የዑለማእ ዚያራ ሳምንት
••••••••••••••••••••••
የሀበሻ ምድር ሀገረ ኢትዮጵያ ከምትታወቅበት ፀጋዎቿ አንዱ አንቱ የተባሉ የነቁ የበቁ ድንቅ የአላህ ባርያዎች መሻይኾች ሀገር መሆኗ ነው። ዑለማኦችን ማክበር፣ እውቃታቸውን መውረስ፣ ከነሱ ጋር አብሮ በመቀማመጥ በረካቸውን ማግኘት ታላቅ ሥጦታ ነው።
★ ስለ ዑለማእ ታላቅነት ቁርአን ሲመሰክር እንዲህ ይላል
√ «አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው» [ፋጢር:28]
(إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ)
√ «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ [ዙመር:9]
(قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ)
√ «አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል» [አልሙጃደላ:11]
( يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ )
√ «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን (ዑለማኦችን) ታዘዙ» [ኒሳእ:59]
(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ )
★ አሽረፈል ኸልቅ የፍጥረቱ ዓይነታ ረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ ዑለማእ ክብር እንዲህ ይነግሩናል
√ "እውቀት ፍለጋ ከቤቱ ለወጣ ሰው የጀነትን መንገድ አላህ ያገራለታል። ለእውቀት ፈላጊ መላእክት ክንፋቸውን ያነጥፋለታል። በሰባት ሰማይ በሰባት ምድር ያለው ፍጥረት ሁሉ በባህር ውስጥ ያለ ዓሳ ሳይቀር ለአንድ ዓሊም ምህረትን ይለምናሉ። አንድ ዓሊም ከተርታው ህዝብ ያለው ብልጫ ጨረቃ ከዋክብትን የምትበልጠውን ያህል ነው። ዑለማእ የነብያት ወራሽ ናቸው፣ ነብያት እውቀትን እንጂ ዲናርና ዲርሃምን አላወረሱም፣ ይህን እውቀት የሸመተ ትልቅ እጣ አገኘ።" ( አቢዳውድ ቲርሚዚይ)
فعن أبي الدرداء - رضي الله عنه -قال: سمعتُ رسول الله - صلى الله عليه وسلم - يقول: ((من سلك طريقًا يلتمس فيه علمًا، سَهَّل الله له طريقًا إلى الجنة، وإن الملائكة لَتضعُ أجنحتَها لطالب العلم؛ رضًا بما يصنع، وإن العالم لَيستغفرُ له مَن في السموات ومن في الأرض، حتى الحيتانُ في الماء، وفضلُ العالم على العابد كفضلِ القمر على سائر الكواكب، وإن العلماء ورثةُ الأنبياء، وإن الأنبياء لم يورِّثوا دينارًا ولا درهمًا؛ وإنما ورَّثوا العلم، فمن أخذه، أخذ بحظٍّ وافر))؛ رواه أبو داود والترمذي،
√ "በረካ ልቅና ያለው ከትላልቆቻቹህ ጋር ነው" (ጦበራኒ፣ ሐኪም)
وعن ابن عباس أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: البركة مع أكابركم. رواه الطبراني والحاكم، وقال صحيح على شرط مسلم
የነገው እሁድ ዑለማኦቻችንን ምንዘይርበት ሳምንት ነው። የአሽረፈል ኸልቅን መውሊድን ስናስብ ወራሾቻቸው ዑለማኦች ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛሉ። በመውሊድ ረሱልን ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ማስታወስ ማላቅ ከፍ ማድረግና ማፍቀር፣ የኢስላምን መልእክት ለዘነጉት ማድረስ፣ ማህበረሰብን በጥበብ ማስተማር፣ መንፈሳዊ እሴትን መፍጠር የቻሉት መሻይኾች ናቸው። ከእነሱ ጋር መቀማመጥ የዲንም የዱንያም የአኼራም ሃሳብ መለዋወጥ በቸገራቸው ነገር አብሽሩ ከጎናችሁ አለን ብሎ ደጀን መሆን ታላቅ እመርታ በመሆኑ የነገውን እሁድ በአካባቢያችን የሚገኙ ዑለማኦችን እና ታላላቅ ሽማግሌዎችን በመዘየር እንድናሳልፈውና የመውሊድን ማህበራዊ እሴት ከፍ እንድናደርገው ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር