኗ ቃል ነበራት
ስትመለከተኝ አተኩሬ ሳያት
ወደድኩህ የሚለኝ ፈለኩህ የሚለኝ
ከንፈርሽ ጣዕሙ ይጥማል መሰለኝ
ብቻ.... የዛኔ ሳገኛት ከንፈሯም ቃል ነበር
ትተኧኝ አትሂድ ካላንተ የለኝም የቤት አባወራ
ይዘኧኝ ጥፋና ስለፍቅር እናውራ
የሚል ቃል ነበር ቀጥርሶቿ ማየው
ፈገግታዋ ቃል ነው ስትስቅ መግባቢያ
ልቤን የምታሳርፍ የሰላሜ መግቢያ
ደሞ የፀጉሯን እርዝመት ልብ ብዬ ያየሁት
ስትሽኮረመም ነው ስትደባብሰው
ፀጉሯም ቃል አለው እንደ ብዛቱ እና እንደ እርዝመቱ
አበጥረኝ ይላል ሳይወጣ ከእግቱ
ባበጠርኩት እና ዳብሼያት ባረፍኩት
ቃል በሌለው ቃል ላይ ስንቱን ሕልም ቃኘውት
ደግሜ ሳያት አይኔ ተነከራቶ ከደረቷ አረፍኩ
ምቾት እንዲያንቀላፋኝ ምነው ካንቺ ባረፍኩ
ቃል ሳያወጣ ተንተራሰኝ ይላል ደረትሽ ደርባባው
እንደው በቻልኩና ወግ ባህሉን ትቼ ከቤትሽ በገባው
የዝምታ ቃልሽን ደግሜ እየሰማው
እናማ ስላችሁ የዛኔ ሳገኛት ቀድሜ የዳበስኩት አለንጋ ጣቶቿ እጇ ቃል ነበራት
ገፅዋ ማይጨበጥ ተዓምረኛ መልክ
በእግዜር የተሰራች የፈጣሪዋ መስክ
ግና የዛኔ ሳገኛት ቃሏ ዝም ነበር
ድጋሜ ከመጣች አግኝቻት እንዳድር
የህልሜን ንግስት ስትመጣ ካያቹህ
መንገድ ተሳስታ ነው ወደኔ መልሷት አደራ ባካችሁ : :

@amanumoon


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፯
ከርታታው ናፋቂሽ
እንደምን ልሁነው ከርታታው ናፋቂሽ
ያንቺውን ባላውቅም አለውስናፍቅሽ
አንቺ የኔፍቅር የአይኔብሌኔ
ካንቺ ተራርቆ አልቻለውም ጎኔ
መልካም የፍቅር ሰው የትይሆንያለሽው
አቅጣጫሽ ጠፋብኝ የትብዬ ልፈልገው
እኔ ያንቺ ወዳጅ ከልቤ አፍቃሪሽ
በየሰከንዳቱ አለው ሳስታውስሽ
ምኑን ከምን አድርጌ እንደምን ልዝለቀው
ካላንቺማ ሕይወት የማይታሰብ ነው
ያይኔ ላይ ብሌኔ የልቤ ትርታ
ስላንቺ እያሰብኩ አለው በቀንምበማታ
ሕይወት ከብዳኛለች አንቺ የሌለሽበት
ካላገኘውሽማ እኔ ምኑን ኖርኩት
የሄድሽበት እለት ቀርቶ ትዝታሽ
በሃሳብ ይወስደኛል ሃያሉ ናፍቆትሽ
አንቺ እንዴት ይዞሻል ተራርቆ ኑሮ
እኔ ጋር አንድነው አምናውም ዘንድሮ
ከኔበላይ አንቺን አንቺንም ከራስሽ
በፈለግሽው ልማል በጣም ነው ምወድሽ
እንደው የመጣሽ ቀን የሚኖረኝ ደስታ
ዝም ብዬ ስስምሽ አልሰጥሽም ፋታ
የምታምሪ ሴትነሽ የልቤላይ ንግስት
አንቺን ሳገለግል ልኑር እስከ ህልፈት
ከሴቶች ሁሉ አንቺ ትለያለሽ
ሁሉንም በባህሪው ታስተናግጃለሽ
በቀንም በማታ መምጫሽን እጠብቃለው
እስከዛላለም ቢሆን እታገስሻለው
በሰላም ወተሽ እንድትገቢ ሁሌም ፀልያለው
ከልቤ ከከንጀቴ በጣም እወድሻለው አፈቅርሻለው


@Neba Hubi


መኖር ባለመኖር ሳይኖር ካኖኗረን
የሚበላ ሞልቶ
የአጎራረስ ስልቱ ጠፍቶ ካስቸገረን

መኖር የፈለገ ሞቶ ከታበየ
ስጋ ጥብስ ያማረው
ጎመን ከገበየ
ደላላው ጰጵሶ ቄሱ ከደለለ
ከዚህ ከኛ ቀየ አለ የጎደለ

ጠቢብ ሞልቶአል እና
ከዚህ ከኛ መሃል
በዛም በዚህ ብለን
የጎደለብንን ስንፈልግ እንዋል
😔😔😔 መልካም ቀን🙏

✍ዝምተኛው ጸሃፊ
@belay_HI

N.B👉ውድድር ዛሬም እንደቀጠለ ነው

https://t.me/yegitimedrek


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፮
.....እጠብቅሃለሁ ......

