ዲነል ኢስላም Tube


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


🍁ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል) (ﷺ)🍁
🍁ሸሪዓዊ ስርዓቶችን ባማከለ መንገድ መማማርና መተራረም በሙስሊሞች መካከል ሊሰፍን የሚገባ የወንድማማችነት መገለጫ ነው::!!!🍁
🍁(በእውቀትህ ተናገር፤ አሊያም ችለህ ዝም በል::!!)🍁

ስለ
ዲናችን
እንማማር
ሀሳብ አስተያየት ካለዎት
@Dinel_Islam_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ረመዳንና መለያ ባህሪዎቹ

ክፍል ❶

የወሮች ቁንጮ የሆነውና ታላላቅ ችሮታዎችን ጠቅልሎ የያዘው የረመዳን ወር ከነሙሉ ስጦታው እነሆ ቤታችን ድረስ ዘልቆ ገብቷል።

ታላላቅ ትሩፋቶችን አዝሎ በአላህ ፀጋዎች ደምቆ ልቦቻችንን በብርሀኑ ሊሞላን አንድ ሁለት እያለ ነው…፤

በመሰረቱ የረመዳን ወር በሙስሊሞች ልብ ውስጥ ምን ያህል ታላቅ ቦታ እንዳለው ለማንም ድብቅ አይደለም፤ አዎ! ረመዳን የእዝነት፣ የምህረትና ከእሳት ነፃ መውጫ ወር ነው፤ በዚህ ወር ብዙ ስጦታዎችና ልግስናዎች ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘንድ ወደ ባሮቹ ይንቧቧሉ።

ከዚህ ቀጥለን ይህ ወር ከሌሎች ወራት የሚለይባቸውን መሰረታዊ ነጥቦች እንመለከታለን።

የረመዳን ወር መለያዎች

❶. የኢስላም ማዕዘን፡- የረመዳን ወር ከኢስላም ማዕዘናት አንዱ የሆነውን ግዴታ የተደረገብንን ፆም የምንተገብርበት ወር ነው።

የማንኛውም ሰው እስልምና ሊሟላ የሚችለው ረመዳንን ሲፆም ነው፤ የረመዳንን ግዴታነት የሚክድ ሰው ካፊር ይሆናል (ከኢስላም ይወጣል)፤ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።” (አል-በቀራ 2፤ 183)

ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ኢስላም በአምስት ነገሮች ላይ ተገነባ፤ የአላህን ብቸኛ አምላክነትና የሙሀመድን የአላህ መልክተኝነት መመስከር፤ ሶላትን መስገድ፤ ዘካን መስጠት፤ ረመዳንን መፆም፤ የተከበረውን ቤት መጎብኘት (ሐጅ ማድረግ)።”(ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)።

❷. የቁርአን መውረድ፡- ከረመዳን ወር መለያዎች አንዱ አላህ (ሱ.ወ) ቁርአንን በሱ ውስጥ ማውረዱ ነው፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ

“(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው።” (አል-በቀራ 2፤ 185)

ቁርዐን የዚህች ኡማ የህይዎት መመሪያ ነው፤ እሱ ግልጽ የሆነ መፅሐፍና ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ በሱ ውስጥ ቃል ኪዳን፣ ዛቻና ማስፈራሪያ አለበት፤ ቁርዐን ለያዘውና ለተገበረው የቅናቻ መንገድ ነው፤ ለሠራበትና ሐላሉን (የተፈቀደውን) ተጠቅሞ ሐራሙን (ክልከላውን) ለራቀ ብርሃን ነው፤ በእውነትና ውሸት መካከል የሚለየው እሱ ነው፤ እሱ ቧልት ሳይሆን ጥብቅ (ምር) ቃል ነው፤ ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች ይህን የጌታችንን መጽሐፍ በማንበብ፣ በመሀፈዝ /በቃል በመሸምደድ/፣ ትርጉሙን በመረዳት፣ በማስተንተንና በተግባር ላይ በማዋል ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።

❸. የሰይጣን መታሰር፡- በረመዳን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች ይዘጋሉ፤ አመፀኛ ሰይጣናትም ይታሰራሉ፤ በፊት ይደርሱበት የነበረው ቦታ መድረስ አይችሉም፤ ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- http://t.me/Dinel_Islam_Tube

إِذَا دَخَلَ رَمَضَانُ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ الجَنَّةِ ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ رواه البخاري ومسلم .وفي رواية لمسلم: ( وَصُفِّدَتِ الشَّيَاطِينُ) .

“ረመዳን ሲገባ የሰማይ በሮች ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናትም ይቀፈደዳሉ።” በሌላ ዘገባም “ረመዳን ሲመጣ የጀነት በሮች ይከፈታሉ” ብለዋል (ቡኻሪ ዘግበውታል)

❹. የስራዎች ምንዳ መደራረብ፡- በረመዳን ወር የሐሰናት (የመልካም ሥራዎች) ምንዳ እጥፍ ድርብ ይሆናል፤ በረመዳን የሚሰሩ ኸይር ስራዎች ከሌላው ጊዜ የበለጠ ምንዳ ይኖራቸዋል፤ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከሰደቃ በላጩ የትኛው ነው ተብሎ ሲጠየቁ “በረመዳን የሚደረግ”ሲሉ መልሰዋል (ቲርሚዚይ ዘግበውታል)።

❺. ፆመኛ ማስፈጠር፡- በረመዳን ወር ፆመኛ ያስፈጠረ (ፆም ያስፈታ) ከጿሚው ምንዳ ምንም ሳይጎድል እሱ የሚያገኘውን የሚያክል ምንዳ ያገኛል፤ ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:-

من فطر صائماً فله مثل أجره من غير أن ينقص من أجر الصائم شيء

“ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው የፆመኛው ምንዳ ምንም ሳይነካ የፆመኛውን ያክል ምንዳ አለው።” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

❻. ከአንድ ሺህ ሌሊቶች በላጭ የሆነቸው “የለይለተል-ቀድር” በውስጥ መገኘት፡- ይህች ሌሊት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በአመቱ የሚከሰቱ ጉዳዮችን የሚጽፍባት የተባረከች ሌሊት ናት። ከአንድ ሺህ ሌሊቶችም በላጭ ናት

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ

“መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት።”(አል-ቀድር 97፤ 3)
የሷን አጅር (ምንዳ) የተከለከለ ሰው በዙ ኸይር (ትሩፋት) ነገር አልፎታል፤ ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

فيه ليلة خير من ألف شهر، من حرم خيرها فقد حرم

“በሱ (በረመዳን) ከአንድ ሺህ ሌሊቶች የምትበልጥ ሌሊት አለች፤ የሷን ትሩፋት የተከለከለ (ያላገኘ) ሰው በእርግጥም ተከልክሏል”(ሰሂህ- አህመድና ነሳኢይ ዘግበውታል)።

በዛች ለሊት በሙሉ እምነትና ምንዳዋን አስቦ የቆመ (ሌሊቱን በኢባዳ ያሳለፈ) ሰው ያለፈውን ወንጀሉን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይምርለታል፤ ነቢያችን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

من قام ليلة القدر إيماناً واحتساباً غفر له ما تقدم من ذنبه

“ለይለተል ቀድርን ሙሉ እምነት አሳድሮና ምንዳዋን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።
በሌላ አህመድ በዘገቡት ሐዲስም:-

من قامها إبتغاءها، ثم وقعت له، غفر له ما تقدم من ذنبه وما تأخر

“እሷን ፈልጎ የቆመና ያጋጠመችው ሰው ያለፈውና የሚመጣው ወንጀሉ ይማርለታል”ተብሏል።

ይህ በትንሽ ስራ ብዙና ግዙፍ ምንዳ ማግኘት የሰማዩም የመሬቱም ካዝና በጁ የሆነው ጌታ ትሩፋት ነው፤ ምስጋናና መመፃደቅ ለአላህ ብቻ ናቸው።

❼. መላአክት በብዛት ወደ መሬት መውረድ፡-አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ይላል፡-

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ

“በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ።” (አል-ቀድር 97፤ 4)

..........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


🌙🌴•||تلاوة رمضانية||•​🌙🌴

الليلة 7 | رمضان 🌙

الجزء السابع من المصحف الشريف

مـن ⇦121 📖المائدة ۝ 82
إلى ⇦141 📖الأنعام ۝ 110

⏱46:59 د

القارئ : صلاح بو خاطر👤

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube
http://t.me/Dinel_Islam_Tube




❓❓ ጥያቄ፡-

በለሊት ከሱብሒ በፊት ረስቼ አልነየትኩም። ከዚያም ከፈጅር በኋላ እንዳልነየትኩኝ ትዝ አለኝ። ጾሜ ትክክል ይሆንልኛል?

መልስ፡-

ጾም ያለኒያ አይሆንም። ተቀባይነት የለውም። አብዝሃኞቹ ዑለሞች ለየዕለቱ መነየት ግዴታ እንደሆነ ያምናሉ። አንዳንዶቹ የመጀመሪያው የረመዷን ለሊት ላይ የወሩን መነየት ይበቃል ብለው ያምናሉ።

የኒያው ጊዜ ፀሀይ ከጠለቀች በኋላ ንጋት ከመቅደዱ በፊት ነው። በዚህ የጊዜ ገደቡ ውስጥ በማንኛውም ወቅት ሰውየው ኒያ ካደረገ በቂው ነው። http://t.me/Dinel_Islam_Tube

ከኒያው በኋላ ከፈጅር በፊት ቢበላና ቢጠጣም ችግር የለውም። አሕመድ፣ አቡዳዉድ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑማጀህ እና ቲርሙዚይ ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል፡-

مَنْ لم يجمع الصّيام قبل الفجر فلا صِيام له

“ለሊት ጾምን ነይቶ ያላደረ ጾም የለውም።”
ኒያን በንግግር መግለፅ ግዴታ አይደለም። የኒያ ቦታው ልብ ነው። በልቡ ነገ እንደሚጾም ከወሰነ በቂው ነው። እንደውም ነገን በመጾም ሃሳብ ሱሑር ከበላ በቂው ነው።

ነገ ሲጾም ጥም እንዳያስቸግረው ውሃ ቢጠጣ እንኳን በቂ ነው። በለሊት ወቅት ከነዚህ አማራጮች አንዱንም ካልከወነ ጾሙ ተቀባይነት አይኖረውም። ቀዷ ማውጣትም ግዴታ ይሆንበታል።

ይህ ጾሙ ፈርድ ጾም ከሆነ ነው። ጾሙ ሱና ከሆነ ግን በቀን ከዙሁር በፊት መነየት ይቻላል።

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube
http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

የመጨረሻው ክፍል

6.የሰዎችን ጉዳይ መፈፀም

ከታላላቅ በጎ ተግባሮች ውስጥ ለሰዎች ጉዳይ መሮጥና ስለሰዎች መጨነቅ አንዱነው።ስለዚህ ምንዳውም የተግባሩ አምሳያ ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህብለዋል፡-

“ከሠዎች መሀል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ለሠዎች ጠቃሚ የሆነ ነው። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ሥራ ሙስሊም ልብ ውስጥ የምታስገባው ደስታ የምትገላግለው ጭንቅ፣ ከዱንያ የምትፈፅምለት ጉዳይ ወይም የምትገፈትርለት ረሀብ ነው።

በአላህ እምላለሁ መስጂድ ውስጥ ወር በሙሉ ኢዕቲካፍ አድርጌ ከምቀመጥ ለሙስሊም ወንድሜ ጉዳይ ብሮጥ እመርጣለሁ።ቁጣውን የሚደብቅ አላህ ነውሩን ይሸፍንለታል።ቁጭቱን የዋጠ ሰው የቂያም ቀን አላህ ልቡን በውዴታው ይሞላለታል።

የሙስሊም ወንድሙ ጉዳይ እስኪፈፀም ድረስ የተንቀሳቀሰ የሰዎች እግር በሚስትበት ቀን አላህ እግሩን (በሲራጥ ላይ) ያረጋለታል። ጥፉ ስብእና ልክ ኮምጣጤ ማርን እንደሚያበላሽ መልካም ሥራን ያበላሻል።”

ባለቤታቸው የሞተባቸው ሴቶችንና ሚስኪኖችን መንከባከብ የተለየ ምንዳ እንደሚያስገኝ ነብያዊ ሐዲሶች አበክረው ይጠቁማሉ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

الساعي على الأرملة والمسكين كالمجاهد في سبيل الله أو القائم الليل الصائم النهار

“ባላቸው ለሞተባቸው ሴቶች እና ለሚስኪን ጉዳይ የሚሮጥ በአላህ መንገድ ላይ እንደሚታገል (ሙጃሂድ) ወይም ለሊት እንደሚቆምና ቀን እንደሚፆም ሠው ነው።”

7.የነፍስ አድን ጥሪ!

ኢብሊስ ብዙ ሰዎችን ማጥመም ችሏል። ከጌታቸው አምልኮ ጋረዳቸውና በዱንያ ጌጦች እንዲታለሉ አደረገ። ወደ እሳት የሚወስዳቸውን መንገድም መራቸው። እና እኛስ እነዚህን ሰዎች እንተዋቸው፤ ይጥፉ!?

አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

“ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ ‘እኔ ከሙስሊሞች ነኝ’ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?” (ፉሲለት 41፤ 33)
እነዚህን ሚስኪኖች ማዳን አለብን። ዳዕዋ ልናደርግላቸው ይገባል። አላህ ዳዕዋ እንድናደርግ አዟል።

ይህን ትእዛዝ የሚተገብሩ ሰዎችን ደረጃ ከነብያትና ከመልእክተኞች ደረጃ ጋር የሚስተካከል አድርጓል። ምንዳው ደግሞ ድንበር የለውም። ታዲያ ውድ ወንድምና እህቶች ይህን ደረጃ ለማግኘት አንጓጓም!?…

ዛሬ ረመዳን ላይ ሰይጣኖች ታስረዋል። ነፍሶችም ታዛዦች ናቸው። ታዲያ ይህን አጋጣሚ ለዚህ ኃላፊነት መጠቀም ብልህነት አይደለምን!?… የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

لئن يهدي الله بك رجلاً واحداً خير لك مما طلعت عليه الشمس

“ፀሀይ የወጣችበት ሁሉ ከሚኖርህ አላህ አንድን ሰው ወደ ቀና መንገድ ቢመራልህ ይሻልሀል።”
በሉ ሁላችንም እንነሳ ሰዎች እንዲመሩ ሰበብ ለመሆን እና ነፍሶችን ለማዳን እንቁም! የዘነጋን ለማስታወስ፣ የተደናገረን ለመምራት፣ የጠመመን ለማቅናት፣ የተኛን ለማንቃት… እንነሳ!

ከቅርብ ዘመዶቻችን እጀምር። የዱንያን ምንነት እናስረዳቸው። እጃቸውን ይዘን ወደ መስጂድ እንውሰዳቸው። በረመዳን ብቻ መስጂድ የሚገቡ ወንድሞችና እህቶችን ትክክለኛው መንገድ ወዴት እንደሆነ እንጠቁማቸው። ይህን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዱዓ ደጋግመን እናድርግ።

“አል-ላሁም-መ ኢጅዐልና ሁዳተን ሙህተዲን”(አላህ ሆይ /ወደ ቀና/ የተመሩና ሰዎችን ወደ ቀና መንገድ የሚመሩ አድርገን።)

የክፍል ❶❷ ማጠቃለያ

የእድል ወይም የሰዐዳ መሰረት እና መሽከርከሪያ ምህዳር ሁለት ነገሮች ላይ ይንጠለጠላል፤

አላህን በኢኽላስ በማምለክና

ለፍጡራን መልካም በመዋል።

የበጎ አድራጎት በሮች ሰፊ ናቸው። ዋናው ነገር በልብ ተነሳሽነት እና በትጋት ተግባር ላይ መሳተፍ ነው። በተለይም ረመዳን በጎ አድራጎትን ለመልመድ መልካም አጋጣሚ ነውና ይህን ወርቃማ ጊዜ እንጠቀምበት።

ለትዳር አጋር መልካም መዋል፣ ልጆችን ማስደሰትና መንፈሳዊ ህይወታቸውን መከታተል… ከጠቀስናቸው ውስጥ ናቸው። በየቀኑ ከቤተሰቦች ጋር የሚደረግ ስብሰባ ይህን ሊያሳካ እንደሚችል ዘክረናል።

ዝምድናን መቀጠል፣ ምግብ ማብላት፣ ስጦታ ማብዛት፣ የሰዎችን ጉዳይ መፈፀም፣ ሰዎችን ማስታረቅ… የጠቀስናቸው የበጎ አድራጎት ደጃፎች ናቸው። ኑ በነዚህ ደጃፎች ወደ አላህ እንግባ!!!

ምክራችን

በመጨረሻም እነዚህ ተግባሮች ለመፈፀም ሁላችንም ለነፍሳችን ቃል እንድንገባ እንጠይቃለን። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِن يَعْلَمِ اللَّهُ فِي قُلُوبِكُمْ خَيْرًا يُؤْتِكُمْ خَيْرًا

“አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር ቢያውቅ የተሻለን ይሰጣችኋል።” (አል-አንፋል 8፤ 70)
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “…መልካምን አጥብቆ የሚሻ ሰው አላህ ይሠጠዋል።”

ምናልባት አላህ እውነተኛ ፍላጎታችንን አይቶ ከፍላጎታችን ጫፍ ያደርሰን ይሆናል። ልመናችንንም ያሟላልናል። “ስጦታ የሚሰጠው በዝግጅታችን መጠን ነው!”

