Ye Haybaw Mender


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


اللهم صلي عل سيدنا ونبينا وحبيبنا وشفعينا محمد 💚💚💚

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter


አሁን ላይ ፍልስጤም ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሁላችንም የሰማን ይመስለኛል ግን አስባቹት ታውቃላቹ በኛ ወንጀል ቢሆንስ እነዛ ምንም ማያውቁ ህፃናት እየተቀጡ ያሉት ??እእ አያሳፍርም አለም ላይ ሙስሊም ሞልቶ ግን ደሞ በዚህ ልክ ሙስሊም ሲሰቃይ ልብ አይሰብርም በአላህ ??አስቡት እኛ Film ላይ ምናየውን በ screen እንኳን ስናየው ሚዘገንነንን ህይወት ነው እነሱ እየኖሩ ያሉት የነሱ ሞተ የኛም ሞት ነው ዱዐ አድርገንላቸው የእውነት አሳስቦን አላህን ስለነሱ ለምነን እናውቃለን ወይስ Free Palestine ብቻ ነው ምናውቀው?? የእውነት ነው ምላቹ እነሱ አሁን ላይ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት በላያቸው ቤት እየፈረሰ አጠገባቸው የእናታቸውን ሬሳ እያዩ ነው ያሉት እኛ ሙስሊሞች ሀይላችን ዱዐችን ነው ምንም ማድረግ ባንችል ዱዐ ማድረግ ግን እንችላለን ስለዚህ ልክ እንደ ግዴታ ወስደን በዱዐ አንርሳቸው
አላህ ሆይ የፍልስጤምን ነገር አደራ!!!!!


እናቴ...........






በቃ ቃላት የለኝም ግን እወድሻለሁ 🥹🥹🥹


ለምንድነው ግን የኛ Future በአላህ እጅ ሆኖ ሳለ እኛ ቀን ከለሊት ወደፊት ምን ያጋጥመን ይሁን እያልን የምንጨነቀው??

ምን ሆነን ነው ግን ሞት በኛ ላይ የሌለች ይመስል አላህን እንዲህ ምናምፀው??

ቆይ ግን በምን ተማምነን ነው ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት በዚህ መልኩ ያራቅነው??

የተፈጠርንበትንስ አላማ ለምንድነው የረሳነው???


ፍቅር ግን ምንድነው??
የእውነት ሰዎች እንደሚሉት ነው??እስካሁን ትክክለኛውን ትርጓሜ አግኝታቹለታል??የተጎዱቱ ፍቅር በሽታ ነው ጎጂ ነው ብለው ሲያስፈራሩን ያልተጎዱት ደስተኛ የሆኑት ደሞ ፍቅር መድሀኒት ነው ብለው ይተርኩልናል so ሁሉም በራሱ ይተረጉማል እንጂ .....
ብቻ እኛ ምን እንላቸዋለን ..ፍቅርን ማወቅ ምንሻው በአላህ ነው ፤መጎዳት የለውምና ልክ ፍቅርን ያወኩት በአላህ ነው እንዳሉት......

💚💚💚💚💚💚


.....ሸብሸብ ያለ እጃቸውን ወደ አይናቸው ሠድረው እንባ ያመቀዉን አይናቸው ይጨምቁት ያዙ


ዛሬ ከጓደኞቼ ጋር ስለሆነች ርዕስ አነሳን እና ላካፍላቹ :-
አግኝቶ ስለማጣት ነበር እና ብዙ ጊዜ እንሰማለን እናያለን አግኝቶ ያጣ ነው ምናምን ሲባል አይደል ??ግን እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ አግኝቶ እንደነበር እኛ ኬት አወቅን መጀመሪያ ያ ነገር..በኛም ሊሆን እኮ ይችላል ያጣነው ነገር መጀመሪያስ የኛ ስለመሆኑ ምን ማረጋገጫ ኖሮን ነው ??አላህ የሰጠን እኛጋ እንዲቆይ ሳይሆን ለጊዜያዊ ቢሆንስ እእ የአላህን ተርቲብ እኛ ልናውቅ አይቻለንም አይደል ??ብቻ ሲሰጠን በቻ ሳይሆን ሲወሰድብንም እናመሰግን አውቃለው አግኝቶ ማጣት ይከብዳል ግን ሁሌም ማሰብ ያለብን መጀመሪያም የኛም አልነበረም by the way እናጣዋለን ብለን አስበን ማናቀውን ነገር ሲያሳጣን እናገኘዋለን ብለን ያላሰበነውን ነገር ሊጀባን ነውና ፏ በሉ ወደድንም ጠላንም አላህ ጥሎ አይጥለንም እና በቃ መጨነቅ አይጠበቅብንም ከኛ ሚጠበቀው በአላህ መተማመን ብቻ 😍😍
እናም ከጓደኞቼ ጋርም ማመስገን እንዳለብን ተስማማን....


