✍ዮኒ-ኣታን


Channel's geo and language: not specified, not specified
Category: not specified


ማሰብ ስታቆም ማመን ትጀምራለህ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
not specified, not specified
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ፍቅር ፡ ያልነካካው
ናፍቆት ፡ ያላቦካው
ንፁ ልብ እንዳለኝ
አሎዳትም እላለሁ ፡ መሄዷ እያመመኝ።

አልወዳትም !!

#በረከት_ሐ(ይሉ)

@Yonny_Athan
@Yonny_Athan


ለመጣ ለሄደው ከወገቤ ጉንብስ
እሱም ጥሎኝ እብስ
ለወደድኩት የምሆን ሟች
ባፍጢም ግንባር የምል ፍግም
እሱም ጥሎኝ ድርግም

የለኝ ምንም ዝና
አላፃፍኩኝ ኣንዳች ገድል
ቀርቦ መራራቅ ነው
መለየት የኔ እድል።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan


Forward from: Ephrem"Try to fly"
አንቺን ከፍ አድርጌ
በጥላሽ ልከለል ለማረፍ ፈልጌ
ምንኛ ቀን ነበር
ስላቺ ያሰብሁት


ስላቺ ያወራሁት
መቀመጥ ከእሾህ ስር
ጥላ የናፈኩት
በይ እንግዲህ ይብቃሽ
ስህተት መሆኔንም አሁን ነው ያወኩት


ያልተፃፈ ፅሁፍ ለንባብ ስጋብዝ
"ንፉግ......................ግብዝ"
ያልተቋጨ ሀሳብ ያልተሞነጨረ
ገና ከጅምሩ ተቀጭቶ የቀረ
    ሳሰፍር ሰሌኑ ላይ
          "ድንጋይ"
አውጡት አውጡት ብለው ወጥቼ ከመድረክ
ብሶቴን ሳካፍል "እሰይ ደግ አደረክ"
የህዝቡ ጫጫታ ሲቀልጥ የእጅ ጥፊ
ሳቀርበው ስቃዬን
              "ውረድ....ቀጣፊ ለፍላፊ"
ተሰምቶኝ ስስ ከንፈር እንባዬን ባራግፍ
            "የእጅህ ግፍ"
ባይበሉባ መዳፍ ጉንጬን ብዳብሰው
       "አስመሳይ ንፉግ ሰው"




ለዚ ብኩን ትውልድ ላልገባው ዝምታ
ገና ከጅምሩ ኑረው በሁካታ
ዶማን ዶማ ብለን ካላስረዳናቸው
      ጉዳቸው።
ሲቀላጠፍ ምሬት ከባዶ ገፄ ስር
አይቶ ካልተረዳው የለንም ትስስር
ሰሌን ላይ ያረፈው የቀለም ድብልቅልቅ
          ማየት ካልተቻለ
ቀለም ተከለለ።

ትርጉምን ለማይሰጥ ለበዛ ሆይሆይታ
የሁላችን መዳፍ በጥፊ ተመታ
ዝም ላለ አንደበት መፃፍ ለተሳነው
ወርደን አሳነስነው።

ያልተፃፈ ፅሁፍ ለንባብ ስጋብዝ
"ንፉግ......................ግብዝ"
ያልተቋጨ ሀሳብ ያልተሞነጨረ
ገና ከጅምሩ ተቀጭቶ የቀረ
    ሳሰፍር ሰሌኑ ላይ
          "ድንጋይ"

ደረጃችን ጎልቶ ኖርንና በርቀት
ለንባብ እንዲሆን
ብናስተላልፈው አንዲቷን ወረቀት
ላልተገነዘበን ላልተረዳን ከንቱ
    አይበቃም እውቀቱ
ሞንጭረን ላክንለት ከነወረቀቱ

ዮኒ
    ኣታን  @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan


ክራር እና ፍቅር
(ኤፍሬም ስዩም)

ትግስት በሌላት በጨከነች ሌሊት
ወዳጅ ለወዳጁ ደብዳቤ ፃፈላት
ከመፃፉ በፊት ...
ከጥቁር ሰማይ ላይ ሦስት ኮከቦች አየ
ለጥቂት ቅፅበታት ከከዋክብቱ ላይ ሀሳቡን አቆየ

