100 ምክሮች ረመዳንን ለመጠቀም
✿ ቤተሰባዊ ምክሮች
➐➏. ቤተሰቦችህ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የረመዳን ወር ሲገባ አበስራቸው።
➐➐. ረመዳንን ምክንያት በማድረግ በቤትህ ውስጥ ለውጥ አድርግ፤ ይህም የሚሆነው ቤቱን በማጽዳት፣ እቃዎችን እንደገና በማደራጀት፣ ቁርኣን የተጻፈባቸውን ፍሬሞችና ሌሎች ጠቃሚ ምክሮች ለማስታወስና ረመዳንን ለማድመቅ በግድጊዳ ላይ ስቀል፣ ህጻናት በረመዳን መምጣት እንዲደሰቱና ደረጃውንም እንዲረዱት በክፍላቸው ውስጥ አንዳንድ ማስዋቢያዎችን ስቀልላቸው።
➐➑. የረመዳንን ወር ጊዜያት በትክክል ለመጠቀም እቅድ አስቀምጥ፤ በየቀኑ የምትቀራውን የቁርኣን መጠንና ተራዊህ ሶላት ለመስገድ ተስማሚ የሚሆንልህን መስጅድ ከአሁኑ ውስን።
➐➒. በረመዳን ወር መስገጃ የሚሆን ቦታ በቤት ውስጥ ለይተህ አስቀምጥ።
➑0. የቤተሰቦችህን ኢባዳና ሥነ-መግባር በመከታተል የተሳሳተ ሁኔታ ካለ አስተካካል።
➑➊. ለረመዳን የሚያገለግል እለታዊ ፕሮግራም በቤትህ ውስጥ በመስቀል ሁሉም የቤተሰብ አባላት እንዲሳተፉበትና እንዲጠቀሙበት አድርግ፤ ፕሮግራሙ እንዳስፈላጊነቱ መቀያያር የሚችል መሆን አለበት።
➑➋. ፍጡርና ሱሑር ከቤተሰብህ ጋር ተመግብ፤ ምክንያቱም አብራችሁ ስትመገቡ ቤተሰባዊ ትስስሩን ያጠብቀዋልና ነው።
➑➌. ከልጆችህ ጋር ሆነህ ለሱብሂ ሶላት ወደ መስጊድ ሂድ፤ የመጀመሪያ ሶፍ ላይም ስገዱ፤ እናት ደሞ ከሴት ልጆች ጋር በቤት ውስጥ ትሰገድ፤ ሁኔታዎች ከተመቻቹ እናት ከባሏና ከልጆቿ ጋር መስጅድ ትሂድ።
http://t.me/Dinel_Islam_Tube
➑➍. ከሳምንት አንድ ቀን ከልጆችህና ሚስትህ ጋር ከፈጅር ሶላት በኋላ ተቀምጣችሁ አንድ ጁዝ ቁርኣን ቅሩ፤ እነዲዚሁ
➑➎. ዋጀብና ትርፍ ኸይር ሥራዎችን የምትከታተሉበት ሠንጠረዥ ከቤተሰቡ ጋር ተስማምተህ አስቀምጥ፤ ሌሎች እንዲነቃቁ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩትን አበረታታቸው።
➑➏. በኑሮህ መካከለኛነትን በመከተል ከገቢህ ጋር የሚመጥን የረመዳን በጀት አስቀምጥ፤ ረመዳን አስፈላጊውን የሚሟላበት ወር እንጂ የብክነት ወር አይደለም።
➑➐. ከባለቤትህ/ሽ ጋር ሁናችሁ ለኸይር ጉዳይና ትርፍ ሰደቃ የሚውል ገንዘብ ወስናችሁ አስቀምጡ።
➑➑. የሚዲያን ብልሹ መልክቶች ተጠንቀቅ፤ በተለይም የሴቶችን ገላ እያጋለጡ የሚያሳዩና ወደ መጥፎ ነገርና ወንድና ሴትን ለማቀላቀል ጥሪ የሚየደርጉ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ራቅ።
➑➒. ልጆችህ የሙስሊሞችን ስብስብ እንዲያዩ በአንድ ታላቅ መስጊድ ለመስገድ ጥረት አድርግ።
➒0. ልጆችህ ቀስ በቀስ ፆም እንዲለማመዱ አድርግ፤ ሱሑር ለመብላትና ለፈጀር ሶላት እንዲነሱ አበረታታቸው።
➒➊. ቤተሰቦችህ የጠዋትና የማታ አዝካሮችን (ውዳሴዎችን)፣ የፍጡር ዱዓና የተሀጁድ ዱዓ እንዲሐፍዙ አድርግ፤ ውድድር እያደረግክ ዱዓዎቹን በቃል ለሸመደዱና ጠብቀው ለሚጠቀሙ ሽልማት በመስጠት ልታበረታታቸው ትችላለህ።
➒➋. በቤትህ ውስጥ ያሉትን ጥሩ ጎኖችና መጥፎ ጎኖች ለይተህ ጥሩውን ለማሳደግ መጥፎውን ደግሞ ለማስወገድ ሥራ።
