Nathan's perspective


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ዶግማ ቀኖና እና ሥርዓት መጠበቅ ወደን የምንሰራው የከበረ አገልግሎታችን ነው።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ድንግል ማርያም "ፍጽምት የቤተክርስቲያን ወካይ መገለጫ[the perfect expression of the church]" ናት። ስለ ቤተክርስቲያን የምናወራው በሙሉ በእርሷ[ማርያም] ውስጥ አለ።

"የቤተ ክርስቲያን ቅድስናዋ ምን ያኽል ነው?" ቢሉን ወደ ድንግሊቱ እንጠቁማለን። ነገረ ቤተክርስቲያንን ሊረዳ ለሚሻ ሕይወተ ማርያም ድንግል ማያ[scope] ነው።

የቤተክርሲያን ስደት በድንግል ማርያም ስደት ፣ የቤተክርስቲያን ሐዘን በሰቆቃዋ ድንግል ፣ የቤተክርስቲያን ምድራዊ ትንሣኤ በሚጠተ ማርያም ፣ የቤተክርስቲያን ዘላለማዊ ክብርም በድንግል ማርያም ትንሣኤ እና እርገት ተወክሎ ይተረካል።

ለቤተክርስቲያን ስደት representation የሆነው የድንግሊቱ የስደት ዘመን አበቃ። በአሳዶጃችንን አንጻር ድንግሊቱን ከሕጻኗ ጋር ሊያሰድድ የቆመው ሄሮድስ ሞ'ተ።

የቤተክርስቲያን ፍጹም መገለጫዋ ድንግል ሆይ ቤተክርስቲያንን ከግብጽ የምትመልሺያት መቼ ነው? ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ሆይ "ቤተ ክርስቲያን ሆይ አሳዳጅሽ ሞ'ተ" የምትላት መቼ ነው?

ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ


የሰሞኑ ሐዘናችን ድንኳን ውስጥ ተቀምጠው ከንፈር ከሚመጡ መንደርተኞች በዓላማው ከፍ ይላል። ስለሞቱት ሰዎች እርማችንን እያወጣን ብቻ አይደለም። በቀጣይ በአከባቢው ባሰረው መስቀል ምክንያት የሚገደል ሰው እንዳይኖር የማንቃት ሥራ እየሰራን ነው።

የምንጽፋቸው ጽሑፎች የምናስጀምራቸው ቻሌንጆች ሁሉ ከዚህ አንጻር shape ሊደረጉ ይገባቸዋል። ኦርቶዶክሳዊውን ማንቃት ነቅቶም ራሱን እንዲጠብቅ ማድረግ የመጀመሪያው አላማችን ሆኖ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እየሆነ ያለውን ጉዳይ እንዲረዳ ማድረግ ተከታዩ ትኩረታችን ነው።

ጠንከር ብሎ ከፊት ቆሞ የሚመራን [መታረዳ*ችንን የሚያስቆምልን] አባት ቢኖረን ደስ ይለናል። ከሌለም "ቤተክርስቲያን የኛ ናት" በሚል የባለቤትነት ስሜት የቤተክርስቲያንን ስደት ሊያስቀር ከሚሰራ ከየትኛውም ሰው ጋር በሕብረት ቆመን ስለ ቤተክርስቲያን እረፍት እንሰራለን።

ስለ አርሲው ጭፍጨፋ ቃል ያልተናገራችሁ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ታዋቂ መምሕራን ፣ ዘማሪያን ፣ ማሕበራት ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እና ሌሎችም ይኼ ጊዜ ያልፋል። ይኼ ጊዜ ያለፈ ቀን ሕዝባችሁን በምን አይናችሁ ታዩታላችሁ? ፈጣሪን አትፈሩም? ሕዝቡን አትፈሩም?


ሰፈር ውስጥ ለቅሶ ሲኖር እንኳን ቴሌቪዥን ይዘጋል እኮ። ሃዘንተኞችን ማስተዛዘን የሚባል የቆየ ልማድ አለን። እንዴት ነው የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት እንዲህ የቀለለባችሁ? "በየቀኑ ኦርቶዶክሳውያን እየታ*ረዱ ነው" እያልንህ በጎን ቀልድ ስትፖስት ሕሊናህ ምንም አይልህም?

