🔥ጭንብል🔥
💞ክፍል 5
✍ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
የሆሊውድ ፊልም የሚመስል ታሪክ
.
.
"ቤተሰቦቼን የት ነው የወሰድሻቸው"አለ ፍቃዱ ሰውነቱ ሁሉ
በንዴት እየተቀጠቀጠ ።
"ኢኒስፔክተር አትጨነቅ ቤተሰቦችህ ያሉት ደስታ በሚሰጥህ ቦታ
ነው...ግን ሳላደንቅህ አላልፍም " አለች መና እንደተለመደው
በወንድ ድምፅ በሞባይሏ በመቀየር።
"በወንድ ድምፅ ማውራት ለምን አስፈለገሽ..ሴት መሆንሽን
አውቄዋለው በራስሽ ድምፅ አታወሪም..?"
" እኔ የምልህ ውይ ለካ ሚስት የለህም አሀ ለዛ ነው ሴት ነች
ሴት ነች የምትለኝ አንተ የእኔ ሴት ወይም ወንድ መሆን አይደለም
ሊያስጨንቅህ የሚገባው... አንድ ወንጀለኛን እንዴት መያዝ
እንዳለብህ ነው መጨነቅ ያለብህ ዘመዴ..እኔን ለመያዝ ፆታዬ እንደማያስጨንቅህ
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታየዋለህ..ነጭ ላብህን አስጨርሼ ቀዩን አስጀምርሃለሁ..ለማንኛውም በርታ" አለች መና በሳቅ በታጀበና
በተረጋጋ በራስ መተማመን።
" የአንቺን የራስ መተማመን አደንቅልሻለው ..... አሁን ቤተሰቤ የት እንዳሉ ንገሪኝ " አለ ፍቃዱ እሱም የጊዜ ጉዳይ እንጂ እጁ
እንደምትገባ እርግጠኛ ሆኖ።
" ይቅርታ አርግልኝና ቅድምም ነግሬሀለው አንተ ቤተሰብ
መመስረት የለብህም... ትጎዳቸዋለህ አስፈላጊም አይደለም..እኔ በሌሎች ላይ የምጫወተውን ጨዋታ በአንተ ላይ አልጫወትም።..የእኔና የአንተ ጨዋታ ፖሊስና ሌባ ወይም አኩኩሉ ነው እንደ
ልጅነታችን ....አሁን ልጅህ ትደውልና የት እንዳለች ትነግረሀለች
እሺ......አኩኩሉ.... ....አኩኩሉ ........ አልነጋም አትለኝም
እንዴ? " አለችና ትንሽ ደቂቃ እየሳቀች ከሄደች በኋላ ስልኳን
ዘግታ ከያዘችው ቦርሳ ወስጥ ከተተችው ። ግን ምሽቱ በጣም
ጨለማ ከመሆኑም በላይ ጭር ያለ ስለነበር ሶስት ወጣቶች
ሊዘርፏት ከሁዋላ ይከተሏታል..መንደር ውስጥ እንደገባች ቆመችና
ዘወር ብላ አየቻቸው ።
" ምን ፈልጋችሁ ነው የምትከተሉኝ ?" አለች መና እግሯ ላይ ባለው ችግር በአንድ በኩል ዘንበል ብላ።
" ወይ ያለሽን ትሰጪናለሽ አሊያም ጤነኛውን እግርሽን ጨምረን
እንደፋሻለን " አሉ እየተጠጉ
" መኖር ከፈለጋችሁ ወደ መጣቹሁበት ተመለሱ " አለቻቸው
ልጆቹ ግን ገርሟቸው እየሳቁ ነበር።
ከትንሽ ደቂቃ በኋላ እሷ ስትሄድ ሶስቱ መሬት ላይ ወድቀዋል።...
🔥🔥🔥
ፍቃዱ በአንድ ትልቅ የግል ሆስፒታል ውስጥ እየሮጠ እያለከለከ በመግባት ወደ ውስጥ ገብቶ የህክምና ልብስ የለበሱ ሰዎችን ጥያቄ እየጠየቃቸው ሳለ ልጁን አያት... እየጠራት ሮጦ በመሄድ አቅፎ ያዛትና ምን እንደሆነና ምን እየተደረገ እንደሆነ ጠየቃት..ልጅቱ የያዘችውን ፖስታ አውጥታ አሳየችው.. በበርካታ ብር የተጫቀ ነበር..እሱም ባየው ነገር ደነገጠ ውስጡ ደብዳቤ አለ።..
