የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የማህበሩ አባል ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት: ከማህበሩ ምስረታ በፊትና ማህበሩ በአዋጅ ከተቋቋመም በኃላ ማህበሩ በሚያዋቅራቸው የተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የጎላ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ከቆዩት ባለሙያዎች አንዱ የሆኑትና ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ሆነው ለተሾሙት ለአቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተሰማውን ከፍ ያለ ደስታ ይገልፃል:: እንዲሁም ለጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ለተሾሙት ዳኛ አበባ እምቢአለ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእቱን ያስተላልፋል::
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ለፕሬዝደንቱና ለመላው አመራራቸው ከሹመታቸው ግዜ ጀምሮ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት ሙሉ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፀ ለተሿሚዎች መልካም የስራ ዘመን ሲመኝ ተሿሚዎች ለምናልመው ጥራት ያለው ፍትህ መረጋገጥ እና ለፍትህ ስርአቱ መዳበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመሪነት ድርሻቸውን እንደሚወጡ በማመን ነው::
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ጥር 09 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