በየቀኑ በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን እየሞቱ ነው። እንዲህ ያሉ ግድ-ያዎች ዓላማቸው ከሚታሰበው በላይ ሰፊ ነው። በአከባቢው ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ደፍረው ኦርቶዶክስ ነኝ ማለት የማይችሉበት ሁኔታ እንዲመጣ እየተሰራ ነው።

በዚህ ሰዓት የማሕበራዊ ሚዲያ አካውንቶቹን አርሲ ላይ የሚፈጠረውን ግፍ ለማሳወቅ የማይጠቀም ኦርቶዶክሳዊ በወገኖቹ ላይ ክሕደት እየፈጸመ ይመስለኛል።

update በትላንትናው እለት ተጨማሪ 5 ሰዎች ተገድ"ለዋል


ሱላማጢስ ቤተክርስቲያን ሆይ ወደ ክብር ሃገርሽ ተመለሺ። የስደት ዘመንሽ ይበቃሻል። ልጆችሽን የሚገድል ከክብር አውርዶ ያሰደደሽ ቤተ ክኅነት ሞቷል። ወደ ከፍታሽ[ገሊላ] ግቢ።

ለድንግል ማርያም የሄሮድስን መሞት ነግሮ ወደ ኢየሩሳሌም የመለሳት መልዓክ ለቤተክርስቲያናችንም የአሳዳጇን የቤተክሕነትን ሞት ነግሮ ወደ ቀደመ ክብሯ ይመልሳት።

ተመየጢ ሱላማጢስ ተመለሺ ቤተክርስቲያን


በኢትዮጵያ ያለ ክርስትና እንዲህ የማንም መጫወቻ ሆኖ ሊቀጥል አይችልም። ሁለት አማራጮች ብቻ አሉን ወይ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ትጠፋለች ወይ ክርስትናው ከፍ ባለ ክብር ይገለጣል።

ክርስትናውን ለማዳን የምናደርገው ትግል ውስጥ ቤተክሕነት የሚባል መዋቅር አያስፈልገንም።[ቢያስፈልገንም የለንም]

አሁን ያለው ቤተ ክሕነት ቤተክርስቲያንን በልቶ ማደሪያ አድርገው የተሰባሰቡ የጅቦች ስብስብ ነው። እነርሱ ላይ ተስፋ የሚያደርግ አንድም ክርስቲያን እስካይቀር ድረስ ክፋታቸውን መናገር ይገባል።


የሚያምር ነገር ላሳያችሁ...

ልደታ ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምሕርት ቤት ባለፈው እሁድ ሕጻናቱ ለድንግል ማርያም ለጽጌ ደብዳቤ ጻፉላት ተብለው ታዘዙ። እንዴት ማርያምን እንደሚወዷት እዩ።

"አበባ ስላላመጣውልሽ ይቅርታ" የሚለው ደሞ🤌


ቤተክርስቲያን መዋቅር አላት። አንተ በአጥር ገብተህ ስለጮህክ የተወገዘም የሚወገዝም መጽሐፍ የላትም። መዋቅራዊ አካሔዱን ጠብቀው ገና ለሕትመት ያልበቃውን ሥርዋጽ ያለበት መጽሐፍ እንዲወገዝ ያቀረቡት መናኒው አባት የደብረ ሊባኖሱ ሊቅ ናቸው።

ያንተ የጴንጤ ጩኸት እዚህ ላይ ምንም አስተዋጽዖ የለውም። ኢምንት አልኩኽ።

በምዕመናን እጅ እና በቤተክርስቲያናችን አገልግሎት በየደብሩ የሚገኘው የመጥምቀ መለኮት የገድል መጽሐፍ ተወግዟል ብለው ከሚያወሩ ከሚያስወሩ ገድል አስጣዮች ተጠበቁ።

የተጠቀምኩት ፎቶ የተወገዘው አይደለም!


my beloved protestants

ቤተክርስቲያን ጉባኤ እግዚአብሔር ናት። በዚህች ቅዱስ ጉባኤ ውስጥ የክርስቶስ ትምሕርት ይነገራል። በዚህች ቤተክርስቲያን ያሉ ክርስቲያኖች ሕብረት የሚያደርጉት ጎን ለጎን ተቀምጠው እጅ ለእጅ ከሚያያዙት ሰው ጋር አይደለም። በቤተክርስቲያን ያለ ሕብረት በphysical touch ከሚፈጠር ሞቅታ ያልፋል።

ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር የሚያውቁት እውቀት ለመላዕክት ከተገለጸው ሌላ አይደለም። ያንኑ አንዱን መገለጥ ከቤተክርስቲያን ይቀበሉታል እንጂ።እርስ በእርስ ሕብረታቸውን የሚያደርጉትም በሰሙት የጌታ ትምሕርት በኩል ነው።