እስቲ ሁላችንም አላህን እናመስግን እእ በሉ አልሃምዱሊላህ 😊😊 ለምን እንዳትሉኝ አላህን ለማመስገን ምክንያት አያስፈልገውም
Alhamdulilah for every thing😊😄😄


እኔ የሚገርመኝ አላህ ከደምስሮቻቹ በላይ ቅርብ ነኝ እያለን ስለ ብቸኝነት ስናወራ ነው ።

አጂብ እኮ ነን🙄🙄


በዚህ አህዋል መኖር መሞት ነው🥹🥹
(-kha-)


በሰለዋት በርቱ 😊😊

اللهم صل على حببينا محمد 💚💚


ለእያንዳንዱ ለምንፈልገው ነገር መታገል አለብን "If you want it work for it "ይሉ የለ??so በቃ የሚያደርገው አላህ ቢሆንም እኛ በምንችለው ሰበብ ማድረስ አለብን ይቺ ዱንያ ለደካሞች ቦታ የላትም ረጋግጣቸው ነው ምታልፈው እና እኛም ከተረጋጮቹ እንዳንሆን እንልፋ በቃ ቢያንስ የሆነ ነገር እንስራ እንትና ተወለደ አደገ ሞተ መባል ምንፈልግ አይመስለኝም ስለዚህ እኛ ካለፍንም በኃላ ማያልፍ ስራ ብንሰራ...እንዲህ እኮ ስላቹ famous እንሁን እያልኩ አይደለም ምናልባት ምናበረክተው ጥሩ ነገር ለfamily ሊሆን ይችላል ብቻ መብላት መተኛት አንሁን የሆነ የምንለፋለት ነገር እናዘጋጅ ፤የምንታገልለት ነገር ቢኖር ጥሩ ይመስለኛል

አላህ ያግዘን🤲🤲


ያአላህ
አንተን ይዞ የወደቀ አላየንም
ጠይቆህ ያጣ አልሰማንም
ያረብብብብ ብቻ በጣም እንወድሀለን🥹🥹🥹🥹


ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ እንግዶች ነን እንግዳ ማለት ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ወደራሱ መኖሪያ ሚመለስ ማለት ነው so እኛም ትክክለኛ መኖሪያችን እዚ አይደለም ማለት ነው እንግዳው የራሱ ያልሆነውን ቤት እንደማያሰራ ሁሉ ለራሳችን ላልሆነው ቤት የዚን ያህል ባንስገበገብ እላለው.....ብቻ ሁሌም እናስታውስ እኛ እንግዶች ነን መቼ እንደምንመለስ ማናውቅ!!


