#ጊምቦ
" እንዲህ ያለዉን አረመኔ ህግ የሚለቀዉ ከሆነ መተማመኛችን ምንድን ነዉ ? " - የአካባቢዉ ነዋሪዎች
" ማስረጃ አሰባስቤ ለፍርድ ቤት ባቀርብም የቀረበዉ ማስረጃ በቂ ሆኖ አለመገኘቱን ተከትሎ ከ3 ወራት እስር በኋላ ሊለቀቅ ችሏል " - ፖሊስ
ከዛሬ 3 ወራት በፊት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በተፈጠረ የእርሻ መሬትን የተመለከተ አለመግባባት አቶ ታሪኩ ኃይሌ የተባለ ግለሰብ የገዛ አባቱን በመጀመሪያ በዱላ በመምታት በኋላም ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በገጀራ ቆራርጦ በመግደል መጠርጠሩን ተከትሎ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ይውላል።
የጊምቦ ወረዳ ፓሊስ ምርመራ ሲደረግ ከቆየ በኃላ ግለሰቡ ከወራት እስር በኋላ ተለቋል። ይህ ጉዳይም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ግርምትን እና ድንጋጤን የፈጠረ ሆኗል።
የግለሰቡን ከእስር መለቀቅ ያዩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተለይም የምስክርነት ቃላቸዉን የሰጡ ግለሰቦች በሁኔታው መደናገጣቸውንና ከመግለጽ ባለፈ " ፖሊስ ምን እየሰራ ነው ? " ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
" እንዲህ ያለዉ ነብሰገዳይ በዚህ ሁኔታ ከተለቀቀ በፖሊስና በህግ አካላት ያለን መተማመን ይቀንሳል " የሚሉት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ ጉዳዩን ሲከታተሉት መቆየታቸውን በማንሳት ግለሰቡ በማስረጃ እጥረት ፍ/ቤት #ሊለቀዉ መቻሉን አንስተዋል።
የማህበረሰቡ ጥያቄ ልክ ቢሆንም የፖሊስ ስራ ከቅድመ መከላከል ባለፈ ወንጀል ሲፈጸም ማስረጃ አጠናቅሮ ፍርድ ቤቱ ማቅረብ ላይ እንደሚገታ የሚገልጹት ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ " አሁን ላይ የሁኔታውን ውስብስብና አሳሳቢ መሆን ተከትሎ የክልሉ ፍትህ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ፕሮሰስ ላይ መሆኑን ከክልል ቢሮ መረጃ ደርሶኛል። ለዚህም ስራ ፖሊስ አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል " ሲሉ ጠቁመዋል።
የማህበረሰቡን ቅሬታ በተመለከተም ፥ " ህግ ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚንቀሳቀስ መሆኑ የግድ በመሆኑ የህግ ሂደቱን በትእግስት መጠበቅ ይገባል " ብለዋል።
ፖሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ጥረት ላይ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
መረጃው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።