ህገ ሐተታ____Higehateta👨‍⚖️👩‍⚖️


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


The main objective is provide adequate
#Legal_mødules
#Pøwer_points
#Cødes
#Job_alerts
#Prøclamatiøns
#Jøurnals
#legal_cømmentaries
#Proposal_&_Research_idea
#Cassation_decision
#Exit_exams
#Legal_CØCs
#Legal_mid_&_final_questions
#pøøls...Etc
0986009967

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ሁሉም ሊያውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ የሕግ ምክሮች

✅ ቅጂውን ሳታገኙ ወይም ሙሉውን ሳታነቡ ምንም ነገር ላይ አትፈርሙ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ለራሳቸው ቀሪ ቅጂ ሳይኖራቸው ወይም የተፃፈውን ሳይረዱ የተለያዩ ስምምነቶችን ይፈርማሉ። በዚህም የተነሳ ወዳልተገባ ክርክርና ጥል ውስጥ ይገባሉ።  ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የፈረሙበትን የስምምነት ቅጂ በወረቀት ኮፒ መያዝ ይመረጣል።  ይህ የማይመች ከሆነ ደግሞ የፈረሙትን እያንዳንዱን ሰነድ በፍጥነት ፎቶ አንስቶ መያዝ ይገባል።

✅ ቤተሰብዎንና ንግድዎን ከሕግ ስጋት ይጠብቁ!

የንግድ ስራ ሲሰሩ ድንገት የገንዘብ ዕዳ  ቢከሰት እራስዎን እና ቤተሰብዎን ከዚህ ተጠያቂነት ማዳን የሚችሉት ኃ/የ/የግ/ማ ወይም አ/ማ ኩባንያ መስርተው ሲሰሩ መሆኑን ተረድተው ሀብትዎን የንግድ ድርጅት በማቋቋም ያንቀሳቅሱ!

✅ የሕግ ባለሙያ እስኪያማክሩ ድረስ_ሃላፊነትን ወይም ተጠያቂነትን አምነው አይቀበሉ

በጭንቀት ወይም በፍርሃት ስሜት ዉስጥ ሆነን የምንናገራቸው ነገሮች እኛኑ መልሰዉ ሊጎዱን ይችላሉ  ስለሆነም በፍርድ ቤት በፖሊስ ጣቢያ ወይም በሌላ መሰል ስልጣን ባላቸው አካላት ፊት የምንሰጣቸውን ቃላት ማስተዋል ያስፈልጋል። ከተቻለ የሕግ ባለሙያ ወይም ጠበቃ እስኪያማክሩ ድረስ ዝምታ ጥሩ መፍትሄ ነው።

✅ የሕግ ጉዳዮችን በተመለከተ የሕግ ባለሙያ ያማክሩ

ከሕግ ባለሙያ ጋር መማከር በጣም አስፈላጊ ነው።  ብዙ ጠበቆች በነፃ ወይም በክፍያ ወሳኝና አስፈላጊ ምክር ይሰጣሉ። የመንግስት አቃቤ ሕግም አቅም ለሌላቸው ወገኖች የሕግ ድጋፍ ያደርጋል። ስለሆነም የሰለጠነ ባለሙያ ጉዳይዎን እንዲመለከተው በማድረግ የሕግ መፍትሄ ማግኘት ይችላሉ።  ለምሳሌ፦ ውል ከመፈረምዎ በፊት ውሉ ልዩ የሕግ ቋንቋ የሚያካትት ከሆነ  እነዚያ ድንጋጌዎች ብዙ ጊዜ ከባድ እና ያልተጠበቁ ውጤቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ውሉን ከመፈረምዎ በፊት የሕግ ባለሙያ ቢያማክሩ ይመረጣል። 

✅ ማናቸውንም ስምምነቶች በጽሁፍ_ያድርጉ! ሰነዱንም ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ያስቀምጡ!

