ክፉ አትሁን . . . ጉዞ ወደ መልካምነት
ሰላም ለእናንተ ይሁን
በአንድ ቀዝቃዛማ ጠዋት ገበሬው በእርሻው ውስጥ ሲዘዋወር በቅዝቃዜ ብዛት
ደርቆ ከመሬት የተጣበቀ እባብ ያገኛል፡፡ ገበሬው እባቡ በቅዝቃዜው ምክንያት
ወደ ሞት እያመራ መሆኑን ስለተረዳ ከመሬት አንስቶ ደረቱ ውስጥ ከተተው፡፡
ከደቂቆች በኀላ እባቡ ከገበሬው ሰውነት ባገኘው ሙቀት አማካኝነት ከሞት
ዳግም ወደ ህይወት ተመለሰ፤ ሙሉ ጥንካሬውን እንዳገኘም መልካም
የሰራለትን ገበሬ ነደፈው፡፡
ገበሬው የተነደፈው በጣም መርዛማ በነበረ እባብ ስለነበር ወደሞት ጉዞ ጀመረ።
በማጣጣር ላይ ሳለም በዙሪያው ላሉ ሰዎች እንዲህ ሲል ተደመጠ፡፡ " ከእኔ
እጣ-ፈንታ ተማሩ፤ መቼም ቢሆን ማንነቱ ከማይቀየር ሰው እራቁ፡፡"
ሰው ከስተቱ ይማራል፤ ከቆሻሻው ታጥቦ ይፀዳል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች
መቼም ቢሆን አብሯቸው ካደገ ማንነት የፀዱ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተለውጠዋል
ብለን ዳግም ዕድል ስንሰጣቸው ልክ እንድ እባቡ ቦታና ምቹ ግዜን ጠብቀው
ዳግም ልባችንን ያቆስሉታል፤ መጠገን እንዳንችል አርገው ይሰባብሩናል፡፡
ስለዚህ በእነዚህ አይነት ሰዎች ስንከበብ ሁሌም ንቁና ጠንቃቃ እንሁን ። ብቻ
ወዳጄ
☞ ፈጣሪ ይምርሃል የማይምርህ የሰው ልጅ ብቻ ነው። ፈጣሪ እኮ ይቅር በለኝ
ስትለው ከነበርክበት የዘቀጠ ህይወት አፅድቶ ወደ እርሱ ያቀርብሃል። የሰው ልጅ
ግን ከባድ ነው። ዛሬ ጥሩ ስትሆን ለማስመሰል ነው ይልሃል...ክፉ ከሆንክ
የለመደው ነው ይልሃል። ላጠፋኸው ጥፋት ይቅርታውን ስትከጅለው ባለፈ
ማንነትህ ያሸማቅቅሃል!!
ፈጣሪ መልካምነትን በውስጣችን ያኑርልን። አሜን!!!
Join 👉 @NeverHesitateFromSuccess