አንደኛዋ ኮከብ እጅግ የደመቀ ብርሃን ትረጫለች
ሁለተኛዋ ግን ደመቅ ትላለች ካንዷ ትሻላለች
ሦስተኛዋ ደሞ እርሱን ትመስላለች
በሁለቱ መካከል ፈዛ ትታያለች

እርሱን ለምትመስለው ብዕሩን አነሳ
ሁለቱን ከዋክብት ልቡን አወረሳ
አሁንም ዳግመኛ ከመፃፉ በፊት
ከአንድ አመት ቀድሞ በርሷ የተፃፈ ደብዳቤዋን አየው
የደብዳቤው ሀሳብ የደም ዕንባ አስነባው
እንባው ማፍቀሯ ነው መፈቀሩም እንባው
የሀሳቧም ሀሳብ ለሁለት ዘላለሞች አፈቅርሃለሁ ነው

በትንሹ ታምኖ ብዙ ያልወደደ
ስለተፈቀረም ትንሽ ካላበደ
በትንሽነቱም ያልተወላገደ
ፍቅርን እንዴት ያውቃል እንዴት ይረዳዋል

ምን ነበር የፃፍሽው  ምንድን ነበር ያልሽው
የሆነ መስመር ላይ አስተውለው ብለሽ ከታች ያሰመርሽው
ፊደል እስኪጠፋው እጁን ያሰርሽበት
የፍቅር ቀለማት የማይጠፉ ቃላት
የእውነት መገነዣ ሌላ ያንቺ እውነት
ያንቺ እውነት ፍቅር የርሱ ፍቅር ፊደል
ካፈቀረስ በቀር ፍቅርን ማን ይገልፃል
ማንበብ ክፉ ነገር መፃፍ መገላገል
ይሄ አይደል መታደል

ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
አስተውለው ብለሽ የሆነ መስመር ላይ ከታች ያሰመርሽው
ይልቅ ያን አስታውሰሽ የክራሩን ድምፅ አሰሚኝ
የዜማ ድምፅ ከዚያ ይውጣ
እኔም ክሩን ሆኜ ባንቺ ጣት ልቀጣ
እኔና አንቺ እንዲያ ነን በሁለት አንድነት ዝንት አለም የታሰርን በቅኝት ቢወጣ ጣት እና ክር ነን
ወይም ድምፅ እና ክር
ፍቅርን ጣት አርገነው ባንድነት ምንዘምር

ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
በፃፍሽው መስመር ላይ መብረቅ ፍቅር አለ
የዝናብ ድምፅ የለም ደመና ግን አለ
ከደመናው በፊት የደብዳቤሽ ቃላት
አንተ ማለት ባህር እኔ ማለት ትነት
በፀሀይ ፈገግታ ጨውን የምንፈጥራት
አንተ ማለት ጸጸት  እኔ ማለት መዳፍ
የቀደመ ዕንባህን ካይንህ ላይ የምገፍ
አንተ ማለት ጥማት እኔ ደሞ እርካታ
በበርሀ ንዳድ የምገኝ ጠብታ

ማንበቡን ቀጠለ
የመብረቅ ብልጭታ የዝናብ ድምፅ አለ
በጥቁር ደመና ቀድሞ የታዘለ
ደብዘዝ ያለ ብርሃን የማትታይ ፀሀይ
የተኳረፈ ፍቅር ያረገፈ አደይ
በሁለታችን አዝኖ የተከፋ ሰማይ

