"ሀዋን ማን ገደላት"
( ✍ አብዲ ኢኽላስ)
ክፍል አምስት (5)
እሁን ከጠዋቱ 3:30 ሆኗል። ሁሉም ከጠረቤዛ ተቀምጠው ቁርስ በመቀማመስ ላይ ይገኛሉ። እትዬ መርየም ማታ ሙና ባደረገችው ድርጊት እጅግ መበሳጨታቸውን እይታቸው ያሳብቃል። ነገር ግን ስሜታቸውንና የተፈጠረውን ማንም እንዲያውቅ ስላልፈለጉ ስሜታቸውን ገታ ንግግራቸውንም ቆጠብ አርገውታል። ምግቡን በመቃመስ ላይ ሳሉ እትዬ መርየም ምን አልባት ሁኔታውን ለሰሚር ቢነግሩት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ውስጣቸው ቢያውቅም እንኳን ሁኔታዎች ከተቀየሩ ብለው ነገሮችን ለመገመት የጥርጣሬ መንፈስ በሚመስል ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ወደሰሚር ለመሰዘር ሞከሩ።
የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም እንዲህ በማለት ጀመሩ። ብለው ጠየቁት። ሰሚር ግን መልስ መስጠት አልፈለገም። ፊቱ ጥቀርሻ ሲመስል አይኖቹ ሲቀሉ እጅጉን በጣም ሲበሳጭና የማይሆን ስሜት ውስጥ ሲገባ ያሳብቃል። ምክንያቱም እትዬ መርየም እያሉ ያሉት እኔ እና አንተ ለሀዋ የስጋ ዝምድና የለንም ትናንሾቹ ልጆችና ሙና ግን ከሀዋ ጋ በስጋ ዝምድናም ጨምር ይቆራኛሉ እና አንተ እና እኔ ይበልጥ አንገባም ይበልጥም አንጎዳም እያሉ እንደሆነ በደንብ ገብቶታል። ነገር ግን እጅጉን ስለሚያከብራቸው እና ስለሚፈራቸው ቃል መተንፈስ አልፈለገም። ምግቡ ተበልቶ ያለቀውን ሰሀን በጣቱ እየጠረገ ለመላስ ሞከረ።
ይሄኔ ወሬ አዳኟ ንግግር የማያመልጣት ሙና ድንገት ጣልቃ ገብታ አለች። ብዙም በማይማርክ አነጋገር ምክንያቱም እየተወራ ያለው ለሀዋ ማን ስጦታ ይስጣት የሚል ሳይሆን ሀዋ አንድ ነገር ብትሆን ማን ክፉኛ ይጎዳል የሚል ከባድ ርዕስ ነውና። ሰሚር ምንም አይነት መልስ አልሰጠም። በልስ ያልሰጠበት ምክንያት ለ እትዬ መርየም በእጅጉኑ ገብቷቸዋል። ምክንያቱም የሀዋ እና የሰሚርን ፍቅር ከሳቸው የበለጠ የሚያውቅ ሰው የለምና ነው። ሀዋ እና ሰሚር እኮ ፍቅራቸው እንኳን ላየው እንኳን ለኖረው ለሰማው እራሱ አጀብ የሚያሰኝ ነው። ለትንሽ ሰከንዶች ድሮ ሀዋ እና ሰሚር እንዴት ይፋቀሩ እንደነበር እስከ ቅርብ ቀናት የሀዋ ደብዛ እስከጠፋበት ግዜ ድረስ የነበራቸውን ያን የሚያስቀና ፍቅራቸውን እትዬ መርየም በአይምሮአቸው መኮምኮም ጀመሩ።
