በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም በከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተጎበኘ፡፡
በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየተተገበረ የሚገኘው ፕሮጀክት፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የጤና ተቋማትን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በተለይም ዘላቂና አስተማማኝ መረጃ አያያዝ ስርዓታቸውን ለማዘመን እየሰራ ይገኛል፡፡ የተሻለ የመረጃ አያያዝ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት፣ ጥራት ያለውና አፋጣኝ የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ከጤና ጋር የተያያዙ ጉዳቶችን ለመቀነስ ወሳኝ ሚና አለው።
ፕሮጀክቱ የጤና ተቋማቱን የድንገተኛ ህብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ ሥርዓት ለማሻሻል በሰራው ሥራ ውጤት ማምጣት መቻሉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰዒድ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ ከወንድበላይ፣ ፕሮጀክቱ የጤና ተቋማቱ ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ የመስጠት አቅማቸውን ለማጠናከር እና በህብረተሰብ ጤና ችግር ምክንያት የሚደርሱ የሞትና የጤና እክሎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሁለት ዓላማዎችን ይዞ እየተተገበረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ዋና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አሳምነው ግርማ በበኩላቸው፣ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባህር አደም፣ ከማኀበሩ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ አንዱ መሆኑን ገልፀው፣ ፕሮጀክቱ የጤና ተቋማቱን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት በማጠናከር የድንገተኛ ህብረተሰብ ጤና አስተዳደርን በከፍተኛ ደረጃ እያሻሻለ ይገኛል ብለዋል።
ይህ ፕሮጀክት ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በተገኘ 12 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና በማኔጅመንት ሳይንስ ፎር ሄልዝ (Management Sciences for Health) ትብብር በሶስት ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለአምስት ዓመታት የሚተገበር ነው፡፡