ኦሮሚያ ባንክ ከሳንቲም ፔይ ጋር በመሆን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ማስተዋወቁን ቀጥሏል፡፡
ይህ በአይነቱ ለየት ያለዉ አዲስ የክፍያ ስርዓት በዛሬ ዕለት የባንካችን ከፍተኛ ዓመራሮች እና ደንበኞች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ ይፋ ተደርጓል!
ኦሮሚያ ባንክ እና ሳንቲም ፔይ በጋራ በመሆን ለአገልግሎት ዝግጁ ያደረጉት አዲስ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀልጣፋ በመሆኑ የግብይት ስርዓቱን ስለሚያሳልጥ በደንበኞች ዘንድ እጅግ ተፈላጊ እየሆነ መጥቷል፡፡
በሀዋሳ ከተማ በተደረገዉ በዚህ የዲጂታል ክፍያን ማስተዋወቂያ መድረክላይ በከተማዋ የሚገኙ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች፤ የእምነት ተቋማት እንዲሁም የንግድ ድርጅቶች ተሳትፈዋል።
ኦሮሚያ ባንክ እና ሳንቲም ፔይ በጋራ በመሆን ቀደም ሲልም በጅግጅጋ እና ድሬዳዋ ከተሞች ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ማስተዋወቃቸዉ ይታወሳል፡፡