የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር - Ethiopian Federal Bar Association


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ በአዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 57 ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




እንኳን ለአንደኛ ዓመት የምስረታ በዓል አደረሰን!!
*******
በኢትዮጵያ የህግ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው ለ30 አመታት በሚጠጋ ትግል ሲደረግበት የቆየው በርካታ የህግ ባለሙያዎች ዋጋ የከፈሉበት የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁጥር 1249/13 ልክ የዛሬ አመት ጥር 15 ቀን 2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርሌግዥሪ (ኢንተርኮቲነንታል) ሆቴል ከ 1600 (ከአንድ ሺህ ስድስት መቶ) በላይ ጠበቆች: ሚኒስትሮች; የፌደራልና የክልል የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንቶች: የክልል ጠቅላይ ዐቃቢያነ ህግ እና ሌሎች በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት በታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ታሪካዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አደረገ::

ማህበሩ በህግ ከተቋቋመበት የመጀመሪያ መስራች ጉባኤው ጀምሮ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ሲሆን የተቋም መሰረት የመጣልና ተቋም ከመፍጠር ስራው ቅድሚያ ተሰጥቶት ያለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሀገር የህግ ስርአት ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና እያሳያቸው ያሉ ጅምሮች ተጠናክረው ዘንድ ለሀገርና ለህዝብ ይተርፍ ዘንድ የመላው አባላቱና የህግ ማህበረሰቡ ድጋፍ የሚያስፈልግ ነው::

እንኳን ለአንደኛ አመት በዓላችን አደረሰን!
ጥር 15 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ




እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!
******
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እና በተለይ ለማህበሩ አባላት ጠበቆች በሙሉ እንኳን ለከተራ እና ለጥምቀተ በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

መልካም በዓል!!
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር
ጥር 10/2015 ዓ.ም




የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ላለፉት አራት ዓመታት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን በፕሬዘዳንትነት እና ምክትል ፕሬዘዳንትነት ለመሩት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እና አቶ ሰለሞን አረዳ በኃላፊነት ዘመናቸው ላበረከቷቸው በጎ አስተዋፅኦዎች ሁሉ ያመሰግናል።

ማህበሩ ከዚህ በኃላ በሚሄዱበት ሁሉ መልካም እድል እንዲገጥማቸው እየተመኘ የቀድሞው ም/ ፕሬዝደንት ሰለሞን አረዳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከፊል ግዜ ዳኛ ሆነው በተሾሙበት ሃላፊነት ስኬት እንዲገጥማቸው ይመኛል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር
ጥር 09 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ




የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የማህበሩ አባል ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት: ከማህበሩ ምስረታ በፊትና ማህበሩ በአዋጅ ከተቋቋመም በኃላ  ማህበሩ በሚያዋቅራቸው የተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የጎላ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ከቆዩት ባለሙያዎች አንዱ የሆኑትና ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ  ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ሆነው ለተሾሙት ለአቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተሰማውን ከፍ ያለ ደስታ ይገልፃል:: እንዲሁም ለጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ለተሾሙት ዳኛ አበባ እምቢአለ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእቱን ያስተላልፋል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ለፕሬዝደንቱና ለመላው አመራራቸው ከሹመታቸው ግዜ ጀምሮ ለሚያከናውኗቸው ተግባራት ሙሉ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን እየገለፀ ለተሿሚዎች መልካም የስራ ዘመን ሲመኝ ተሿሚዎች ለምናልመው ጥራት ያለው ፍትህ መረጋገጥ እና ለፍትህ ስርአቱ መዳበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመሪነት ድርሻቸውን እንደሚወጡ በማመን ነው::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ጥር 09 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ




የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የሚደረገው ውይይት ቀጥሎ ተካሄደ

******

የኢትዮዽያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁ.1249/2013 ተቋቁሞ አደረጃጀትና መዋቅሮችን ፣ የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና አሰራሮች በመቅረፅ በሂደቱም ተቋም የመፍጠር ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል::

በዚህም እየተከናወኑ ያሉ በርካታ ተግባራት እንዳሉ ሆነው ጠንካራ ተቋም የመፍጠሩ ጉዳይ ቅድሚያ የተሰጠው ሲሆን የዚሁ ተግባር አንደኛው አካል የሆነው የተቋሙን ህጎች ፣ ደንብና መመሪያዎችን ማርቀቅ ነው::

የማህበሩን አደረጃጀት በዋናነት የሚወስነው በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ላይ እየተደረገ ያለው ምክክር በማህበሩ በተቋቋመው ልዩ ኮሚቴ አማካኝነት ቀጥሎ በበርካታ ጉዳዮች መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የረቂቅ የመተዳደሪያ ደንቡ አርቃቂ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው በእለቱ የረቂቁን መነሻ እሳቤዎች እና በልምድ የተወሰዱ የበርካታ ሀገራት የጠበቆች ማህበር አደረጃጀቶችን በዝርዝር አቅርበው ካለፈው የቀጠለ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል:: የጠበቆች ማህበሩ ሀገራችንን ጨምሮ በአፍሪካ፣ በአውሮፖና በአሜሪካ ያሉ በርካታ Bar Associations መዋቅሮችን በማጥናት ተወዳዳሪ መዋቅር እንዲኖረው ለማስቻል እየተሞከረ መሆኑም ተገልጿል::