ሰዎች ያለማቋረጥ ስምምነቶችን ያደርጋሉ። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ እነኚህን ስምምነቶች በፅሁፍ አድርገው በጥንቃቄ ሲዋዋሉ አይስተዋልም።
ለምሳሌ እንደ ቤት ሽያጭ፣ የመኪና ሽያጭ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስጦታ ወዘተ ስምምነቶች ሕጋዊ ለመሆን ግዴታ በጽሁፍ መሆን አለባቸው። ስለሆነም ሁልጊዜ ስምምነቶችዎን በጽሁፍ የመፃፍ፣ ሁሉም ተዋዋይ ወገኖችና እማኞች መፈረማቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ሰነዱን በጥቅቃቄ ማስቀመጥ ስምምነቱ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ይረዳዎታል::
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


Репост из: የኔ ቻነል
ተፅኖ ፈጣሪ የሚድያ ሰው መሆን ይፈልጋሉ ?እንግዲያውስ ይቀላቀሉን


#የወንድማማቾችን_ፀብ_ለመገላገል_የገቡትን_የገዛ_እናቱን_በእንጨት_በመምታት_የገደለው_ግለሰብ_በእስራት_ተቀጣ

✔️በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ሙሉ ገብረ ኪዳን የአራት ወንድ ልጆች እና  የአንዲት ሴት ልጅ እናት ሲሆኑ ባለቤታቸው   ባለመኖሩ ከልጆቻቸው መካከል  እንዳለው አበራ የተባለው የመጀመሪያ ልጅ  ቤተሰብ አስተዳድራለሁኝ  በማለት ሃላፊነት ወስዶ እንደነበር ተገልጿል ።

ይሁን እንጂ እህት እና ወንድሞቹ ይህንን ኃላፊነቱን ሳይቀበሉ በመቅረታቸው አለመግባባት ተፈጥሮ  የነበረ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት ኃላፊ  ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል። ታናናሾቹ አንቺ ለእሱ ታዳያለሽ በማለት  እናታቸውን ይወቅሱ የነበረ መሆኑ እና እሱም እህት እና ወንድሞቹ ከእናታቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይከታተላቸው እንደነበር ተነግሯል ።  

ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት  ላይ ጫላ አበራ ፣ ደማ አበራ ፣  አታለሉ አበራ ፣ አራርሳ አበራ እናታቸው ቤት ተገናኝተው እያወሩ እያለ  ወንድማቸው እንዳለው  አንድ ላይ መሰባሰባቸው  በሰላም ላይሆን ይችላል በማለት በንዴት እናቱ  ቤት በመሄድ  አንድ ላይ ሆናችሁ እየዶለታችሁብኝ ነው በማለት  ጸብ ለማንሳት መሞከሩ ተጠቁሟል። ይህንኑ ተከትሎ ጫላ አበራ እና ዳማ አበራ ከቤት ይወጣሉ። እንዳለው ለእናቴ ያልሆነ ነገር እየነገራችሁ እኔን እንድትጠራጠር  የምታደርጉት እናንተ ናችሁ በማለት ወንድሞቹን ተከትሎ ከቤት ወጥቷል።።

እናትም ጸብ እንዳይፈጠር ሲለምኑ   በተፈጠረ አለመግባባት እንዳለ  እንጨት በመያዝ  ለጸብ ይጋበዛል። እናትን ጡታቸውን አውጥታ ባጠባችኋቸው ጡቴ እያሉ በመሃል ገብተው ሲለምኑ የመጀመሪያ ልጃቸው  ለወንድሞቹ የሰነዘረው የአጥር ፍልጥ እንጨት እናቱን ጭንቅላት ላይ በማረፍ ከባድ ጉዳይ ይከሰታል። ወንድማማቾች  እናታቸውን ወደ ጤናጣቢያ  ቢወስዷቸውም የደረሰባቸው ምት ከፍተኛ ነበር እና ህክምና ሲደረግላቸው ቢቆይም ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስተኛው ቀን ህይወታቸው አልፏል። ፖሊስ ጉዳዩን  በተመለከተ እንዳለውን እና ወንድሞችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩን  ሲያጣራ ጫላ እና ደማ አበራ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ቢኖሩም በግድያ ውስጥ ባለመኖራቸው  በዓቃቢ ህግ  ክስ  ሳይመሰረትባቸው በነጻ ሊለቀቁ ችለዋል። 

ዓቃቢ ህግ በእንዳለ ላይ በቂ ማስረጃ በማግኘቱ  ክስ በመመስረት መዝገቡን ለፍርድ ቤት  አቅርቧል። የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ክሱን ሲከታተል ቆይቶ  ለማገላገል የገቡትን እናቱ በአጥር እንጨት  በመግደል ጥፋተኛ በመሆኑ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ11 ዓመት  እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ  መምሪያ የኮሙኒኬሽን  ጽ/ቤት ሃላፊ  ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል።
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


Репост из: የኔ ቻነል
የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️


#በመዲናዋ_በስድስት_ክፍለ_ከተሞች_የስምና_ንብረት_ዝውውር_ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው፥ ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡

አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱ ተጠቁሟል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ ስድስት ክ/ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተመላክቷል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣየዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


Репост из: የኔ ቻነል
🔰 እድሜዎ ስንት ነው ?

በእድሜያቹ ልክ የተከፈተ ቻናል አለ መርጣችሁ ተቀላቀሉ ⬇️

Add your channel
@gofx19


#በአዋጅ_ቁጥር_1353_2017_አንቀፅ_99_የዲሲፕሊን_እርምጃ_አወሳሰድ

1/ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት መደበኛ የዲስፕሊን ምርመራ የሚያካሂድና የውሳኔ ሀሳብ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የሚያቀርብ የዲስፕሊን ኮሚቴ ማቋቋም
አለበት፤
2/ የዲስፕሊን ቅጣት የማንኛውንም ፍርድ ቤት ውሳኔ ሳይጠብቅ ወይም ሳይከተል ሊወሰን ይችላል፤
3/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በተቋቋመ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት ተጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበለት የመሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ የውሳኔ ሀሳቡን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለመቀበል ወይም ውድቅ ለማድረግ ይችላል፤
4/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የማንኛውም መንግሥት መሥሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 98 ንዑስ አንቀፅ (3)፤ (7)፤ (9)
ወይም (10) ላይ የተመለከተውን ከባድ የዲስፕሊን ጥፋት መፈፀሙን ካመነ
በዲሲፕሊን ኮሚቴው ውሳኔ ሃሳብ ላይ በራሱ ከመወሰን ይልቅ ከባድ የዲስፕሊን
ጥፋት የፈጸመው ሠራተኛ ከስራ እንዲሰናበት ጉዳዩን ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ
አመራር ጉባኤ በማቅረብ ሊያስወስን ይችላል፤
5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 4 ድንጋጌ መሠረት በአንድ መስሪያ ቤት የሥራ አመራር ጉባኤ አማካይነት የተሰጠ ከሥራ የማሰናበት ውሳኔ በዚህ አዋጅ ወይም በሌላ ሕግ በተቋቋመ ማንኛውም አስተዳደራዊም ሆነ መደበኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ ሊታይ አይችልም።
****
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


Репост из: የኔ ቻነል
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

የሚገራርሙ PROFILE እና WALLPAPER ይፈልጋሉ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
እንግዲያስ አንዴ ብቻ ንኩት👇👇👇👇👇👇👇

Wave ለመግባት @gofx19


#የመፋለም_ክስ (#petitory_action)

✔️ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከል ንብረቱ ያለ እርሱ ፈቃድ ከህግ ውጪ በሌላ ሰው ወይም ሀይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፋለም መብት አንዱ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1206 ድንጋጌ ያስረዳል፡፡

ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርዕስ  ስር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1192 የተመለከተው በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላከተ ሲሆን የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም፡፡