ነፍስ ታካች ናት። እረፍት በሰጠሀት ቁጥር ጨምርልኝ ትላለች። የረመዳን ወር በቁጥር የሚለኩ ሰዓታት ድምር ነው። ስለዚህ ያሳለፍናቸውን ተግባራት ለመፈፀም በነፍስህ ላይ ቃልን ያዝ። ከአላህ እርዳታ ለምን። እንዲቀበልህም ተማፀን።

❶የቀን እንቅልፍ እንቀንሳለን።

❷ምግብና መጠጥ እንቀንሳለን።

❸ንግግርና ሳቅ አናበዛም።

❹ቁርአንን ማስተንተንና በዘነጋ መንፈስ ያነበብነውን መድገም።

❺ቢያንስ በቀን ሃያ ጊዜ ሞትን ማስታወስ አለብን።

❻ መስጂድ ውስጥ ብዙ መቆየት መልካም ነው።

❼በጊዜ ወደ ጀመዐ ሶላት መሄድ እናዘውትር።

❽ቤታችን የሚመች ከሆነ ለሚስትና ለልጆች የሚሆን የመስገጃ ስፍራ (መስጊድ) እንወስን።

❾በየቀኑ ከትዳር አጋር እና ከልጆች ጋር የሚደረግ ለክትትልና ለንባብ የሚሆን ፕሮግራም እንወስን።

❿ከፈጅር በፊት ተነስተን ተሀጁድ መስገድ፣ ዱዐ እና ኢስቲግፋር ማብዛት አለብን።

❶❶ምርጥ ወቅቶችን መጠቀም አለብን። በእንቅልፍና መሰል ነገሮች ማባከን የለብንም።

❶❷ልባችንን ሰብስበን ዱዐ ማብዛት አለብን። በተለይም ለዱዐ የተመረጡ ወቅቶችን አጥብቀን እንያዝ!

❶❸ ቤታችን ውስጥ ሶደቃችንን የምናጠራቅምበት ሳጥን እናስቀምጥ እና ውስጡ ላይ የየቀን ሶደቃችንን እንክተት።

❶❹ዚክራችንን ከፊክር ጋር እናቆራኝ። የምንሰራቸውን ዒባዳዎችና በጎ ሥራዎች ከኢኽላስ ጋር እናስተሳስር።

❶❺በቀን ለአንድ ሰዐትም እንኳን ቢሆን ኢዕቲካፍ እናድርግ። የመጨረሻዎቹን አስር ቀናት ደግሞ ጠቅልለን እንድንገባ አደራ።

❶❻በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስለፈፀምነው ኃጢያት እና ስህተት ነፍሳችንን መተሳሰብ አለብን።

❶❼በጎሥራዎችን ማብዛት አለብን።

❶❽ለወዳጆቻችንና ለሚስኪኖች ምግብ ማብላት አለብን።

❶❾ለሙስሊሞች ጉዳይ መሯሯጥ አለብን።

❷0የበደለንን ይቅር ማለት እና ልባችንን ማስፋት አለብን።

❷❶ ወደ አላህ መንገድ ሠዎችን መጥራት አለብን።

በመጨረሻ፡-

ውድ አንባቢዎች! ሁላችንም የተለያየ ሁኔታ ላይ የምንኖር ሠዎች ነን። በድንገት ረመዳን ወጥቶብን ግራ እንዳንጋባ የየቀን ፕግራሞቻችንን አሁኑኑ አውጥተን እናጠናቅቅ።

መልካም ረመዳን!! አላሁመ ባሪክ ለና ፊ ረመዳን!!

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❶❶

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ما من ذنب أجدر أن يعجل الله تعالى لصاحبه بالعقوبة في الدنيا مع ما يدخره له في الآخرة من قطيعة الرحم، والخيانة والكذب، وإن أعجل الطاعة ثواب لصلة الرحم، حتى إن أهل البيت ليكونوا فجرة فتنموا أموالهم، ويكثر عددهم إذا تواصلوا

“ዝምድናን እንደመቁረጥ፣ እንደ ክዳትና ውሸት አኼራ ላይ ከሚከማች ቅጣት በተጨማሪ ዱንያ ውስጥ ቅጣት የሚያቻኩል ምንም አይነት ኃጢያት የለም።

ዝምድናን እንደመቀጠል በፍጥነት ምንዳው የሚሠጥበት በጎ ሥራ የለም። የመፍጠኑም ማሳያ ጠማሞች ቢሆኑም እንኳን የዝምድና ቀጣዩ ቤተሰቦች ገንዘብ ሲበረክት ልናይ እንችላለን። ዝምድናቸውን በቀጠሉ ቁጥር ቁጥራቸው ሲበዛም እናያለን።”

የረመዳንን መግባት ዘመዶቻችንን ለመዘየር መልካም አጋጣሚ እናድርገው። ምናልባት የማያዘያይር ችግር ከገጠመን ስልክ እና መሠል የመገናኛ መንገዶችን በመጠቀም ከዚህ በጎ ሥራ ተጠቃሚ እንሁን።
بلوا أرحامكم ولو بالسلام

“…በሰላምታም ቢሆን ዝምድናችሁን ቀጥሉ።”ብለዋል የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)።
ማንም ሰው ያለፈን ጥል እና ቅያሜ ላለመጠያየቂያ ሰበብ ሊያደርገው አይችልም።

አንድ ሠው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መጣና “እኔ ዘመዶች አሉኝ። እቀጥላቸዋለሁ ይቆርጡኛል። መልካም እውልላቸዋለሁ፤ እነርሱ ያስከፉኛል። እኔ ስችላቸው እነርሱ ድንበር ያልፉብኛል።” አለ። መልእክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ አሉ፡-

لئن كان كما تقول فكأنما تسفهم الملل ولا يزال معك من الله ظهير عليهم ما دمت علي ذلك

“እንደምትለው ከሆንክ ልክ ረመጥ እንደምታቅማቸው ነው። በዚህ ሁኔታ እስካለህ ድረስ ላንተ ከአላህ በኩል ጠባቂ ከመኖር አይወገድም።”

4.ምግብ ማብላት

ይህ ትልቅ የበጎ ተግባር ደጃፍ ነው። ነገር ግን ብዙዎች ችላ ብለውታል።

إن من الجنة غرفا يري ظاهرها من باطنها، وباطنها من ظاهرها قالوا: لمن هي يا رسول الله؟ قال: لمن أطعم الطعام وأطاب الكلام، وصلى بالليل والناس نيام

“ጀነት ውስጥ ሰገነቶች አሉ። የውጭው ክፍል ከውስጥ ይታያል። የውስጡን ደግሞ ከውጭ በኩል ማየት ይቻላል።”

አሉ፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)። የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለማን የተዘጋጁ ናቸው? ብለው ጠየቁ፤ ሶሐቦቹ። “ምግብ ላበላ፤ ንግግርን ላሳመረ፤ ሰዎች ተኝተው ሳሉ በለሊት ለሰገደ።”
ሱሀይብ (ረ.ዐ.) ብዙ ምግብ ያበላ ነበር።

ከዚያም ዑመር (ረ.ዐ.) “ሱሀይብ ሆይ! አንተ ብዙ ምግብ ታበላለህ። ይህ ደግሞ ገንዘብን ማባከን ነው።” አሉት። እርሱም “የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ከእናንተ መሀል ምርጣችሁ ምግብ ያበላና ሰላምታን የመለሰ ነው። ብለውኛል። እኔንም ብዙ እንዳበላ ያደረገኝ ይህ ነው።” አለ።

ዐሊይ ኢብኑ አቢጣሊብ (ረ.ዐ.) እንዲህ ይሉ ነበር። “ወደ ሱቅ ወጥቼ አንዲት ባርያ ገዝቼ ነፃ ከማደርግ ጓደኞቼን ሰብስቤ አንዲት ቁና ምግብ ባበላ እመርጣለሁ።”

በመሀላችን ያለውን ትስስርና ፍቅር ለማጠንከር ጓደኞቻችንን፣ ወዳጆቻችንን፣ ወንድሞቻችንን እና ጎረቤቶቻችንን ሰብስበን ብንጋብዝ መልካም አየር እንፈጥራለን። ከዚሁ ጋር ምስኪኖችን ማብላት ደግሞ ልዩ ጥቅም አለው።

ልቡ በመድረቁ እየተጎዳ መሆኑን የመሰሞተን አንድ ሰው የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ሲሉ መክረውታል።

إن أحببت أن يلين قلبك فأطعم المسكين وأمسح رأس اليتيم
 
“ልብህ እንዲለሰልስ ከፈለክ ሚስኪኖችን መግብ። የየቲምን ራስ አብስ።”
ለድሆችና ለሚስኪኖች የማፍጠሪያ ግብዣዎችን እናዘጋጅ።

ከነርሱም ጋር አብረን በመቀመጥ ምግባቸውን ብንቋደስ እና የወንድምነትና የእህትነት ስሜታቸውን ለማሳደግ ብንሞክር ልብ ላይ የሚፈጥረው የኢማን ስሜት ልዩ ነው።

ከዚህም ጋር ችግር ያለባቸውን፣ በበደል ስር የሚኖሩ፣ ነእስር የሚማቅቁት፣ በመሳደድ ላይ የሚገኙና በረሀብ አረንቋ እየተንገላቱ የሚገኙ ህዝቦችን እናስብ።

من فطر صائما كان له مثل أجره غير أنه لا ينقص من أجر الصائم شيئا

“ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው የፆመኛው ምንዳ ሳይቀንስ ለርሱም የፆመኛው አምሳያ ምንዳ።”የሚለውን የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ብስራት እንዳንረሳ።

5.ሠዎችን ማስታረቅ

ብዙ ጊዜ ሠዎች የሚቀያየሙባቸውን ነገሮች ብንመለከት ተራ ጉዳዮች እንደሆኑ እንታዘባለን። ነገር ግን ሰይጣን በመሀል ገብቶ ያቀጣጥለዋል።

ከዚያም አባትና ልጅን ያቆራርጣል። ጎረቤትን ከጎረቤት ጋር ያቃቅራል። ወዳጅን ከወዳጁ ያጣላል። በዚህ በተመረዘ አየር ላይ ጥርጣሬዎች ይበዛሉ። ዝምድናዎችም ይቆረጣሉ። ጠላትነትም ይዋረሳል። ስለዚህ ሠዎችን ለማስታረቅ መጣር ታላቅ ምንዳ አለው።

ብዙ ጊዜ ሠዎች የሚቀያየሙባቸውን ነገሮች ብንመለከት ተራ ጉዳዮች እንደሆኑ እንታዘባለን። ነገር ግን ሰይጣን በመሀል ገብቶ ያቀጣጥለዋል። ከዚያም አባትና ልጅን ያቆራርጣል። ጎረቤትን ከጎረቤት ጋር ያቃቅራል። ወዳጅን ከወዳጁ ያጣላል።

በዚህ በተመረዘ አየር ላይ ጥርጣሬዎች ይበዛሉ። ዝምድናዎችም ይቆረጣሉ። ጠላትነትም ይዋረሳል። ስለዚህ ሠዎችን ለማስታረቅ መጣር ታላቅ ምንዳ አለው።

لَّا خَيْرَ فِي كَثِيرٍ مِّن نَّجْوَاهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَاحٍ بَيْنَ النَّاسِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

“ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም። ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን።” (አን-ኒሳእ 4፤ 114)

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ የሚሳተፍን ሠው ከፆመኞች፣ ከሠጋጆችና ከመፅዋቾች የላቀ ደረጃ እንዳለው ቃል ገብተዋል። ምክንያቱም ይህ ተግባር በማህበረሰብ መሀል እርቅን ማስፋፋት፣ እዝነትና ፍቅርን ማጎልበት ነው። መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ)

ألا أخبركم بأفضل من درجة الصيام والصلاة والصدقة؟ قالوا: بلي، قال: صلاح ذات البين فإن فساد ذات البين هي الحالقة

“ከፆም ከሶላት እና ከሶደቃ ደረጃ በላይ የሆነን ነገር አልነግራችሁም!?” አሉ። “አዎን! ንገሩን” አሉ፤ ባልደረቦቻቸው። “ሰዎችን ማስታረቅ ነው። በሰዎች መሀል ያለ ግንኙነት መበላሸት (ዲንን) ይላጫል።”የተጣሉ ሠዎችን ይህን የአላህ አንቀፅ እናስታውሳቸው።

وَالصُّلْحُ خَيْرٌ

“መታረቅም መልካም ነው።” (አን-ኒሳእ 4፤ 128)
ከነፍሳችን እንጀምር። የበደለንን ይቅር እንበል። ላስከፋን በጎ እንዋል። ለሌሎች ወገኖች የመቻል፣ የትእግስት፣ የእዝነት እና የሰፊ ልብ ምሳሌ እንሁን።

.........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http:


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❿

ከሠዎች ጋር…

ለበጎ ተግባር መሮጥ ለሠዎች መልካም ውለታ ለመዋል መጣር ለቀልብ የሚያተርፈው ትልቅ የኢማን ፀጋ አለ።

ኢማን ይጨምራል። ሠውየውንም አላህ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ያደርገዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

أحب الناس إلي الله أنفعهم، وأحب الأعمال إلي الله عز وجل سرور تدخله علي مسلم، أو تكشف عنه كربة، أو تقضى عنه دينا، أو تطرد عنه جوعا، ولأن أمشي مع أخي المسلم في حاجة، أحب إلي من أن أعتكف في المسجد شهراً، ومن كف غضبه ستر الله عورته، ومن كتم غيظاً – لو شاء أن يمضيه أمضاه – ملأ الله قلبه رضا يوم القيامة، ومن مشى مع أخيه المسلم في حاجته حتى يثبتها له، أثبت الله قدمه يوم تزل الأقدام، وإن سوء الخلق ليفسد العمل كما يفسد الخل العسل

“ከሠዎች መሀል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ለሠዎች ጠቃሚ የሆነው ነው። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ሥራ ሙስሊም ልብ ውስጥ የምታስገባው ደስታ፣ የምትገላግለው ጭንቅ፣ ከዱንያ የምትፈፅምለት ጉዳይ ወይም የምትገፈትርለት ረሀብ ነው።

በአላህ እምላለሁ መስጂድ ውስጥ ወር በሙሉ ኢዕቲካፍ አድርጌ ከምቀመጥ ለሙስሊም ወንድሜ ጉዳይ ብሮጥ እመርጣለሁ።

መበቀል እየቻለ ቁጣውን የሚደብቅ አላህ ነውሩን ይሸፍንለታል። ቁጭቱን የዋጠ ሰው የቂያም ቀን አላህ ልቡን በውዴታው ይሞላለታል።

የሙስሊም ወንድሙ ጉዳይ እስኪፈፀም ድረስ የተንቀሳቀሰ የሰዎች እግር ሲራጥ ላይ በሚስትበት ቀን አላህ እግሩን ያረጋለታል። ጥፉ ስብእና ልክ ኮምጣጤ ማርን እንደሚያበላሽ መልካም ሥራን ያበላሻል።”
ውድ አንባቢዎች!

በረመዳን ውስጥ ቢሠሩ የምንመርጣቸው ውስን መልካም ተግባራትን በሚከተለው የፅሁፋችን ክፍል ላይ እናቀርባለን። ዋናው ነጥብ ግን እንዳይዘነጋ። በረመዳን የምንሠራቸውን ተግባራት ከረመዳን ውጭም ማስለመድ አለብን።

ረመዳን ግን የመለማመጃ ጊዜ ነውና መልካም ነገሮችን በሙሉ መለማመድ አለብን። “መልካም ተግባርን ተለማመዱ፤ መልካም ነገር ልምድ ነውና!” ይባል የለ!!

1.ለሚስትና ለልጆች መልካም መዋል

ለሚስትና ለልጆች መልካም ውለታ መዋል የሚጀምረው እጃቸውን ይዞ ወደ አላህ መንገድ በመምራት፣ ወደ ጀነት የሚደረግ እሽቅድድም ላይ ፈጣን ተወዳዳሪዎች እዲሆኑ በማገዝ ነው። አላህ ይህን እንድናደርግ አዞናል። አንዲህ ብሏል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ።

በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ። አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም። የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።” (አት-ተሕሪም 66፤ 6)

ከረመዳን ሥጦታ መጠቀም አለብን። የቤተሰቦቻችንን ኢማን ማሳደግ አለብን።

ስብእናቸውንም ወደ ላይ ከፍ ማድረግ አለብን። ረመዳን ከመግባቱ በፊት ከነርሱ ጋር እንቀመጥ። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የሚመጥነውን የፕሮግራም ዝርዝር ያውጣ።

ፕግራሙም የጠቀስናቸውን ሁለቱን ምሶሶዎች (ከአላህ ጋርና ከሠዎች ጋር) ማሟላት አለበት።
እንደዚሁም ወቅታቸውን በሙሉ ልናስተናብርላቸው ይገባል።

ግዴታ የሚሆንባቸውን ተግባር የሚፈፅሙበት መንገድም ልናመቻችላቸው ያስፈልጋል። ቤት ውስጥ እንደ መስጂድ አድርገው የሚይዙት ቦታ ማመቻቸት አለብን።

በየቀኑ አብረናቸው የምንሆንበት ለሁሉም የሚመች አጭር የመሰብሰቢያ ጊዜ እናድርግ። ከዚያም የቻልነውን ያህል አብረን ቁርአን እንቅራ።

ከንባባችንም ባሻገር ውስጣችን የተፈጠረውን የማስተንተን ስሜት እንለዋወጥ። ከዚያም አንድ ጠቃሚ የሆነ መፅሀፍ እናነባለን። ምናልባት ሪያዱሷሊሂን ወይም አንድ የሲራ መፅሀፍ ቢሆን እንላለን።

በስተመጨረሻ የቀን ውሎአችንን ተገማግመን መልካም የሠራን በማመስገን ያጓደለውን ደግሞ ስሜቱን በመጠገን እና ለራሳችን እና ለሙስሊሞች በሙሉ ዱዓ በማድረግ ስብሰባችንን እናጠናቅቃለን። ይህን ስብሰባ ከፈጡር በፊት ብናደርገው ደስ ይላል።

2.ችሮታና ልግስና

ይህ የበጎ አድራጎት በር ትልቅ ነው። በተለይም በረመዳን ሁላችን እንድንገባበት ያሻል። “የአላህ መልእክተኛ ቸር ነበሩ። በተለይም በረመዳን ጂብሪል ስለሚያገኛቸው ይበልጥ ቸር ይሆናሉ።

በረመዳን በየለሊቱ ጂብሪል ያገኛቸዋል። ቁርአን ያጣናቸዋል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ከተለቀቀ ጎርፍ የበለጠ ቸር ነበሩ።”

በዚህ ወር ውስጥ መልካም ተግባርን በመፈፀም እራሳችንን ለአላህ እይታ እናቅርብ። እርሱ የቸርነትና የሥጦታ ባለቤት ነው።

إن الله كريم يحب الكرماء جواد يحب الجودة، يحب معالي الأمور ويكره سفسافها
 
“አላህ ለጋስ ነው። ለጋሶችን ይወዳል። ቸር ነው። ቸሮችን ይወዳል። ታላላቅ ነገሮችን ይወዳል። ጅላጅል ነገሮችን ይጠላል።” ይላሉ የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ)። ከቸርና ከለጋስ ሰዎች ባህሪያት መሀል ያለሀሳብ ያላቸውን ሁሉ መስጠታቸው ነው።

ይህ ስጦታቸው ገንዘብ፣ እውቀት፣ ጊዜ ወይም ጉልበት ሊሆን ይችላል። ቁምነገሩ ያላቸውን ሁሉ ይሠጣሉ፤ አይሰስቱም።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አስማእ ቢንት አቢበክርን እንዲህ ብለው መክረዋታል።

لا تحصي فيحصي عليك

“አትቁጠሪ ይቆጠርብሻል!”

