መግለጫ
****
ማኅበሩ 20ኛ ብሔራዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 04፣ 2017 — የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር 20ኛውን ብሔራዊ ጠቅላላ ጉባኤ በነገው ዕለት ማለትም ቅዳሜ ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ያካሄዳል።
ማኅበሩ መደበኛ ብሔራዊ ጠቅላላ ጉባዔውን በየሁለት ዓመቱ የሚያካሄድ ሲሆን፣ የዘንድሮው ጉባዔ የማኅበሩን ያለፉት ሦስት ዓመታት (ከ2014-2016 በጀት ዓመት) ክንውኖች በመገምገም፣ የማኅበሩን ቀጣይ የሰብዓዊ ሥራዎች ወደ ላቀ እርከን ለማሸጋገር የሚያስችሉ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሰባቱን የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ንቅናቄ መሰረታዊ መርሆዎች በጠበቀ መልኩ የተጎጂ ወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ እና መከራ ለማቃለል ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ወደ 6 ሚሊዮን አባላትን እና 47,000 በጎፈቃደኞችን በመያዝ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች ሰብዓዊ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡ የዘንድሮውንም ጉባዔ ማኅበሩ 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር በዝግጅት ላይ በሚገኝበት ወቅት መደረጉ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ማኅበሩ ባለፉት ሦስት ዓመታት ዓመታዊ ገቢውን ከ750 ሚሊዮን ብር ወደ 2.5 ቢሊዮን ብር በማሳደግ፣ ወደ 16 ሚሊዮን ለሚሆኑ ወገኖቻችን በድንገተኛ አደጋ ምላሽ እንዲሁም በአደጋ ሥጋት ቅነሳና መልሶ ማቋቋም ሥራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ ለአብነትም በቦረና ድርቅ እንዲሁም በጎፋ የመሬት መንሸራተት ባጋጠመበት ወቅት ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ግንባር ቀደም ሚና ነበረው፡፡ በትግራይ ክልልም እንዲሁ በመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን፣ ይህን የመልሶ ማቋቋም ተግባር በሁሉም አካባቢዎች በሰፊው እያከናወነ ይገኛል፡፡ በአምቡላንስ አገልግሎት እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታም ወደ 900 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች በሚገኙት ከ70 በላይ ፋርማሲዎቹ እና መድኃኒት መደብሮቹ አማካኝነት በዓመት 6 ሚሊዮን የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የመድኃኒት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
የውጭ ዕርዳታ ጥገኝነትን በመቀነስ በሀገር ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ እና ማልማት ሥራዎችን በመስራት በገቢ ራሱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ጥረቶችን በማድረግ፣ በተለይም ለረጅም ዓመታት በገንዘብ እጥረት ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የቆየውን የፍልውሃ ሁለገብ ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በጋራ ለማልማት ስምምነት ላይ በመድረስ ፕሮጀክቱ ያለበትን የገንዘብ ችግር መቅረፍ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉትን ሀብቶች በማስጠናት የለሙትንና ያለሙትን በመለየት፣ ያለሙትን ሀብቶች ብሔራዊ ቦርዱ ከክልል ቦርዶች ጋር በመሆን የሚለሙበትን አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ባለፉት ዓመታት በሀገራችን የተከሰቱ ግጭቶችን መነሻ በማድረግ እየታዩ ያሉ ከሰብዓዊነት ያፈነገጡ ድርጊቶች ለመቅረፍና ቀጣዩ ትውልድም በስነምግባር እና በሰብዓዊነት መርሆዎች የታነፀ እንዲሆን ለማስቻል በማለም ‹‹የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት›› እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡
ማኅበሩ እነዚህን ሰብዓዊ ተግባራት ሲያከናውን ከሠራተኞቹ፣ አባላቱ እና በጎፈቃደኞቹ በተጨማሪ የአጋሮቹ ድጋፍም ከፍተኛ የነበረ ሲሆን፣ የንቅናቄው አካላት ማለትም አለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ አለም አቀፉ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን እንዲሁም እህት ማኅበራት የማኅበሩን ሰብዓዊ ሥራዎች በመደገፍ ረገድ የነበራቸው ሚና ወሳኝ ነበር፡፡ በርካታ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተቋማት ለማኅበሩ የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ በማድረግ ሰብዓዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡ መንግስትም ለማኅበሩ ሰብዓዊ አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር በተጨማሪ በየዓመቱ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ከ5 ሚሊዮን ብር ወደ 10 ሚሊዮን ብር በማሳደግ አጋርነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 260 ሚሊዮን ብር በመመደብ ከማኅበሩ ጋር በመተባበር በደቡብ ኦሞ ዞን በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ያደረገው ድጋፍ በማኅበሩና በመንግስት መካከል ያለውን አጋርነት ያሳየ ነው፡፡ በተጨማሪም የንቅናቄው አካላት ያልሆኑ አጋሮቻችን በተለይም የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID)፣ የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይና የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO)፣ የአውሮፓ ህብረት (EU) እና የአውሮፓ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅት (ECHO) የማኅበሩን የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽነት ከማስፋት አንፃር ጉልህ ሚና የነበራቸው ናቸው፡፡
ማኅበሩ የተጎጂ ህብረተሰብ ክፍሎችን ህይወት ለመታደግ አቅምና ብቃት እያለው በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት አስቻይ ሁኔታዎች ስላልነበሩ ፈጣን ምላሽ እንዳይሰጥ ተግዳሮት ሆኖበታል፡፡
በዘንድሮ 20ኛ ብሔራዊ ጠቅላላ ጉባዔ እያጋጠሙ ላሉ ችግሮች መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ማኅበሩ እንደሁልግዜው ግንባር ቀደም ምላሽ ሰጪ በመሆን በተለይም ለተጎጂ የህብረተሰብ ክፍሎች ያለውን አለኝታነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል፡፡ ጉባዔው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የበላይ ጠባቂ ክቡር አቶ ታዬ አጽቀስላሴ እንደሚከፈት ይጠበቃል፡፡