#በገጠር_የመሬት_ሽያጭ_እና_ግዢ_የሚያከናውኑ_ሰዎችን_እስከ_አምስት_አመት_በእስር_የሚያስቀጣ_አዋጅ_በፓርላማ_ጸደቀ
✔️የገጠር መሬትን የሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።
የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል።
አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል።
ማንኛውም ሰው መሬት የሸጠ ወይም የገዛ እንደሆነ፤ ከ100 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ወይም ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም በሁለቱም ሊቀጣ እንደሚችል በአዲሱ ድንጋጌ ላይ ሰፍሯል። በኢፌዲሪ ሕገ መንግስት መሰረት “መሬት የማይሸጥ፣ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው”።
ሕገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የባለቤትነት መብትን የሰጠው “ለመንግስት እና ለህዝብ” ነው። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ የወረረ ማንኛውም ሰው፤ ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አሊያም ከ30 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተደንግጓል።
በእነዚህ ይዞታዎች ላይ ጉዳት አድርሶ የተገኘ ማንኛውም ሰው፤ ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ወይም ከ50 ሺህ እስከ 150 ሺህ ብር እንደሚቀጣም በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ማንኛውንም ግንባታ የሰራ ወይም እንዲሰራ የፈቀደ ሰው ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከ1 ዓመት እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት አሊያም ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ይቀጣል።
እነዚህ ቅጣቶች፤ ከመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ውጪ ይዞታውን ጥቅም ላይ አውሎ የተገኘ ሰው ላይ በተመሳሳይ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል። ሀሰተኛ የመሬት ይዞታ ማስረጃ ያቀረበ ባለይዞታ እንዲሁም ማስረጃ የሰወረ ወይም የተሳሳተ ማስረጃ የሰጠ ባለሙያ ላይ የሚጣለው እስራት ከላይ እንዳሉት የህግ ጥሰቶች ተመሳሳይ ቢሆንም የገንዘብ ቅጣቱ መነሻ ግን ወደ 20 ሺህ ብር ዝቅ ብሏል።
#ኢትዮጵያኢንሳይደር
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ #Share & #likeያድርጉ እንዲሁም ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ👇👇
Join here⬇️
http://t.me/Higehateta