ድምፄን🗣🗣🗣
እስቲ አትሞናደይ ኧረ ወዲያ ዞር በይ
ሽር ብትን እያልሽ ቀልቤን አትቀበይ
እንዳው ከዛው ቁጭ በይ አትወናጨፊ
ሀሳብሽስ ዝሏል በስጋሽ እረፊ
ተይ አትገላመጭ ዐይንሽ አይድከመው
መስታወትም አትይ ይበቃሻል ተይው
ብቅ በይ ተደጁ ጥላሽስ ማን አለው
እሱም እንዳይከፋው
እሚልሽ ይመስል ተሰድሮ ቦታው
ያይሻል የቤቱ ሁሉ እቃው
እኔስ በምን አቅሜ ምን እናገራለሁ
ወይ እሰበራለሁ
ወይም አጣሻለሁ
እጆችሽ ላይ ሞቼ
አንችም እንዳታጪኝ እፈራልሻለሁ
ለዛም ምንም አልል
ምትሆኚውን ሁሉ ዝም ብዬ አያለሁ
ድምፄን ውጠሽብኝ ምንስ አወራለሁ
በዚች ምፀታሽ ውስጥ ሳልናገር ብሞት
እያልኩ እፈራለሁ
እንደ መስታወቱ እቴ እንደ ጥላሽም
እንደ ቤቱም እቃ
ውዴ አመልሽን ይዤው እኖራለሁ::
@Be_nayas
@flawsome_poetry
እስቲ አትሞናደይ ኧረ ወዲያ ዞር በይ
ሽር ብትን እያልሽ ቀልቤን አትቀበይ
እንዳው ከዛው ቁጭ በይ አትወናጨፊ
ሀሳብሽስ ዝሏል በስጋሽ እረፊ
ተይ አትገላመጭ ዐይንሽ አይድከመው
መስታወትም አትይ ይበቃሻል ተይው
ብቅ በይ ተደጁ ጥላሽስ ማን አለው
እሱም እንዳይከፋው
እሚልሽ ይመስል ተሰድሮ ቦታው
ያይሻል የቤቱ ሁሉ እቃው
እኔስ በምን አቅሜ ምን እናገራለሁ
ወይ እሰበራለሁ
ወይም አጣሻለሁ
እጆችሽ ላይ ሞቼ
አንችም እንዳታጪኝ እፈራልሻለሁ
ለዛም ምንም አልል
ምትሆኚውን ሁሉ ዝም ብዬ አያለሁ
ድምፄን ውጠሽብኝ ምንስ አወራለሁ
በዚች ምፀታሽ ውስጥ ሳልናገር ብሞት
እያልኩ እፈራለሁ
እንደ መስታወቱ እቴ እንደ ጥላሽም
እንደ ቤቱም እቃ
ውዴ አመልሽን ይዤው እኖራለሁ::
@Be_nayas
@flawsome_poetry