በማህበሩ መሪዎች አስተባባሪነት የተዋቀረው በዘርፉ የተረጋገጠ ልምድ ያላቸው አንጋፋ ጠበቆችን የያዘው ግብረ ሀይል አባላትም በርካታ ሀሳቦችን አንስተው ጠንካራ ውይይት ተደርጎል:: የተቋሙ አደረጃጀት ሲወሰንም የአመራር ወጥነትን ማረጋገጥ የቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አባላቱ አፅእኖት ሰጥተዋል::

በሌላ በኩል በአዋጅ ቁ.1249/2013 አንዳንድ ድንጋጌዎች በተግባር ጭምር የተፈተሹ ክፍተቶች ያሉባቸው መሆናቸው በመታመኑ ለህግ አውጪው አካል ለማሻሻያ ሀሳብ ጭምር ሊያገልግል የሚችል የህግ ማብራሪያ “Explanatory note” እንዲዘጋጅ አቅጣጫ ተቀምጧል:: ይህውም በአጭር ግዜ ውስጥ ተጠናቆ የሚቀርብ ይሆናል::

በምክክሩ ማጠቃለያ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የማህበሩ ተ/ፕሬዝደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው "እንደዛሬው ያሉት እጅግ የበሰሉ የህግ ሙግቶች እና ክርክሮች የተቋሙ ዋነኛ የታሪክ አካል በመሆናቸው በአግባቡ ተቀርፀውና ተሰንደው ሊቀመጡ እንደሚገባ" አሳስበው ፣ በሂደቱ ላይ ሙያና ግዜአቸውን ሰጥተው እየተሳተፉ ላሉ አንጋፋ ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: አያይዘውም ረቂቁ በቅርብ ግዜ የመጨረሻው ቅጂው ተጠናቆ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ እንደሚፀድቅ አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር
አዲስ አበባ
ጥር 2015 ዓ.ም




ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ከእስር ተለቀው የገና በአልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳልፈዋል::
********
ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ወንድሙ ኢብሳ እስር ከተፈፀመባቸው ጊዜ ጀምሮ ማህበሩ ተገቢውን ክትትል እያደረገ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር አመራር በስልክ እንደገለፁት በእስር ቆይታቸው ይህ ነው የተባለ የአያያዝ ችግር ያልገጠማቸውና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል::

ጠበቃው ችሎት በመድፈር በሚል ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ በሚገኘው የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ጋር በተፈጠረ የቃላት ልውውጥ መነሻ ተደርጎ የአራት ወራት እስራት የተፈረደባቸው መሆኑ የሚታወስ ነው::

የይግባኝ ክርክሩም በተሟላ ሁኔታ ታህሳስ 26 ቀን 2015ዓ.ም በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የተደረገ ሲሆን ችሎቱም ከፍተኛው ፍ/ቤት ለችሎት መድፈር መነሻ አድርጌአቸዋለሁ ካላቸው "17 ነጥቦች" 16ቱን ውድቅ በማድረግ የ4 ወራት እስራት ቅጣቱን በመሻር ከ 18 ቀናት እስር በኃላ እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል::

ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ይህ የእስር ቅጣት ከተላለፈባቸው ቀን ጀምሮ "ከፍተኛ እገዛ" ላደረገላቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር እና ለማህበሩ መሪዎች እንዲሁም በሂደቱ ለተሳተፉ የህግ ባለሙያዎች ምስጋናቸውንም አቅርበዋል:: የጠበቆች ማህበሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ እና በችሎት የሚሰየሙ ጠበቆችን ከመመደብ ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግሮችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በቀጣይ ከጉዳዩና ተያያዥ ነጥቦች ዙሪያ የተሟላ ሪፖርት እና አቋሙን ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ይገልፃል::

ለኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
አዲስ አበባ




የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

መልካም የገና በዓል!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር
ታህሳስ 29 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ






የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳን በተመለከተ እስር ከተፈፀመባቸው ግዜ ጀምሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል::
-----------------------------------
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ጉዳዩ አሁንም በፍርድ (በይግባኝ ሂደት) ላይ ያለ እንደመሆኑ መጠን ማህበሩ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቷል::

በዚህም በታሰሩበት ኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ላይ ፍቃድ ያላቸውን ሁለት ጠበቆች ማህበሩ በመመደብ ተገቢው የህግ ሂደት እየተፈፀመ ይገኛል:: ከዚህ በተጨማሪ ማህበሩ የጉዳዩን ትክክለኛ ምክንያት ከተለያዩ አካላት ለማጥራትና ለማረጋገጥ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል::

