Репост из: 💎🎀سيرة امهات المؤمنين❄️🌷
بسم الله الرحمن الرحيم
እንብበሽ እለፊው‼️‼️
‼️ነቃ በይ እህቴ ‼️
ስሚኝ ጠንቀቅ በይ ስሚኝ በጥሞና
ያለንበት ዘመን ተሞልቷል በፊትና
አንቺንም በፊትና ሊያጦዙሽ የመጡ
ተልዕኮ ያላቸው ከዲንሽ ሊያስወጡ
ዴሞክራሲ ብለው ከወደ ውጭ መጡ
በቁምሽ ሊገድሉሽ ሳትሞቺ ሊገድሉሽ
የወደዱ መስለው ሳትሞቺ ሊቀብሩሽ
ከቤት ውጪ አሉሽ መስለው ያሰቡልሽ
ማይክራፎን ሰጡሽ ይሰማልሽ ድምፅሽ
ፖለቲካም ግቢ ጥሩ MIND አለሽ
ሀያዕ እፍረትሽን ወደ ኋላ ጥለሽ
ፍጥጥ በይ CONFIDENCE ይኑርሽ
ታምሪያለሽ ቆንጆ ነሽ ይታይ ውበትሽ
ቅንድብብ ቅጥል አ'ርገው ሞዴል አ'ረጉሽ
ለዕቃ ማጣሪያ ቅባት ላይ ለጠፋሽ
የተንቦራፈፈ ሰፊ ልብስ ትተሽ
ንፋስ የገባባት ቧለኒ ኳስ መስለሽ
ዘመናዊሁኚ እያሉ መከሩሽ
ሠልጥኒልን ብለው እያሰየጠኑሽ
የካፊሩን መንገድ ተከታይ አረጉሽ
እስኪ ልጠይቅሽ ነፃነት ማን ሰጠሽ?
እስኪ በይ ንገሪኝ ማ' ናት ሴት ሞዴልሽ?
አብርሃም ሊንከን ነው ነፃነት የሰጠሽ?
ሒላሪ ክሊብተን እሷ ናት ሞዴልሽ?
ስሚኝ' ማ እህቴ አድምጭኝ ዝ'ብለሽ
ሌላ ሳታስቢ ልብሽን ሰብስበሽ
ሀቅን ለመቀበል ቀልብሽን አስፍተሽ
በጅህልና ዘመን ምን ቦታ ላይ ነበርሽ?
ማንም የማይወድሽ ዕቃ ውርስ ነበርሽ
በጅህልና ዘመን ሴት ከተወለደ
ያ ጃሒል አባቷ በጣም ተዋረደ
በማፈሩ ምክንያት ፊቱን አጠቋቁሮ
ከቤትም ሲወጣ አንገቱን ቀርቅሮ
ለምን መሸማቀቅ ባ'ንዲት ትንሽ ሴት
ያለምንም ጥፋት ግድግዳ ውስጥ መክተት
ይህ ነበር መላቸው እሷን ለማጥፋት
ከኖረችም ደግሞ ካ'ፈር ከዳነች
የውርደትን ህይወት ትኖራታለች
ካገባችም ደግሞ ባሏ ቢሞትባት
ልክ እንደ ዕቃው ነበር እሷን 'ሚወርሷት
ተይው አይወራ በጣም ያሳዝናል
ግን ለዚህ ሁሉ ነገር ኢስላም መቶልናል
ምርጥ ዲን ወረደ በጣም ተቆርቋሪ
ነፃነት ዘነበ ሆነሽ ሰላም ኗሪ
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ግን ዛሬ ልዩ አንቺ ዲኑን ተኻልፈሽ
ጌታሽን ተውሽና ነጭ አምላኪ ሆንሽ
ጤና ይስጠው እያልሽ ነፃነት ለሰጠን
ዴሞስን ላመጣው እኩል ላደረገን
ብለሽ ሽምጥጥ ካድ እውነታውን
የወደዱሽ መስሎሽ መረጥሽ እነሱን
የእነሱ መንገድ እውነት ሀቅ መስሎሽ
የእነሱ መንገድ ዋጅብ ሱና መስሎሽ
ዓለይኪ ነጮችን ዓለይኪ እንደተባልሽ
ከሱና አፈንግጠሽ እነሱ ጋር ገባሽ
እስኪ እንደው ልንገርሽ ከ'ነሱ ጅልነት
ሳናይ እምነት የለም ሳናረጋግጣት
የምን ጀነት ጀሒም የቀብር ውስጥ ቅጣት
አናምንም በማለት ሳናረጋግጣት
Camera አስቀመጡ ጅሎቹ ቀብር ውስጥ
ታዲያ አንቺም የነሱን ጥመት ተከትለሽ
ዝም ብለሽ ታያለሽ በቁምሽ ሲቀብሩሽ።
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ስትር ሽፍን በይ ሒጃብ ልበሽ አለሽ