የዚህ ንግግር ትርጉም- ኢማም ኢብኑ ሐጀር ፈትህ የተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዳሉት- “ያልቃል ብለሽ ሶደቃ አትከልክይ ማለታቸው ነው። ይህ በረካን የሚያጠፋ ትልቅ ሰበብ ነው። ምክንያቱም አላህ ያለሂሳብ ይመነዳል።

ምንዳው ለማይተመን ጌታ የምንሰጠውን ስጦታ ደግሞ እንዴት እንተምነዋለን! ካላሰበበት አላህ እንደሚመግበው የሚረዳ ሰው ሳያስብና ሳይቆጥር ሊሰጥ ይገባል።”

ረመዳንን ችሮታና ልግስናን የምንለምድበት አጋጣሚ እናድርገው። ከገንዘባችን፣ ከጊዜያችን እና ከጉልበታችን አላህ ላይ አንሰስት። ያለሂሳብ ለአላህ እንለግስ።

በኢማም በይሀቂይ “ሹዐቡል ኢማን” በተሰኘው መፅሀፍ ላይ እንዲህ የሚል ተዘግቧል። “የዚድ ኢብኑ መርዋን ብዙ ገንዘብ መጣለት። ከዚያም እየዘገነ ለወንድሞቹ ይልክ ገባ።

እንዲህም ይል ነበር “እኔ ለወንድሞቼ ጀነት እንዲሰጣቸው እየተማፀንኩት ከገንዘቤ ብሰስትባቸው አላህን አፍረዋለሁ!!”

3.ዝምድና መቀጠል

በረመዳን ውስጥ ያለውን የዝምድና ሐቅ ከመናገራችን በፊት ተከታዩን ሐዲስ አብረን እንድናስተነትን እጋብዛለሁ።

ከሐዲሱ በነፍሳችን ላይ ያጓደልነውን ትርፍ እንገነዘባለን። በዱንያና በአኼራ ለሚሠጡ መልካም ስጦታዎች ያለንን ቸላተኝነትም እንመለከታለን።

...........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❾

“ዓቅል ያላቸው ሰዎች ዚክርን ከፊክር ጋር ፊክርንም ከዚክር ጋር ከማቆራኘት አልቦዘኑም። ከዚያም ልባቸውን አናገሩት ጥበብ ተናገረ።” ብለዋል፤ ሐሰኑል በስሪይ።

የዚክር መጀመሪያው ተፈኩር ነው። አንድን ጉዳይ አስታውሶ ከማስተንተን ዚክር ይወለዳል። ለምሳሌ አንድ ሰው ወንጀሉን ካስታወሰ እና ከአላህ መብት ያጓደለውን ካስተነተነ ኢስቲግፋርን ያስከትላል።

የአላህን ጥበብና ኃያልነት የሚጠቁሙ ፍጥረታትንና ተአምራትን ሲመለከትና ሲያስተነትን ተስቢሕና ተሕሚድ (ምስጋናና አላህን ከጉድለት ማጥራት) ይከተላል።

ከባድ ችግር ሲገጥመውና ወደ አላህ ያለውን ክጃሎት ሲያስብና ሲያስተነትን “ላሐውለ ወላቁው-ወተ ኢል-ላ ቢል-ላሂል-ዓሊዪል ዓዚም” ይላል፤ ከአላህ በቀር ኃይልና ብልሀት የለም ማለት። ሌሎችም ዚክሮች ላይ እንዲሁ፤ ከፊክር ዚክር ይወለዳል።

ለነፍሳችን የዚክርና የፊክር ፕሮግራም እናድርግ። ከዚያም የዚክር ፋይዳ ወደ ልብ እንዲደርስ የሚያስፈልገውን እናድርግ። የሥራችን ምንዳ የሚሟላው በሠራነው ሥራ ምሉዕነት ተመዝኖ ነው። ሥራዎች በቅርፃቸውና በቁጥራቸው አይለያዩም። የሚለያዩት ልብ ውስጥ ባለው የተመስጥኦ ልዩነት ብቻ ነው። ስለዚህ የሁለት ሥራዎች ቅርፅ አንድ ሆኖ የሠማይና የምድር ያህል ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል።

የጧትና የማታ ዚክር ውስጥና የአንዳንድ ሁኔታዎች (አዝካሩል አህዋል) ዚክር ላይ መንፈስን የሚያነቁ ታላላቅ ጉዳዮች ተወስተዋል። ስለዚህ እነዚህን ዚክሮች በወቅታቸው ስንላቸው ውስጣቸው ያቀፈውን ትርጓሜ መዘንጋት የለብንም። ማስተንተን አለብን።

10. ነፍስን መተሳሰብ

ከጥቂት የረመዳን ቀናት በኋላ ነፍስ ለጌታዋ መመሪያ ታዛዥ ትሆናለች። ስለዚህ ባሳለፈችው ጊዜ ስለሠራችው ሥራ መተሳሰብ ብንጀምር አታስቸግረንም። ነፍሳችንን የምንተሳሰብባቸው የተለያዩ ጉዳዮች አሉ።

እነዚህ ጉዳዮች የሙስሊምን ህይወት በሙሉ የከበቡ ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰው እያንዳንዱን የህይወቱን ክፍል መገምገም እና ማስተዋል ይጠበቅበታል። ከዚያም እያንዳንዱ ጉዳይ ላይ እግሩ ያረፈበትን ደረጃ መመልከት ይችላል።

በተለይም ኃጢያታችንን ብንቆጥርና ያጓደልናቸውን ሐቆች ብንዘረዝር መልካም ተውበት እንድናደርግና አካሄዳችንን እንድናሳምር ጠቃሚ ጉልበት ይሰጠናል።

የሙሐሰባ (ራስን የመተሳሰብ) ፈኖች

የአካል ዒባዳዎች፡- አምስት ወቅት ሶላቶችን በመጀመሪያ ወቅታቸው ላይ መስጂድ ውስጥ መስገድ፣ ፈርድ ሶላቶችን ተከትለው የሚመጡትን ሱናዎች መስገድ፣ የሶላት ዚክሮችን ማሟላት፣ የረመዳን ፆምና ሱና ፆሞች፣ በአላህ መንገድ አዘውትሮ መለገስ፣ የጧትና የምሽት ዚክር፣ ንግግርና ተግባር ላይ ሱናን መጠበቅ….

የአካል ኃጢያቶች:- ሐሜት፣ ነገር ማዋሰድ፣ ሰው ላይ ማሾፍ፣ ስላቅ፣ ክርክር፣ የሠውን ምስጢር ማጋለጥ፣ ዘለፋ፣ ውሸት፣ ውድቅ ንግግር፣ የማያውቁትን ማውራት (ሰርሰራ)፣ ዓይንን ከክልክል እይታ አለመጨፈን፣ ብላሽ ነገር ውስጥ መዘፈቅ፣ ቸኩሎ መቆጣት፣ ቃል ኪዳንን ማፍረስ….

የልብ አምልኮዎች:- ሶላት ውስጥ ኹሹዕ (ተመስጥዖ)፣ አላህን መፍራትና እርሱን መጠባበቅ (ሙራቀባህ)፣ የአላህን ውሳኔና ፍርድን መውደድ፣ በአላህ መመካት፣ በአደጋ ጊዜ መታገስ፣ በፀጋ ጊዜ ማመስገን…

የልብ ኃጢያቶች:- በራስ ሥራ መደነቅ፣ መልካም ሥራው እንዲሠማለት መፈለግ፣ ትችትን መስጋት፣ ምቀኝነት፣ ራስን ማታለል፣ ፉክክር፣ በሥጦታ መመፃደቅ፣ ሌሎችን መናቅ፣ ስሜትን መከተል፣ ቂም…

ሐቆች:- የሚስት/የባል ሐቅ፣ የልጆች ሐቅ፣ የወላጆች ሐቅ፣ የዝምድና ሐቅ፣ የጎረቤት ሐቅ፣ የመንገድ ሐቅ፣ የዳዕዋ ሐቅ፣ የወንድማማችነት ሐቅ….

መልካም ሥራዎች፡- የሙስሊሞችን ጉዳይ ለመፈፀም መሯሯጥ፣ ጎንን ማቅለል፣ መተናነስ፣ ህመምተኛን መጠየቅ፣ አስክሬን መሸኘት፣ መልካምን ነገር ለሌሎች መዋል፣ አደራን መወጣት፣ ደስታንና ፈገግታን ማሳየት፣ ሥራን አሳምሮ መሥራት…

ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት እራሳችንን የምንገመግምባቸው ነጥቦች ናቸው። ከእያንዳንዱ ግምገማ በኋላ የአላህን ምህረት መለመን አለብን።

ከተቻለንም በውስጧ ኢስቲግፋር የምናበዛባት ሶላት (ሶላቱት-ተውባ) ብንሰግድ መልካም ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ

“ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ። (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)።” (አሊ ዒምራን 3፤ 135)

የዘጠነኛው ክፍል ማጠቃለያ

እዚህ ክፍል ውስጥ የተጠቀሱት የረመዳንን ፍሬዎች የምንጠቀምባቸው አስር ነገሮች ናቸው። እነዚህን ጥቆማዎች አስታከን ወሩን በሙሉ የምንገለገልበት ፕሮግራም ብናወጣ መልካም ነው።

ለእያንዳንዱ ቀንም የማንለውጣቸው ቋሚ ሥራዎች እንያዝ። መስጂድ ውስጥ ለምናደርገው ኢዕቲካፍ ቋሚ ጊዜ እንወስን።

ከፈጅር ሶላት በኋላ ፀሐይ እስከሚወጣ ድረስ ብናደርገው፤ ይህን ካልቻልን ደግሞ ከዐስር ሶላት በኋላ እስከ መቅሪብ ሶላት ድረስ ብንወስን፤ ይህንን የኢዕቲካፍ ጊዜያችንን ከዚህ በፊት በተናገርነው መልኩ ቁርአን በመቅራት ብናሳልፍ ጥሩ ሠርተናል።

ቤታችን ውስጥ አንድ ሳጥን ብናዘጋጅና የየቀን ሶደቃችንን እዚያ ውስጥ ማጠራቀም ብንለምድ። ከፈጅር በፊት ሰላሳ ደቂቃም ቢሆን ከሶላቱ-ት-ተራዊሕ ውጭ ለተሀጁድ የተወሰነ ጊዜ ብናደርገው…

ከዚክሮች መሀል በቀን ቢያንስ መቶ ጊዜ “ሱብሐነል-ላሂ ወቢሐምዲሒ” ብንል፣ መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ብናደርግ፣ “አል-ላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዲን ወአሊሂ” እያልን መቶ ጊዜ በነብዩ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ሶለዋት (እዝነት) ብናወርድ፣ መቶ ጊዜ “ላሓውለ ወላ ቁው-ወተ ኢል-ላ ቢል-ላሂል-ዓሊዪል ዓዚም” ብለን ኃይልም ሆነ ብልሀት እንደሌለን ብናውጅ….

ከዚያም እነዚህን ዚክሮች ለቀንና ለሌት ብንመድባቸው ዚክራችንን አሳምረን ሰራን ማለት ነው።

ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባቸውን ወቅቶች ጠብቀን አብዝተን ዱዓ ብናደርግ፣ ባህር ውስጥ ሊሰምጥ እንደቀረበ ችግረኛ ጌታችንን ብንለማመን፣ ለወንድሞቻችን እና ለሙስሊሞች ባጠቃላይ ዱዓ ብናደርግ ዱዓንም አሳምረን አደረግን ማለት ነው።

አንዳንድ ወቅቶች ላይ ደግሞ ከሠዎች ተነጥለን ያሳለፍነውን ሁሉ እያሰብን ምህረት ብንለምን ስራችንን በግምገማ ጠበቅነው።

ያለንበትን የኢማን ደረጃም አወቅን ማለት ነው። ከዚያም ስህተታችንን ለማረምና ይበልጥ ለማደግ በኢስቲግፋር አዲስ መዝገብ መጀመር ነው።…

.........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❽

7. ዱዓ

“ዱዓ ዒባዳ ነው።” “ከርሱ በቀር ቀደርን የሚመልስ ሌላ ነገር የለም።” የነገሮች ባለቤትነት በእጁ ላይ ለሆነው አምላክ የሚደረግ መተናነስና መዋረድ የሚንፀባረቅበት ታላቅ ማሳያ ነው።…

ዱዓ ተወዳጅ የሚሆንባቸው ወቅቶች አሉ። ከእነዚህ መሀል እነዚህን እንጥቀስ።

አዛንና ኢቃማ መሀል፣ ከፈርድ ሶላት በኋላ፣ የለሊቱ የመጨረሻው ሲሶ ሲቀር፣ የጁሙዓህ ቀን ኢማሙ ለኹጥባ ሚንበር ላይ ከወጣ አንስቶ ሶላት እስከሚያበቃ፣ የጁሙዓ ቀን የመጨረሻዎቹ ሰዓታት፣ ለይለቱል ቀድር ላይ፣ ዝናብ ሲዘንብ፣ ፆመኛ ሲያፈጥር፣ ሙሳፊር (መንገደኛ)…

የረመዳን እያንዳንዱ ለሊት ላይ ከእሳት ነፃ የሚደረጉ ሰዎች አሉ… ባርያ ወደ ጌታ ከሚቀርብባቸው ጊዜያት ዋነኛው ሱጁድ ላይ ነው። ስለዚህ እነዚህን አጋጣሚዎች እንጠቀምባቸው። ለአላህ ያለንን ክብርና መተናነስ እንግለፅባቸው።

ከኃይልና ብልሀታችንም እንፅዳ። እዝነቱንና ቸርነቱን እንለምነው። የዱንያና የአኼራ መልካም ነገሮችን ሁሉ እንጠይቀው። ልባችን ሳንሰበስብ በምላሳችን ብቻ ከምናደርገው ዱዓም እንጠንቀቅ።

የአላህ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡-

واعلموا أن الله لا يستجيب الدعاء من قلب غافل لاه

“እወቁ! አላህ ዝንጉና ቸላተኛ ከሆነ ልብ ልመናን አይቀበልም።”

በየቦታው በበደል ለሚረግፉት እና ለሚጨፈጨፉት ሙስሊሞች የተለየ ዱዓ እናድርግ። እንዲሁም በየሥፍራው ድንበር የሚያልፉ እና በደል የሚፈፅሙ ጠማማዎች ላይ እርግማን እናውርድ።

አላህ የሙስሊሙን ጭንቀት እንዲገላግል፣ ችግሩን እንዲቀርፍና ቃል የገባልንን ድል እንዲያወርድልን እንለማመነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَكَانَ حَقًّا عَلَيْنَا نَصْرُ الْمُؤْمِنِينَ

“ምእመኖቹንም መርዳት በእኛ ላይ ተገቢ ሆነ።”(አር-ሩም 30፤ 47)

8. ሶደቃ (ምፅዋት)

የአላህን ኪታብ የሚያጠና ሰው ሁሉ አላህ ሙስሊሞች ገንዘባቸውን በአላህ መንገድ ወጭ እንዲያደርጉ ሲቀሰቅስ ይመለከታል።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከማንም በላይ ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ነው። አላህ እንዲህ ይላል

خُذْ مِنْ أَمْوَالِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم

“ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ።” (አት-ተውባ 9፤ 103)

ከሶደቃ የሚጠቀመው የመጀመሪያው ሰው ሶደቃ አድራጊው ነው። ምክንያቱም ከስስት ታጠራዋለች። ከኃጢያትም ትጠብቀዋለች። ከመከራም ትከላከልለታለች።

ነፍስ ወደ ላይ ከፍ ለማለት የምታኮበኩብበትና ከምድር ስበት የምትርቅበት የመጀመሪያ ርምጃዋም ከስስት መዳኗ ነው።

ሁሌም ቢሆን ሶደቃ ማብዛት አለብን። ቸርነት የስብእናችን መገለጫ እስኪሆን ድረስ ወጪ መልመድ አለብን። ከዚያም ከገንዘብ ፍቅር እንድናለን። ለአኼራ ያለን ዝንባሌም ያብባል።

ሶደቃ በዱንያም ሆነ በአኼራ ታላቅ ትርፍ ያስገኛል። ህመምተኞችን ይፈውሳል። በላእን ይገፈትራል። ጉዳይን ያግራራል። ሪዝቅ ያመጣል። ከክፉ አወዳደቅ ይጠብቃል። የጌታን ቁጣ ያጠፋል። የኃጢያት ፋናን ያስወግዳል። የቂያም ቀን ለሶዳቂው ጥላ ይሆናል። ከእሳት የሚከላከልበት ጋሻም ይሆንለታል።

ከቅጣት የሚከላከልበት መደበቂያ ይሆንለታል። ሶደቃ ወደ አላህ ከምናደርገው ጉዞ ጋር ጠንካራ ትስስር አለው።

አላህ እንዲህ ይላል፡-

فَآتِ ذَا الْقُرْبَىٰ حَقَّهُ وَالْمِسْكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ لِّلَّذِينَ يُرِيدُونَ وَجْهَ اللَّهِ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

“የዝምድናን ባለቤት ተገቢውን ስጠው። ለድኻም ለመንገደኛም (እርዳ)። ይህ ለእነዚያ የአላህን ፊት (ውዴታውን) ለሚሹ መልካም ነው። እነዚያም እነርሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው።” (አር-ሩም ፤ 38)

ማንም ሰው ቢሆን ሰደቃ ማድረግ ይችላል። ሶደቃ የሚተውበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። ሶደቃ የምናደርግበት መጠን ገደብ የለውም። የምንችለውን ሶደቃ እናድርግ። በሩ ለሁሉም ክፍት ነው።

ሶደቃ ፍሬ እንዲኖረው በየቀኑ መደጋገም አለበት። አላህ እንዲህ አለ፡-

الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም በግልጽም የሚለግሱ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው። በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም።” (አል-በቀራ 2፤ 274)

የተምር ክፋይ የሚያህልም ቢሆን በየቀኑ ሶደቃ እናድርግ። ቤታችን ውስጥ የሶደቃ ሳጥን እንወስን። ባመቸን ጊዜ ሶደቃችንን እናጠራቅምና ለሚገባቸው እናድርስ። በዚህ መልኩ ሶደቃ ላይ እንዘውትር።

9. ፊክርና ዚክር

አላህን ማውሳት የልብ ቀለብ ነው። የህይወቱም መሰረት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

مثل الذي يذكر ربه والذي لا يذكر ربه مثل الحي والميت

“ጌታውን የሚያወሳ ሰውና ጌታውን የማይዘክር ሰው ምሳሌያቸው ህይወት እንዳለውና እንደሞተ ሠው ነው።”

ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ብለዋል፡-

الذكر للقلب مثل الماء للسمك، فكيف يكون حال السمك إذا فارق الماء ودور الجنة تبنى بالذكر، فإذا أمسك الذاكر عن الذكر أمسكت الملائكة عن البناء. فإذا أخذ في الذكر أخذو في البناء

“ዚክር ለቀልብ ልክ እንደ ውሀ ለአሳ ነው። አሳ ከውሀ ውስጥ ሲወጣ እንዴት ይሆናል!!?… የጀነት ቤቶች የሚሰሩት በዚክር ነው። ዛኪር ከዚክር ሲቋረጥ መላኢካዎቹም ከመገንባት ይቋረጣሉ። ሲዘክር ደግሞ ይገነባሉ።”

ሙስሊም ከዚክር እንዲጠቀም፣ ልቡንና ምላሱን አንድ እንዲያደርግ እና የሚፈለገውን ጥቅም ለማግኘት እንዲረዳው ከተፈኩር (ከማስተንተን) ጋር ማስተሳሰር መልካም ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ لَآيَاتٍ لِّأُولِي الْأَلْبَابِ * الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ

“ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንንም በመተካካት ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ። (እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- ‘ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን’ የሚሉ ናቸው።” (አሊ ዒምራን 3፤ 190-191)

.........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?

