📚 ካነበብኩት ላካፍላቹ 📚
የደራሲ ፓውሎ_ኮኤልሆ የህይወት ተሞክሮ የቀጠለ.......
እራሴን ጠየቅሁ ፣ "ሽንፈቶች አስፈላጊ ናቸው?" ደህና! አስፈላጊ ሆኑም አልሆኑ ያጋጥማሉ ። ለመጀመርያ ግዜ ለህልማችን ዕውን ፍልምያ ስንጀምር ፣ ልምድ ስለሌለን አያሌ ስህተቶችን እንሰራለን ። የሕይወት ምሥጢርም ሰባት ጊዜ ወድቆ በስምንት መነሳት ነው።
ታድያ ከሌሎች ሰዎች የበለጠ የሚያሰቃየን ከሆነ ከግላዊ ጥሪያችን ጋርመኖር ጥቅሙ ምንድነው ? የዚህ ምክንያት እንዴት ሽንፈቶቻችንን ከተወጣን ምንግዜም እንደምናደርገው በታላቅ ሀሴትና በራስ የመተማመን ስሜት እንሞላለን ። በፀጥታ በተዋጠ ልባችን ለህይወት ትንግርት ብርቱዎች መሆናችንን እናረጋግጣለን ። እያንዳንዷ ቀንና ሰዓት የፍልሚያው አካል ናት። ከምንጓጓለትና ከምንደሰትለት ስቃይ ጋር መኖር እንጀምራለን። የሚቻል ከሆነው ሥቃይ ይልቅ ፣ ፅኑውና የማይጠበቀው ስቃይ ፈጥኖ ይጠፋል። የበፊተኛው ስቃይ ግን ከመራርነቱ እራሳችንን ነፃ ሳናወጣና ከቀሪው ህልውናችን ጋር በአንድነት የሚኖርበት ቀን እንደሚመጣ ግንዛቤ ሳይኖረን ነፍሳችንን እየበላ ለአያሌአመታት አብሮን ይቆያል ።
ወደ ህልማችን ጓዳ ዘልቀን ካልገባንና የፍቅርን ኃያልነት ተጠቅመን እንዲያብብ ካላደረግነው፣ አያሌ አመታት ከጠባሳችን ጋር ካሳለፍን በኋላ ድንገት ዘወትር ስንፈልገው የነበረው ነገር ምናልባትም ልክ በቀጣዩ ቀን እዚያው እየጠበቅን ያለ መሆኑንን እናስተውላለን። ቀጥሎም አራተኛው መሰናክል ይመጣል ፤ መላው ህይወታችን ስንፋለምለት የነበረ ህልማችንን ዕውን የማድረግ ፍርሃት።
"እያንዳንዱ ሰው የሚያፈቅረውን ነገር ይገድላል" ይላል ኦስካር ዋይልድ። ይህ ፍፁም ሀቅ ነው።
የሚፈልገውን ማጣት የተራውን ሰው ነፍስ በፀፀት ይሞላዋል ። የምንመለከተውም ማግኘት የሚፈልጉትን ማግኘት ያቃታቸውንና "ከምንፈልገው አንዱን ወይም ሌላውን እንኳን ማግኘት አንችልም ።" የሚል ስሜት የሚሰማቸውን ነው ። የተሸገረውን አሽከላ ፣ አብረን የኖርነውን ሥቃይ፣ ይህን ያህል ርቀት ለመሄድ ስንል የተወጣናቸውን ነገሮች በሙሉ ዘንግተናቸዋል። የግል ጥሪያቸው በእጃቸው ውስጥ በነበረ ጊዜ፣ ተደጋጋሚ ጅላጅል ስህተቶችን እየፈፀሙ ወደ ግባቸው ለመድረስ አንድ እርምጃ ብቻ ሲቀራቸው እርግፍ አድርገው የተው አያሌ ሰዎችን አውቃለሁ።
ከአራት መሰናክሎች ሁሉ ይህኛው እጅግ አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም ይህ መሰናክል ደስታንና አሸናፊነትን የሚያደባይ፣ ቅዱስ መሰል የእሾህ አክሊል ነገር ስላለው ጽኑ ፍልሚያ ካደረግህ፣ ያኔ የአምላክ መሣሪያ እየሆንክ ትመጣለህ። የዓለምን ነፍስ ከመረዳትህም ሌላ ለምን ወደዚህ ምድር እንደመጣህ ይገባሃል።
ከ ዘ አልኬሚስቱ
የተመቸው 👍
ያስተማረው 😇
ያልተመቸው👎
@yisakgizaw 15/1/2013