አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት/Addis Ababa Diocese


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ሚካኤል ወደ መንበረ ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ!!!
**********************************
(ጥር 13 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ)

በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በወጣቶች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሣ ወደ ኋላ ተመልሰው ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በጊዜያዊነት ያረፉት የወይብላ ቅድስት ማርያምና ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንበራቸው ክብራቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የተፈጠረውን ችግር በማረጋጋትና ምእመናንንም በማጽናናት ታቦታቱን ወደ መንበረ ክብራቸው የመመለስ ጉዞውን እየመሩ ይገኛሉ።


የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ: የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም እጅግ በርካታ ኦርቶዶክሳዊ ምእመናን በቦታው ተገኝተዋል።

የተፈጠረውን አለመግባባት ምክንያትና በክስተቱ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት አስመልክቶ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ሌሎች የቤተ ክርስቲያናችን ክፍሎች የሚሰጡትን ዝርዝር መረጃ ተከታትለን ከቆይታ በኋላ የምናቀርብ ይሆናል።


በመ/ር ሽፈራው እንደሻው


የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጥምቀተ ባሕር የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል በፎቶ


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፍ  አሳሰቡ !!!
**
                    (ጥር  11 ቀን  2014 ዓ.ም
                       አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ሁሉም ሰው ለሰላም የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለሕዝቡ ደህንነት እንዲሰራ  ጥሪ አስተላልፈዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህር ጥምቀት ላይ በድሬዳዋ እና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም በ ውጭ ጉዳይ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ በብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

መተው ነገሬን ከተተው በሚለው በአበው ብሂል
እና በበዓለ ጥምቀት አስተምህሮ ላይ ተመሥርቶ ሁሉም ሰው በእውነተኛ ንስሐ መንፈስ ቅራኔን፣ ጥላቻን፣ በቀልን እና ቂምን እርግፍ አድርጎ በመተው ወደ ቀደመ ፍቅራችን መመለስ እንደሚገባ ቅዱስነታቸው  አሳስበዋል።

የቅዱስ ፓትርያርኩን አባታዊ መልዕክት በንባብ ያሰሙት ብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ፓትርያርኩ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና በቅርቡ ሕክምናቸውን አጠናቀው ወደ መንበረ ፕትርክናቸው እንደሚመለሱ አብስረው፣ በዓሉ የሰላም: የአንድነትና የፍቅር ይሆን ዘንድ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

            በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!

1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese




በለቡ መብራት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

++++++++++++++++++++++++++++

ጥር 11 ቀን 2014 ዓ/ም
(አዲስ አበባ: ኢትዮጵያ)

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በለቡ መብራይት ኃይል አደባባይ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በባሕረ ጥምቀቱ እጅግ በርካታ ምእመናን ከዋዜማው ጀምሮ በስፍራው የተገኙ ሲሆን በዓሉ ሌሊት በማኅሌት ደምቆ አድሮ ንጋት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴውን ተከናውኖ በመልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥተዋል።

የምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ወቅድስት አርሴማ ወአቡነ አዳም አብያተክርስቲያናት ዋና አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ይርጋ "እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞአል" ዮሐ. 1:26 በሚል መነሻነት በዓሉን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል ።

በአሁን ሰዓት ታቦታቱ በበርካታ ምእመናን ታጅበው፥ በሊቃውት እና በወጣት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የዝማሬና የመዝሙር ምሥጋና ደምቀው ወደየመጡበት አብያተ ክርስቲያናት እየተመለሱ ይገኛሉ።


በመ/ር ኪደ ዜናዊ

ለተጨማሪ መረጃ የሀገረ ስብከቱን ማኅበራዊ ድረ-ገጾችን ይጎብኙ፣ like እና Join በማድረግ ይቀላቀሉ፣ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ!!!

1. ድረ-ገጽ:- www.addisababa.eotc.org.et
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- www.facebook.com/AddisAbabaDiocese/
3. ተሌ ግራም ቻናል:- t.me/AddisAbabaDiocese



Показано 6 последних публикаций.

1 166

подписчиков
Статистика канала