ክፍል ❼

5. ከተከበሩ ወቅቶች መጠቀም

ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ፡-

“አላህ ለአንዳንድ ወራት የተለየ ክብር ሰጥቷል። አንዳንድ የለሊትና የቀን ክፍሎችን ልዩ ክብር እንደቸረ ማለት ነው። ለይለቱልቀድርን ከአንድ ሺህ ወራት በላይ እንድትሆን አድርጓል።…

እያንዳንዱ ልዩ አጋጣሚ ወደ አላህ የምንቃረብበት የራሱ የሆነን ተግባር አካቷል። በእነዚሁ አጋጣሚዎች አላህም ለባሮቹ የሚቸረው ልዩ ስጦታ አለው።

እድለኛ ማለት እነዚህን አጋጣሚዎች ጌታውን ለማገልገል በመንቀሳቀስ የተጠመደና በተከበሩት ወራትና ሰዓቶች ውስጥ ያለውን የጌታ ስጦታ የዘረፈ ሰው ነው። እነዚህን ስጦታዎች ማግኘት ማለት ከእሳት እራስን መጠበቅ ማለት ነው።

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-“ጌታችሁ በአመቱ ቀናት ውስጥ ታላላቅ ስጦታዎች (ነፈሓት) አሉት። እራሳችሁን ለነርሱ አቅርቡ። ምናልባት አንዱን ስጦታ ያገኘ ሰው ለዘላለም እድለቢስ አይሆንም።”

እራሱን ለነዚህ ነፈሓት ያቀረበ ያለጥርጥር ትርፎችን ያገኛል። ዝንጉ የሆነና እራሱን ለስጦታዎቹ ያላቀረበ የተነፈገ ሰው ነው!!

በሀያ አራት ሠዓት ውስጥ ወደ አላህ ይበልጥ የምንቀርብባቸው ሦስት ወቅቶች አሉ። እነርሱም የለሊቱ መባቻ፣ የቀኑ መጀመሪያ እና የቀኑ መጨረሻ ናቸው።

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-

إن هذا الدين يسر ولن يشاد الدين أحد إلا غلبه فسددوا وقاربوا وابشروا واستعينوا بالغدوة والروحة وشيء من الدلجة

“ይህ ዲን ገር ነው። ዲንን የሚያካብድ ሰው የለም የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ። (በአላህ ትእዛዝ ላይ) ቀጥ በሉ። መሀለኛ ሁኑ። አይዟችሁ። በጧትና በከሰዓት እንዲሁም በለሊቱ ጥቂት ሠዐት ታገዙ።”

የጧትና የምሽት ውዳሴን የዘገቡ ብዙ ሐዲሶች ላይ ጧትና ማታ አላህን ማወደስ ልዩ ትርፍ እንዳለው ተጠቅሶ እናገኛለን። ሰለፎች በበኩላቸው የከሰዓት በኋላውን ጊዜ ከመጀመሪያው ይበልጥ ያልቁት ነበር።

ኢማም ሐሰን አል-በና እንዲህ ይላሉ፡-

أيها الأخ العزيز أمامك كل يوم لحظة بالغداة ولحظة بالعشى ولحظة بالسحر تستطيع أن تسمو فيها كلها بروحك الطهور إلى الملأ الأعلى، فتظفر بخير الدنيا والأخرة.. وأمامك مواسم الطاعات وأيام العبادات وليالي القروبات التي وجهك إليها كتابك الكريم ورسولك العظيم صلى الله عليه وسلم، فأحرص أن تكون فيها من الذاكرين لا من الغافلين، ومن العاملين لا من الخاملين.. واغتنم الوقت فالوقت كالسيف، ودع التسويف فلا أضر منه

“የተከበርክ ወንድሜ ሆይ! በጧት፣ ከሰዓት በኋላና ዶሮ ጩኸት አካባቢ ንፁህ መንፈስህን ወደ ላይኞቹ ባለሟሎች ማሳደግ ትችላለህ።

ከዚያም የዱንያና የአኼራን ኸይሮች ታገኛለህ።… ከፊትህ ወደ አላህ የምትቃረብባቸው፣ ለአላህ ይበልጥ ታዛዥ መሆንህን የምትገልፅባቸው፣ አምልኮ ላይ የምትበረታባቸው ጊዜያት አሉ።

እነዚህን ቀናቶች እንድትጠቀምባቸው ቁርአንና መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) አስተምረውሀል። ስለዚህ በነዚህ ጊዜያት አላህን ከሚያወሱ እንጂ ከሚዘናጉ እንዳትሆን። ከሠራተኞች እንጂ ከሥራ ፈቶች እንዳትደመር።…

ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም። ጊዜ ሰይፍ ነው። ነገ-ዛሬ ማለትን ተው። ከርሱ የበለጠ ጎጂ ነገር የለምና።”
በየሳምንቱ የሚከሠቱ ልዩ ወቅቶችም አሉ። ከቀናት ውስጥ የጁሙዓ ቀን ታላቅ ክብር አለው።

ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ልዩ ሠዓትን በውስጡ አካቷል። ስለዚህ ለዚህ ቀን ስጦታ ራሳችንን እናቅርብ። ኢማም አን-ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡-

“የጁሙዐህ ቀን ውስጥ ከፈጅር ጀምሮ ፀሐይ እስከሚጠልቅ ድረስ በሙሉ ዱዓ ማብዛት ይወደዳል።

ምክንያቱም የኢጃባው (ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት) ሠዓት መች እንደሆነ ስለማይታወቅ እንዳያመልጠን ለማድረግ ነው። ይህ ቀን ላይ ለዒባዳ መታገል አለብን።

ልዩ የዒባዳ ፕሮግራምም ልናወጣለት ይገባል። የጁሙዐህ ሶላታችንን ለማሳመር ጧት በጊዜ ወደ መስጂድ እንሂድ።…”

ረመዳን ከወራት መሀል ልዩ እንደመሆኑ ለይለቱል-ቀድር ደግሞ ከረመዳን ቀናቶች መሀል ልዩ ስፍራ አለው።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

من قام ليلة القدر إيمانا واحتسابا غُفر له ما تقدم من ذنبه

“ለይለቱል-ቀድርን በኢማንና ከአላህ አጅር አገኛለሁ ብሎ በማሰብ የቆመ ሠው ያስቀደመውን ኃጢያት ሁሉ ይማራል።”

ለይለቱል-ቀድርን መፈለግ የሚገባው አስሩ የመጨረሻ የረመዳን ቀናት ላይ ነው። ስለዚህ እጅግ በጣም መጠንከር ያስፈልጋል።

ለዚህ ነው“የአላህ መልእክተኛ የረመዳን ወር የመጨረሻው አስር ቀን ሲገባ ሽርጣቸውን ያጠብቃሉ። ለሊታቸውን ህያው ያደርጋሉ። ቤተሰቦቻቸውን ያነቃሉ።”

ከእነዚህ ምርጥ የስጦታ አጋጣሚዎች መሀል ሌላኛው የዑምራ አጋጣሚ ነው። ሁላችንም ይህን ስጦታ ለማግኘት እንመኝ።ሁሉ ነገራችንን ለእነዚህ ስጦታዎች ለመጣድ እናሰናዳ። አንዱ አጋጣሚ ቢያመልጠን ሌላኛውን ለማግኘት እንታገል።

6. ኢዕቲካፍ

ኢዕቲካፍ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው። ረመዳን ውስጥም ይሁን ከረመዳን በኋላ የሚወደድ ዒባዳ ነው። በተለይ የረመዳን አስሩ ቀናት ውስጥ ይበልጥ ይወደዳል።

ምክንያቱም እነዚህ ቀናት ውስጥ ከአንድ ሺህ ወራት በላይ የሚሆነው ለይለቱል-ቀድር ይገኛል። ኢማም አህመድ ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ሰው ከሠዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ባይኖረው ይመርጣሉ።

ቁርአን ለማስቀራት ወይም ዒልም ለማስተማርም ቢሆን ከሠዎች ጋር ባይገናኝ ጥሩ ነው። ኢዕቲካፍ ያደረገ ሰው መገለል ይወደድለታል። ከጌታው ጋር በመዋየትና በዱዓ ቢጠመድ መልካም ነው።

ይህ መገለል (ኸልዋ) የጀመዓና የጁሙዓ ሶላት የማይተውበት ሸሪዓዊ ተግባር ነው። በረመዳን ቀናት ውስጥ ምንም ቢያጥር የተወሰነ ሰዓት ኢዕቲካፍ ነይተን የምንቀመጥበት ሠዓት ያስፈልገናል።

በተለይም በአስሩ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ አብዝሀኛ ጊዜያችንን በመስጂድ ውስጥ ማሳለፍ አለብን። ቀን ሥራ ላይ የሚያሳልፍ ወይም በቀን ኢዕቲካፍ ማድረግ የማይችል ሠው ለሊቱን ይጠቀም።

መስጂድ ኢዕቲካፍ ብለን ከገባን ደግሞ ከአላስፈላጊ ቅልቅልና ከማይጠቅም ወሬ መገለል ያስፈልጋል። ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ይላሉ፡-“የኢዕቲካፍ ዓላማ ለፈጣሪ ኺድማ ሲባል ከፍጡራን ጋር ያለንን ግንኙነት ማቋረጥ ነው።”

ሙስሊም እህቶቻችንም በቤታቸው መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላሉ፤ እንደ ሐነፊያዎች አስተያየት።

ስለዚህ ከቀን ውስጥ የተወሰኑ ሠዓታትን ወደ አላህ ለመዞር የቤቷ መስጊድ ውስጥ ብትቀመጥ ይበቃታል።

..........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?

ክፍል ❻

4. የለሊቱ እርጋታና የኢማን ዑደት

የለሊት ሶላት ልብን ህያው የሚያደርግ መልካም መንገድ ነው። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-

عليكم بقيام الليل فإنه دأب الصالحين قبلكم، وقربة إلى الله تعالى، ومنهاة عن الإثم وتكفير للسيئات ومطردة للداء عن الجسد

“ለሊት እንድትሰግዱ አደራ ብያችኋለሁ። እርሱ ከናንተ በፊት የነበሩ ደጋግ ሰዎች ቀለብ ነው። ወደ አላህ መቃረቢያ ነው። ከኃጢያት ያግዳችኋል። ከአካልም በሽታን ያስወግዳል።”

የለሊቱን የልግስና ድግስ መታደም፣

የሚታደለውን ስጦታ ለማግኘት ከሙተሀጂዶቹ ጋር መሰለፍ ኢማን ከሚገኝባቸው መንገዶች አንዱ ነው። አምስቱ ሶላቶች ግድ ከመደረጋቸው በፊት የለሊት ሶላት በመልእክተኛውና ባልደረቦቻቸው ላይ ግዴታ ሆኖ ነበር።

ምክንያቱም ሰው የለሊቱ መሀል ላይ ወደ ጌታው ሲገለል፣ ልቡ ከርሱ ጋር ሲቀጠል ይበልጥ ይፀዳል። ብዙ የፈጣሪ ስጦታዎች ይዘንቡለታል።
ይህ መንገድ ለሊቱን ለብዙ አገልግሎት እንድንጠቀምበት ይረዳናል።

በቁርአን እንድናስተነትን፣ ሩኩዕና ሱጁድ ላይ ያሉትን ድልብ በረከቶች እንድንዘርፍ፣ እራስን ለጌታ በማዋረድ የሚገኘው ምርጥ ስሜትና አላህን በማውሳት የሚገኝ የልብ መረጋጋት… እነዚህ ልብን ወደ ፈጣሪው የሚቃርቡ ምርጥ መንገዶች ናቸው። ስለዚህ የረመዳን አንዲት ለሊትም ብትሆን ያለ ተሀጁድ ሶላት ማለፍ የለባትም።

ስለዚህ የተሻለው አማራጭ ተራዊሕ መስጊድ ውስጥ ከመስገዳችን ባሻገር ከፈጅር ሶላት በፊት ለሶላትና ለኢስቲግፋር የሚበቃ ጊዜ እያለ መነሳት ነው።

እስኪ ይህን እንሞክረው! ወላሂ እውነተኛው ህይወትን እዚያው እናገኛለን። የንጋትን ውበት ከጌታችን ጋር እያወጋን ስናገኘው! እንዴት ይማርካል!!

አንዳንድ ሷሊሆች እንዲህ ብለዋል፡-

ليس في الدنيا وقت يشبه نعيم أهل الجنة إلا ما يجده أهل التملق في قلوبهم بالليل من حلاوة المناجاة

“ዱንያ ውስጥ የጀነት ሰዎች የሚያገኙት አይነት ፀጋ የለም። ነገርግን ተቅዋ ያላቸውና ጌታቸውን የናፈቁ ሰዎች ለሊት ላይ ከጌታቸው ጋር ሲያወጉ የሚያሳልፉት ጣፋጭ ጊዜ የጀነቱን ፀጋ ይመሳሰላል።”

ኢቅባል እንዲህ ይላሉ፡-

“ምንም አይነት ሰው ሁን። የፈለገውን ያህል እውቀትና ጥበብ ይኑርህ። በለሊት የምትረጋበት ጊዜ ከሌለህ ጠብ የሚል፣ ዋጋ ያለው ሥራ የለህም።”

ይህን ንግግር ላብራራው። እንዲህ ማለት ነው። ምርጥ ዳዒ፣ አንደበተ-ርቱዕ መካሪ፣ አንጋፋ መምህር… ወይም የሻኸውን ሁሉ ሁን።

ለሊት ላይ ከአላህ ጋር የምታሳልፈው፣ የስሜት ልብስህን የምታወልቅበት፣ የክብር ካባህን የምትገፍበት… ጊዜ ከሌለህ ነፍስህን መርዳት አትችልም።

ለሊት ላይ ከንቱ ማዕረጎችህን አውልቀህ የጌታውን ቁጣ የሚፈራና ምህረቱን የሚመኝ ባሪያን ምስኪንነት ልበስ። ፍላጎትህን ጠቅልለህ አዘጋጅ።

ዓላማህን ወስን። እንቅልፍ ቀንስ። ከውዱ ጌታህ ጋር ለምታደርገው ግንኙነት እራስህን አዘጋጅ። ሰከንዶቹን ሁሉ እየቆጠርክ የሚከፈትልህን በር ጠብቅ። ከዚያህም ጉዳይህን ሁሉ ይዘህ ግባ። የምትሻውን ሁሉ ይቸርሀል።

የለሊት ሶላት ፊቅሆች

አላህ ለግሶልን ከፈጅር በፊት ከተነሳን መቆማችንን ብቻ ሳይሆን ሩኩዕና ሱጁዳችንንም ማርዘም አለብን። 

“ባርያ ሁሉ ለጌታው ይበልጥ የሚቀርበው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው።” ሱጁድ ላይ ንግስና ሁሉ በእጁ ለሆነው አምላክ ያለንን መተናነስ፣ ፍላጎት፣ ውርደትና ምስኪንነት እናሳይበታለን።

እዚህ ጋር የምናነሳው ምርጥ ግንዛቤ አለ። ዶክተር ዐብዱስ-ሰታር ፈትሑላህ የነገሩንን ነው። እንዲህ ይላሉ።

በሱረቱል ሙዝ-ዘሚል ውስጥ አላህ በነብዩ ላይ የለሊት ሶላት ግዴታ አደረገባቸው። ሱረቱል ሙዝ-ዘሚል መጀመሪያ ከወረዱት የቁርአን ሱራዎች መሀል አንዱ ነው።

በዚህ ጊዜ በወረዱት ጥቂት አንቀፆች ከግማሽ ለሊት በኋላ እንዲያነጉ እንዴት ታዘዙ!? ይህ የሚያሳየው ከቂያሙ ጋር ሱጁድና ሩኩዕ መርዘማቸውም ተፈላጊ ነበር ማለት ነው።
ሱጁድ አላህን የማዋየት፣ ወደርሱ የመጠጋትና ወደርሱ የመሸሽ ምርጥ ማሳያ ነው።

ውዴታውን የምንለምንበት፣ ይቅርታውን የምንጠይቅበት፣ መዋረዳችንን እና ለርሱ መተናነሳችንን የምናሳይበት ምርጥ ሁኔታ ነው። እርሱ ላይ ጉዳያችንን ሁሉ ለአላህ ማቅረብና ችግራችንን መመስሞት እንችላለን።

ስገድም (ወደ አላህ) ተቃረብም

የሱጁድን አላማ ማሳካት እና ወደርሱ መቃረቢያ ማድረግ ከፈለክ ሱጁድህን የሞቀ አድርገው። ወደ ጌታህ እንዲደርስልህ የምትሻውን መልእክት በእምባህ ጎርፍ አሻግረው። በለቅሶህ ክተበው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ እንዲህ ብለዋል፡-

“ለሊቱ ሲጨልም ይታገሉበታል
እስኪወግግ ድረስ በሶላት ይነጋል
ፍርሀት አብርሮት እንቅልፋቸውን
ጎናቸው ራቀ መንጋለያውን
ፍርሀተ-ቢሶች ከአላህ የራቁ
ለሊቱን ሲገፉ እንቅልፍ ሲደልቁ
ጨለማ ዋጣቸው ደጋግ ሰዎችን
እየተማፀኑ ታላቅ ጌታቸውን
የጨለማን ውበት
በጌታ አብርተውት
መስገጃቸውንም በምባ አርጥበውት
ንጋቱ ይመጣል እየነፈረቁ በለቅሶ አጅበውት”

የለሊት ሶላት ከተነፈግን ምን እናድርግ?!