የሆነች ነገር ልንገራቹ:-
ለቤተሰባችን እየሰጠነው ያለው value እንዴት ነው??ትክክል ነው??የሚገባቸውን ቦታ እየሰጠናቸው ነው??ማድረግ ያለብንን ነገር እያደረግን ይመስላችኋል የምሬን እኮ ነው በጣም ያበዛነው አልመሰላቹም ?? ማለት ለነሱ መስጠት የነበረብንን ጉዜ ለሌላ እየሰጠን እንደሆነ ግን ልብ ብላችኋል እእ በጣም ሚቆጨን ጊዜ እንደሚመጣ ታውቃላቹ አይደል so በቃ መጃጃሉ ቢበቃን ጥሩ አይመስላቹም ዛሬ ከቤተሰብ በላይ ነው ብለን ያሰብነው ሰው የነሱን ሩብ እንደማይደርስ ታውቃላቹ አ ነገ ላይ ብንታመም ከነሱ ውጪ ማንም አጠገባችን እንደማይሆን ፤ለጊዜው ብቻ እንደሆነ ታውቃላቹ አ ብቻ ግዴታ ሁሉም በኛ ደርሶ ካላየነው አንበል የሌላው ህመም ለኛ በቂ ነው ብላቹ አታስቡም እስቲ ምንም ብንሰጣቸው ባይገባቸውም በምንችለው ግን እንሞክር እእ አይሻልም???


ዝምታ ሁሉን ይገልፃል😊😊😊😊


አንዳንዴ ብቻችሁን መሆን ተመኝታቹ ታውቃላቹ ??በቃ ከራሳቹ ውጭ ከማንም ጋር አትግባቡም ብቻቹን ብ..ዙ ታወራላቹ ትስቃላቹ አንዳንዴም ታለቅሳላቹ በህይወት መፈጠራቹ ከቶ አስጠልቷቹ ያውቃል ???እእእ በቃ the same የሆነ ቀን ማሳለፍ like ትላንትን እየደገማቹ ያህል ተሰምቷቹ ያውቃል ??የሆነ በቃ ብጮህ ይወጣልኛል ብላቹ አስባቹ ታውቃላቹ??ኡፍፍፍፍ ብቻ ግን ይደክማል 🥹🥹🥹🥹ግን አንድ ነገር ላስታውሳቹ አላህ ሁሉንም እየተመለከተ እኮ ነው እና ሚተወን ይመስላችኋል ??እእ አረ በቃ ፈገግ በሉ አላህ አለ 😊😊

መልካም ምሽት


አላህ እኮ የባሪያውን ልብ አይሰብረውም ወደ ራሱ ሊያስጠጋው ቢፈልግ እንጂ🥹

so Alhamdulilah ወላሂ 🙏🙏🙏🙏


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የምንናገረውን ነገር እንምረጥ!!🥹🥹


አንዳንዴ ትልቅ ቦታ የሰጠሀቸዉ ሰወች በህይወት ውሰጥ ማትረሳውን ትልቅ ህመም ሰጥተውህ ያልፋሉ ጥፋቱ የማን ነው ብለህ ታስባለህ???
ጥፋቱ ያንተው ነው ማንኛውም ነገር overdose ሲሆን effect አለው አይደል ??ያድንሀል ተብሎ የተሰጠህ መድሀኒት ከተባልከው በላይ ከወሰድክ ምናልባት የሞትህ ሰበብ ሊሆን ይችላል ተረዳሀኝ አይደል??ለሁሉም ነገር ገደብ ማበጀት አለብህ ማለት ነው ጎዱኝ ብለህ ከማልቀስህ በፊት ለምን ፈቀድኩኝ ብለህ ራስህን ጠይቅ 🙄🙄
የሁላችንም ጥፋት ምን እንደሆነ ታውቃላቹ:-ለአላህ መስጠት የነበረብንን ቦታ ነው ለመኽሉቅ የሰጠነው እና እንዴት ልባችን አይሰበር??እእእ እንዴትስ አንዘን ቢያንስ ካሁን በኋላ ባንሸወድ እላለሁ የእስካሁኑ ቢበቃን....
So በቃ አታለቃቅሱ ጥፋቱ የኛው ነው አላህን ለማወቅ ጉዞ እንጀምር
አይሻልም??????


አላህ ብሎ ማለት እኮ ልናምፀው በሩን ስንዘጋ በበሩ ቀዳዳ ምንተነፍሰውን አየር የሚልክልን ነዉ
አላህ ማለት እኮ ምህረት ማድረግ የማይሰለቸው ጌታችን ነው

እኛ ደግሞ ወንጀል መስራት ማይበቃን ባሮቹ....😞😞

20 last posts shown.

755

subscribers
Channel statistics