ታስታውስ እንደሆን ትዝታን ካልረሳህ
አምና በዚ ጊዜ ስለትዳር ሳወሳህ
እኔ በቬሎዬ አንተ ደሞ በሱፍ
ከሁሉም ከፍ ብለን በደመና ስንከንፍ
.........................
ሚዜዎቻችንን መርጠን አዘጋጅተን
ወጪውን ደምረን ቀንሰን
የሰርጋችንን ቀኑን እየመረጥን
በቁርባን💒በዘፈን🎵ብለን ተጨቃጭቀን
ከቶ አይመስልምነበር የምንቀር ተጣልተን
...........
ማነው ተወቃሽ የማን ነው ጥፋቱ
ይሀው በሰርጌለት አልተወኝ ጭንቀቱ
ላገባ ነው ብዬ የነገርኩህ ለታ
መጣለው ነበር መልስህ ተሞልተህ በርጋታ

ይሀው እየጠበኩህ ነው ቀሚሴን ለብሼ
ሐዘኔን በሳቅ እባዬን በሜካፕ ደብሼ
አትቀርም አይደል?ከንቱ አይቅር ሕልሜ
ሙሽራዬም ባትሆን አጃቢ ሁንልኝ አለሜ

የፀጋዬን ዘፈን ከቶ እንዳትሰማ
አጣዋትኝ ብለህ ፍፁም አትድማ
በድኔን ነው የዳርኩለት እንጂ
ልቤ አንተ ጋር ናት ፍፁም እስካረጅ

እ
ጠ
ብ
ቅ
ሃ
ለ
ው 👰🙏
✍️SK


ቤተሰብ ለተወዳዳሪዎች ድጋፋችሁን አሳዩአቸው👍


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፭
#እንሁን
.
.
ከትዝብት ድባብ አፈትልኬ ላመልጥ፣
የውስጤን ላወራ ላለማለት ፀጥ፣
በመዳፌ እፍኝ ጣሳ ስጨብጥ።


ልረሳሽ ስል ሣልጠራሽ ምትመጪ፣
የትዝታ በትር ሆነሽ እኔን ልትቀጪ፣
ለበደልኩሽ ካሳ መልስ ልትሰጪ።

በአይነ ህሊናዬ ምስልሽ ተቀረፀ፣
የፈረሰው ትዝታ በጠላዬ ታነፀ።

ምነው
      ድንቅር አልሽ ከፊቴ፣
      ምን ተሻለኝ እቴ።

        ያኔ......

ስለ ፍቅር እንዲያ እንዳላልሽኝ፣
ለበደሌ
ብድር በምድር አልሽኝ።

ፍቅር እኮ
      በደል አይቆጥር ካሳ አይጠይቅ፣
       መስጠት እንጂ መቀበል አያውቅ።

                ስሚኝ......

ክርስቶስ
ለበደው አዳም ህግን ላፈረሰው፣
መሻት ፈልጎ እብሪተኛ ለሆነው።
                ክሶታል፣
               ሞቶለታል።

ለተካደው አዳም
                    እምነትን ሊያድለው፣
ምቾት ላጣው ጎኑ
                      ምቾት ሊሰጠው።
.........ላፈሰሰው ላብ፣
.......ለተጎሳቆለበት ሂሳብ።

ተክዷል በጴጥሮስ፣
ተሸጧል በይሁዳ በብር ሱስ፣
ተፈርዶበታል በጲላጦስ፣
በደለኛው አዳም ሳለ ክርስቶስ ሊክስ።
ተሰቅሏል ተገርፏል አጥንቱ እስኪታይ ደሙ እስኪፈስ።

                በቃ.........

ክርስቶስን ምሰይ አዳም ባለ ተስፋውን ልሁን፣
ትንቢት ተናገሪ የመምጫሽን ዘመን፣
መቁጠር እንድጀምር ቀን።

            ካሳ ይሁንሽ መናፈቄ ለበደልኩሽ፣
               መጠጤን አቁሜ ልጠብቅሽ፣
              ቀኑ መቼ ነው መምጫሽ።
              ታጥቤ በደሌን፣
              ቀን ልቁጠር የመዳኔን።

ትመጫለሽ
               ልጠ
                       ብቅ
                            ሽ??????
✍aman


Forward from: Kirubel Goshu


ዝምተኛው ቤት
ተወዳዳሪ ፬

20 last posts shown.

891

subscribers
Channel statistics