ለማስቸገር ሳይሆን ላንቺው ታስቦልሽ
ከጩልሌ አሞራ ከቁራ ሊያድንሽ
ቆሻሻ ሚወዱ ዝንቦች እንዳይወሩሽ
አንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
መሰተሩን ትተሽ ሒጃቡን አውልቀሽ
ዲኑ ገር ነበረ ራስሽን አስቸገርሽ
ጩልሌም አሞራም አልጠፉም ከዙሪያሽ
ዝንቡም ከቆሻሻ አንቺን ስላገኘሽ
እሽ እንኳን ቢባሉ አይሄዱም ወረውሽ
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ያለመህረም ሠፈር አትውጪ እያለሽ
ዱርዬ ገገሞች አንቺን እንዳይጎዱሽ
እንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
በረጅም ጠያራ አረብ ሀገር በረርሽ
አገሩን አዳረሽ ስራ ፍለጋ እያልሽ
የጌታን ቃል ጣሽሽው ዱንያን ሀገር
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ታዘዥው አክብሪው ቅን ሁኚ ለባልሽ
ይህን ሰበብ አ'ርጎ ጀነቱ ሊያስገባሽ
ስትባይ ለራስሽ ጥቅም ታስቦልሽ
አንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
የእሱን እጅ እኔ አልጠብቅም ብለሽ
ብርር ብለሽ ወጣሽ መልካሙን እረግጠሽ
ጨዋነትን ላንቺ ተመርጦልሽ
አንቺው በገዛ እጅሽ ባርነትን
ምን ትጠብቂያለሽ ዶማ ነው አካፋ
የተቆፈረውን ሲያወጡት ባካፋ
ዶማ አትጠብቂ ሲቆፍሩ አታይም
ሲግድሉሽ ሲቀብሩሽ ዟሂሩን አታይም
ባጢን ባጢኑን ነው ላንቺ አያስታውቅም
ውስጥ ውስጡን መተው ነው አንቺን የቀበሩሽ
ኸይር አሳቢ መስለው ኩፍርን ያስተማሩሽ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
መቼ ያልቃልና ላሳጥረውና
መድሀኒት ልስጥሽ ውጪ ከልመና
ትንሽ ላመላክትሽ ግቢ ወደ ሱና
ወደ ሰለፎቹ ወደ ቀደምቶቹ
ወደ እነ ዒኢሻህ ወደ ምርጥ ሴቶቹ
ወደ እነ ፋጢማህ ምርጥ ሰለፎቹ
ግቢ ወደ ሱና ወደ ሰለፍያ
ጧሊበል ዒልም ሁኚ كني ሰለፍያ
ከሱንይ ተማሪ ከሱና አስተማሪ
ሙዘብዘብን አይተሽ አትደናበሪ
ኪታብ ሀዲስ ይዘሽ በዑስታዝ ተማሪ
ያለ ዕውቀት ህይወት ባዶ ናት እወቂ
ሀቅ ነው 'ምነግርሽ ምክሬን እንዳትንቂ
ለመጥፎ አልሰጥሽም እህቴ እወቂ
ትክክለኛውን መንገድን ከፈለግሽ
ሳታወላውሊ ተጓዥ ቀጥ ብለሽ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
እንቢ አልሰማም ይቅርብኝም ካልሽ
ቢድዓው ከጣመሽ ሱናው ከመረረሽ
ዱንያ ከጣፈጠሽ አኼራን ከረሳሽ
ዓመተ ዱንያ ሁነሽ ጀነትን ካልፈለግሽ
ካፊርን ካከበርሽ اللهን ካልፈራሽ
ስሪ ሁኚ እንደፈለግሽ ትመነጅዋለሽ
ያውም ከታላቁ الرحمن ፊት ቀርበሽ
እኔስ ተናገርኩኝ እህቴ ልንገርሽ
ይህ ነው የሚጠቅምሽ ለዛንኛው ቤትሽ
الله اعلم
