ሕግጋት በአጠቃላይ ይዘታቸዉ መሠረታዊ ሕግ (Substantive laws) እና የሥነ-ሥርዓት ሕግ
(Procedural laws) ተብለው በሁለት ይከፈላሉ፡፡ የሥነ-ሥርዓት ሕግ በበኩሉ የወንጀል ሥነ-
ሥርዓት እና የፍትሐብሄር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ተብሎ ይከፈላል፡፡ አንዳንዴም የማሥረጃ ሕግ
እንደ ሦስተኛ ክፍል ይታያል። መሠረታዊ ሕግጋት የሚባሉት የሰዎችን መብትና ግዴታ
የሚደነግጉ ሲሆን፤ የሥነ ሥርዓት ሕጎች ደግሞ ጥሰት ሲያጋጥም እነዚህ መብትና ግዴታዎች
ሕግን ተከትለው የት እና እንዴት ሊተገበሩ እንደሚገባ አቅጣጫ ይጠቁማሉ፡፡1
የሥነ-ሥርዓት ሕግ ዜጎች በመሠረታዊ ሕግ የተደነገገዉን መብታችውን ለማስከበር የትና
እንዴት እንደሚሄዱ እንዲሁም ክአቤቱታ አቀራረብ ጀምሮ እስከ መጨርሻው ደረጃ (ዉሳኔ
እና አፈፃፀም ድረስ) በሚኖረው ሂደት ሊከተሏቸው የሚገቡ የሥነ-ሥርዓት ደንቦችን
የሚደነግግ ነው። የሥነ-ሥርዓት ሕግ ብቻዉን የሚቆም ሳይሆን መሠረታዊ ሕግጋት
ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል “[ዓ]ላማዉም የፍትሐብሄር ጉዳዮችን ፍትሐዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ቀልጣፋ በሆነ ሁኔታ ዉሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ (…) በመሆኑ (…) እጅግ
ጠቀሜታ ያለዉ ነዉ”፡፡2 የሥነ-ሥርዓት ሕጎችን ማወቅ እና አለማወቅ እንዲሁም ማክበርና
አለማክበር በሕግ የተሰጠንን መብት እና ግዴታ መጠቀም እንደመቻልና አለመቻል ያህል
ነው፡፡3
“የአንድን ክርክር ዉጤት ከመሠረታዊ ሕግ ልዩነት ይልቅ የፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት
ሕግና አተገባበር ልዩነት በበለጠ እንደሚለዉጠዉ በዘመናችን ግንዛቤ ያገኝ ጉዳይ ነዉ፡፡”
http://t.me/lawabelethio