የሞቱም በሕይወት ያሉም ሰማያውያንም ምድራውያንም ሌላ የሚሰሙት ድምጽ የላቸውም። አንድ ድምጽ ሰምተው ተሰብስበዋልና ቃለ አሚናቸው አንድ አይነት ነው።

"በጥምቀት ልጅነት አይገኝም" ብለህ ምታምን አንተ "ሰው ከውሃ ተወልዶ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" ብሎ ከሚያምን ሰው ጋር "በጌታ ወንድሜ" ስትባባል ማስመሰል አይሆንብህም? አንተስ "ጥምቀት ለመዳን አስፈላጊ ነው" ብለህ ምታምን ሰው ጥምቀትን እንደ ሻውር ከሚቆጥረው ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ስትጸልይ ጌታህ ላይ እያለገጥክበት አይመስልህም?

ያኔ በገድላት እና በተዓምራት ላይ የስተት ታሪኮችን አጊኝቻለው ብለህ ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የወጣህ ሰው ዛሬ የገባህበት ቤትህ ውስጥ ያለው ነገረ መለኮታዊ ተፋልሶ ሲገለጥልህ ጥለኸው እንዳትወጣ ማን ነው የያዘህ?

ያኔ "ጌታን አገኘው" ካልክ በኋላ የኖርካቸውን እድሜዎችህን አስብ... በነዚያ አመታትህ የቀያየርካቸውን ነገረ መለኮታዊ አቋሞችህን አስብ... ተራ የ ideology ለውጦች ብቻ አልነበሩም። የተለያየ የግል አቋምህን ስትይዝ የከረምከው መዳን በሚገኝበት የጌታ ትምሕርት ላይ ነበር።

ጥምቀት አያድንም ያልክ ቀንም "በጌታ" ነበርክ በጥምቀት የሚሰጥ ዳግም ልደት ሲገባህም "በጌታ" ነህ። ኢየሱስ ከማርያም ሥጋ አልነሳም ብለህ ምታምን ጊዜም "በጌታ" ነህ ኢየሱስ ከድንግል ሥጋን ነሳ ብለህ ስታምንም "በጌታ" ነህ።

ወዳጄ አሁን እንዲህ ያለው በራስ ላይ መቀለድ ይብቃህ። ዝም በልና ለእግዚአብሔር እና ለራስህ ታመን። ሊፈርስ የደረሰውን ሰው ሰራሽ ጉባኤህን ተወው። ራስህን አድን!


ኃጢዓት ምንድነው?  ሕግን መጣስ ወይስ መንፈሳዊ መበላሸት?

ነገረ ድኅነትን ለመረዳት የሚደረግ ማንኛውም ፍለጋ የኃጢአት ምንነትን በጥልቀት በመመርመር ይጀመራል። በነገረ-መለኮት ጥናት ታሪክ ውስጥ ካሉ አመለካከቶች መካከል በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው ልዩነት እጅግ ሰፊ ነው። ይህ ልዩነት የመዳንን ሂደት (Soteriology)፣ የእግዚአብሔርን ፍትሕ (Justice) እና የሰው ልጅን ተፈጥሮ (Anthropology) በተመለከተ ያሉትን መሠረታዊ ልዩነቶች አስከትሏል።

በምዕራባዊው የሃይማኖት ፍልስፍና፣ በተለይም በሐዳሲያኑ (reformes) ትምህርት ውስጥ፣ ኃጢአት በዋናነት ሕግን መጣስ ተደርጎ ተተርጉሟል። ይህ አመለካከት በዋነኛነት የመካከለኛው ዘመን የሕግ ፍልስፍናን (Legal Philosophy) መሰረት ያደረገ ነው።

በዚህ አተረጓጎም የአዳም የመጀመሪያው በደል እንደ ሕጋዊ ወንጀል ይቆጠራል።ይኽም የእግዚአብሔርን የተቀመጠ ሕግ በመተላለፍ የተፈጠረ ዕዳ (Debt) ነው። በዚህም ምክንያት የሰው ልጆች ሲወለዱ በሕግ ፍርድ ሥር የወደቁ ባለዕዳዎች ሆነው ነው።

የኦርቶዶክስ ነገረ-መለኮት ግን ከዚህ አመለካከት ይሰፋል። በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ኃጢአት በዋናነት መንፈሳዊ በሽታ (Spiritual Sickness)ነው። -የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር መለየት-

