Matric Fetena


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


📑Matric Fetena የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት የሚያዩበትና ለፈተና የሚያዘጋጆትን ጥያቄዎች የሚያገኙበት ገፅ ነዉ።
🌏 ዉጤት ለማየት : @MatricFetenabot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




🛑በራስህ እመን!

ለራስ አነስተኛ ግምት አትስጥ! ፈጣሪ ለታላቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር ያመጣህ። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ነገ ከፍታው ላይ እንደምትወጣ ማሰብ እና ማመን ከዛ የምትችለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብህ!

ሰዎች ባንተ ከማመናቸው በፊት አንተ በራስህ እመን፤ ወዳጄ አሁን ያለህበት ሁኔታ ነገ የምትደርስበትን ትልቅ ቦታ አይወስንም። ሁሌም በምታደርገው ጥረት ታሪክህ ይለወጣል!

@Matric_Fetena
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑ዲስፕሊን ያስፈልግሃል!

ከልብህ መለወጥ ከፈለክ የሚያስፈልግህ ዲሲፕሊን ነው። ይሄ ማለት ደበረህ ደስ አለህ ካንተ የሚጠበቀውን ጥረት በየቀኑ ታደርጋለህ፤ ውጤትህ ከፍ ቢል፤ ዝቅ ቢል፤ አንተ ግን ታነባለህ፤ ታጠናለህ፤ ብዙ ጥያቄ ትሰራለህ።

ይሄ ጥረትህ ተጠራቅሞ ያሰብከው በሙሉ ይሳካል! ዳይ ጥረቱን አሁኑኑ ጀምር!

@Matric_Fetena
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑ምንድነው መቀየር ያለብህ?

በየቀኑ ተመሳሳይ ነገር እያደረክ ራስህን መቀየር አትችልም፤ ቢያንስ የምታጠናበት መንገድ መቀየር አለበት!

ትናንት የነበረው ፀባይህ፣ ልማድህ፣ ደጋግመህ የምታደርገው ነገር መቀየር አለበት! ያኔ ሰዎችን የሚያስገርም ለውጥ እና እድገት ማየት ትጀምራለህ።

@Matric_Fetena
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


🛑 ጊዜህን ተጠቀምበት!

ከፈተና በኋላ እንዳይቆጭህ ከፈለክ አሁን በደምብ ጊዜህን ተጠቅመህ አጥና፣ ጥያቄ ስራ። እስካሁን አልጀመርኩም ካልክ አሁን ጀምር! የምትችለውን ሁሉ አድርግ!

ግንቦት 6 ወር ብቻ ነው የቀረው፤ ካሁኑ ሳትዘጋጅ ኢንትራንስ ስንት ታመጣለህ? ያንተን ስኬት በጉጉት የሚጠብቁ፣ በጣም የሚወዱህ ሰዎች አሉ በዙሪያህ! ከሁሉ በላይ ለራስህ ስትል በየቀኑ ማጥናት፣ ብዙ ጥያቄ መስራት አለብህ!

@Matric_Fetena
ለውጥ አሁን ይጀምራል!


40 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተዋል

ለ2017 የመጀመርያ ዓመት የፍሬሽማን እና በ2016 በሪሜዲያል ማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎቻቸውን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች


👉1. Addis Ababa University - ገብተዋል
👉2. Adama ST University - ገብተዋል
👉3. Addis Ababa ST University - ገብተዋል
👉4. Salale University - ጥቅምት 21 እና 22/2017 - ገብተዋል
👉5. Kebri dehar University - ጥቅምት 25,26/2017 - ገብተዋል
👉6. Mizan Tepi University - ህዳር 2 እና 3/2017 - ገብተዋል
........................................................................
👉7. Hawassa University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉8. Haramaya University - ህዳር 9,10,11/2017
👉9. Raya University - ህዳር 2 እና 3/2017
👉10. Oda Bultum University - ህዳር 4,5/2017
👉11. Jigjiga University - ህዳር 7-9/03/2017
👉12. Dire Dawa University - 16 እና 17/2017
👉13. Kotebe University - ህዳር 4 እና 5 /2017
👉14. Ambo University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉15. Wollega University -  ህዳር 4 እና 5/2017
👉16. Aksum University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉17. Borana University - ህዳር 12 እና 13/2017
👉 18. Woldia University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉 19. Dambi Dollo University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉 20. Wolaita Sodo University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉21. Dilla University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉22. University of Gonder - ህዳር 12 እና 13/ 2017
👉23. Arba Minch University - ህዳር 7 እና 8/2017
👉24. Wollo University - ህዳር 13 እና 14/2017
👉25. Debark University - ህዳር 18 እና 19/2017
👉26. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉27. Debre Tabor University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉28. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉29. MizanTepiUniversity - ህዳር 11 እና 12/2017
👉30. Werabe University - ህዳር 19 እና 20/2017
👉31. Injibara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉32. Madda Walabu University - ህዳር 09 እና 10/2017
👉33. Mattu University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉34. Jinka University - ህዳር 11 እና 12/2017
👉35. Assosa University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉36. Bule Hora University - ህዳር 9 እና 10/2017
👉37. Gondar University - ህዳር 12 እና 13 2017
👉38. Bahir Dar University - ህዳር 16 እና 18/2017
👉39. Samara University - ህዳር 16 እና 17/2017
👉40. Wachemo University - ህዳር 19 እና 20/2017
..................................................................................
🎯Federal Technical and Vocational Training Institute  - ህዳር 3 እና 4/2017 ዓ.ም

N.B: ራያ ዩኒቨርሲቲ አራዝሟል - ቀኑ ህዳር 9 እና 10/2017

@Matric_Fetena


🛑ፉክክሩን አቁም!

ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም።

በራስህ ለውጥና ጥረት ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ።

አይንህን ከጓደኞችህ ላይ ነቅለህ ወደ ራስህ ባየህ ቁጥር እድገትህ ፈጣን ነው፤ እነሱ ቢያጠኑም ባያጠኑም አንተ ግን አጥና! ሌሎችን ለመብለጥ ብለህ ሳይሆን የተመኘኸውን ለማሳካት እስከምትችለው ልፋ!

መልካም ጊዜ ተመኘንላችሁ🙏
@Matric_Fetena


🛑አታመንታ!

ቁጭ ብለህ እንዲህ ባደርግ እንዲህ ቢሆን አትበል! አድርገው! ወደ ተግባር ግባ! ወዳጄ ባህሩ ላይ ማፍጠጥ አያሻግርህም ተነስተህ ጀልባውን መቅዘፍ አለብህ።

ከአልጋህ ተነስ፣ ስፖርቱን ስራ፣ መፅሀፉን አንብብ፣ አጠናለው ያልከውን ቀኑ ሳያልፍ ጨርሰው ፤ ወዳጄ የተግባር ሰው ካልሆንክ በሀሳብ መንሳፈፍ ነው ስራህ! ዳይ አሁን ጀምረው! ተነስ!

@Matric_Fetena


🛑የዕለቱ ማስታወሻ!

በተማሪዎች ውጤት ላይ ትልቁ ልዩነት ያለው ሰነፉ ረጅም ሰዓት ፈታ ብሎ በተረፈው ጊዜ ያጠናል። ሰቃዩ አጥንቶ ሲጨርስ የሚያስደስተውን ያደርጋል። 

ፈተናው ቀላል እንዲሆንልህ አሁን ጊዜ ሰጥተህ አጥና፣ ብዙ ጥያቄ ስራ! ጊዜ አታባክን! ከኢንትራንስ በኋላ ብዙ ፈታ የምትልባቸው ወራት አሉ። ለእሁዱ ፈተና ዝግጅት፤ ዳይ ወደ ጥናት!

