TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
Ayu ????

27 Nov 2018, 22:48

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

የድሀ ፍቅር

ክፍል 5
በእውነተኛ ህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ
ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ እየጠበቅን ነው ሜላት ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ
አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ አኮረፈች ሁሌም ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው
የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና ጉንጫን በእጆቼ ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት
ደስ
አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ,.
ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ ደንግጠን ዞር ስንል የሜላት አባት መኪና
ነበር
ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ,ሜላትም እሽ ብላ ቻው ብላኝ ወደ መኪናው ገባች አባቷ
እኔን
ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ.,
ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል ነበር ብዬ አሰብኩ ቀኑ አርብ
ስለነበር
ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን የለኝ ብቻ ጨነቀኝ እቤት ገብቼ
ለእናቴ
የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ አምላክ ያለው ይሆናል አለችኝ ,እሽ
አልኳት
በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ ሜላት የለችም ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ
ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም.,እሁድም አላገኝኃትም ይበልጥ ጨነቀኝ.,
ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ ሜላት ግን የለችም ተደውሎ ወደ
ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር ላይ ሲቆም ሰማሁ ዞር ስል የሜላት
ወንድም ሜላትን ይዞ መጣ ,ተንደርድሬ ሄጄ ሰላም ልላት ስል ዝም ብላኝ በቆምኩበት
ትታኝ ገባች ፈዝዜ ቀርሁ ለምን አልኩ ወንድሟ ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ እኔም
ቀስ እያልኩ ሜላት በቃ ተለየችኝ ተለያየን እያልኩ ወደ ክፍሌ አመራሁ.,
እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት እንደመጣች ሳላውቅ መጥታ
ተጠመጠመችብኝ
ከንፈሬን አንገቴን አይኔን
ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ አለችኝ ምን ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው
አልኳት ለረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ መምህር ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና
እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን.,
የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት የተፈጠረውን እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም
ጨንቆኝም ነበር ,መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ ሰአቱን መግፋት ብችል ገፍቼ አሳልፈው
ነበር
ግን አልቻልኩም ,የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ አይቀር ወጥቼ ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ
ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ አለችኝና ቁጭ አልን,.
ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ ጋር ከታየች ችግር
እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም እንዲጎዱህ ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት
ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም ብዬህ የገባሁት ከዚህ በኃላ ከ ትምህርት
ቤት
ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም ምናልባት ማታ ማታ ቤተክርስቲያን እንገናኛለን
አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት .,
ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ አውጥታ በዚህ ስልክ እንደዋወል
አለችኝ
እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ እንደምጎዳ በደንብ ገባኝ ከዝይች ቀን
ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ መገናኝት አቆምን
ሜላት
ማጥናት ትታለች በቃ ከኔጋር ለምዳ ብቻዋን ማጥናት አልቻለችም.,
የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት ተወጥሪያለው ሜላት ግን ማጥናት ትታ
እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ ላስጠናት እንደምችል ግራ ገብቶኛል ,ማታ
ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም እንዳላጠናች ነገረችኝ አጥኚ ነገ ከትምህርት
መልስ
እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ ብላኝ ቻው ተባብለን ስልኩ
ተዘጋ..በድጋሚ
ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር,........
ይቀጥላል.......
@ like 👍👍👍👍
@bosbitch ❤️

63 0 0
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot