ህወሓት ጋዜጠኛ አታኽልቲ እምባዮን ረሽናለች
ጁንታው በከፈተው ጦርነት ብዙ የትግራይ ልጆች መሞታቸው ሰምተናል፣ የትግራይ እናት እስካሁን ልጅዋ የት እንዳለ አታውቅም፣ ለጢቂቶች ተብሎ በሚደረገው ውግያ ከተራ ትግራዋይ እስከ ሙሁር ትግራዋይ ድረስ ከንቱ መስዋእትነት እየከፈለ ነው። ጀነራል ሓየሎምን ገድሎ የትግራይን ህዝብ ያስለቀሰ ህወሓት፣ ዘንድሮም ራሱ ገድሎ የትግራይን ህዝብ እያስለቀሰ ይገኛል፣ ማሓሪ የውሃንስ መች እንደሚገድሉት ባናቅም፣ እድሉ ግን ከነ አታኽልቲ አምባየ ውጭ አይሆንም። ጋዜጠኛ አታኽልቲ በጦርነት ሞተ ካሉን እስካሁን ድረስ ለምን ዝም አሉ? መከላከያ የለቀቀ ጊዜ መንገር ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን ራሳቸው ረሽነው በጦርነት እንደ ሞተ አድርገው ለህዝብ መርዶ ነግረውታል.
ጁንታው ራሱ ገድሎ የአታኽልቲ አምባየ መርዶ በድምፂ ወያኔ ቲቪ ነግሮ ሁለተኛ ቀብር በተወለደባት ከተማ እንዲደረግ አድርገዋል። ድምፂ ወያኔን ጨምሮ ሁሉም የትህነግ ሚዲያዎች የማች አታኽልቲ አምባየ ታሪክ በሚመቻቸው ፅሁፍ እና ውሸት አቅርበዋል። አታኽልቲ አምባየ ከህወሓት አመራሮች ጋር ከፍተኛ ቂም የነበረው ሰው ነው፣ አሁን በህወሓት ተረሽኖ ከሞተ ቦሃላም ቢሆን እውነተኛው ታሪኩ ለትግራይ ትውልድ አላስተላለፉም።
ሓቀኛው ታሪኩ ግን ይህ ይመስላል፣ አታኽልቲ አምባየ ህወሓት ለሁለት ሲከፈል፣ የነ አቶ ገብሩ አስራት ደጋፊ ነበር፣ ከክፍፍሉ ቦሃላ ነብሰ ገዳዩ መለስ ዜናዊ እንዳይገድለው ወደ ውጭ አምልጠዋል፣ አሁን ጁንታው ይህ የአታኽልቲ አምባየ ታሪክ ሳይፅፈው አልፈዋል። ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ በሚል የ አቶ ገብሩ አስራት መፅሓፍ ገፅ 402 እንዲህ ይላል።
“በዚህ በተጧጧፈ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ አንድ አስገራሚ ድርጊትም ተፈፅሞ ነበር። እነ መለስ በተሃድሶ ወቅት አፈንጋጮችን እንዲያጋልጡ ከተማመኑባቸው የህትመት ተቋማት አንድ ወይን የተባለ የህወሓት ጋዜጣ ነበር። የዚህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው አታኽልቲ አምባየ አፈንጋጮችን የሚያጋልጥ ፅሁፍ እንዲያዘጋጅ፣ ከነ መለስ መመርያ ተሰጥቶት ለፅሁፉ እንዲረዳው ለአንድ ወር ያህል ያደረግነውን ውይይት የያዘ ሰነድ ተልኮለት ነበር። አታኽልቲ ሰነዱ ካነበበ ቦሃላ ሓቁን ዘክዝኮ አውጥቶ ጋዜጣው ታትሞ ከመውጣቱ በፊት፣ ብርሃነ ረዳኢ /ወዲ ረዳ ኢ/ የተባለ በወቅቱ የመለስ ደጋፊ የነበረው የህትመት ሰራተኛ የጋዜጣውን ይዘት አይቶ ለመለስ ነገረው። ይህ ተከትሎም የታተመው ጋዜጣ እንዳይሰራጭ ተደርጎ በብዙ ሺ የሚቆጠር የወይን ጋዜጣ ህትሞች ደብዛቸው ጠፋ ይላል”።
ጋዜጠኛ አታኽልቲ አምባየ ከዛን ቀን ጀምሮ መለስ እንዳያስገድለው ወደ ውጭ ወጣ፣ መለስ እስኪሞት ድረስ አገሩ ሳይመለስ በስደት ቆይተዋል፣ አታኽልቲ አምባየ ወደ አገርቤት የገባው ከለውጥ ቦሃላ ነበር። የጁንታው ሚዲያዎች ይህ ትክክለኛው ታሪኩን እንዳይፃፍ አድርገዋል፣ ልብ በሉ፣ አታኽልቲ አምባየ ቤተሰቦች;አታኽልቲ አምባየ ህወሓት ለሁለት ሲከፈል መለስ እንዳይገድለው መጥፋቱ ያውቃሉ፣ ዞሮ ዞሮ አሁንም አልቀረለትም ብጁንታው ተገድለዋል፣ ተረኛው ማን ይሆን? አታኽልቲ ብቻ ከዚህ ሁሉ አመራር እንዴት በጦርነት ሊሞት ቻለ፣ ለምንስ እንደ ሌላው ታጋይ ተሰውተዋል ተብሎ ዝም አልተባለም?