▩▩▩▩▩▩ #ጣና ▩▩▩▩▩▩
ጣና ከመከራው ውሃ የተረፈ፣ከኤዶም ገነት የተጨለፈ፣የቃል ኪዳኗን መርከብ ያንሳፈፈ፣ፍጥረቱንም ሁሉ ያተረፈ ሐይቅ ነው።
በልብ አምሳያ የተሰራ፣ከልብ የመነጨ ሀይማኖት፣እምነት ፣ታሪክ፣ትውፊት፣አርቆ አሳቢነትንና ደግነትን አቅፎ ይዟል።
ጣና ምንጩ ከኤዶም ገነት ሚወርደው ግዮን በላዩ ላይ ይሄዳል።
ጣና ሀይቅ በጥንታዊ ቋንቋ(ግዕዝ) አገላለፅ ይባላል።ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ "ፀአና በደመና" በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሐይቁ መጠሪያ ስም "ጣና"መጠሪያ ስም ሆኖታል ነው የሚባለው።
ጣና ምድር የጥፋት ውሃ አለምን ባጠፋች ጊዜ ዘር እንዲተርፍ ቃልኪዳን የተሰጠው የኖህ መርከብ ማያ አይኀ መጉደል ሲጀምር በ7ኛው ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአናቱ ላይ ያረፈበት ታላቅ ሐይቅ ነው።የኖህ መርከብ ያረፈበትም አራራት ተራራ በጣና ራስጌ(ዘጌ) የይጋንዳ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስትያን ላይ ነው።
ከ3000 ዓመት በፊት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነው ታቦተ ጽዮን ቀዳማዊ ሚኒሊክ ከ12 ነገደ እስራኤል ጋር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ ያረፈችው ጣና ቂርቆስ ገዳም ላይ ነው። እናም ለ 800 አመታት እዛ ቆይታለች ከዛን የተለያዩ ቦታዎች አርፋለች በመጨረሻም በአሁኑ አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች። ዛሬም ጣና ቂርቆስ ከ4000ሺህ 518 ዓ/ዓ ጀምሮ መስዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ፣አራት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይና የኦሪት የብረት መስዋዕት ማቃጠያ በስፍራው ይገኛል። ከታቦተ ጽዮን ጋር የመጣው ሊቀ ካህኑ አዛርያስ ጣና ቂርቆስ ገዳም ላይ ነው የተቀበረው።
ከ3000ሺህ አመት በፊት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ባረፈችበት ጣና ቂርቆስ ገዳም በአንደኛው ክፍለ ዘመን ሄሮዶስ ጌታን ሊገድል በፈለገ ጊዜ ለቅድስት ድንግል ማርያም ከልጃ ፣ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር 3 ወር ከ 10 ቀናት የተቀመጠችበት ቦታ ነው።
ጣና ባጠቃላይ በውስጡ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩት 27 ገዳማትን አቅፎ ይይዛል ገዳሞቹ በ14 ምዕት አመት አቡነ መድሀኒ እግዚእ ባመነኮሷቸው ተብለው በሚጠሩት ቅዱሳን አባቶች የተመሰረቱ ናቸው ከገዳማቶቹ መካከል
➲ ደብረ ማርያም
➲ ክብራን ገብርኤል
➲ ዑራ ኪዳነምህረት
➲ መሀል ዘጌ ጊዮርጊስ
➲ አቡነ በትረ ማርያም
➲ አዝዋ ማርያም
➲ ዳጋ እስጢፋኖስ
➲ ይጋንዳ ተክለሃይማኖት
➲ ናርጋ ስላሴ
➲ ደብረ ሲና ማርያም
➲ ማንድባ መድሀኒአለም
➲ ጣና ቂርቆስ
➲ ክርስቶስ ሳምራ
➲ ራማ መድሕኒ ዓለም
➲ ኮታ ማርያም.......እና ሌሎችም ገዳም ይገኙበታል።
ሰባቱ ከዋክብት የሚባሉት አክሱም አቅራቢያ የሚገኘው የደብረ በንኮል ገዳም መስራች አቡነ መድኃኒ እግዚእ ደቀ መዛሙርት ናቸው።እነሱም፦
1 ➽ #አቡነ_ታዲዮስ ደብረ ማርያም መስራች
2 ➽ #አቡነ_ዘዮሐንስ የክብራን እና የእንጦስ ገዳም መስራች
3 ➽ #አቡነ_በትረማርያም የዘጌ ጊዮርጊስ መስራች
4 ➽ #አቡነ_ኂሩት_አምላክ የዳጋ እስጢፋኖስ መስራች
5 ➽ #አቡነ_ኢሳይ የመንደባ መድሀኒአለም መስራች
6 ➽ #አቡነ_ዘካሪያስ ደብረ ገሊላ መስራች
7 ➽ #አቡነ_ፍቁረዮሐንስ ጣና ቂርቆስ መስራች
ዳጋ እስጢፋኖስ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግስት በአቡነ ሂሩት አምላክ የተመሰረተ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኑ ውኃ ዘመን የሰው ዘር በኖህ መርከብ አማካኝነት መዳኑን ለማመልከት በመርከብ ቅርፅ የተሰራ ነው።የዐፄ ዳዊት (1365-1395) የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ (1426-1460) የዐፄ ሱስኒዮስ (1596-1624) እና የዐፄ ፋሲል (1924-1659) አስክሬን ሳይፈርስ በክብር የሚገኘው በዚሁ ገዳም ነው።
ቅዱስ ያሬድ ምልክት የሌለውን ድጓ የፃፈባትና መፅሐፉ እና መስቀሉ የሚገኝበት ገዳም ነው።
ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሐይቅ ነው። አጠቃላይ ስፋቱ 695,885 ሔክታር ነው። ከሰሜን እስከ ደቡብ ያለው የሐይቁ ርዝመት 85 ኪሎ ሜትር ሲቃረብ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ያለው ስፋቱም 66 ኪሎ ሜትር ተገምቷል።
#አንባቢ #ትውልድ #እንፍጠር
share for your friends
@ethio_treca