ድንጋጌው የሚንቀሳቀስ ንብረትን የባለሀብትነት ጥያቄ የጊዜ ገደብ ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት በሌለው በፍ/ብ/ህግ አንቀፅ 1845 ስር የተመለከተው ተመሳሳይ የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ እንደሆን ተፈልጎ ካለመሆኑ በላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀስ ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት ባህሪ ያለው እና ከትውልው ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በመሆኑ የባለሀብትነቱ መብት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በሌሎች ሁኔታዎች( አንቀፅ 1168....)  ይሆን ዘንድ ተፈልጎ የተቀመጠ ድንጋጌ መሆኑን እንገነዘባለን።

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፋለም ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም። (የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/መዝ/ቁ 43600)

N.B= ይህ ሲባል ግን ከውርስ፣ ከሽያጭ፣ ከስጦታና ከሌሎች ውሎች በመነጨ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ክርክር ይርጋ የለውም ማለት የሚቻል ሳይሆን ለጉዳዩ አግባብነት ባላቸው ህጎች በተቀመጡ የይርጋ ጊዜዎች የሚስተናገዱ ይሆናል።
*
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


እውቀት ወይስ ገንዘብ ይፈልጋሉ ?


Hof on remarriage file no. 804_16.pdf
906.6Кб
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


🌐 📶 ነፃ ኢንተርኔት ፈላጊዎች የምትፈልጉ በ ሙሉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።

የ Http ወርሀዊ Un limited file ይለቀቅበታል።

ፊጠኑ File ለመገኘት  ቻይናሎችን ተቀላቀሉ
               👇👇👇👇
                   
                      Wave ለመግባት  ➽ @gofx19
                                                      


It's concerned about suspension of two Human Right organizationŝ...

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ-1.pdf
742.3Кб
የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ኢንግሊዘኛ-1.pdf
519.7Кб
የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ -1.pdf
680.3Кб
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


#Major_Changes_in_the_New_NBE_Proclamation_1359_2024_and_The_amended_Banking_Business_Proclamation_1360_2024

1⃣. Short-Term Debt Instruments: The NBE is now authorized to issue its own short-term debt instruments as part of its open market operations, enhancing its monetary policy tools.
2⃣. Regulatory Sandbox: A regulatory sandbox framework will be established to facilitate the testing and introduction of innovative financial services, encouraging fintech development and experimentation within a controlled environment.
3⃣. Authorized Capital: The authorized capital of the NBE has increased significantly to 20 billion Birr, with a minimum paid-up capital requirement of 10 billion Birr, up from the previous half a billion Birr.
4⃣. General Reserve Fund: The net profit generated by the NBE will be transferred to a General Reserve Fund until it reaches 5% of the NBE's monetary liabilities, reinforcing financial stability.
5⃣. Board Composition: The board of the NBE will expand from seven to nine members, allowing for greater diversity of thought and expertise in governance.
6⃣. Financial Stability Committee: A seven-member Financial Stability Committee will be established to regularly assess systemic risks within the financial system and propose necessary macro and microprudential policies.
7⃣. Monetary Policy Committee: A dedicated Monetary Policy Committee, also comprising seven members, will be responsible for preparing and proposing monetary policy initiatives.
8⃣. Central Bank Digital Currency: The NBE's Board may issue directives regarding the operation of Central Bank Digital Currency (CBDC), signaling a move towards modern digital financial solutions.

▎Implications for Economic Development

The ratification of these proclamations, alongside the amendment to the Banking Business Proclamation allowing foreign banks to operate in Ethiopia, signifies a monumental shift in the country's banking landscape. Key implications include:

• Enhanced Financial Inclusion: By integrating fintech solutions and allowing data-driven lending decisions, more individuals and businesses can access financial services, fostering entrepreneurship and innovation.