በሰማነው ባነበብነው ተጠቃሚ ያድርገን
አሚንንን
https://t.me/misalaallahisone
እንብበሽ እለፊው‼️‼️
‼️ነቃ በይ እህቴ ‼️
ስሚኝ ጠንቀቅ በይ ስሚኝ በጥሞና
ያለንበት ዘመን ተሞልቷል በፊትና
አንቺንም በፊትና ሊያጦዙሽ የመጡ
ተልዕኮ ያላቸው ከዲንሽ ሊያስወጡ
ዴሞክራሲ ብለው ከወደ ውጭ መጡ
በቁምሽ ሊገድሉሽ ሳትሞቺ ሊገድሉሽ
የወደዱ መስለው ሳትሞቺ ሊቀብሩሽ
ከቤት ውጪ አሉሽ መስለው ያሰቡልሽ
ማይክራፎን ሰጡሽ ይሰማልሽ ድምፅሽ
ፖለቲካም ግቢ ጥሩ MIND አለሽ
ሀያዕ እፍረትሽን ወደ ኋላ ጥለሽ
ፍጥጥ በይ CONFIDENCE ይኑርሽ
ታምሪያለሽ ቆንጆ ነሽ ይታይ ውበትሽ
ቅንድብብ ቅጥል አ'ርገው ሞዴል አ'ረጉሽ
ለዕቃ ማጣሪያ ቅባት ላይ ለጠፋሽ
የተንቦራፈፈ ሰፊ ልብስ ትተሽ
ንፋስ የገባባት ቧለኒ ኳስ መስለሽ
ዘመናዊሁኚ እያሉ መከሩሽ
ሠልጥኒልን ብለው እያሰየጠኑሽ
የካፊሩን መንገድ ተከታይ አረጉሽ
እስኪ ልጠይቅሽ ነፃነት ማን ሰጠሽ?
እስኪ በይ ንገሪኝ ማ' ናት ሴት ሞዴልሽ?
አብርሃም ሊንከን ነው ነፃነት የሰጠሽ?
ሒላሪ ክሊብተን እሷ ናት ሞዴልሽ?
ስሚኝ' ማ እህቴ አድምጭኝ ዝ'ብለሽ
ሌላ ሳታስቢ ልብሽን ሰብስበሽ
ሀቅን ለመቀበል ቀልብሽን አስፍተሽ
በጅህልና ዘመን ምን ቦታ ላይ ነበርሽ?
ማንም የማይወድሽ ዕቃ ውርስ ነበርሽ
በጅህልና ዘመን ሴት ከተወለደ
ያ ጃሒል አባቷ በጣም ተዋረደ
በማፈሩ ምክንያት ፊቱን አጠቋቁሮ
ከቤትም ሲወጣ አንገቱን ቀርቅሮ
ለምን መሸማቀቅ ባ'ንዲት ትንሽ ሴት
ያለምንም ጥፋት ግድግዳ ውስጥ መክተት
ይህ ነበር መላቸው እሷን ለማጥፋት
ከኖረችም ደግሞ ካ'ፈር ከዳነች
የውርደትን ህይወት ትኖራታለች
ካገባችም ደግሞ ባሏ ቢሞትባት
ልክ እንደ ዕቃው ነበር እሷን 'ሚወርሷት
ተይው አይወራ በጣም ያሳዝናል
ግን ለዚህ ሁሉ ነገር ኢስላም መቶልናል
ምርጥ ዲን ወረደ በጣም ተቆርቋሪ
ነፃነት ዘነበ ሆነሽ ሰላም ኗሪ
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ግን ዛሬ ልዩ አንቺ ዲኑን ተኻልፈሽ
ጌታሽን ተውሽና ነጭ አምላኪ ሆንሽ
ጤና ይስጠው እያልሽ ነፃነት ለሰጠን
ዴሞስን ላመጣው እኩል ላደረገን
ብለሽ ሽምጥጥ ካድ እውነታውን
የወደዱሽ መስሎሽ መረጥሽ እነሱን
የእነሱ መንገድ እውነት ሀቅ መስሎሽ
የእነሱ መንገድ ዋጅብ ሱና መስሎሽ
ዓለይኪ ነጮችን ዓለይኪ እንደተባልሽ
ከሱና አፈንግጠሽ እነሱ ጋር ገባሽ
እስኪ እንደው ልንገርሽ ከ'ነሱ ጅልነት
ሳናይ እምነት የለም ሳናረጋግጣት
የምን ጀነት ጀሒም የቀብር ውስጥ ቅጣት
አናምንም በማለት ሳናረጋግጣት
Camera አስቀመጡ ጅሎቹ ቀብር ውስጥ
ታዲያ አንቺም የነሱን ጥመት ተከትለሽ
ዝም ብለሽ ታያለሽ በቁምሽ ሲቀብሩሽ።
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ስትር ሽፍን በይ ሒጃብ ልበሽ አለሽ