ለሊት ተሀጁድ ላይ ለመንቃት የሚረዱንን ነገሮች ሁሉ አድርገናል። ነገርግን የሚቀሰቅሰን የፈጅር አዛን ነው። ምን እናድርግ? የሚል ጥያቄ ቢከሰት እንዲህ ብለን እንመልስ።

ይህ መነፈግ የአላህ መልእክት ነው። ለባሪያው ትምህርትና ተግሳፅ የያዘ መልእክት። መልእክቱ በተለያየ መልኩ ሊተረጎም ይቻላል። ለምሳሌ በሰራነው ኃጢያት እየተቀጣን ሊሆን ይችላል።

ከአላህ መብቶች መሀል ያላሟላናቸው አሉ ማለትን ሊጠቁመን ይሆናል። ለሊት ለመስገድ ያለን ፍላጎት ደካማ ስለሆነም ሊሆን ይችላል። ወይም ምን እንደምንሠራ ለማወቅ አላህ ሊፈትነን ይሆናል።….

እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲገጥሙ ወደ አላህ መሸሽ ይገባል። ሶላት ሰግደን፣ ምህረት እየለመንን፣ ዱዓ እያደረግን፣ ይቅር እንዲለን እየተማፀንን ወደ አላህ መዞር አለብን።

የለሊት ሶላት ያመለጠው ሰው ከፈጅር እስከ ዙህር ድረስ ባለው ወቅት ቀዳ ያውጣው የሚል- ሙስሊም በዘገቡት ላይ- የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ምክር ላይ እናገኛለን።

አንዳንድ ጊዜ ከሱብሒ በፊት እንነቃና ወደ ሶላት ውስጥ ስንገባ ግን ልባችን ወደ ዱንያ ሸለቆ ይሸሸጋል። እርሱን ለመሰብሰብ ብንጥርም ከሽሽት መመለስ አልቻልንም። ምን እናድግ!?
ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ፡-

“በለሊቱ ጨለማ ውስጥ ከጌታህ ፊት ስትቆም የህፃን ባህሪ ተላብሰህ ቁም። ህፃን ከአባቱ የሆነን ነገር ፈልጎ ካልተሰጠው ያለቅስበታል።”

አደራ አላህን ችክ ብለን መለመን አለብን። ደጋግመን ምህረት መለመን አለብን። በሩ እስኪከፈትልን ማንኳኳት አለብን። አላህ እንዲህ ይለናል፡-

فَلَوْلَا إِذْ جَاءَهُم بَأْسُنَا تَضَرَّعُوا

“ታዲያ ቅጣታችን በመጣባቸው ጊዜ አይዋደቁም ኖሯልን?” (አል-አንዓም 6፤ 43)

ለሊት አለመቆም ወይም የለሊት ሶላት ጥፍጥና መነፈግና ልብ ወደ አላህ እንዳይዞር መከልከል አላህ እኛን የሚቀጣበት አንድ መንገድ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ ወደርሱ መመለስ፣ መተናነስ፣ ምህረት መለመን… አለብን። ምናልባት በዚህ ሁኔታ ሲያየን ሊምረንና ይቅር ሊለን ይችላል።

.......ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?

ክፍል ❺

ማንም ሠው ከቁርአን ጋር ተቀምጦ ሳያተርፍ ወይም ሳይከስር አይነሳም። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا

“ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን። በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም።” (አል-ኢስራእ 17፤ 82)

በምላሳችን ቁርአንን ደግመን ደጋግመን አንብበነው ይሆናል። ብዙ ጊዜ ምኞታችን ከማኽተም (አንብቦ ከመጨረስ) አይዘልም። እንደውም አንዳንዴ ደጋግሞ የማኽተም ውድድር ውስጥ ብዙዎቻችን እንገባለን። በተለይም በረመዳን ይህ ውድድር ይበረታል። ከዚህ ውድድር ግን ለልባችን የሚሆን ጥቅም አናገኝም።

ንባባችን በምላሳችን ብቻ ሆኖ ቁርአን ህይወታችንን ሊቀይር አይችልም። ልክ እንደ ገለባ ነው የኛ ውሎ። ትልቅ ነው። ግን ጥቅም የለውም። ይህ ደጋግ ሠዎች ሁሉ አበክረው የመከሩት አብይ ጉዳይ ነው። ሰይዲና ዓሊይ እንዲህ ይላሉ፡-

لا خير في قراءة ليس فيها تدبر

“ማስተንተን የሌለው የቁርአን ንባብ መልካም ፋና የለውም።”

ሐሠን አል-በስሪይም የህንኑ ያብራሩታል፡-

كيف يرق قلبك وإنما همك أخر السورة؟

“ጭንቀትህ የሱራውን መጨረሻ መድረስ ሆኖ እንዴት ልብህ ይቅጠን?!” ይላሉ።
ኢብኑል ቀዪምም የበኩላቸውን ያክላሉ፡-

لا شيء أنفع للقلب من قراءة القرآن بالتدبر والتفكر، فإنه جامع لجميع منازل السائرين، وأحوال العالمين، ومقامات العارفين .. فلو علم الناس ما في قراءة القرآن بالتدبر لاشتغلوا بها عن كل ما سواه، فقراءة آية بتفكر خير من ختمة بغير تدبر وتفهم

“በእስትንታኔና በማስተዋል ቁርአንን እንደመቅራት ለልብ የሚረባ ነገር የለም። ቁርአን ወደ አላህ የሚጓዙ ሠዎችን ማረፊያዎች (መናዚል)፣ የዓለማትን ሁኔታዎች (አሕዋሎች) እና የዓሪፎችን ደረጃዎች (መቃማት) ሁሉ አሟልቶ ይዟል።…

ሠዎች ቁርአንን አስተንተኖ በማንበብ የሚገኘውን ጥቅም ቢያውቁ ሌሎችን ሥራዎች በሙሉ ትተው በርሱ ይጠመዱ ነበር። አንድ አንቀፅን በማስተንተን እና በግንዛቤ ማንበብ በግርድፍ ከሚነበነቡ ኺትሚያዎች ይሻላል።”

ረመዳን ከቁርአን ጋር ያለንን ትስስር ብቻ ሳይሆን ትድድር የምናስተካክልበት ምርጥ አጋጣሚ ነው።

በቁርአን እንዴት እንጠቀም?!

ቁርአን ቀልብን የማለስለሻ ምርጥ መንገድ ነው። ዉሀይብ ኢብኑል-ወርድ እንዲህ ይላሉ፡- “ብዙ ተግሳፆችን፣ በርካታ ምክሮችን ተመልክተናል። ነገርግን ልብን የሚያለሰልስና ትካዜን የሚፈጥር ቁርአንን እንደማንበብና እንደማስተንተን ያለ ነገር አላየሁም።

ቁርአንን በሚገባው መልኩ ማንበብ- አቡሐሚድ አል-ገዛሊይ ዝንደሚሉት- አእምሮ፣ ምላስና ልብ (ቀልብ) በአንድነት የሚተገብሩት ሥራ ነው። የምላስ ተግባሩ ፊደላቱን አሳምሮ በምላስ ማውጣት ነው። የአእምሮ ተግባር ቃላቱን መተርጎም ነው። የልብ ድርሻ በመልእክቱ መነካትና ተግሳፁን ማስተዋል ነው። ምላስ አንባቢ፣ አእምሮ ተርጓሚ፣ ልብ ደግሞ የተግሳፁ አድማጭ ናቸው።

እነሆ በቁርአን እንድንጠቀም የሚረዱ ተግባራዊ ዘዴዎችን እንጠቁማለን። አላህ የምንጠቀም ሠዎች ያድርገን!

i. ከመቅራታችን በፊት፡- ቁርአን መቅራት ከመጀመራችን በፊት ዱዐ እናድርግ። አላህ ልባችንን እንዲከፍትልን፣ የቁርአኑን ብርሀን እንዲለግሰን እንማፀን።

በቁርአን ልባችን እንዲነካና እንድናስተነትነው እንዲያግዘን እንለምነው። ይህ ዱዓ ልብ ቁርአኑን እንዲቀበል በማዘጋጀት ረገድ ትልቅ ሚና አለው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَمَا يَتَذَكَّرُ إِلَّا مَن يُنِيبُ

“ወደእርሱም የሚመለስ ሰው ቢኾን እንጂ ሌላው አይገሰጽም።” (ጋፊር 40፤ 13)
ii. ቁርአን ማንበብ ማብዛት፡- ከቁርአን ጋር ያለንን ቆይታ ማርዘም እና ቁርአንን አብዝቶ ማንበብ ከቁርአን እንድንጠቀም ይረዳናል።

ከቁርአን ጋር ያለን ቆይታ በሰከነ ስፍራ ላይ ቢሆን መልካም ነው። ከጫጫታ የራቀ ስፍራ ቢሆንም ተመራጭ ነው። ይህ ዘዴ ቁርአን ላይ ትኩረት እንዲኖረን ያደርጋል። ልብን ይሰበስባል። ቂርአት ከመጀመራችን በፊትም ሲዋክና ዉዱእ ማድረግ አንርሳ።

iii. ከሙስሐፍ ላይ፣ በሚሰማ ድምፅና በዝግታ ማንበብ፡- እነዚህ ነጥቦች ቁርአን ከልባችን እንዲሰርግ ከሚረዱ ነገሮች መሀል ናቸው።

በዝግታ ማንበብ (ተርቲል) ስሜትን የሚያንኳኳ የሆነ ነገር አለው። ስሜት ከተቆረቆረ ከግንዛቤያችን ጋር ይጣመራል። ከዚያም ማስተንተን (ተደብ-ቡር) ይወለዳል። ከዚያም ኢማን ይጨምራል።

iv. ያማረ አነባበብ እና ትካዜ፡- ቁርአንን ስናነብ ለእያንዳንዱ ፊደል፣ መሳቢያ (መድ-ድ) እና ድምፅ የድርሻውን እየሰጠን መሆን አለበት። በዚህ መልኩ ካነበብነው የቁርአኑን ውበት ይበልጥ እናገኘዋለን።

ከአናቅፆቹ ጋር ያለንን ቆይታም ጣፋጭ ያደርግልናል። ቁርአንን ስናነብ በትካዜ ድምፅ ብናነበውም በመልእክቱ እንድንነካ ያግዘናል።

v. የአናቅፁ ጠቅላላ ትርጉም፡- ዓቅላችንን የቁርአኑን ትርጉም እንዲረዳ ስናደርግ ከንባባችን ጋር እንድንኖርና ትኩረታችን እንዳይሰረቅ ይረዳናል። ዓቅላችንን እናሰራ ስንል እያንዳንዱ ቃል የያዘውን ምስጢር ለመረዳት እንዳክር ማለታችን አይደለም።

አናቅፆቹ የሚያስተምሩትን ጥቅል ትርጉም ለመረዳት መሞከር ይበቃል። ከዚህ የጀመረው የእስትንታኔ አቅማችን ቀስ በቀስ ያድግና ለትርጓሜዎቹ ያለን መነሳሳትና መነካት ፈጣን እና ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል።

vi. ቁርአን እያናገረህ ነው፡- ቁርአንን ስታነብ እራስህ ላይ እንደወረደና አንተን እንደሚያናግር እያሰብክ አንብብ። ለዚህ እንዲረዳህ አንዳንድ አናቅፆች ጥያቄ አዘል ንግግሮችን ሲያነሱ ለነርሱ መልስ ስጥ። የዱዓ ቦታዎች ላይ አሚን በል።

ስለ ጀነት የሚያወሩ አንቀፆች ላይ ጀነትን ከልብህ ተመኝተህ ለምን። ስለ ጀሀነም ሲነግርህ አላህ እንዲጠብቅህ ተማፀን። አንዲህ ስታደርግ ከቁርአን ጋር ያለህ መግባባት ይጨምራል።

vii. ልብህን የነኩ አናቅፆችን መደጋገም፡- ልብህ ውስጥ የሚገባውን የብርሀን መጠን ለማሳደግና ኢማንህን ለመጨመር አንዳንድ ልብህን የነኩህን አናቅፅ ደጋግመህ አንብባቸው።

viii. ከጎንህ አጠር ያሉ የቁርአን ትርጉም መፅሀፍት ቢኖሩ፡- ትርጉማቸውን መረዳት ይረዳህ ዘንድ የቁርአን ትርጉምና ትንታኔ የያዙ መፅሀፍት ከጎንህ ቢኖሩህ መልካም ነው። ነገርግን አንብበህ ሳትጨርስ እነርሱን እንዳትከፍት።

ምክንያቱም ከቁርአን አየር ያወጣሀል። ከምትኖርበት የመንፈስ እርካታና ተመስጦም ይመልስሀል። የከበዱህን ቃላት ያዛቸውና ከቂርአትህ በኋላ ትርጓሜያቸውን ፈልግ/ጠይቅ።

4. የለሊቱ እርጋታና የኢማን ዑደት

የለሊት ሶላት ልብን ህያው የሚያደርግ መልካም መንገድ ነው። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-

...........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❹

ከአላህ ጋር…

ረመዳን እያንዳንዱ ሙስሊም ልቡን ህያው የሚያደርግባቸው እና ከጌታው ጋር ያለውን አብሮነትና ግንኙነት የሚያዳብርባቸው ብዙ አማካዮችን (ወሳኢል/means) ይፈጥራል። ከእነዚህ ጥቂቶቹን እነሆ፡-

1. ፆም

ይህ ነፍስን ለመቆጣጠር የሚረዳ ምርጥ መንገድ ነው። እንዲህ የምንለው ለምን መሰላችሁ? ነፍስ የአላህን ባሮች ከአላህ መንገድ የምታሰናክል ክፉ ነገር ናት።

ተፈጥሮዋ ደስታን እንድትፈልግና ከግዴታዎቿ እንድትሸሽ ያደርጋታል። እርሷን የሚያርቅ (የሚያርም) ምርጥ መንገድ ደግሞ ፆም ነው።

እርሱ የስሜቷን በር የሚያጣብብ ነገር አለው። ስለዚህ በፆማችን ይህን መጠቀም ከፈለግን የቀኑን አብዝሀ-ክፍል በእንቅልፍ ማሳለፍ የለብንም።

ኢፍጣር ላይ ምግብና መጠጥ ስንጠቀምም መሀከለኛ መሆን አለብን። የምግብ አይነቶችን ማብዛት የለብንም። አንድ አይነት ምግብ በቂያችን ነው።
አል-ሐሊሚይ እንዲህ ይላሉ፡-

“…ሐላል የሆኑ ምግቦችን ማብዛት ጥሩ አይደለም። ምናልባት ሰውነቱን ያከብደውና እንቅልፍ እንቅልፍ ያሰኘዋል።

ከዒባዳና ከዚክር ያግደዋል። ስለዚህ ረሐቡን የሚቆርጥበት ያህል ከተበላ በቂ ነው። ምግብ የሚበላበት አላማም በዒባዳ ለመጠንከር ይሁን።”

ከምግብና መጠጥ ከመፆም ጋር በቻልነው ያህል ከክፉ ንግግሮችና ሳቅ ራሳችንን ማፆም ይገባናል።

“ምላስህን ያዝ!” ይሁን ለራሳችን የምናነሳው መፈክር። ከአልባሌ ጨዋታዎችና ከሌሎችም የምላስ ጣጣዎች እራሳችንን እንጠብቅ።

2. ከመስጊድ ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር

መስጊድ ልብን የሚያበራ ታላቅ ሚና አለው። አላህ እንዲህ ይላል፡-

اللَّهُ نُورُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ 

“አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው።” (አን-ኑር 24፤ 35)
ከዚያም ቀጥሎ ያለውን አንቀፅ ደግሞ እንመልከት።

فِي بُيُوتٍ أَذِنَ اللَّهُ أَن تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ يُسَبِّحُ لَهُ فِيهَا بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ

“አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)። በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ።” (አን-ኑር 24፤ 36)

የእነዚህ ሁለት አንቀፆች ትርጉም እንዲህ ሊለን ፈልጓል።

መስጊድ ውስጥ ልብህ ከአላህ ጋር ይተሳሰራል። ነፍስህም ከኃጢያት ይጠበቃል።

ألا أدلكم على ما يمحو الله به الخطايا ويرفع به الدرجات، قالوا بلى يا رسول الله، قال: إسباغ الوضوء على المكارة وكثرة الخطى إلى المساجد وانتظار الصلاة بعد الصلاة، فذلكم الرباط فذلكم الرباط
“አላህ ኃጢያት የሚምርበት ደረጃ ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልነግራችሁም?!” አሉ የአላህ መልእክተኛ። “አዎን! የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሉ፤ ባልደረቦቻቸው።

“ቅዝቃዜ በሚኖር ጊዜ ዉዱእ አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጊድ እርምጃ ማብዛትና ከሶላት በኋላ ሶላትን መጠበቅ። ይኻችሁ ነው ዒባዳን በዒባዳ ላይ ማነባበር (ሪባጥ) ማለት።”