➒➌. እናት ልጆቿን ምግብ በማዘጋጀትና በማቅረብ እንዲሳተፉ በማድረግ በመካከላቸው ተባብሮ የመስራት ዋጋን እንዲረዱ ማድረግ አለባት።
➒➍. የኸይር ከረጢት (ሻንጣ) በያንዳንዱ ቤተሰብ አለያም በጎረቤቶች ደረጃ አዘጋጅታችሁ ድሃዎችና ችግረኞች ለረመዳን እንዲጠቀሙበት በማድረግ በሙስሊሞች መካከል ሊኖር የሚገባውን ማህበራዊ ትብብር ህያው አድርጉ።
➒➎. ከአጉል ወገንተኝነት፣ ከስሜታዊነትና ስሞታ ከማብዛት ተቆጠብ፤ በማንኛውም ሁኔታ ልበ ሰፊና የተረጋጋህ ሁን፤ አላህን ሁል ጊዜ አውሳ።
➒➏. ዚያራ በማድረግና ስጦታ በመለዋወጥ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ተሳተፍ፤ ከቤተሰቦችህና ከጎረቢቶች ጋር ኢባዳ የምትሠሩበትና በመካከላችሁ ያሉ አለመግባባቶችን የምታስተካክሉበት መገናኛ ጊዜያት አድርጉ።
➒➐. በየሳምንቱ ቤተሰብህን የምትይዝበት ሳምንታዊ መልክት ምረጥ፤ ለምሳሌ “የማያዝን አይታዘንለትም” የሚለውን ሐዲስ የሳምንቱ መልክት በማድረግ የእዝነት ባህሪን አትኩሮት መስጠትና መላበስ ይቻላል። በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ “ጌታችሁን ማህርታ ጠይቁት፤ እርሱ ማሀሪ ነውና።” የሚለውን የቁርኣን አንቀጽ በመጠቀም የኢስቲግፋርን አስፈላጊነት ታስተምራለህ። በሦስተኛው “ጌታዬ ወደ አንተ ፈጠንኩ” የወሩ ግማሽ ተገባደደ፤ ስለዚህ አላህ (ሱ.ወ) እንዲቀበለን የበለጥ በኢባዳ መጠናከር አለብን። ከዚያም በአራተኛው ሳምንት ደግሞ“ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና” (ዛሪያት 51፤ 50) ወይም “ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ።” (አል-ኢምራን 3፤ 132) የሚሸሸው ወደ አላህና ወደ ጀነቱ መሆን አለበት። ይህን የመሳሰሉ መልክቶች…
➒➑. ሚስትህን የተለያዩ የምግብ አይነቶች በማዘጋጀት እንድትጠመድ አታድርግ፤ በማዕድ ቤት ውስጥ ልትጠቀምበት የሚቻል ፕሮግራም እንዲኖራት አድርግ፤ ለምሳሌ የቁርኣንና የዲን ካሴቶችን ማዳጥ…፤ ፆመኞችን ለማስፈጠር የምታደርገው ትግል ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝላት መሆኑንም አስታውሳት።
➒➒. በረመዳን ወር በሙሉ ለልጆችህ ሊጠቅማቸው የሚችል ማራኪ መጽሐፍ በመምረጥ፣ የንባብ ውድድር አድርግ፤ ለምሳሌ ሐያቱ ሶሐባ (አብዱረህማን ረእፈት የጻፉት)… ለዚሁም ሸልማቸው፤
➊00. በቤተሰብ አባላት መካከል ያለውን ልዩነት (የግል ባህሪ) አትዘንጋ፤ ለአንድኛው የሚስማማው ነገር ለሌላው ላይሆን ይችላል፤ ከዚህም አኳያ አንዱን ልጅህን በሒፍዝ ላይ ልታበረታታው ትችላለህ፤ ሌላውን ደግሞ በቂራኣ ላይ…
አላህ ከኛም ከናንተም ሶላታችንና ፆማችንን ሌላውንም ሥራችንን ይቀበለን።
አሚን!!
🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂 ሼር 🔂
🍀 ዲነል ኢስላም Tube
🔑"ለመልካም ነገር ቁልፍ ሁን!!"
http://t.me/Dinel_Islam_Tube http://t.me/Dinel_Islam_Tube