• Strengthened Regulatory Framework: The introduction of stringent regulatory measures enhances the stability and integrity of the banking sector, ensuring consumer protection and confidence in financial institutions.

• Increased Competition: Allowing foreign banks to enter the market encourages competition among banks, leading to improved services and innovative financial products tailored to consumer needs.

• Collaboration with Fintech: The reforms facilitate collaboration between traditional banks and fintech companies, promoting advancements in financial technology and service delivery that can better meet the evolving demands of consumers.

In summary, these reforms reflect Ethiopia's commitment to creating a robust, resilient banking system that supports sustainable economic growth and adapts to emerging challenges and opportunities in a rapidly changingI global financial landscape
  #Justice
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎች በፍርድ ቤቶች ምዝገባ ነገ እንደሚጀመር ተገለጸ
*
የሲቪል ምዝገ
ባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚመዘግባቸው ኩነቶች መካከል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉዲፍቻ እና ፍቺ በፍርድ ቤቶቹ ከነገ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚጀምር ተቋሙ አስታውቋል።

ሁለቱ ተቋማት የኩነት ምዝገባን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ፤ ምዝገባው ነገ ታሕሳስ 9/4/2017 ዓ.ም እንደሚጀምር ነው የተነገረው።

በዚህም መሰረት በአራዳ እና ቦሌ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች የፌደራልና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት፤ ሶር አምባ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ምድብ ችሎት ምዝገባው መሰጠት እንደሚጀምር ታውቋል።
#FFIC
መዝገብ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


#የሰ/መዝ/ቁ 179416
=====//////====
✔️መነሻ ቅጣታቸው ከ12 ዓመት በታች ሆኖ መድረሻ ቅጣታቸው ግን ከ12 ዓመት በላይ የሆኑ የወንጀል ጉዳዬችን ተከሳሽ በሌለበት ማየት ይቻላል ወይስ አይቻልም?

በብዙ ዳኞች መካከልእና በፍርድ ቤቶችም ዘንድ የተለያየ ትርጉም ሲሰጠው የነበረው የወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 161(2)(ሀ) ድንጋጌ በሰበር ችሎቱ የህግ ትርጉም አከራካሪነቱን በሚያጠፋ መልኩ "አንድን የወንጀል ክስ ተከሳሽ በሌለበት ማየት የሚቻለው የቅጣቱ መድረሻ ከ12 ዓመት በላይ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን መነሻውም ከ12 ዓመት በላይ መሆን እንዳለበት ወይም መነሻ ቅጣታቸው ከ12 ዓመት ፅኑ እስራት በታች የሆኑ የወንጀል ጉዳዬችን ፍርድ ቤት ቀርቦ ከመከራከር ህገ መንግስታዊ መብት አንፃር ተከሳሽ በሌለበት ማየት እንደማይቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዚህ መዝገብ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


Statement concerning the reinstatement of suspended human right organization in Ethiopia ....

መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta


#የሌላ_አካል_ይዞታን_በሀሰተኛ_ሰነድ_በ700_ሚሊየን_ብር_ለመሸጥ_የተደራደረው_አትሌት_ድሪባ_መርጋ_በ3ዓመት_ከ4_ወር_እስራት_ተቀጣ

**

የሌላ አካል ይዞታን በሀሰተኛ ሰነድ በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ በመደራደር የተከሰሰው አትሌት ድሪባ መርጋ በ3 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወሰነ።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ 1ኛ አትሌት ድሪባ መርጋ እና 2ኛ በግል ስራ የሚተዳደሩት ወ/ሮ መንበረ አበበ ገብረጻዲቅ ላይ የተሳትፎ ደረጃ ጠቅሶ ተደራራቢ ክሶችን አቅርቦባቸዋል።

በዚህም በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስ ቀርቦበታል።

ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሆነውንና በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 08 ስር የሚገኘውን 4 ሺህ 972 ካሬ ሜትር ይዞታን በመጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሚመለከተው ተቋም እንደተሰጠ በማስመሰል ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለሶስተኛ ወገን ለሽያጭ ማቅረቡን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በክሱ አስፍሯል።