የሙእሚን ቀልብ ከአንድ ሁኔታ ወደሌላ ይገላበጣል። ውስጡ የሚደረጉ የኢማንና የስሜት ጥሪዎች መሀል የሚደረግ ጦርነት አለ።

በኢማን ጥላ ስር እንዲቆይ ማድረግና ማረጋጋት ይገባል። ይህን ጊዜ የመስጊድ ሚና ጎልቶ ይታያል። ሰይዲና አባሁረይራህ (ረ.ዐ) ተከታዩን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اصْبِرُوا وَصَابِرُوا وَرَابِطُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ ተበራቱም (በጦር ሜዳ ኬላ ላይ) ተሰለፉም ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ።” (አሊ ዒምራን 3፤ 200)

“በነብዩ ዘመን ሪባጥ (በጦር ሜዳ ኬላ ላይ የሚደረግ ሰልፍ) የሚደረግበት ዘመቻ አልነበረም።

ይህ አንቀፅ ለመንገር የፈለገው ዋና ነጥብ ከሶላት በኋላ ሶላት መጠበቅን ነው።”
መስጊድ በጧት እንግባ። ከሰገድን በኋላም ቦታችንን አንተውም። ምክንያቱም መላኢካዎች ዱዐ ያደርጉልናል።

በሃዲስ እንደተዘገበው“እያንዳንዳችሁ በሰገዳችሁበት ስፍራ ከተቀመጠ ዉዱእ እስካልፈታ ድረስ ‘አላህ ሆይ! ማረው። አላህ ሆይ! እዘንለት እያሉ’ መላኢካዎች ዱዓ ያደርጉለታል።”

ይህ ቱሩፋት አብዝሀኛው ሰላቷን ቤቷ ውስጥ የምትሰግድ እህታችን አታጣውም። ቤቷ ውስጥ አንዲት ስፍራ መስጊድ ብላ ብትወስን፣ ወደዚያው ስፍራ በጊዜ ብትሄድ፣ ከሶላት በኋላም ሶላት ብትጠብቅ፣ እዚያው ሶላቱን ብትደጋግምበትና የችሎታዋን ያህል እዚያው ብትቀመጥ ታገኘዋለች።

3. ቁርአን ህይወት ነው

ረመዳን የቁርአን ወር ነው። የነብዩ ተግባር የሚጠቁመው ረመዳን ውስጥ ቁርአንን አብዝቶ ማጥናት አስፈላጊ መሆኑን ነው። ቁርአን ልብን ህያው ለማድረግ ፍቱን መድሀኒት ነው፤ መንፈስን በብርሀን ለማሸብረቅ መልካም መንገድ ነው።

يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ

“እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ።” (ዩኑስ 10፤ 57)

ሙስሊም ለቁርአን ባለው ቅርበት ያህል ለአላህ ይቀርባል። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-

أبشروا!! فإن هذا القرآن طرفه بيد الله وطرفه بأيديكم فتمسكوا به فإنكم لن تهلكوا ولن تضلوا بعده أبداً

“አይዟችሁ! ይህ ቁርአን ጫፉ በአላህ እጅ ነው። ጫፉ ደግሞ እናንተ እጅ ላይ ነው። ከርሱ በኋላ አትጠፉም። አትጠሙምም።”

ይህ መድኃኒት ፍቱን የሚሆነው እና የልባችንን ህመም የሚፈውስልን አላህ እንደሚፈልገው ስንጠቀምበት ነው። ቁርአን የወረደው እንድናስተነትነው ነው።

ከውስጡም ለህይወታችን የሚበጁ ትምህርቶችን እንድንቀስም ታዘናል። በምላሳችን እንድናነበው ብቻ አይደለም ወደኛ የመጣው። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

“(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው። አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)።” (ሷድ 38፤ 29)

አንዳንድ ደጋግ ሰዎች እንዲህ አሉ፡-
ማንም ሠው ከቁርአን ጋር ተቀምጦ ሳያተርፍ ወይም ሳይከስር አይነሳም። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?

ክፍል ❸

لَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ أَن يُجَاهِدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ  وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالْمُتَّقِينَ

“እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትበገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው(ለመቅረት) ፈቃድን አይጠይቁህም። አላህምየሚፈሩትን ዐዋቂ ነው።” (አት-ተውባ 9፤ 44)
ለተግሳፅ እና ለመመሪያዎች በፍጥነት ይታዘዛል።

ذَٰلِكَ يُوعَظُ بِهِ مَن كَانَ مِنكُمْ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ

ዱንያን ችላ ሲል አላህ ዘንድ ላለው ምንዳ ሲሰስት ታየዋለህ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

إذا دخل النور القلب أنشرح وأنفتح قالوا: يا رسول الله وما علامة ذلك؟ قال: الإنابة إلى دار الخلود والتجافى عن دار الغرور والإستعداد للموت قبل نزوله

“ብርሀን ልብ ውስጥ ሲዘልቅ ይሰፋል፤ይከፈታል።” ባልደረቦቻቸውም “የዚህ ምልክትምንድን ነው?” ብለው ጠየቁ። “ወደመዘውተሪያይቱ ዐለም መናፈቅ፣ ከመታለያይቱዓለም መራቅና ሞት ከመድረሱ በፊትመዘጋጀት።” አሉ፤ መልእክተኛው።

እንግዲህ ይህ ከሆነ የአላማችን መሳካት ምልክቱ አንድ ጥያቄ ብቻ ይቀረናል። አላማችንን እንዴት እናሳካዋለን?

ግባችን እውን የሚሆንባቸውን አማካዮች (means/ ወሳኢል) እናውቃቸዋለን። እንደውም አብዛኞቹን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ተግብረናቸዋል።

አዲሱ ነገር እንዴት እንጠቀምባቸው የሚለው ነጥብ ነው። ረመዳን ውስጥ ለሚታሰቡት ዓላማዎች እንዴት እናውላቸው የሚለው ጥያቄ ነው አሳሳቢው። እነዚህን አማካዮች (means/ ወሳኢል) ለሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን።

አንደኛው ክፍል አንድ ባሪያ በርሱና በጌታው መሀል ያለን ችግር የሚያስተካክልበት ነው። አብዝሀኛ ትኩረቱም የመንፈስ እድገቱን የሚያበለፅጉት ላይ ነው።

ሁለተኛው ክፍልም አንድ ባሪያ ከማህበረሰቡ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ዙሪያ ያሉትን ነገሮች የሚያስተካክሉለት አማካዮች ናቸው።

ከእነዚህ ክፍሎች መሀል አንዱን ይዞ ሌላኛውን መተው አይበቃም። ሁለቱም የሙስሊምን የምድር ሚና የሚያሟሉ መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው። አላህ እንዲህ አለ፡-

وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

“እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠናየኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾንከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማንነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅአድርጐ ያዘው።” (አን-ኒሳእ 4፤ 125)

ፊትን ለአላህ መስጠት መንፈሳዊና ከስሜት ጋር የተገናኘ ነገር ነው። ነገር ግን ለፍጥረት መልካም መዋል ሊከተለው ይገባል። አንዳንድ ሰዎች ግን ይህን ስተውታል።

ለአንዱ ትኩረት ሰጥቶ ሌላውን ትኩረት ይነፍገዋል። ሙሉ ትጋቱን በርሱና በፈጣሪው መሀል ያለውን ርቀት ለማጥበብና ግንኙነቱን ለማስተካከል በማዋል ጥቅሙ ለሠዎች የሆነን ተግባር የተወ ሰው ኢማኑ ጎዶሎ ነው።

ኢማን ንግግርና ተግባር ነው። መልካም ሥራዎች የመልካም ሠሪውን ኢማን ይጨምራሉ። የኢማኑን መሠረቶችም ልብ ውስጥ ያሰርፃሉ። አላህ እንዲህ አለ፡-

إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ

“መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል። በጎሥራም ከፍ ያደርገዋል።” (ፋጢር 35፤ 10)
የአንዳንድ ቀደምት ሙስሊሞች ዘገባ ላይ የተገኘ ንግግርን እናድምጥ። እንዲህ ይላል፡-

إن العبد إذا قال لا إله إلا الله بنية صادقه نظرت الملائكة إلي عملة، فإن كان موافقاً لقوله، صعدا جميعاً، وإن كان العمل مخالفاً وقف قوله حتى يتوب من عمله

“አንድ የአላህ ባሪያ በንፁህ ኒያ ‘ላኢላሀ ኢል–ለ–ሏህ’ ሲል መላኢካዎች ሥራውንይመለከታሉ። ተግባሩና ንግግሩ ከተጣጣሙበአንድ ላይ ይዘዋቸው ያርጋሉ። ተግባርከንግግር የተለየ እንደሆነ ከተግባሩእስከሚቶብት ድረስ ንግግሩ እዚሁ ይቆያል።”

በአንፃሩ በሰዎች መሀል የሚደረጉ የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴዎች ላይ መጠመድ፣ የሰዎችን ጉዳይ ለመፈፀም የሚደረግ ሩጫ፣ ችግራቸውን ለመፍታት የሚደረግ ርብርብ፣ ሰዎችን ለመርዳትና ለመጥቀም የሚሠራ ሥራ ከአላህ ጋር ግንኙነት ካለው ልብ ካልመነጨ አደጋ አለው። ምናልባትም በመልካም ሠሪው ልብ ውስጥ አሉታዊ ተፅእኖ ሊፈጥር ይችላል።

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ ያስጠነቅቃሉ፡-

مثل الذي يعلم الناس الخير، وينسى نفسه مثل الفتيلة، تضيء للناس وتحرق نفسها

“ለሠዎች መልካምን ነገር እያስተማረ ነፍሱንየሚዘነጋ ልክ እንደ ሻማ ነው። ለሠዎችእያበራች እራሷን ታነዳለች።”

አል-ራፊዒይ እንዲህ ይላሉ፡-

إن الخطأ أكبر الخطأ أن تنظم الحياة من حولك وتترك الفوضى في قلبك

“ከስህተት ሁሉ ትልቅ ስህተት የሠዎችንህይወት እያሳመርክ የራስህን ልብ ማዝረክረክነው።”
ስለዚህ ሁለቱም ነገሮች በአንድነት መኖር አለባቸው።

............ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል ?

ክፍል ❷

እስቲ እነዚህን አንቀፆች እናስተውል፡-

قَالَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِي الْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ * قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَاسْأَلِ الْعَادِّينَ * قَالَ إِن لَّبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا ۖ لَّوْ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَعْلَمُونَ * أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

“በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትንቆያችሁ?” ይላቸዋል። “አንድ ቀንን ወይምከፊል ቀንን ቆየን። ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ”ይላሉ። “እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥበምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂአልቆያችሁም” ይላቸዋል። “የፈጠርናችሁለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱመኾናችሁን ጠረጠራችሁን?” (ለከንቱየፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)” (አል-ሙእሚኑን 23፤ 112-115)

የቀብር ሰዎች ውድ ምኞት ለአፍታም ቢሆን ወደ ዱንያ መመለስ ነው። አንድ ጊዜ ወደ ህይወት ተመልሶ አላህን ማወደስ፣ ሱብሀነሏህ ማለት፣ አንዲት ጊዜም ቢሆን ለአላህ መስገድ…
እኛስ ከነርሱ አንማርም!? አሁንም ከእንቅልፋችን አንነቃም?! የሚጠብቀንን ፍጥጫ ለመጋፈጥ አንዘጋጅም!? አሁን ዱንያ ውስጥ ፊታችን ላይ የቆሙ ለመጪው አለም የምንሰነቅባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው።

ይኸው ረመዳን ወዲህ እየጠራን ነው። እስኪ እጅጌያችንን አጠፍ አድርገን፣ ፍራሻችንን ትተን፣ ቤተሰቦቻችንን አንቅተን፣ በነፍሳችንና በስሜታችን ላይ የጂሀድ ባንዲራ አንግበን እንነሳ!!

🎈 ኑ የአላህን ጥሪ አሺ እንበል!

اسْتَجِيبُوا لِرَبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَ يَوْمٌ لَّا مَرَدَّ لَهُ مِنَ اللَّهِ ۚ مَا لَكُم مِّن مَّلْجَإٍ يَوْمَئِذٍ وَمَا لَكُم مِّن نَّكِيرٍ

“ለእርሱ መመለስ የሌለው ቀን ከአላህከመምጣቱ በፊት ለጌታችሁ ታዘዙ። በዚያ ቀንለእናንተ ምንም መጠጊያ የላችሁም።ለእናንተም ምንም መካድ የላችሁም።” (አሽ-ሹራ 42፤47)

🎈 ሠዎችና ረመዳን

አዎን! ረመዳን በአመት አንዴ ብቻ የሚከሰት ታላቅ እድል ነው። ነገር ግን ሙስሊሞች በዚህ መልኩ ይተዳደሩት ይሆን? አንዳንዶች የዚህን ወር መምጣት እንደ ከባድ ሸክም ይመለከቱታል። ቶሎ እንዲያልቅም ይመኛሉ።

እነዚህ ከረመዳን የሚያተርፉት ከረህመት መባረር ብቻ ነው። ረመዳን ገብቶ ወጣ እንጂ በህይወታቸው ላይ የሚጥለው መልካም አሻራ የለም። አንዳንዶች ደግሞ የረመዳንን ዋጋ ተረድተዋል። እንዲህ አይነቱ ሰው የበረታ ክንዱን አዘጋጅቷል።

የቻለውን የአምልኮ ተግባር ለመፈፀም መንፈሱ ነቅቷል። ልቡ አብሮት ባይኖርም ብዙ ጊዜ ቁርአን ለማኽተም፣ ብዙ ለመስገድ፣ ብዙ ዒባዳዎችን ለመሥራት አቅዷል። ይህ አይነቱ ሰው መዳረሻ የነበሩትን የአምልኮ ተግባራት ግብ አድርጎ ይዟቸዋል።

ፆም ሊያረጋግጠው የመጣለትን ትልቁን አላማ ግን ዘንግቷል። በእርግጥ ረመዳን በእነዚህኞቹ ልብ ላይ ጥሩ ስሜት ጥሎባቸው ያልፍ ይሆናል። ግን ረመዳን እንደወጣ ቀናት እንዳለፉ ወኔያቸው አብሮ ይከስማል።

አንዳንዶች ደግሞ ረመዳንን ቀልብን ህያው ለማድረግ፣ ከእንቅልፉ ለማንቃትና በውስጡ ላይ የተቅዋን ችቦ ለማቀጣጠልና የኢማንን ሥር ለመትከል ምርጥ አጋጣሚ አድርገው ያዙት። እነዚህኞቹ የፆምን አላማ ሲያስሱ ቆዩና አላህ እንዲህ ሲላቸው አገኙት፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተበፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈበናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁይከጀላልና።” (አል-በቀራ 2፤ 183)

አላህን መፍራት የሁሉም ዒባዳዎች መሪ ዓላማ ነው። አላህ እንዲህ አለ፡-

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንምከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁንተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁይከጀላልና።”(አል-በቀራ 2፤ 21)

በልብ ውስጥ ባለው የተቅዋ መጠንም የሰው ልጅ ለአላህ ያለው ቅርበትና ርቀት ይለካል።

إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ

“አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህንፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልጽን ዐዋቂውስጥንም ዐዋቂ ነው።” (አል-ሑጁራት 49፤ 13)

እንደነዚህ ባሉት ሰዎች አመለካከት- ረመዳን- ሠዎችን ከጌታቸው ለማቅረብ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የመጣ ነው። የሰዎችን ልብ ከዱንያ እድፍ ሊያፀዳ እና ምርጡን ስንቅ እንዲሰነቁ ሊያግዛቸው የተከሠተ ነው።

وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ 

“ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ(አላህን መፍራት) ነው። የአእምሮዎችምባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ።” (አል-በቀራ 2፤ 197)

እርሶም የበረታ ክንዶን ይሰብስቡ። ኢስላም በዚህ ወር ውስጥ ያኖራቸውን የተቅዋ ምንጭ የሆኑ መሳሪያዎችን ተጠቀሙ። የልብና የአካል አምልኮዎችን በአንድነት ይከውኑ። ጥርጥር የሌለው እርግጠኛ ነገር እነዚህ ሦስተኞቹ ሰዎች የወሩ አትራፊዎች ናቸው።

በረመዳን ተጠቅመው ልባቸውን አንፅተዋል። ከዚያም ወደ አላህ የሚያስጠጋቸውን የህይወት ስንቅ ይዘዋል። ለአመታት የሚቆዩበትን ወኔ ሰንቀዋል። ወደ አላህ ከሚጓዙ የአላህ ወዳጆች መሀል ተሰልፈዋል።

🔑 የቀልብ መስተካከል ምልክቶች

ረመዳን የሚያመጣው የልብ ፅዳት ምንድን ነው?! ስትል ያየሁህ መሰለኝ። ልብ ውስጥ ያለው ኢማን ሲነቃቃ… ሥሮቹም ልብ ውስጥ ሲጠልቁ የልብ ፅዳት ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ። ነብያችን እንዲህ ይላሉ፡-

ألا إن في الجسد مضغة إذا صلحت صلح الجسد كله، وإذا فسدت فسد الجسد كله ألا وهي القلب

“ንቁ! አካል ውስጥ ቁራጭ ሥጋ አለች። እርሷከተስተካከለች ሁሉም አካል ይስተካከላል።እርሷ ከተበላሸችም ሁሉ ነገር ይበላሻል። ንቁእርሷም ልብ ናት!!”

የዚህን ልብ ባለቤት ለመልካም ሥራዎች ሲጣደፍ፣ የአላህን ዲን ምልክቶችን ሲያከብር ትመለከተዋለህ። አላህ እንዲህ ይላል፡-

ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ

“(ነገሩ) ይህ ነው። የአላህንም የሃይማኖትምልክቶች የሚያከብር ሰው እርሷ ከልቦችየኾነች ጥንቃቄ ናት።” (አል-ሐጅ 22፤ 32)

..........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


በረመዳን ምን ይጠበቅብናል?

