ትልቅ ሰውን የሚያውቀው ትልቅ ሰው ነው:: ፊቱን ወደ አህሉሏህ ያዞረለት አሏህ ኸይር የሻለት ሰው ነው::
ሲሆን ልጃቸው ሁን አለዛ ጦሌያቸው
ቀርበህ እንድታሸት ተቡልቅያቸው
ቀርበህ እንድትሰማ ተሹኩሹካቸው
ቀርበህ እንድበላ ከበሉት እሳቸው
ዛሬ የነብያችንﷺ ቤተሰብ የሆኑት የሞሮኮው ሸይኽ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን አብዱልራሕማን አልማሊኪይ አልዓለዊይ አልመግሪብይ በሠይዲ ቤት ያደረጉት ዚያራ እጅግ ልዩና ውብ ነበር:: ለዚህ ያማረ ዚያራ መሳካት ሸይኽ ሸሪፍ የጨካ ሸይኽ ኸሊፋ ፣ ዑስታዝ አስለም ፣ ዑስታዝ ዐዲል ፣ ዑስታዝ ሙዘሚል ፣ ዑስታዝ ሸምሰዲን ፣ ዑስታዝ ሐቢብ ሌሎቹም ዑስታዞች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው ሰምቻለው::
ሸይኹ ከሠይዲ ቤት ሲደርሱ በታላቅ ተዋዱዕ በዐደብ "ሠይዲ" "መውላዬ" እያሉ ነበር የገቡት አሉ:: ገብተውም ዝቅ ብለው ውስጥ እግራቸውን ስመው ነው የዘየሯቸው:: ሠይዲም በተዋዱዕ በታላቅ ክብር ተቀበሉዋቸው:: ውሎው እጅግ ያማረ ፣ ብዙ ጥቅም የነበረው ፣ በአደብ በሙሓባ የተሞላ ብዙ ጉድ የነበረው መጅሊስ ነበር::
የአብሬትይ አልሳኒ ሁለት መንዙማዎች "ሸራበል ሙሓባ" እና ስለ አሕለል በይት ብዙ የሚለው "ሠይዱል ኢስጢፋ" በሙነሺድ ፉአድ መልካ እና አብዱ ተቀሩ ፣ እንዲሁም ከመናቂብ ፣ ከሚስባህ ፣ ከመጅሙዕ በዑስታዞቹ ተቀራ ፣ ከሠይዲ መድሆችም "ሰላቱሏህ" የሚለው መድህ ተቀራ:: እሳቸውም ልክ መንዙማዎቹን ከዚህ በፊት እንደሚያውቁት ሆነው አሸቁ::
ሸይኹ ስለመደሁት መድህ ኢንሻአሏ እመለስበታለው::