ይህ ሁሉ ቢሆንም
መዳፍሽ እርቋል
ጨውነቱም ጠፍቷል
ቃሎችሽ ሰክረዋል
በዚያ ታላቅ ዝናብ ምድር ስትቀጣ
በመብረቅ ብልጭታ ነፍሳችን ስትወጣ
እኮ በምን እግሬ ከደጃፍሽ ልምጣ
አንቺ እንደሆን ንግስት የመኳንንት ልጅ
ህንፃ ፍቅር ልብሽ ጉብዝናን የሚያስረጅ
እኮ በምን ሀይሌ ልርገጠው ያንቺን ደጅ
ማን በምን ጉልበቱ በየት ጀግንነቱ
ዝም ባለ ቅፅርሽ ያንቺ ጉርፊያ ነግሶ
ፊትሽን ፍራቻ ልቦናዬ ፈርሶ
በሳምንት ዘመንሽ ዐይኔ ደም አልቅሶ
እኮ በምን አቅሙ እንዴትስ ተደፍሮ ደጅሽ ይረገጣል
አይኑስ እንዴት ደፍሮ ዕንባውን ጠራርጎ ያንቺን ዐይን ያያል
ምን ነበር የፃፍሽው ወይስ እኔ ፃፍኩኝ
ከፍቅርሽ ላይ ወይን ደብልቄ ጠጣኹኝ

ፍቅር እና ወይን
የሁለት አንድነቱን የጣትና ክሩን
በስልት የተቃኘ ክር ድምፅነትን
ፍቅርን ጣት አርገነው በተነካን ቁጥር
በስሱ ከላይዋ እንደተመታች ክር
በራሳችን ቃና በራሳችን መዝሙር
ለዘላለም እድሜ ባንድ ተገመድን
ወይስ ምንም ሆንን
እውነት ምንም ሆንን

ዜማ ሰጭ ፍቅራችን ተበጠሰ ላላ
የኛ ቅኝታችን በኔነት ተበላ
ያለሙያው ገብቶ ያለመጠን ነክቶ
ያለስልቱስ ቃኝቶ
ክራር ፍቅራችንን ክሩን ማን በጠሰ
በምን አይነት ስልትስ ዜማችን ታደሰ

ከሐሳቡ ነቃ

በራሱ ክር ላይ የራስ ስልቱን ቃኘ
ለደብዳቤዋ መልስ ሊመልስ ተመኘ
ላንተ ያለችውን ላንቺ ብሎ ፃፈ
በራስ የቃል ስልቷ ቃሉን አከነፈ

ረስቶት ነበረ  ...
ከጠረቤዛው ስር በፅዋ ተሞልቶ ወይኑ ተቀምጧል
ጥቁር የወይን ደም ከፅዋው አንስቶ አንደዜ ጠጣለት
አንዱን ሳያጣጥም ፅዋዉ ወደቀበት
የፈሰሰው ወይን ልብሱን አረጠበው መሬቱን አራሰው
ፍንጥቅጣቂው ደሞ አይኑን አስለቀሰው
የብርጭቆው ፅዋ አልተሰባበረም
ሁሉም ፈሶበታል የተረፈ የለም

ለመፃፍ ከበደው
ደብዳቤው ቀፈፈው
መሬት አጎንብሶ እጁን ተንተርሶ
ስለሆነው ሁሉ ያስተውል ጀመረ

እንቆቅልሽ
የወደቀ ፅዋ ያልተሰባበረ
የፈሰሰ ወይን ባንድ ጉንጭ የቀረ
ያላለቀ ፅሑፍ በረቂቅ የኖረ
ያኮረፈች ፍቅር ደጇ የታጠረ
አራቱ ሚስጥሮች ሳይተረጎሙ ሳይመረመሩ
ባፍቃሪው ልቦና እንቆቅልሽ ሆነው ለዘላለም ቀሩ

@Yonny_Athan


አንችየዋ
ገላ መልክሽ ምን ቢኖረው
ቀልቤን ባንች ጣልኩት የትም:
አንዳች ነገር ቢኖር እንጅ
እንዲህማ ከቶ አልስትም:
         .
አውቀዋለሁ ይህን ልቤን
         .
ደንዳና ነው ከድሮውም
ማጥበቅ ያውቃል መሰረቱን:
ትንግርት ነው የሆንሽብኝ
ሲናፍቅሽ ምንተ'ፍረቱን:
እንዴት ሁኖ ምን ቢያይብሽ
ልቤ ልቡን የጣለብሽ?

@JahOnyx


ለወደድናት ሁሉ "አንቺዬ" እያልን ዜማ ሲሸበረቅ
ለናፈቅናት ሁሉ "ናፈቅሽኝ" እያልን ቅኔ ሲነፈረቅ
አመታት ነጎዱ ለሴት ብቻ ሲፃፍ
ልቦና ለነሱን ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ

ያለንን ክህሎት ለ አንቺዬ ሰጠን ብንፈራገጥም
ሴት ብቻ አይደለችም የፅሁፍ ውሃ ጥም
ምን ነበረ ግጥም???

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

@Yonny_Athan
@Yonny_Athan


ቃላት ተደርድሮ ሀሳብ ቢያመነጩ
ሆሄያት ተጨምቀው ስንኝን ቢቋጩ
የሀረግ ስብስብ ጥዑም ዜማን ቢረጩ
      ሰሚ አጠው ቢንጫጩ

ፋይዳ ካላመጡ
አንባቢን ካልቀጡ
ትምህርት ካልሰጡ
ሆሄያት ይቆጠብ ባዶ ገፁን አምጡ።

ዮኒ
     ኣታን       @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan


❤️‍🔥ግ❤️‍🔥
❤️‍🔥ጥ❤️‍🔥
❤️‍🔥ም❤️‍🔥


❤️‍🔥ለተወዳዳሪዎች ተላልፎ የነበረ የመወዳደሪያ ነጥብ:
"አንድ ሰብሉን ያጣ ገበሬ አንድ ጊዜ ሲያማርር አንድ ጊዜ ደሞ ሲያመሰግን የሚኖር ግራ የገባ ባህሪን ስለታቀፈ ገበሬ እስከ 15 ስንኝ ያለው ግጥም እስከ እሁድ ድረስ በተለመደው አካውንት አስገቡ።"❤️‍🔥


Forward from: ✍ዮኒ-ኣታን
#3
❤️‍🔥
አመድ አፋሽ ሆንኩኝ!!!
ትረገም ፀሀይዋ ይረገም ዝናቡ
ስራቸው ከንቱ ነው
ስለፋ ከርሜ ዘር ነስተውኝ ገቡ።
ሌት እንቅልፍ ተቀጣሁ ወፎች ቀሰቀሱኝ
ህሊናን እንዲዳኘን በጥሬ ከሰሱኝ።
ባዶ ሆንኩኝ ብዮ እኔ አንተን ስወቅስህ
ዛሬም ፃም አላደርኩ ትመግበኛለህ
የምትሰጥም ሆነ የምትነሳ አንተነህ።
ግን እስኪ ልመርምር ልጠይቅ እራሴን
ያበቀለኝ እርሱ ለፍሬ መብቃቴን።
ሀሳቤ ተምታታ ጠፋብኝ መስመሩ
አንድ ጊዜ ከፍጡር
አንድ ጊዜ ከእግዜሩ
ስጋጭ እውላለሁ ልቤ ገራገሩ።
❤️‍🔥
❤️‍🔥Ephrem❤️‍🔥


❤️‍🔥❤️‍🔥የ 1ኛ ዙር አሸናፊ የሆነውን ተወዳዳሪ ያሸነፈበትን ግጥም ከሰዓታት በኋላ ይለቀቃል❤️‍🔥❤️‍🔥


❤️‍🔥2ኛ ዙር የስነጽሑፍ ውድድር በቅርብ ቀን በዮኒ-ኣታን እንጀምራለን❤️‍🔥


🌟🌟❤️‍🔥❤️‍🔥 አዲስ ጅማሬ❤️‍🔥❤️‍🔥


1.
የተነቃነቀን አጠበቅን ብለው የሚቀጠቅጡት
በሀገሬው ምድር ህፃንን አብዝተው
ወልደው ያላረጡት።
ከጨቅላ መንጋጋ የእናት ጡት ወትፈው
ለቅሶን ሚያስታግሱ
መመገቢያ ቋቱን እሬት እየቀቡ ድግስ የደገሱ።
አፈር ስሆን ብለው በጥቅልል እንጀራ
ሚያጣድፉ ጉርሻ
ለታይታ ለወሬ እህል ለሚዘሩ በደረቀ እርሻ

እናመሰግናለን!