የይግባኝ ክርክሩም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በመጪው እሮብ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ይሰማል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ቁ. 1249/2013 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ዋነኛው የህግ የበላይነት መከበር ጋር የተያያዙ ተግባራት መሆናቸው እንዳሉ ሆኖ ጠበቆች በሀገራችን የህግ ስርአት ላይ የሚኖራቸውን  የጎላ ሚና መወጣት እንዲችሉ እና ለደንበኞቻቸው ጥራት ያለው የህግ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችሏቸው መብቶች መከበራቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት::

በጉዳዩ ላይ ማህበሩ ተገቢውን ክትትል እያደረገ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣይ ተቋሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር በተገቢው የሚሄድበት መሆኑንና የሚደረስባቸው ሂደቶች በይፋ እንደሚገልፅ ያሳውቃል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ታህሳስ 23 2015ዓ.ም




ከፌዴራል ጠበቆች ማህበር በወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና ማስረጃ ሕግ የተገኘው ግብዓት ረቂቅ ሕጉን ለማዳበር እንደሚያግዝ ተገለጸ
*******

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር በወንጀል የሕግ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ ላይ ውጤታማ የፍትህ ሥርዓት ለማምጣት መሻሻል ያለባቸውን ሕጎች ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በግብዓትነት ማቅረቡ ይታወሳል።

ታህሣሥ 12፣ 2015 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተደረገው ወይይት፤ በወንጀል የህግ ሥነ ሥርዓት እና ማስረጃ ረቂቅ ሕግ ላይ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር የተገኘው ግብዓት ረቂቅ ሕጉን ለማዳበር እንደሚረዳ ገልጿል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህንን ያለው የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ ሕግ ላይ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተወያየበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ እንዳሉት ረቂቅ ሕጉን ለማዳበር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ግብዓት ሲሰበሰብ በመቆየቱ ረቂቅ ሕጉ መዳበሩንና አሁን በዌብሳይት የተጫነው ረቂቅ ሕግ መጀመሪያ ሲመራ ከነበረው የተለየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አባላት ረቂቅ ሕጉን ቃል በቃል በማንበብ ለሰጡት አስተያየት አመስግነው፤ ቋሚ ኮሚቴው ለጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርትና ውሳኔ ከማቅረቡ በፊት ለማዳበር የሚያስችለውን ግብዓት ለመጨመር ረቂቁን እንደገና ማየት እንዳለበት እና ረቂቅ ሕጉ እስከሚፀድቅ ድረስም የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ባለሙያዎችን በመላክ ረጅም ጊዜ የሚያሰራ ሕግ እንዲወጣ የበኩሉን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላትም በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ረቂቅ ሕጉን ቃል በቃል አንብቦ መስተካከል አለባቸው በማለት የሰጣቸውን አስተያየቶች መነሻ በማድረግ ረቂቅ ሕጉን እንደገና አይተው ለማዳበር የሚያስችል ግብዓት ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ አክለውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ረቂቅ ሕጉን ለማዳበር ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ አስተያየት መስጠቱ ረጅም ጊዜ የሚያሰራ ሕግ ለማውጣት የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንትና ረቂቅ ሕጉን ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው እንዳሉት በረቂቅ ሕጉ አንዳንድ የሚጣረሱ አንቀጾች እና ግልፅነት የሚጎድላቸው ቃላት ስላሉ እንደገና ታይተው ሊስተካከሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ አክለውም ረቂቅ ሕጉን በሚገባ በመመርመር ረጅም ጊዜ የሚያሠራ ሕግ እንዲወጣ ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ለመሥራት ፈቃደኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር አባላት በበኩላቸው ረቂቅ ሕጉን የበለጠ ማዳበር እንዲቻል ማህበሩ በረቂቅ ሕጉ አስተያየት እንዲሰጥ ቋሚ ኮሚቴው ስለፈቀደላቸው አመስግነው፤ በረቂቅ ሕጉ በተለያዩ አንቀጾች የተገለጹትን ግልጽነት የሚጎድላቸው አንቀጾች ማስተካከል ከተቻለ ረጅም ጊዜ የሚያሰራ ሕግ ማውጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

በረቂቅ ሕጉ ላይ የማያሰሩ አንቀጾች ተስተካክለው ሕጉ ቢወጣ ጠበቆች፣ አቃቤ ሕጎችና ዳኞች ያንን አክብረው ስለሚሰሩ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል የኢትዮጵያ ጠበቆች ማህበር አባላት ጨምረው አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ዜና ፓርላማ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት


ዜና አረፍት:
ታህሳስ 11 ቀን 2015ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በዳኛ ትንሳኤ በላይነህና በጏደኛው ዙፋን ተፈሪ ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋና አሰቃቂ ህልፈት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልፃል:: ለሟቾች ቤተሰብ; ወዳጅ ዘመድ እና የስራ ባልደረቦች መፅናናትን ይመኛል::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
አዲስ አበባ

Показано 20 последних публикаций.

1 881

подписчиков
Статистика канала