የሰው ልጅ የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳል (Image) እና ጸጋ (Grace) የተሞላ "እጅግ ያማረ" ፍጡር ሆኖ ነበር። ኃጢአት ይህንን ውበትና ክብር አላጠፋውም፤ ይልቁንም አበላሸው። ኃጢዓት በሰው እና በፈጣሪ መካከል ያለ ግንኙነት መበታተን ነው። ልክ አንድ ቀሳዊ አካል ከፀሐይ (የሕይወት ምንጭ) ሲርቅ ወደ ጨለማ[darkness] እንደሚገባ የሰው ልጅም ከእግዚአብሔር ሲለይ ወደ ሞት፣ መበላሸት (Corruption) እና ሥቃይ ይገባል።

የክርስቶስ መስዋዕትነት

በምዕራባዊው ሕግ-ተኮር አስተሳሰብ ውስጥ የክርስቶስ ሞት ዋና ዓላማው ሕጋዊ ዕዳን መክፈል ነው። ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቁጣ (Wrath) ለማርካት እና ሕጋዊ ፍርድን ለመክፈል የቀረበ "ካሳ" (Satisfaction/Substitutionary Atonement) ነው። በዚህም የመዳን ሂደት ከፍቅር ይልቅ ወደ ፍርድ ቤት ሂደት (Courtroom Procedure) ይወርዳል። የእግዚአብሔር ፍትሕ በሕግ መሠረት እርካታን ያገኛል።

በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ግን የመስቀሉ ሚና ፍጹም የተለየ ነው።

የክርስቶስ ተግባር: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን መስዋዕት በማድረግ በራሱ ሰውነት (Human Nature) ውስጥ ሞትን ገደለው። ሞት የኃጢአት የመጨረሻው ውጤት ነው። ክርስቶስ ሞትን በመውሰድና በማሸነፍ የሞትን ኃይል ከሰው ልጅ ማንነት ላይ ሽሮታል።

የክርስቶስ ሞት የቁጣ ፍርድን የማርካት ሳይሆን የፍቅር ሕክምና (Therapy of Love) ነው። እርሱ የኃጢአት ውጤት በሆነው በሞት ላይ ድል ነስቷል በዚህም የሰው ልጅን የተበላሸውን ማንነት ዘላለም ፈውሷል። መዳን ከሕግ ዕዳ ነፃ መውጣት ሳይሆን ከበሽታው (ከሞትና ከጥፋት) የመፈወስና ከፈጣሪ ጋር የነበረን የፍቅር ግንኙነት እንደገና የማደስ ሂደት ነው።

የእግዚአብሔር ፍትሕ እና ፍቅር

በኦርቶዶክሳዊው ነገረ መለት ውስጥ የእግዚአብሔር ፍትሕ ከፍጹም ፍቅሩ ጋር ፈጽሞ የማይነጣጠል ነው።

የእግዚአብሔር ፍትሕ (Dikaiosyne) በእርሱ ውስጥ ያለውን ሥርዓታዊ ምሉዕነት የሚያሳይ ነው። ይህ ፍትሕ ከውጭ ሆኖ ሕግን የማስከበር ሂደት አይደለም፤ ይልቁንም የእርሱን ፍጹም ሥርዓታዊ ቅድስና በፍጥረቱ ላይ በፍቃድ የማኖር ሂደት ነው።

ኃጢአት የሕግ ጥሰት ብቻ አይደለም። የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር መለየት ነው። በዚህም ምክንያት የመዳን ሂደትም የሕግ ዕዳን መክፈል ሳይሆን በክርስቶስ በኩል ወደ ሕይወትና ወደ ፍቅር ግንኙነት መመለስ ነው። የእግዚአብሔር ፍትሕ ከፍጹም ፍቅሩ ጋር እንጂ ከምድራዊ የሕግ ፍልስፍናዎች ጋር አይገናኝም!


ከቤተክርስቲያን ምሥረታ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ ክርስቲያን በሆኑ ማሕበረሰቦች መሃል ዓለም አይቶት የማያውቀው መተሳሰብ እና መዋደድ ታይቷል። ይኽ መተሳሰብ በድንገት የመጣ አልነበረም።"አንድ የክርስቶስ አካል"1ኛ ቆሮ 12 ከሚለው ማዕከላዊ የክርስትና ትምሕርት የተቀዳ መተሳሰብ ነው።