@Matric_Fetena


#RayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የማጠናከሪያ ትምህርት (Remedial Program) ወስዳችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ህዳር 9/2017 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

@Matric_Fetena


📣ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች   የምዝገባ  ጊዜ ኀዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
• የማህበራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ:-

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት            
  
@Matric_Fetena


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


🛑 ማጥናት ጀምር!

ከፈተና በኋላ እንዳይቆጭህ ከፈለክ አሁን በደምብ አጥና፣ ጥያቄ ስራ። እስካሁን አልጀመርኩም ካልክ አሁን ጀምር! የምትችለውን ሁሉ አድርግ!

አለበለዚያ ሰኔ ቶሎ ይደርሳል፤ ውጤት ሲመጣ ታዝናለህ! ያንተን ስኬት የሚጠብቁ ጥግ ድረስ የሚወዱህ አባት፣ እናት ወይ ቤተሰቦች አሉ! ብቻህን አይደለህም አሁኑኑ ተነስና ማጥናት ጀምር!

ልዩ ቀን ተመኘንላችሁ🙏
@Matric_Fetena


#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተቋሙ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ኅዳር 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

- የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ
- የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት፣ - ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
- ዘጠኝ 3×4 ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

@Matric_Fetena


#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም አይኖርም በሚል በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች እየተዘዋወረ የሚገኘው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሆነው የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም "በዚህ ዓመት በበጀት እጥረት ምክንያት ተቋርጧል" በሚል የተሰራጨው መረጃ #ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮቹ ባጋራው መረጃ አረጋግጧል፡፡


@Matric_Fetena


🎓በሚቀጥሉት ሳምንታት ዩንቨርስቲዎች ለአዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎቻቸው ጥሪ ማድረግ ይጀምራሉ::ጥሪ ሲደረግ ብዙ ጊዜ ላይሰጧቹ ስለሚችሉ ዝግጅታቹን ካሁኑ ጨርሱ::

👨‍🏫እንዲሁም የሬሜዲያል ተማሪዎች በዚህ ሳምንት ወይም እስከ ቀጣይ ሳምንት ምደባ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ። ስለዚህ የ2017 አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዝግጅታችሁን ጨርሱ።

@Matric_Fetena


ምደባ ይፋ ሆኗል

የ2017 ዓ. ም የዪኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት  ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ለማየት እነኚን አማራጮች ተጠቀሙ

https://placement.ethernet.edu.et

ወይም
@moestudentbot

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister


🔥 በጥረትህ ብለጣቸው!

ሁሌም የምትችለውን ሁሉ አድርግ! አሁን የዘራኸውን ነው ነገ የምታጭደው። አሁን ስትለፋ ወይ አላማህን ስታስቀድም እንደ ሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ፤ አንተም ለጊዜው የተሸወድክ ይመስልሀል፤ ግን ልክ ነህ አልተሳሳትክም።

ሰዎችን በብልጠት ሳይሆን በጥረትህ ብለጣቸው ምክንያቱም በጥረትህ ከፍ ስትል ብልጡን ሰው ቀጥረህ ታሰራዋለህ። ለዛ ነው አሁን እየደበረህ ማጥናት፣ ለኢንትራንስ ካሁኑ መዘጋጀት ያለብህ!

ደስ የሚል ቀን ተመኘንላችሁ!
@Matric_Fetena


#ማስታወቂያ

♾የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጻል።

በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ስለሚገለጽ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

ትምህርት ሚኒስቴር


አሁን ላይ ቦቱ መስራት አቁሟል!!

ሁላችሁም ተረጋጉ ቀጥታ ትምህርት ሚኒስቴር ሚያወጣዉን መረጃ ጠብቀን የምንለቅላችሁ ይሆናል ::

ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey | Join Now

Показано 20 последних публикаций.

5 695

подписчиков
Статистика канала