2.
ለፈሰሰ እንባ ከንፈር ተመጦለን አለሁኝ ለሚለን
አባሽ ያጣ አይን ደም ለብሶ ደም ቢያለቅስ
ዞር ብሎ ላላየን።
ለመሸበት ሯጭ አዳር ፈቅደውለት እንቅልፉን ቢያሸልብ
ከመተኛው ስፍራ ባንድ ከፍተውበት
ቀልቡን ላሳጡት ልብ።

እናመሰግናለን!

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan




……ህልሜን አደራ!
((በውቀቱ ስዩም))

ባይመረመሬ ፥ ጥበብ ተሽከርክሮ
ከወርቃማ ብርሃን ፥ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር ፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ ፥ ከህልሞቼ በቀር፤
:
የኔ ውድ እንግዲህ
ህልሜን እግሮችሽ ስር ፥ ከዘረጋሁ ወዲህ
ዝግ ብለሽ እርገጪ ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና ፥ የምትራመጂ።

°°°°°°° የማለዳ ድባብ  °°°°°°°



Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan


ታድለሽ

የሰብለ መመንኮስ
የዴዝዴሙና መኮሰስ
የሮሚዮን እንክርት
የጃክን መስዋዕት
በምዕናቤ እያሰብኩኝ
ደሞም ...
ባንቺ ቦታ ሲገቡ ሲያንሱብኝ
እያየው...ታድለሽ እላለው
ጨረቃ አይንሽን ለማጀብ የምቶጣ ሲመስል
ጥርሶችሽ ሊያበሩ ከንፈርሽ ሲከፈል
የምስራቋ ጀምበር
በሳቅሽ ስትደናበር
ምዕራቧን ትታ በሰሜን ስትበር
እያየው...ታድለሽ እላለው

Share
@yonny_athan🫧
@papa
mua✨


አንዳንዴ ህይወትን መቃኘት ያምረናል፣ሌላ ጊዜ ደሞ ያልጀመርናት ህይወት በተራራ አምሳል ትገተርብናለች...እንሰለቻታለን። ብዙ ጊዜ ከልቤ ላወጣሽ ሞክሬያለሁ...ሞኝ እና ወረቀት አይደል የሚባለው....ማልቀስ እፈልጋለሁ ግን አልችልም ወንድ ነኛ! ኩራቴስ! ...... መጮህ እፈልጋለሁ ደግሞ አበደ እንዳልባል እፈራለሁ...ጩኸትን ወደ ውስጥ ምን ያህል ይጎዳል?.....እረሳሁሽ እልና ውስጤን ማታለል እጀምራለሁ ግን አይሆንም...ስምሽ ሲነሳ ባንቺ ስም የተሰየመ ይመስል ጥርሴ አብሮ ይፈጋል...በቃ መሆኛዬን ያሳጣኛል....ደግሞ ኮስተር እልና "ጅል ምን ያስገለፍጥኻል እሷ እንደው አታውቅህም ከረሳችህ ቆይታለች በሆነው ባልሆነው አትገልፍጥ" እራሴ ላይ እሳለቃለሁ....በተዘፈነው በተዘመረው ያስተክዘኛል....እራሴ ጋር ሙግት ይዣለሁ...መነጫነጭ የቀን ቀለቤ ከሆነ ሰነባብቷል....ማፍቀር ሚሉት ትግል ምኑም አልጣመኝም...ደሞ እኮ ደስ የሚል ስቃይ ነው ተብሎ ይወራል ምኑ ነው ደስ የሚለው ባንቺ ምክንያት እራሴን ማጣቴ ወይስ ከ አንድም ሁለቴ ራሴን ለማጥፋት መሞከሬ የቱጋር ነው ደስታው....ምንም አልገባኝም ምንምምምምም።

ብቻ እንደፈለክሽ....ምርጫሽ ምርጫዬ ነው(እያረሩ ኑሮ አሉ!..) ግን ደህና ነሽ?......


ከ እገሌ ለ እገሊት

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan

20 last posts shown.

806

subscribers
Channel statistics