ጌቶች ከባሮቻቸው ጋር አይሁድ ከአሕዛብ ጋር ወንዶች ከሴቶች ጋር በጌታ ሰውነት ውስጥ ራሳቸውን አንድ አድርገዋልና ለባልንጀራቸው የሚያደርጉትን ለራሳቸው እንዳደረጉት ይቆጥራሉ። ይኽ መተሳሰብ ተራ ሰውን የመውደድ ፍልስፍና አይደለም ከሙሴ ሕግ ከፍ ይላል። "ባልንጀራሕን እንደ ራስህ ውደድ" ማር 12፣31 በሚለው የጌታ ቃል የተመሰረተ የክርስቲያኖችን አኗኗር ዘይቤ ነው።

የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን ማሕበረሰባዊ አበርክቶ ሊያሳየን የሚችል ድንቅ የቤተክርስቲያን ገጽታ መዋቕራዊ የሆነ የቸርነት ሥራ ነው። እንደዛሬው ምግባረ ሰናይ ተቋማት ባልነበሩበት በዚያ ዘመን ቤተክርስቲያን ቦታውን ሸፍና ቆይታለች። በሐዋርያት ሥራ ፮ኛው ምዕራፍ ላይ ተሹመው የምናገኛቸው የመጀመሪያዎቹ ዲያቆናት ለመበለቶች የሚያስፈልጋቸውን የዕለት ጉርስ ለማሰራጨት የተሾሙ ነበሩ።

በ2ኛ ቆሮንቶስ ፰ኛው ምዕራፍ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ በቆሮንቶስ በሮም እና በሌሎችም ከተሞች ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በኢየሩሳሌም ለምትገኘው "ደኃዋ" ቤተክርስቲያን ስጦታ ሲያሰባስብ እንደነበር መመልከት እንችላለን። ይኽ የቅዱስ ጳውሎስና የአብያተ ክርስቲያናቱ ተግባር ዛሬ ላሉ አጥቢያዎች እና የአጥቢያ መሪዎች ትልቅ ትምሕርት የሚሰጥ ነው። አንድ የጌታ አካል በምትሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ አጥቢያዎች መሃል የሰማይ እና የምድር ልዩነት ሊኖር አይገባም። በከበረ መጎናጸፊያ ከሚቀደስበት መቅደስ በኪሎ ሜትሮች ልዩነት መቀደሻ አጥተው የሚዘጉ መቃድሶች ሊኖሩ አይገባም።

ትኩረታችንን ባደረግንባቸው 200 ዓመታት ውስጥ በተከሰቱ ጦርነቶች ረሃቦች እና ሌሎች ቀውሶችም ክርስቲያኖች የሌሎችን ሸክም ተሸክመዋል።

ቀለሜንጦስ ዘ ሮም ወደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን በላከው መልዕንቱ ላይ ችሮታ ማድረግን ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ጋር ከአብርሃም እምነት ጋር ከረዓብ እንግዳ ተቀባይነት ጋር እያያያዘ አስተምሯል። በሁለተኛው ክፍለ ዘመንም ሄርማ "እረኛው" በተባለ የታወቀ ሥራው ላይ ክርስቲያኖች ያደርጉት የነበረውን የመተሳሰብ እና የመልካምነት ሥራ ከጌታ የተቀበሉትን መስጠት ነው ካለ በኋላ በመስጠት የሰጣቸውን ጌታ እየመሰሉ እንደሆነ ያብራራል።


ጥቂት ነጥቦች በእንተ መርገም

“ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን” ዘፍ3፥17 የሚለው በአንጻረ ምድር በሠው ላይ የተላለፈ ቃለ መርገም በምድር ታሪክ የመጀመሪያው እንጂ ብቸኛው ቃለ መርገም አይደለም።

“ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤” -ሮሜ 5፥14- ብሎ ሃዋርያው በመጀመርያው ቃለ መርገም የሰው ዘር በሙሉ እስከ ጌታ ቤዛነት ድረስ ለመርገሙ ተገዢ እንደነበር ገለጸ።

“ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤” ገላ 3፥13 በማለቱም ዓለሙን ሁሉ አንድ አድርጎ ሲገዛ ከነበረው መርገም ክርስቶስ "እርግማን" ተሰኝቶ አለሙን ነጻ እንዳደረገ ጻፈ።

በአዲስ ኪዳን ከመርገም በታች የሆኑ(ያልተጠመቁ) ሰዎችን በተመለከተ ግን መርገሙ ከ አዳም የወረሱት ሳይሆን ኢየሱስን ባለመውደዳቸው የመጣ ስለመሆኑ “ጌታን ኢየሱስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን።” 1ኛ ቆሮ 16፥22 በማለት ብጹዕ ሃዋርያ ጳውሎስ ገልጿል።