ክፍል ❶

አላህ ለኛ ካለው እዝነትና ርህራሄ የተነሳ በዚህች ዱንያ ውስጥ ኢማን እና ተቅዋ የምንሰንቅባቸው ማረፊያዎችን አዘጋጀልን። በኛ ላይ የተንጠለጠሉ የኃጢያትና የመዘንጋት እድፎችን የምናወልቅባቸው ጊዜያትን ፈጠረልን። 

ነፍሳችንን ከፍ የምናደርግባቸው፣ የመዝገባችንን ስህተቶች የምናርምባቸው፣ በአዲስ መንፈስ የምንቀዝፍባቸው፣ ወኔያችን የሚጠነክርባቸው፣ የህይወትን ዐቀበት የምንወጣባቸው፣ አደጋዎቿን የምንቋቋምባቸው፣ አላህ እኛን የፈጠረበትን አላማ እንድንወጣ የምንታገዝባቸው… አንዳንድ ውድ ጊዜያትን አደረገልን።

እነዚህን ጊዜያት በቁጥር ለመገደብ የሚሞክር ሰው ከአቅሙ በላይ ይሆንበታል።
በየቀኑ የሚመላለሱት የአምስት ወቅት ሶላቶች፣ በየሳምንቱ የሚናፈቀው ጁሙዓህ፣ በየአመቱ የሚመጣው ረመዳን፣ በእድሜ አንዴ የሚያጓጓው ሐጅ… ከእነዚህ መሀል የምንጠቅሳቸው ናቸው። እነዚህ ብቻ አይደሉም።

በአመት ውስጥ ተበታትነው የምናገኛቸው፣ የአላህ እዝነት የሚንሰራፋባቸውና ብዙ ትሩፋቶች የሚገኙባቸው ጊዜያት አሉ።
እድለኛ ማለት የመልካም ሥራ መዝገቡን ያስተካከለ፣ ከእነዚህ የእዝነት ጊዜያት ለመጠቀም ራሱን ያዘጋጀ ሰው ነው።

አትራፊ ማለት እድሉ ሳያመልጠው እጅጌውን ሰብስቦ በሥራ የተጠመደ ነው፤ ወደ አላህ ለሚያደርገው ጉዞ የሚያስፈልገውን ስንቅ ሳይሰንቅ እነዚህ ጊዜያት ያላመለጡት። አላህ እንዲህ አለ፡-

وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ

“ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ(አላህን መፍራት) ነው። የአእምሮዎችምባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ።” (አል-በቀራህ 2፤ 197)

ለሙስሊሞች ከተከወኑ እነዚህ ማረፊያዎች መሀል በየአመቱ የሚከሰተው ረመዳን አንዱ ነው። ረመዳን የቀናት ጥርቅም ነው። በረከትን፣ ምህረትንና እዝነትን ይዞ የሚመጣ ወር። ነገር ግን በአግባቡ የተቀበሉትን እና ያስተናገዱትን ብቻ አክብሮ የሚከንፍ እንግዳ ነው። አላህ በመልካም ተግባሮች መሽቀዳደሚያ ያደረገው ወር።

ረመዳን ውስጥ የሚሰሩ ትርፍ ሥራዎች (ነዋፊሎች) ሌላ ጊዜ እንደሚሠራ አንድ ግዴታ (ፈርድ) ይታሰባል። እርሱ ውስጥ የሚሠራ አንድ ግዴታ (ፈርድ) ሌላ ጊዜ ከሚሠራ ሰባ ፈርድ ጋር ይስተካከላል።

ረመዳን – “ኸይር ፈላጊ ሆይ! ፍጠን!…” የሚል መፈክር አለው። በርሱ ውስጥ ሰይጣናት ይታሰራሉ። የእሳት ደጃፎች ይዘጋሉ። አየሩ በሙሉ ምህረትን፣ እዝነትን፣ ከእሳት ነፃ መባልን… ለማግኘት ምቹ ነው። ጀነት ትጣራለች። ወደኔ ዙሩ ፈጠን ብላችሁ ኑ! እያለች ናፋቂዎቿን ትጋብዛለች። ገበያው ክፍት ነው። ውድ እቃዎችም ተዘርግተዋል። ንጉሱም ቸር ነው።

እነሆ ረመዳንን ለመጠቀም እንቸኩል። ድንገት አልፎ እንዳንደነግጥ። ለዝግጅት የሚሆነን አንድ ቁም ነገር አለ። እነዚህን ጥያቄዎች መልሰን መገኘት። ከረመዳን ምን እንጠብቃለን? የእንግዳችንን ክብርስ ምን ያህል እናውቃለን? እንግዳችንን ለማስደሰትስ ምን እናድርግ?እነዚህ ፊታችን ያሉት ገፆች እነዚህ ጥያቄዎችን ለመመለስ ይሞክራሉ።

አላህ ከፍላጎታችን በላይ ያለን የሚያሟላ ጌታ ነው። ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራም እርሱ ነው።

የምህረት ወር

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡-
رغم أنف رجل دخل عليه رمضان ثم انسلخ قبل أن يغفر له
“ረመዳን ገብቶ ከዚያም ምህረት ሳያገኝየወጣበት ሰው አፍንጫው ይታሽ (ውርደትያግኘው)!”
በረመዳን ምህረትን ያላገኘ መቼ ያገኘዋል እንበል?…

ከአኼራ ርቆ የዱንያ ባህር ውስጥ እየዋኘ ምህረት ሊያገኝ?… የብርና የወርቅ ኮቴን እየላሰ… በልጆችና በሚስት ፍላጎት እየተነዳ ምህረት ሊቸር?…

በእርግጥ እኛ ማንንም ከአላህ ምህረት ተስፋ አናስቆርጥም። ነገር ግን አላህ እንደነገረን ምህረት ሠበቦች አሉት። ጀነት ለመግባት መስፈርቶች አሉ። ኢማን በምኞት አይደለም። ልብ ውስጥ የዘለቀ እና በተግባር የተረጋገጠ ካልሆነ። የምንለው እውነት ነው! ከፈለጋችሁ ይህን አንቀፅ አስተውሉት። እንዲህ ይላል፡-

وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ * الَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي السَّرَّاءِ وَالضَّرَّاءِ وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ * وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ * أُولَٰئِكَ جَزَاؤُهُم مَّغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ

“ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋእንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህንለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ። ለእነዚያበድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታአድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)። አላህም በጎሠሪዎችን ይወዳል። 

ለእነዚያም መጥፎ ሥራንበሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህንየሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትንየሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችንየሚምር አንድም የለ። (በስሕተት) በሠሩትምላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩለኾኑት (ተደግሳለች)። እነዚያ ምንዳቸውከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎችሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውገነቶችም ናቸው። የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች!።” (አሊ ዒምራን 3፤ 133-136)
ለጀነት የተዘጋጀ ይኖር?!

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለው ጠየቁ፡-
“ለጀነት የተዘጋጀ ሰው አለ?! ጀነት ልብ ውስጥትዝ ብላ የምታውቅ አይደለችም። 

በካዕባ ጌታእምላለሁ አንፀባራቂ ብርሀን ናት!የሚንቀጠቀጥ ደስታ ያላት፣ ብርቱ ህንፃዎችያሉባት፣ ሰፋፊ ጅረቶች ያሉባት፣ ብስልፍራፍሬዎች የሞሉባት፣ ያማሩ ሚስቶችያሉባት፣ ብዙ ሙሉ ልብሶች የሚገኙባት፣ዘላለም የሚኖርባት፣ ሰላም የሠፈነባት፣ ባማሩአረንጓዴ አትክልቶች የተሸፈነች፣ በታላቅ ደስታናአስገራሚ ፀጋዎች የተሞላች ሀገር ናት።”

ጀነት መግባት- ከአላህ ከሚከጀል እዝነት በተጨማሪ- ብዙ ድካም ይጠይቃል። አላህን ለመታዘዝ የምንከፍለውን መስዋእትነት ይፈልጋል።አዎን! በዚህች ዱንያ ውስጥ የምንቆየው ጊዜ አጭር ነው። ከዚያም ረዥም አመታት ይከተላሉ። መጨረሻ የላቸውም።

ቀብር ከዚያም የምፅአት ሀገር….በዚህች አጭር የዱንያ ህይወት ውስጥ ተዘናግተው ያለፉ ሰዎች ከአላህ ጋር ሂሳብ ለማድረግ በሚቆሙ ጊዜ ልባቸውን የሚሞላው ቁጭት ምን ያህል ከባድ ይሆን!? ከጌታቸው መብት ያጓደሉ ባሮች አስፈሪው ሚዛን ላይ ሲቆሙ የሚሰማቸው ብስጭትስ ምን ያህል የከፋ ይሆን?!

.............ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


አሁን ደግሞ ፦

የረመዳን ወርን ትሩፋቶችና በዚህ ወር ውስጥ የሚሠሩ መልካም ተግባራትን ምንዳ እንመልከት።

❶. አቡ ሁረይራ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) ረመዳን በቀረበ ጊዜ እንዲህ ይሉን ነበር፡-

قد جاءكم شهر مبارك افترض عليكم صيامة تفتح فية ابوب الجنة و تُغلق فية أبواب الجحيم و تُغل فية الشياطين , فية ليلة خير من ألف شهر , من حُرم خيرها فقد حُرم

“የተባረከው ወር መጣላችሁ ይህን ወር እንድትፆሙት አላህ በእናንተ ላይ ግደታ አድርጓል፣ የጀነት በሮች በዚህ ወር ውስጥ ይከፈታሉ፣ የገሃነም በሮች ደግሞ ይዘጋሉ፣ ሰይጣኖችም ይታሰራሉ።

በዚህ ወር ውስጥ ከአንድ ሺህ ወር የምትበልጥ አንድ ሌሊት አለች የእርሷን ጥሩ ነገር የተነፈገ ሰው በእርግጥ (ጥሩ የተባለ ነገር ሁሉ) ተነፍጓል።” (አህመድ፣ ነሳኢይና በይሃቂይ ዘግበውታል)።

❷. ዐርፈጃህ እንዲህ አሉ “አንድ ቀን ዑትባህ ኢብኑ ፈርቀድ ስለ ረመዳን ሲናገር እርሱ ዘንድ ነበርኩኝ። ከነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባልደረቦች የሆነ አንድ ሰው ወደ እኛ ገባ። ዑትባህ ይህንን ሰው ባየው ጊዜ አፈረና ዝም አለ።

ከዚያም ሰሀባው ስለረመዳን እንዲህ በማለት ተናገረ፡- ‘ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አንዲህ በማለት ሲነገሩ ሰምቻለሁ፡-የእሳት በሮች ይዘጋሉ፣ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፣ ሰይጣናት ይታሰራሉ፣ መላእኩ ረመዳን እስከሚያልቅ ድረስ በየቀኑ እንዲህ በማለት ይጣራል፡- አንተ ለመልካም ነገር የምትጣደፈው ሆይ ተበሰር፣ አንተ ለመጥፎ ተግባር የምትሮጠው ሆይ ተቆጠብ’።” (አህመድና ነሳኢይ የዘገቡት ሲሆን ሰነዱም ጠንካራ ነው)

❸. አቡ ሁረይራ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-

الصلوات الخمس و الجمعة إلى الجمعة و رمضان إلى رمضان مكفرات لما بينهن إذا اجتنبت الكبائر

“አምስቱ የግዴታ ሶላቶች፣ ጅመዓ እስከ ጁመዓ፣ ረመዳን እስከ ረመዳን ከባባድ ወንጀሎችን እሰከ ተከለከልክ ድረስ በመካከላቸው ላለው ጊዜ ወንጀልን ያብሳሉ።” (ሙስሊም ዘግበውታል)
http://t.me/Dinel_Islam_Tube

❹. ከአቡ ሠዒድ አል-ኹድሪይ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ አሉ፡-

من صام رمضان و عرف حدودة و تحفظ مما كان ينبغى ان يتحفظ منة , كفر ما قبلة

“ድንበሮቹን አውቆ ረመዳንን የፆመ፣ መጠበቅ ከሚገባው ነገር የተጠበቀ ያለፈው ወንጀሉ ይታበስለታል።” (አህመድና በይሃቂይ ዘግበውታል)

❺. አቡ ሁረይራ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-

من صام رمضان إيماناً و إحتساباً غفر له ما تقدم من ذنبة

“ረመዳንን ከውስጡ አምኖና አስቦ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።” (አህመድና አስሀቡ አስ-ሱነን ዘግበውታል)

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህንን የተባረከ ወር ፣ በትክክል ፆመው በእርሱ መስፈሪያ ከሚመነዱት ያድረገን!! አሚን!!

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


ከጾም ማዕድ

በእዝነቱ ወደር የማይገኝለት አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ለሰው ልጆች የሚያዘንበው ፀጋ ተቆጥሮ የሚያልቅ አይደለም። በተለይም ደግም ለእኛ ለሙስሊሞች በየሰዓቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየአመቱ የእዝነት አዝመራውን ያለማቋረጥ ያዘንብልናል።

በአሁኑ ወቅትም አንድ ትልቅ የበረከት እንግዳ ጥላውን ዘርግቶ ወደ እኛ እንዲገሰግስ ከፈጣሪ ትእዛዙን ተቀብሎ እየተጣደፈ እነሆ ከቤታችን ገብቷል።
ይህ እንግዳ ረመዳን ይባላል።

ለመሆኑ የረመዳንና ባጠቃላይም የፆም ትሩፋቶች ምን ይሆኑ? ይህ አጭር ፅሁፍ እነዚህን ጉዳዮች ለመዳሰስ ይሞክራል።
በመጀመሪያ ፆም ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት።

ፆም በቋንቋ ትርጓሜው ከአንድ ነገር መታቀብ ነው። ለዚህም ምሳሌ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መርየምን እንዲህ በማለት እንድትናገር አዟት የነበረውን እንመልከት

إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنسِيًّا

 
“እኔ ለአልረሕማን ዝምታን (ፆም) ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም” (መርየም 19፤ 26)

በሸሪዓ ትርጓሜው ደግም ፆም ማለት ከማንኛውም ከሚያስፈጥሩ ነገሮች ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ የፈጣሪን ትእዛዝ በማሰብ መታቀብ ማለት ነው።

የፆም ትሩፋቶች አጅግ በርካታ ሲሆኑ በተወሰነ መልኩ የሚከተሉትን ሀዲሶች እንመልከት።

❶. አቡ ሁረይራ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል

كل عمل ابن آدم له إلا الصيام فإنه لى وأنا  أجزى به, والصيام جُنة فإذا كان يوم صوم أحدكم لا  يرفث  ولا  يصخب  ولا  يجهل  فإن شاتمة أحد او قاتلة أحد فليقل إنى صائم , مرتين , و الذى نفسى بيده لخلوف فم الصائم أطيب عند الله يوم القيامة من ريح المسك , و للصائم فرحتان يفرحهما : إذا أفطر فرح بفطرة , و إذا لقى ربه فرح بصومه

“የልዕልና ባለቤት የሆነው አላህ እንዲህ አለ፡- የአደም ልጅ ሥራዎቹ ሁሉ ለራሱ ናቸው፤ ፆም ሲቀር፤ እርሱ (ፆም) ለእኔ ነው፤ በእርሱም የምመነዳው እኔ ነኝ። ፆም ጋሻ ነው። አንድኛችሁ በፆመ ጊዜ ፀያፍ አይናገር፣ አይጩህ፣ ሌሎችን አያቂል።

ሌላ ሰው ቢሰድበው ወይንም ሊጋደለው ቢሞክር ሁለት ጊዜ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለሁ የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ የቂያማ ዕለት ከሚስክ ሽታ ይጣፍጣል።

ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡- ሲያፈጥር ይደሰታል፣ (በዕለተ ቂያማ) ከጌታው ጋር ሲገናኝ ደግሞ ይደሰታል።” (አህመድ፣ ሙስሊምና ነሳኢይ ዘግበውታል)

በቡኻሪና በአቡዳውድ ዘገባ ደግሞ ይሄው ሀዲስ እንዲህ ተወርቷል “ፆም ጋሻ ነው። አንድኛችሁ ፆመኛ በሆነ ጊዜ ፀያፍ አይናገር፣ ሌሎችን አያቂል።

አንድ ሰው ሊጋደለው ቢሞክር ወይንም ቢሰድበው ሁለት ጊዜ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል። የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለሁ የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ የቂያማ ዕለት ከሚስክ ሽታ ይጣፍጣል።

ለእኔ ብሎ ምግቡን፣ መጠጡን ስሜቱን ይተዋልና፤ ፆም ለእኔ ነው፣ በእርሱም የምመነዳው እኔ ነኝ፤ እያንዳንዱ መልካም ሥራ በአሥር ይባዛል።”

ከላይ ከተጠቀሰው ሀዲስ የምንረዳው አንድ ሰው አንድ መልካም ሥራ ቢሠራ ያመልካም ሥራው በአሥር ይባዛለታል።
http://t.me/Dinel_Islam_Tube

ፆም ግን በዚህ የብዜት ስሌት የታጠረ አይደለም። ስንት እንደሚመነዳው የሚያውቀው አላህ ነው፣ በብዙ እጥፍ ድርብ። ፀጋው መቸም ለማይነጥፈው ለቸሩ ፈጣሪያችን እጅግ ምስጋና ይገባውና ምንም ሳይጎድልበት ይደራርብለታል።

❷. ከአብደላህ ኢብን ዐምር አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-

الصيام و القرآن يشفعان للعبد يوم القيامة, يقول الصيام :أى رب منعته الطعام والشهوات بالنهار فشفعنى فية و يقول القرآن: منعته النوم بالليل فشفعنى فية فيشفعان

“ፆምና ቁርአን ለአንድ ባሪያ የቂያማ ዕለት አማላጅ ሆነው ይቀርባሉ። ፆም ይላል፡- ጌታየ ሆይ በቀን ከምግብና ከስሜት ከልክየዋለሁና ምልጃየን በርሱ ተቀበለኝ፣ ቁርአንም ይላል፡- በሌሊት ከእንቅልፍ ከልክየዋለሁና ምልጃየን በርሱ ተቀበለኝ፤ አላህም ምልጃቸውን ይቀበላቸዋል።” (ትክክለኛ በሆነ ሰነድ አህመድ ዘግበውታል)።

❸. አቡ አማማህ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተናገሩት:-

أتيت رسول الله صلى الله عليه و سلم فقلت : مُرنى بعمل يدخلنى الجنة , فقال: عليك بالصوم فإنه لا عدل له

“ወደነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) መጣሁና ጀነት የሚያስገባኝን ሥራ እዘዙኝ አልኳቸው። ነብዩም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በፆም አደራ እልሃለሁ እርሱን የሚስተካከል የለም አሉኝ።

ለሁለተኛ ጊዜም መጥቸ እንዲሁ ጠየቅኳቸው እርሳቸውም በፆም አደራ እልሃለሁ አሉኝ።” (አህመድ፣ ነሳኢይና ሃኪም ዘግበውታል፤ ሀዲሱንም ትክክለኛ ነው ብለዋል)።