🔥🔥🔥
አነስተኛ የቆርቆሮ ግቢ ነው የሰዎች መግቢያ ቀይ ብረት በር ነው..መና ከፍታ ገባች 6 ወይም 8 እርምጃ ተራምዳ ወደ ውስጥ ዘለቀች... ሶስት ክፍል ያለው
ኤል ሼፕ ነው ...አነስተኛ በረዳ አለው..ግቢው ሰፊ ባይሆንም
ዙሪያውን በአትክልቶች ተከቦ የፀዳ በመሆኑ ለእይታ ይማርካል..የድሮ የመሰለና ማራኪ የሆነ የእንጨት በር ከፍታ ገባች መልሳም
ዘጋችው።
" እማማ እንዴት ዋሉ መጥቻለው " አለች መና...
ከጓዳ ወፍራም አጠር
ያሉ እርጅና የተጫጫናቸው አሮጊት መጡና ፈገግ ብለው አዩዋት።
ከእሳቸው ኋላ ያቺ በሌላኛው በር ከሆቴል የወጣችው ባለ ክብ ፊቷና ቀጭኗ ኤፍራታ ተቀምጣለች... መና ታላቅ እህቷ ነች.. ኤፍራታን ማንም በስሟ ጠርቷት አያውቅም ቀጮ ነው የሚሏት ።
" ቀጮዬ የኔ ተናፋቂዋ እህቴ መቼም በእግርሽ መጥተሽ
አልቀደምሽኝም ንፋስ አሩጦ አንሳፎ አምጥቶሽ እንጂ " አለቻት መና ልትስማት ወደ እሷ እየተጠጋች.....እጅግ በጣም ነው የሚዋደዱት ፍቅራቸው የተለየ ነው።
" መንዬ ስወድሽ እኮ ለምን እንደሆነ ታውቂዋለሽ..ሽንፈትሽን
ስለማታምኚ" በፍቅር ተያያዙ መሳሳምና መላፋት ጀመሩ...
አሮጊቷ "ውይ ስራ አስፈቺዎች ናችሁ ሁለታችሁ ስትገናኙ" ብለው
ቆመው በፈገግታ ያዩዋቸዋል ፍቅራቸው እንዳበቃ " ቀጮዬ የሰውየውን ልጅ ጨርሼዋለው ደውይለት..አሁን ለሰውዬው የልጁን ሬሳ አንሳ በይው..እንዲሁም የሚቆም ነገር እንደሌለና የተጠየቀውን እስከሚያሟላ እርምጃችን ካለ ሀዘኔታ እንደምቀጥል
ንገሪው...እና አዲስ ነገርስ የለም...? እንደተለመደው ጠንቀቅ ብለሽ እሺ" አለቻትና ፀጉሯን አሸት አሸት አድርጋት ግንባሯን ስማት ወደ ውስጥ መኝታ ክፍል ሄደች... አልጋ ላይ የተኛውን የረዥም ጊዜ
በሽተኛ ልጇን ለማየት ገባች..ከላይ የለበሰችውን ልብስ
ስታወልቀው በቦዲ ብቻ ሆነች ከፊት ደረቷ ጡቷ አካባቢና ከጀርባዋ እንዳለ ሰውነቷ ጠባሳ በጠባሳ ነው..ብዙ መከራ ያየች እንደሆነች እንዲሁ ሰውነቷ ላይ በግልፅ የሚታዩትን ጠባሳዎች አይቶ መገመት ይቻላል...
ሰውነቷ ላይ ደህና ቦታ በባትሪ ተፈልጎም የሚገኝ አይመስልም።...ጫማዋን ለማውለቅ ስታጎነብስ በህመም በጣም ጮኸች ።...
🔥🔥🔥
ለእነዛ መሬት ላይ ለተዘረሩት ሶስቱ ወጣቶች ለሊቱ አይነጋ የለምና
ነግቶላቸው ፖሊስ ጣቢያ በፍቃዱ ፊት ተቀምጠው በጥያቄ
አጨናንቋቸዋል ።
" መርማሪ ሴት መሆኗን ለአንተ በመናገሬ ሁላ መውጣት እየፈራሁ ነው..እንዴ አንድ ጊዜ እግሯን አንስታ ሲያርፍብኝ ይታወቀኛል..ስንነቃ በህይወት
ያለን አልመሰለንም.. እንደሞትን አንዳችን ሲኦል ነን ያለነው ስንል...ሌላው ገነት ነን ሲል።..ምን መልካም ስራ ሰርተን ገነት እንገባለን እያልን ስንወራከብ ነበር...ለካ የዛች ሴት ካራቴ ጥፊ አእምሮዋችንን በጥብጦት ስለነበር በብዥታ ውስጥ ሆነን ነው ስናወራ የነበረው።... ወይ ፍዳ እኔ በበኩሌ ይቅር ትበለኝ እንጂ ስለ እሷ ምንም አላወራም.. ሰለ እሷ ብቻ ሳይሆን ሰለማንም ሴት " አለ አንደኛው በጉንጩ ጫት ወጥሮ የያዘ የሚመስለው...
ይቀጥላል...
@comeoncomrades
@comeoncomrades
አስተያየታችሁን
👇👇👇
@Accolademan