ይህም ባለማመን ውስጥ ያለ ሰው ኢየሱስን ባለመውደዱ ባመጣው አዲስ እርግማን ውስጥ እንጂ በ አዳም በደል በመጣበት እርግማን ውስጥ አለመሆኑን ሚያሳይ ነው።

“ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።”ገላ 1፥8 እንዲል ሃዋርያው ከ ቤተክርስቲያን ውጪ ያሉ ሰዎች በጠቅላላ ከያዙት ልዩ ወንጌል የተነሳ በመርገም ውስጥ ይኖራሉ።

603 0 2 12 11

"ሄሮድስ አሁን ያለው የት ነው?"
ቤተክህነት!
"ምን ሊሰራ?"
ሕጻን ክርስቶስን ከልባችን ያሰድድ ዘንድ!

እኛ ግን በልባችን እንዲህ እንላለን:-
እንዘ ተሓቅፍዮ ለህጻንኪ ንኢ ማርያም!
ንኢ ንኢ ንኢ ማርያም!"

Michael


“ውዴ ነጭም ቀይም ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።” መኃልየ. 5፥10


አበባ ስታዩ ክርስቶስን አስቡ !


እዩ ሴቶች...

በጣም ሚያማምሩ crochet materials የምትሰራ ጓደኛዬ አለችና join ብላችሁ ሥራዎቿን እዩላት...

ምትወዱትን ነገር ካገኛችሁ ደሞ እዘዟት። nathan ነው የነገረን ካላችኋት discount ራሱ ልታረግላችሁ ትችላለች።

ወንዶችም ጆይን በሉ😊

https://t.me/tsioncrochet21




መቅድም በኦሪገን[PHD]

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዘመናት የአምልኮ ስርአቷ ውስጥ ባልተቀየረና በጸና መልኩ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከምትከውንባቸው መገልገያዎቿ በቀዳሚነት የምናገኘው ታቦትን ነው፡፡ አጽራረ ቤተክርስቲያንና ጸላዔ አምልኮተ እግዚአብሔር በመሆን ራሳቸውን በተለያየ መልኩ እየቀየሩ የሚገልጡ መናFቃን በታቦት አገልግሎት ላይ ከቤተክርስቲያኒቷ አስተምህሮ በራቀ መልኩ ጥያቄ በማስነሳት የዋህ እና በሃይማኖት ያልጸኑ አማኞችን ለማሳት እና የምንፍቅና ዘራቸውን ለመዝራት ለዘመናት ጥረዋል፡፡

ከእነዚህ ወገኖች ከሚነሱት አበይት ነጥቦች መካከል "የታቦት አገልግሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብቻ ያለና በሌሎች አብያተ ክርስተያናት የሌለ የአምልኮት መፈጸሚያ ነው፡፡" የሚልና ይኸንኑ እንደማስረጃ በመያዝ "የታቦት አገልግሎት በዘመነ ብሉይ ተተግብሮ በሐዲስ ኪዳን የሌለ እና የቀረ አገልግሎት ነው፡፡" በማለት የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት ከብሉዩ ታቦት ጋር በተነጻጽሮ ሚያስቀምጡት የተዛባ አመክንዮ ናቸው፡፡

የ‹‹ነገረ ታቦት›› ምክንያተ ጽሒፍ ከላይ የተጠቀሱትን ዋነኛ ነጥቦች ማዕከል በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጋር ሐዋርያዊ አንድነት ባላቸው አብያተ ክርስተያናት ዘንድ ያለውን የታቦት አገልግሎት፤የታቦትን የአምልኮ ማእከልነት፤የታቦት ስያሜና እና ታሪካዊ ዳራዎችን በመዳሰስ ለአንባብያን የተሟላ ግንዛቤ መፍጠር እና ለመናፍ*ኑ ምላሽ መስጠት ነው፡፡

ታቦትን እና የታቦትን አገልግሎት አስመልከቶ በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን ያለውን ዳሰሳ በየጊዜው ከነበሩ ቅዱሳን አባቶች አስተምህሮ፤ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አንድነት ባላቸው አብያተ ክርስተያናት መዛግብት ዘንድ ከተገኙ መጽሐፍት እና ሌሎች ልዩ ልዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማመሳከር የተዘጋጀ ጽሑፍ በመሆኑ ለአጽራረ ቤተክርስቲያን በማስረጃ መልስ መስጠት ይልቁንም በቤተክርስቲያናችን ላሉ መምህራን ተጨማሪ መረጃ መስጠት የዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ዓላማ ነው፡፡"


academic review ለመባል መስፈርቷን አታሟላም በየምዕራፉ የታዘብኩትን ነገር ለማስቀመጥ ብቻ ነበር የሞከርኩት።


ከ 5ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለሆነው መለያየት ትልቁን ቦታ የሚወስደው "የክርስቶስን ባህርይ" የሚመለከተው ትምህርት ነው። ይሄን ልዩነት ለማጥበብ የሚያግዙ ቢቻል ደሞ ወደ አንድነት የሚያመጡ ንግግሮችን ለማድረግ የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የቤተክርስቲያኒቱን አቋም ለነገረ መለኮታዊ ንግግሮች በሚመጥን ቋንቋ ማስቀመጥ ነው።

የ ፖፕ ሺኖዳ መፅሃፍ ይሄን በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋጽዖ ያለው ነው። የነገረ መለኮት አዋቂያንም ደግሞም የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ መረዳት የሚፈልጉ ወጣቶችም በቀላሉ አንብበው እንዲረዱት በሚያደርግ ባልተወሳሰበ ቃላት የቀረበ ሥራ ነው።

የሐይማኖት መሠረት በሆነው በክርስቶስ ባህርይ ላይ ልዩነት ባላቸው ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ንግግሮች መደረግ የጀመሩት በ 1971 austria vienna ላይ ነው። "pro oriente" ብለው popኡ የሚጠሯቸው ቡድኖች ናቸው ንግግሩ እንዲደረግ ያመቻቹት።

እና በዚህ ውይይት ላይ የግብጽ እና የሶሪያ ቤተክርስቲያን በአንድነት አስቀምጠው የነበረው theological formula በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ያገኘ ነው። "የሮም ቤተክርስቲያን እና የeastern orthodox እንስማማበታለን ላሉት ለዚህ theological formula የሚገዛ ልምምድ ተከተሉ ወይ?"የሚለው ሌላ ጥያቄ ቢሆንም።

We believe that our Lord and Saviour, Jesus Christ, is God the Son Incarnate; perfect in his divinity and perfect in his humanity. His divinity was not separated from his humanity for a single moment, not for the twinkling of an eye. His humanity is one with his divinity without commixtion, without confusion, without division, without separation. We in our common faith in the one Lord Jesus Christ, regard his mystery inexhaustible and ineffable and for the human mind never fully comprehendible or expressible."

መፅሃፉን የሚጀምሩት የክርስቶስን ባህርይ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምታምነው እምነት አንጻር በመግለጽ ነው። ቤተክርስቲያናችን ክርስቶስ እርሱ በእውነት እግዚአብሔር እንደሆነ ታምናለች።

ቅድምና ያለው የእግዚአብሔር ቃል ፍጹም የሆነ የሠው ስጋን ከማርያም ወስዶ ከራሱ ጋር እንዳዋሃደ በተዋሃደው ስጋም አንድ የሆነ እርሱ እንደተገለጠ ታምናለች።፡

“And without controversy great is the mystery of godliness: God was manifest in the flesh, justified in the Spirit, seen of angels, preached unto the Gentiles, believed on in the world, received up into glory.”
1 Timothy 3:16 (KJV)

በቅድምና የነበረ የመለኮት ባህርይም መጀመሪያ ያለው የሰውነት ባህርይም ካልጠፋ ታድያ ይሄ አንድ ባህርይ የምትሉት የክርስቶስ ባህርይ ምንድነው? የሚል ጥያቄንም ይመልሳል። ይህ አንዱ ባህርይ ሥግው ቃል ወይንም incarnate logos የምንለው ነው።



Theological ንግግሮች በሚደረጉበት ቦታዎች ላይ የምንታዘበው አንድ ነገር አለ። አንድ ባህርይ ብላ የምታምነውን ቤተክርስቲያን monophysite ብላ እንደምታምን አድርጎ መሣል እንግዲህ ቤተክርስቲያን አንድ ባህርይ ስትል ስለ ሆነ ነጠላ ባህርይ እያወራች አይደለም በተዋህዶ 1 ስለሆነው ስለ ስግው ቃል እያወራች ነው። እንዲያውም እንዲህ ያለው ትምህርት በቤተክርስቲያኒቱ ፈጽሞ የተጠላ ና በ ዲዮስቆሮስ በኩል የተወገዘ ነው።

መጽሃፏን ሳነብ ቅር ያለኝን ነገር በመኻል ላንሳ። የቤተክርስቲያን ትምህርት ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ነው። ይሄ ክርስቶስ 1 ባህርይ የሚለው ትምህርትም በኢትዮጵያም ደግሞም በሶሪያም በግብጽም በሌሎችም ኢ ኬልቄዶናውያን አብያተ ክርስቲያናት ያሉ አባቶች እና አማኞች ደግሞም አብያተክርስቲያናቱም እንደ ተቋም ዋጋ የከፈሉበት ነው።

ግን የፖፑ ገለጻ ትንሽ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ያገለለ በሚመስል መልኩ" the coptic and the syrian orthodox christian were cruely persecuated because of their belief" ብሎ አስቀምጧል። አንድ ባህርይ ለሚለው የቀና ትምህርት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የከፈለችውን ዋጋ የሱስንዮስን ዘመን በማስታወስ መረዳት ይቻላል።

ቤተ ክርስቲያን አንድ ባህርይ ስትል ቤተክርስቲያን ከውጪ ሆነው የሚሰሙት ጋር የሆነ misunderstanding ይፈጠራል ይሄም ምንድነው ወይ ሰውነቱን ወይም አምላክነቱን ቀንሰዋል የሚል ግምት የወለደው ሃሳብ ነው።

በክርስቶስ ባህርይ ላይ የተነገሩ ጥንታውያን ኑፋቄዎችን ይዘረዝራል መጽሐፉ ነክተናቸው እንለፍ እነሱም arianism, apolanirus,eutychensን ያነሳልናል።

“ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥”
— ሮሜ 16፥25-26

"It is one nature but it has all properties of two natures" የሚል ገለጻም አላቸው። ከላይ አትናቴዎስን እና ቄርሎስን አብነት አድርጎ " ለአይን ርግብግቢት ለሚሆን ለቅጽበት ያክል ጊዜ እንኳን መለኮት ከሰውነት አልተለየም ብሎናል። እንዲያው በሞተ ጊዜ ነፍሱ ከስጋው እንደተለየ መጻህፍት በአንድነት ይነግሩናል በዚህ ሁሉ ግን መለኮት ከስጋውም ከነፍሱም ጋር ያለመለያየት ተዋኅዶ ነበር።

ስለ ሁለት ባህርይ እያወራን ስለ ቤዛነት ማውራትም አንችልም በነገራችን ላይ ቤዛ ሊሆን የሚገባው አካል ሰው መሆን አለበት ከዚያ ደግሞ የሰዎችን ገደብ የለሽ ሃጢዓት ለመቤዠት የሚያስችል ስልጣን ያለው መሆን አለበት። ለዚህ ደሞ ስግው ቃል ነው ብቸኛ መፍትሔ መሆን የሚችለው። እንደ ሁለት ባህርይ አማኞች የመስቀል ላይ መስዋዕትነት በሰው በብቻው ባህርይ ያለ መለኮት ሱታፌ የተፈጸመ ነው ብንል ቤዛነቱ ሙሉ አይሆንም ወይም ይቅርታን ለማሰጠት አቅም አይኖረውም።

“አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤” 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥8 የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ገለጻም ይሄንን የሚያሳይ ነው። የተሰቀለው ሰውነቱ ብቻ ሳይሆን በተዋህዶ የሰውነትን ግብር ግብሩ ያደረገው መለኮትም ነው ይኸውም አንዱ ስግው ቃል ነው።

በተጨማሪም በሐዋርያት ስራ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ "የሕይወትን ራስ ሰቀላችሁት" ማለቱ የተሰቀለው መለኮት የተለየው ስጋ ብቻ ሳይሆን ስግው ቃል የተባለ አንዱ ክርስቶስ መሆኑን የሚያሳይ ነው።  መለኮት የተለየው ሰውነት ብቻውን ተሰቅሎ የህይወት ራስ ሊባል አይችልማ! ተሰቅሎ የሞተውን ኢየሱስን የህይወት ራስ ያልነው ከተዋሃደው መለኮት የተነሳ ነው

ስለዚህ የሞተውም በመልዕክተ ጳውሎስ የክብር ጌታ ተብሎ የተጠቀሰውም የህይወት ራስ የተባለውም ደግሞም በራዕይ ዮሃንስ ላይ ፊተኛው ና ኋለኛው ብሎ የተናገረው አንዱ ባህርይ ስግው ቃል ኢየሱስ ነው

የቀጠለውን ኮሜንት ላይ ያንብቡ

Показано 19 последних публикаций.

769

подписчиков
Статистика канала