በተጨማሪም ተከሳሹ በውል ቁጥር 2036/2012 ዓ.ም ደግሞ በውል ሰጭ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ዘርፍ እና በውል ተቀባይ ናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል የተፈረ በማስመሰል የተዘጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተሰጠ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኮድ ቁጥር 2929/2929/2015 የሊዝ ውልን በማሻሻል እንደላከ በማስመሰል የተጋጀ ሀሰተኛ የሊዝ ውል ለሽያጭ አቅርቧል።

በተጨማሪም ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ውክልና ባልሰጠችበት ሁኔታ ላይ በህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ1ኛ ተከሳሽ ይዞታውን በሽያጭ እስከ ማስተላለፍ ድረስ እንዲያስተዳድር ውክልና እንደሰጠች ተደርጎ የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ ማቅረቡ በክሱ ላይ ተመላክቷል።

1ኛ ተከሳሽ በታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በይዞታው ላይ የተጠቀሱ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማቅረብ ይዞታውን በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ ሲደራደር የመያዙን ጠቅሶ ዐቃቤ ሕግ በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።

ሁለተኛ ክስ ላይ ደግሞ ከዚህ በፊት እስኪያዝ ድረስ ለጊዜው ክሱ በተቋረጠለት ማለትም ስዩም አሰፋ ወንድማገኝ በተባለ ግለሰብ ላይ የቀረበ ክስ ነበር።

ይኸውም ክስ በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ንዑስ ቁጥር 1 (ሀ) ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል የሚል ነው።

በዚህም 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት አስበው በ1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በሆነው እና በስራ አስኪያጅነት የሚተዳደረው ናይስ ሪል ስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ይዞታ ላይ ተመሳስሎ የተሰራ ሀሰተኛ ካርታ፣ የሊዝ ውልና የውክልና ሰነድ ማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ቀርቦባቸዋል።

3ኛ ክስ ደግሞ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ የቀረበ ሲሆን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 390 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን መተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል።

በዚህም በታህሳስ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው አረንጓዴ ሰፈር ተብሎ ከሚታወቀው ቦታ አካባቢ በሚገኘው የስራ ቦታዋ ውስጥ በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት በተደረገ ብርበራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በልደታ ክ/ከ ትምህርትና ስልጠና ጽ/ቤት የዕውቀት ለህብረት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ካርድ እና በትምህርት ሚኒስቴር አባይ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት የተማሪ ውጤት መግለጫ ካርድ የተገኘባት በመሆኑ የሐሰት ስራ ለመፈጸም የሚያገለግሉ መሳርያዎችና መስርያዎች ይዞ መገኘት ወንጀል ተከሳለች።

በዚህ መልኩ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የቀረበባቸው ክስ ዝርዝር በችሎት እንዲደርሳቸው የተደረገ እና ክሱን በንባብ እንዲሰሙ ተደርጓል።

3ኛ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 1 በሌለበት ሊታይ የማይችል በመሆኑ ምክንያት እስኪያዝ ድረስ ለጊዜው ክሱ እዲቋረጥ ተደርጓል።

ከዚህም በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው የእምነት ክህደት ቃል በመስጠታቸው ዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ሲሆን ተከሳሾቹ ግን የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መከላከል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ 1ኛ ተከሳሽ አትሌት ድሪባ መርጋን በ3 ዓመት ከ4 ወራት ጽኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

ሁለተኛ ተከሳሽን በሚመለከት የጤና እክል እንዳለባት፣ ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኗንና ሌሎች ያቀረበችውን የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ በ2 ዓመት ከ9 ወራት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የተጣለው ቅጣት እንዲገደብ አድርጓል።
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta
http://t.me/Higehateta



Показано 20 последних публикаций.