Репост из: Bahiru Teka
👉 የመውሊድ ታሪክ
መውሊድ የሚለው ቃል የትውልድ ቦታና ጊዜን የሚያመለክት ሲሆን ሰዎች ዘንድ የተለመደው መውሊድ ሲባል የነብዩ ሙሐመድ የልደት ( እሷቸው የተወለዱበት ) ቀን መሆኑን ነው
ስለሆነም ይህ ቀን በዐለም ላይ አብዛኛው ሙስሊም ዒድ አድርጎ ያከብረዋል ይህ ተግባር በሸሪዓ እይታ እንዴት ይታያል የሚለውን ለማወቅ መጀመሪያ ሸሪዓዊ ብያኔ ወይም አንድ ነገር ይፈቀዳል የሚባለው አላህ ያዘዘው ወይም ነብዩ ሙሐመድ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ያዘዙት ወይም ፈለጋቸውን እንድንከተል ያዘዙን ሶሓባዎች የሰሩት ሲሆን ነው
ከዚህ አንፃር መውሊድ ማክበር አላህ አላዘዘውም ነብዩም አላዘዙበትም ሶሐባዎችም አልሰሩትም ከዛ በኀላም የመጡት አራቱም አኢማዎች አልሰሩትም አያውቁትምም ታዲያ እንዴት ተጀመረ ከተባለ በ461ኛው አመተ ሂጅሪያ ግብፅ ውስጥ ዑበይዲዎች የተባሉ የሺዓ አንጃዎች ስልጣን ላይ በወጡበት ጊዜ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ለማድረግ ነብዩንና ቤተሰቦቻቸውን እንወዳለን ለማለት የጀመሩት ነው
የነብዩን መውሊድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ 6 መውሊድ ነበር የጀመሩት እነርሱም
--- የነብዩ መውሊድ
--- የዓልይ " "
--- የፋጡማ " "
--- የሐሰን " "
--- የሑሰይን " "
--- የመሪያቸው " " ነበሩ
እነዚህ ሰዎች ማን ናቸው
ዑበይዲዎች የሚባሉ ሺዓዎች ሲሆኑ ፋጢሚዮች ቀራሚጣዎች ኢስማኢሊዮች በመባል ይታወቃሉ መሰረታዊ የሆኑ የእስልምናን መርሆች የሚንዱ በዐልይና ኢማሞች በሚሏቸው መሪዎቻቸው ድበር የሚያልፉ አምልኮትን ከአላህ ውጪ ለተለያዩ አካላት አሳልፈው የሚሰጡ እስልምና ግልፅና ድብቅ ሚስጥር አለው እኛ ድብቁን ነው የምናውቀው ነብያቶች ግልፁን ነው የሚያውቁት እሱን መከተል ኩፍር ነው የሚሉ ናቸው
በዚህም የመጣ ነብዩ ያስተማሩትን ሸሪዓ ተግባራዊ የሚያደርግን እንደ ካፊር በማየት መግደል ይበቃል ንብረቱም መዝረፍ ይቻላል የሚሉ ሲሆኑ
በዚህም ምክንያት በ300 አመተ ሂጅሪያ አካባቢና ከዛ በኀላ ከዐለም ወደ መካ ለሐጅ የሚመጡትን ሱንይ ሙስሊሞችን በመግደልና በመዝረፍ ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ የነበሩ ሑጃጆች ከሐጅ እንዲቀሩ ያደረጉ የነበሩ ሲሆን
በ317ኛው አመተ ሂጅሪያ ተውበት አድርገን ተመልሰናል በሚል ወደ መካ በመግባት የሐጅ ስራ በሚጀመርበት የ8ተኛው የዙልሒጃ ቀን መሪያቸው አቡ ጣሂር የሚባለው ለተከታዮቹ መካ ውስጥ
ያገኙትን ሁሉ እንዲያርዱ ትእዛዝ በመስጠት ከዐለም የተሰበሰቡ ሑጃጆችን ከነ ኢሕራማቸው አጋድመው እያረዱ ወደ 30000 ( ሰላሳ ሺህ ) የሚሆን ሙስሊም ጨርሰው ጀናዛቸውን በዘምዘም ጉድጓድና በየቦዩ በመጣል ካዕባ በሐጅ አድራጊዎች ደም እንዲጨቀይ ካደረጉ በኀላ መሪያቸው የካዕባን በር ገንጥሎ አውጥቶ ካዕባ ላይ ወጥቶ ቆሞ ዝሆንን ያጠፋው ጌታችሁ የት አለ እኔን ለምን አያጠፋኝም ብሎ በመፎከር ለተከታዮቹ ሐጀረል አስወድን ነቅለው እንዲያወጡ አዞ ሐጀረል አስወድ ተነቅሎ ይዘውት ሄደው ለ20 አመት ያክል ባዶ አድርገውት ያቆዩ ናቸው
እነዚህ ሶዎች ናቸው እንግዲ ታሪካቸውን ከሙስሊሙ አእምሮ ለመፋቅ ነብዩንና ቤተሰቦቻቸውን እንወዳለን ለማለት መውሊድን የጀመሩት
የነብዩ ወዳጆች ወይስ ጠላቶች ?
ወዳጆቹማ አያውቁትም አቡበከር ዑመር ዑስማን ዐልይ ረዲየላሁ ዐንሁም
በመሆኑም አዲስ ፈጠራ በዲን ላይ አላህን ያመፁ ሶዎች ያመጡት ቢዳዓ ነው የነብዩን ጠላት ትተን ወዳጆቻቸውን በመከተል ሱናቸውን እንተግብር
አላህ ሐቅን አውቆ ከሚከተል
ባጢልን አውቆ ከሚርቅ ያድርገን
http://t.me/bahruteka