❹. ከአቡ ሠዒድ አል-ኹድሪይ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ አሉ፡-

لا يصوم عبد يوماً فى سبيل الله إلا باعد الله بذلك اليوم النار عن وجهه سبعين خريفاً

“አንድ የአላህ ባሪያ በአላህ መንገድ እየታገለ (ጅሃድ) ባለበት አንድ ቀንን አይፆምም አላህ ከዚህ ሰው ፊት እሳትን ለሰባ አመት ያክል የሚያስኬድ እርቀት ቢያርቅለት እንጅ።” (ከአቡ ዳውድ በስተቀር ‘ጀመዓው’ የሀዲስ ዘጋቢዎች ዘግበውታል)።

❺. ከሠህል ኢብኑ ሰዓድ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተወራው ነብዩ (ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይውረድ) እንዲህ ብለዋል፡-

إن للجنه باباً يقال له الريان , يقال يوم القيامة : أين الصائمون ؟ فإذا دخل آخرهم أُغلق ذلك الباب

“ለጀነት ረያን የሚባል በር አላት፡ የቂያማ ዕለትም ፆመኞች የት አሉ? ይባላል፡ ከእነርሱም የመጨረሻው ሰው ሲገባ ይሄ በር ይዘጋል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

እንግድህ ከላይ በተጠቀሱት ሀዲሶች አጠቃላይ የፆምን ትሩፋቶች አይተናል።

.............ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


100 ምክሮች ረመዳንን ለመጠቀም

✿ ቤተሰባዊ ምክሮች

➐➏. ቤተሰቦችህ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የረመዳን ወር ሲገባ አበስራቸው።

➐➐. ረመዳንን ምክንያት በማድረግ በቤትህ ውስጥ ለውጥ አድርግ፤ ይህም የሚሆነው ቤቱን በማጽዳት፣ እቃዎችን እንደገና በማደራጀት፣ ቁርኣን የተጻፈባቸውን ፍሬሞችና ሌሎች ጠቃሚ ምክሮች ለማስታወስና ረመዳንን ለማድመቅ በግድጊዳ ላይ ስቀል፣ ህጻናት በረመዳን መምጣት እንዲደሰቱና ደረጃውንም እንዲረዱት በክፍላቸው ውስጥ አንዳንድ ማስዋቢያዎችን ስቀልላቸው።

➐➑. የረመዳንን ወር ጊዜያት በትክክል ለመጠቀም እቅድ አስቀምጥ፤ በየቀኑ የምትቀራውን የቁርኣን መጠንና ተራዊህ ሶላት ለመስገድ ተስማሚ የሚሆንልህን መስጅድ ከአሁኑ ውስን።

➐➒. በረመዳን ወር መስገጃ የሚሆን ቦታ በቤት ውስጥ ለይተህ አስቀምጥ።

➑0. የቤተሰቦችህን ኢባዳና ሥነ-መግባር በመከታተል የተሳሳተ ሁኔታ ካለ አስተካካል።

➑➊. ለረመዳን የሚያገለግል እለታዊ ፕሮግራም በቤትህ ውስጥ በመስቀል ሁሉም የቤተሰብ አባላት እንዲሳተፉበትና እንዲጠቀሙበት አድርግ፤ ፕሮግራሙ እንዳስፈላጊነቱ መቀያያር የሚችል መሆን አለበት።

➑➋. ፍጡርና ሱሑር ከቤተሰብህ ጋር ተመግብ፤ ምክንያቱም አብራችሁ ስትመገቡ ቤተሰባዊ ትስስሩን ያጠብቀዋልና ነው።

➑➌. ከልጆችህ ጋር ሆነህ ለሱብሂ ሶላት ወደ መስጊድ ሂድ፤ የመጀመሪያ ሶፍ ላይም ስገዱ፤ እናት ደሞ ከሴት ልጆች ጋር በቤት ውስጥ ትሰገድ፤ ሁኔታዎች ከተመቻቹ እናት ከባሏና ከልጆቿ ጋር መስጅድ ትሂድ።
http://t.me/Dinel_Islam_Tube

➑➍. ከሳምንት አንድ ቀን ከልጆችህና ሚስትህ ጋር ከፈጅር ሶላት በኋላ ተቀምጣችሁ አንድ ጁዝ ቁርኣን ቅሩ፤ እነዲዚሁ

➑➎. ዋጀብና ትርፍ ኸይር ሥራዎችን የምትከታተሉበት ሠንጠረዥ ከቤተሰቡ ጋር ተስማምተህ አስቀምጥ፤ ሌሎች እንዲነቃቁ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩትን አበረታታቸው።

➑➏. በኑሮህ መካከለኛነትን በመከተል ከገቢህ ጋር የሚመጥን የረመዳን በጀት አስቀምጥ፤ ረመዳን አስፈላጊውን የሚሟላበት ወር እንጂ የብክነት ወር አይደለም።

➑➐. ከባለቤትህ/ሽ ጋር ሁናችሁ ለኸይር ጉዳይና ትርፍ ሰደቃ የሚውል ገንዘብ ወስናችሁ አስቀምጡ።

➑➑. የሚዲያን ብልሹ መልክቶች ተጠንቀቅ፤ በተለይም የሴቶችን ገላ እያጋለጡ የሚያሳዩና ወደ መጥፎ ነገርና ወንድና ሴትን ለማቀላቀል ጥሪ የሚየደርጉ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ራቅ።

➑➒. ልጆችህ የሙስሊሞችን ስብስብ እንዲያዩ በአንድ ታላቅ መስጊድ ለመስገድ ጥረት አድርግ።

➒0. ልጆችህ ቀስ በቀስ ፆም እንዲለማመዱ አድርግ፤ ሱሑር ለመብላትና ለፈጀር ሶላት እንዲነሱ አበረታታቸው።

➒➊. ቤተሰቦችህ የጠዋትና የማታ አዝካሮችን (ውዳሴዎችን)፣ የፍጡር ዱዓና የተሀጁድ ዱዓ እንዲሐፍዙ አድርግ፤ ውድድር እያደረግክ ዱዓዎቹን በቃል ለሸመደዱና ጠብቀው ለሚጠቀሙ ሽልማት በመስጠት ልታበረታታቸው ትችላለህ።

➒➋. በቤትህ ውስጥ ያሉትን ጥሩ ጎኖችና መጥፎ ጎኖች ለይተህ ጥሩውን ለማሳደግ መጥፎውን ደግሞ ለማስወገድ ሥራ።

➒➌. እናት ልጆቿን ምግብ በማዘጋጀትና በማቅረብ እንዲሳተፉ በማድረግ በመካከላቸው ተባብሮ የመስራት ዋጋን እንዲረዱ ማድረግ አለባት።

➒➍. የኸይር ከረጢት (ሻንጣ) በያንዳንዱ ቤተሰብ አለያም በጎረቤቶች ደረጃ አዘጋጅታችሁ ድሃዎችና ችግረኞች ለረመዳን እንዲጠቀሙበት በማድረግ በሙስሊሞች መካከል ሊኖር የሚገባውን ማህበራዊ ትብብር ህያው አድርጉ።

➒➎. ከአጉል ወገንተኝነት፣ ከስሜታዊነትና ስሞታ ከማብዛት ተቆጠብ፤ በማንኛውም ሁኔታ ልበ ሰፊና የተረጋጋህ ሁን፤ አላህን ሁል ጊዜ አውሳ።

➒➏. ዚያራ በማድረግና ስጦታ በመለዋወጥ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ተሳተፍ፤ ከቤተሰቦችህና ከጎረቢቶች ጋር ኢባዳ የምትሠሩበትና በመካከላችሁ ያሉ አለመግባባቶችን የምታስተካክሉበት መገናኛ ጊዜያት አድርጉ።

➒➐. በየሳምንቱ ቤተሰብህን የምትይዝበት ሳምንታዊ መልክት ምረጥ፤ ለምሳሌ “የማያዝን አይታዘንለትም” የሚለውን ሐዲስ የሳምንቱ መልክት በማድረግ የእዝነት ባህሪን አትኩሮት መስጠትና መላበስ ይቻላል። በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ “ጌታችሁን ማህርታ ጠይቁት፤ እርሱ ማሀሪ ነውና።” የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ በመጠቀም የኢስቲግፋርን አስፈላጊነት ታስተምራለህ። በሦስተኛው “ጌታዬ ወደ አንተ ፈጠንኩ” የወሩ ግማሽ ተገባደደ፤ ስለዚህ አላህ (ሱ.ወ) እንዲቀበለን የበለጥ በኢባዳ መጠናከር አለብን። ከዚያም በአራተኛው ሳምንት ደግሞ“ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና” (ዛሪያት 51፤ 50) ወይም “ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ።” (አል-ኢምራን 3፤ 132) የሚሸሸው ወደ አላህና ወደ ጀነቱ መሆን አለበት። ይህን የመሳሰሉ መልክቶች…

➒➑. ሚስትህን የተለያዩ የምግብ አይነቶች በማዘጋጀት እንድትጠመድ አታድርግ፤ በማዕድ ቤት ውስጥ ልትጠቀምበት የሚቻል ፕሮግራም እንዲኖራት አድርግ፤ ለምሳሌ የቁርኣንና የዲን ካሴቶችን ማዳጥ…፤ ፆመኞችን ለማስፈጠር የምታደርገው ትግል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝላት መሆኑንም አስታውሳት።

➒➒. በረመዳን ወር በሙሉ ለልጆችህ ሊጠቅማቸው የሚችል ማራኪ መጽሐፍ በመምረጥ፣ የንባብ ውድድር አድርግ፤ ለምሳሌ ሐያቱ ሶሐባ (አብዱረህማን ረእፈት የጻፉት)… ለዚሁም ሸልማቸው፤

➊00.  በቤተሰብ አባላት መካከል ያለውን ልዩነት (የግል ባህሪ) አትዘንጋ፤ ለአንድኛው የሚስማማው ነገር ለሌላው ላይሆን ይችላል፤ ከዚህም አኳያ አንዱን ልጅህን በሒፍዝ ላይ ልታበረታታው ትችላለህ፤ ሌላውን ደግሞ በቂራኣ ላይ…

አላህ ከኛም ከናንተም ሶላታችንና ፆማችንን ሌላውንም ሥራችንን ይቀበለን።

አሚን!!

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube


100 ምክሮች ረመዳንን ለመጠቀም

ክፍል ❸

✿ መሰረታዊ ምክሮች

➎➊. አላህ (ሱ.ወ) ለሱ ሲባል ብቻ የተሠራን እንጂ አይቀበልም እና ኒያህን ለአላህ አጥራ፤ በፆምህም ወደ አላህ ብቻ ዙር።

➎➋. በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ስራ ለመስራት ሞክር፤ ለምሳሌ እየሄድክ ዚክር ማለትና በትራንስፖርት ውስጥ ሆነህ ቁርኣን መቅራት…።

➎➌. ሱሑር በመብላት ታገዝ፤ “ሱሑር ብሉ፤ ሱሑር መብላት በረካ አለው።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➎➍. ፊጥርን አቻኩል፤ “ሰዎች በኸይር ላይ ከመሆን አይወገዱም፤ ፊጥርን እስካፋጠኑ ድረስና ሱሑርን እስካዘገዩ ድረስ።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➎➎. ማግኘት ከቻልክ በቴምር አፍጥር፡- “ቴምርን ያገኘ በሱ ያፍጥር፤ ቴምርን ያላገኘ በውሃ ያፍጥር፤ ውሃ ንጹህ ነውና።”(አህመድ ዘግበውታል)።

➎➏. ቁርኣንን እያስተነተንክና እየተረዳህ በብዛት አንብብው፤ በየቀኑ የምትቀራው የተወሰነ የቁርኣን ክፍል ሊኖርህ ይገባል፤ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ጋር በየሌሊቱ እየተገናኘ ቁርኣንን ያጠኑ ነበር።

➎➐. ምላስህን ከውሸት፣ ከሐሜት፣ ነገርን ከማዛመትና ከመጥፎ ንግግር ጠብቅ። ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “ውሸት ንግግርንና በሱም መስራትን ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን መተው ለአላህ (ሱ.ወ) ጉዳዩ አይደለም።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)።

➎➑. አይንህን ከሐራም ከልክል፡- “(የሐራም) እይታ ሰይጣን የሚወረውረው ጦር ነው፤ እኔን ፈርቶ የተወን ሰው ጥፍጥናውን በልቡ የሚያገኘውን ኢማን እተካዋለሁ።” (ጦብራኒ ዘግበውታል)።

➎➒. በሰዎች መካከል የሚካሄዱና አንተን የማይመለከቱህን ወሬዎችና ውይይቶች ከማዳመጥና ከመከታተል ጆሮህን ቆጥብ።

➏0. ራስህንና ስሜትህን እንዴት መቆጣጠር እንደምትችል ተማር፡- “ፆም ጋሻ ነው፤ አንድኛችሁ ፆመኛ በሆነ ጊዜ መጥፎ ቃል አይናገር፤ አንድ ሰው ቢሰድበው ወይም ቢጋደለው እንኳ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል።” (ሙስሊም ዘግበውታል)።

➏➊. ሰደቃ አብዛ፤ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ኸይርን በመለገስ ከሰዎች ሁሉ ቀዳሚ ነበሩ፤ በጣም የሚለገሱት ደግሞ በረመዳን ነበር።
http://t.me/Dinel_Islam_Tube

➏➋. በፍጡር ጊዜ ምግብ አታብዛ፤ ምግብ ማብዛት መዳከም ያመጣል፤ ሁልጊዜ ጠግቦ መመገብ ደካማነትንና ቀልብ መድረቅን ያስከትላል፤“የሰው ልጅ ወገቡን ቀጥ የሚያደርጉለት ትንሽ ጉርሻዎችን መመገብ በቂው ነው፤ ከዚህ በላይ አብዝቶ መብላት ግድ ከሆነም አንድ ሦስተኛውን ለምግብ፣ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጥ፣ አንድ ሦስተኛውን ደግሞ ለአየር ያድርግ።” (ቲርሚዚይ ዘግበውታል)።

➏➌. ከፍጡር በኋላ ቀልብህን በአላህ ፍራቻና ተስፋ መካከል አድርግ፤ ምክንያቱም ፆምህ ተቀባይነት አግኝቶ ከአትራፊዎች ትሆን ወይስ ፆምህ ተመልሶብህ ከከሳሪዎች መሆንህን አታውቅም።

➏➍. ረመዳንን ግዴታነቱን አምነህና ምንዳውን አስበህ ፁም፤ “ረመዳንን አምኖና አስቦ የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➏➎. ረመዳንን አምነህና ምንዳውን አስበህ ቁም (የሌሊት ስግደት አከናውን)፡- “ረመዳንን አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➏➏. ለይለተል ቀድርን አምነህና ምንዳውን አስበህ ቁም፡- “ለይለተል ቀድርን አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።”(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➏➐. በመጨረሻዎቹ አስር የረመዳን ቀናት በኢባዳ ታገል፡- “ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) አስሮቹ ቀናት ሲገቡ ሌሊቱን ህያው ያደርጉ ነበር፤ ቤተሰቦቻቸውንም ያነቁ ነበር፤ እርሳቸውም ታጥቀው ለኢባዳ ይነሱ ነበር።” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።

➏➑. የፆምን ፍሬና ግድ የተደረገበት ውስጠ ሚስጠር አብሮህ እንዲቀጥል በነገርህ ሁሉ የአላህን ትዕዛዝ ጠብቅ፤ በድብቅም በግልጽም እርሱን ተጠባበቅ (ትዕዛዙን ከመጣስ ተጠንቀቅ) “እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና።” (አል-በቀራ 2፤ 183)

➏➒. በድካም፣ በረሀብና ጥም በማመካኘት የረመዳንን ቀን እየተኛህ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነው ጀማዓ ሶላት አይለፍህ።

➐0. በንግድና ገንዘብ ነክ ጉዳዮችም ይሁን በምክክርንና በውይይት ጊዜ ከማታለል በእጅጉ ራቅ፡- “ያታለለን ከኛ አይደለም።” (ሙስሊም ዘግበውታል)።

➐➊. አደራ! ጥሩ ሥነ-መግባርን ተላበስ፤ ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሰዎችን በብዛት ጀነት የሚያስገበው ነገር ምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ “አላህን መፍራትና ጥሩ ሥነ-ምግባር ነው” ሲሉ መልሰዋል። (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

➐➋. የታጋሽነት፣ ይቅር ባይነትና ቁጣን መዋጥ ችሎታ ይኑርህ፤ የበለጠ ለማሻሻልም ራስህን ታገል “ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)። አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል።” (አሊ ዒምራን 3፤ 134)

➐➌. ያለ አግባብ የያዝከውን ነገሮች ለባለቤቶቻቸው በመመለስ ከሰዎች ሐቅ ነፃ ሁን፡- “የወንድሙ ሐቅ ያለበት ሰው ዛሬውኑ ነጻ ይሁን፤ ነገሩ እዚያ (አኺራ) ወርቅም ይሁን ብር የለም፤ አንድ ሰው የወንድሙ ሐቅ ካለበት ከኸየር ሥራው እየተወሰደ ለወንድሙ ይከፈላል፤ ኸይር ሥራ ከሌለው ደግሞ ከወንድሙ ወንጀል እየተወሰደ እርሱ ላይ ይጣላል።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)።

➐➍. አገልጋዮችንና ሠረተኞችን በረመዳን ብዙ በማሰራት አታድክማቸው፤ “ከባሪያው ያቃለለ ሰው አላህ (ሱ.ወ) ወንጀሉን ይምረዋል፤ ከሳትም ነፃ ያወጣዋል።” (ኢብኑ ኹዘይማህ ዘግበውታል)።

➐➎. ወደኸይር ነገር ጥሪ ያደረገልህን ሰው ግብዣውን ተቀበል፤ “በአላህ የተጠበቀን ጠብቁት፤ በአላህ ስም የለመነን ሥጡት፤ ጥሪ ያደረገላችሁን ተቀበሉት፤ ለናንተ ውለታ የዋለላችሁን ሰው ውለታውን መልሱለት።” (አህመድ ዘግበውታል)።

...........ይቀጥላል

🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂


🍀 ዲነል ኢስላም Tube

🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"

http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube

Показано 20 последних публикаций.

121

подписчиков
Статистика канала