ለማስቸገር ሳይሆን ላንቺው ታስቦልሽ
ከጩልሌ አሞራ ከቁራ ሊያድንሽ
ቆሻሻ ሚወዱ ዝንቦች እንዳይወሩሽ
አንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
መሰተሩን ትተሽ ሒጃቡን አውልቀሽ
ዲኑ ገር ነበረ ራስሽን አስቸገርሽ
ጩልሌም አሞራም አልጠፉም ከዙሪያሽ
ዝንቡም ከቆሻሻ አንቺን ስላገኘሽ
እሽ እንኳን ቢባሉ አይሄዱም ወረውሽ
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ያለመህረም ሠፈር አትውጪ እያለሽ
ዱርዬ ገገሞች አንቺን እንዳይጎዱሽ
እንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
በረጅም ጠያራ አረብ ሀገር በረርሽ
አገሩን አዳረሽ ስራ ፍለጋ እያልሽ
የጌታን ቃል ጣሽሽው ዱንያን ሀገር
ተቆርቋሪ አሳቢ ምርጥ ዲን ነበረሽ
ታዘዥው አክብሪው ቅን ሁኚ ለባልሽ
ይህን ሰበብ አ'ርጎ ጀነቱ ሊያስገባሽ
ስትባይ ለራስሽ ጥቅም ታስቦልሽ
አንቺ ግን...
እንቢ እንኳን እሰይ ብለሽ
የእሱን እጅ እኔ አልጠብቅም ብለሽ
ብርር ብለሽ ወጣሽ መልካሙን እረግጠሽ
ጨዋነትን ላንቺ ተመርጦልሽ
አንቺው በገዛ እጅሽ ባርነትን
ምን ትጠብቂያለሽ ዶማ ነው አካፋ
የተቆፈረውን ሲያወጡት ባካፋ
ዶማ አትጠብቂ ሲቆፍሩ አታይም
ሲግድሉሽ ሲቀብሩሽ ዟሂሩን አታይም
ባጢን ባጢኑን ነው ላንቺ አያስታውቅም
ውስጥ ውስጡን መተው ነው አንቺን የቀበሩሽ
ኸይር አሳቢ መስለው ኩፍርን ያስተማሩሽ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
መቼ ያልቃልና ላሳጥረውና
መድሀኒት ልስጥሽ ውጪ ከልመና
ትንሽ ላመላክትሽ ግቢ ወደ ሱና
ወደ ሰለፎቹ ወደ ቀደምቶቹ
ወደ እነ ዒኢሻህ ወደ ምርጥ ሴቶቹ
ወደ እነ ፋጢማህ ምርጥ ሰለፎቹ
ግቢ ወደ ሱና ወደ ሰለፍያ
ጧሊበል ዒልም ሁኚ كني ሰለፍያ
ከሱንይ ተማሪ ከሱና አስተማሪ
ሙዘብዘብን አይተሽ አትደናበሪ
ኪታብ ሀዲስ ይዘሽ በዑስታዝ ተማሪ
ያለ ዕውቀት ህይወት ባዶ ናት እወቂ
ሀቅ ነው 'ምነግርሽ ምክሬን እንዳትንቂ
ለመጥፎ አልሰጥሽም እህቴ እወቂ
ትክክለኛውን መንገድን ከፈለግሽ
ሳታወላውሊ ተጓዥ ቀጥ ብለሽ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
እንቢ አልሰማም ይቅርብኝም ካልሽ
ቢድዓው ከጣመሽ ሱናው ከመረረሽ
ዱንያ ከጣፈጠሽ አኼራን ከረሳሽ
ዓመተ ዱንያ ሁነሽ ጀነትን ካልፈለግሽ
ካፊርን ካከበርሽ اللهን ካልፈራሽ
ስሪ ሁኚ እንደፈለግሽ ትመነጅዋለሽ
ያውም ከታላቁ الرحمن ፊት ቀርበሽ
እኔስ ተናገርኩኝ እህቴ ልንገርሽ
ይህ ነው የሚጠቅምሽ ለዛንኛው ቤትሽ
الله اعلم
በሰማነው ባነበብነው ተጠቃሚ ያድርገን
አሚንንን
https://t.me/misalaallahisone