ሰሚር ወደስራ የሚገባው ዘውትር ሁለት ሰአት ላይ ነው። ወደስራ ለመሄድ የሚነሳው አንድ ሰአት ላይ ነው ከእንቅልፉ የሚነቃው ደግሞ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ሰሚር እጅግ በጣም ጠንካራ ሰራተኛ ነው።በዚህም ከንቅልፉ ከነቃ በኋላ ሁሉን ጣጣውን ጨራርሶ ቁርሱን በልቶ ልብሱን ለባብሶ ልጆቹን እና ባለቤቱን ተሰናብቶ ሁሉን አድርጎ አንድ ሰአት ላይ ከቤት ይወጣል። ነገር ግን ሁሌም ቢሆን አንድ ነገር መርሳቱ አይቀርም ወይ መነፅሩን ወይ ኮፍያውን ወይ ከረባቱን ወይ ቦርሳውን ብቻ ሞባይሉንም ይሁን አንዳች ነገር ሆን ብሎ አስቀምጦ ይወጣል። ይህን የምታውቀው ሀዋ የረሳውን ነገር ቶሎ አፋልጋ ድንገት ካስቀመጠበት በማግኘት በመስኮት በኩል ብላ ታስቆመውና እየሮጠች ተንደርድራ ሄዳ ትሰጠዋለች። ከሰጠችው በኋላ ምንም ቢመጣ የሚያላቃቸው አይመስልም በጣም ይተቃቀፋሉ። አብረው የነበሩ አብረው ምሽቱን ያሳለፉ ሳይሆን ተነፋፍቀው እንደተገናኙ ሰዎች ተቃቅፈው ለትንሽ ደቂቃ የሚያላቃቸው አጥተው በሀይል ይተቃቀፋሉ።
በዚህ ሁኔታ ትንሽ እንደቆዩ አቅፎ ወደ እቤት ካላስገባት በፍፁም እንደማትለቀው ነግራው ሁሌም እያቀፈ ወደ መኝታ ክፍል ይዟት ይገባል። ነገር ግን አልጋው ላይ ቆይተው ሲጫወቱ ሲላፉ እና ሲሳሳቁ እረጅም ሰአታትን ሳያሳልፉ አሁንም መለያየት ይሳናቸዋል። ይህ ሲሆን አንድ ሰአት የተነሳው ሰሚር ብዙ ሰአታትን አሳልፎ ከሁለት ሰአት ሶስት ሰአት እና ሶስት ተኩል በኋላ ወደስራ ለመሄድ ድንገት ይቆማል። የፍቅር ውሎዋቸው በዚህ አያበቃም። በነሱ ነገድ በነሱ ቤት አብዝቶ መናፈቅ አብዝቶ መውደድ እጅግ አርጎ ማፍቀር እንጂ መኩራት እና ስሜት መቀነስ መቀዛቀዝና መስመሰል ፈፅሞ ቦታ የላቸውም። ለዚህ ይመስላል ሁሌ ቢሮ ሲገባ ምሳ ሰአት እንደደረሰ ሀዋ የቋጠረችለትን ምግብ ካልሆነ ንክች ማያደርገው ይህ ውድ ባሏ ሰሚር ልክ ምሳቃውን ከፍቶ መመገብ ሲጀምር ሁሌም ምግቡ ላይ ጨው ያንሰዋል።
ሰሚር እጅግ በጣም የተካነ ሼፍ ከመሆኑ ባለፈ ምግብን በጣም አጣጥሞ የሚያውቅና ለጥሩ ምግብ እጅ የሚሰጥ ሰው በመሆኑ ጨው ያነሰበት ምግብ እንብዛም አይወድም። ታድያ ገና ምግቡን ከፍቶ አንድ ጎርሶ ምግቡ ጨው እንደሌለው ሲያረጋግጥ ፈገግ ይላል። ለጥቂት ሰከንዶች ውዷ ሚስቱን ሀዋን ያስታውሳል። በዚህም በትንሽ ተመስጦ ሰከንዶች ያልፋሉ። ታድያ ሀዋም እጅግ የፍቅር ተንኮለኛ ነችና ወድያውኑ በር ታንኳኳለች። ልክ እንደ ባለጉዳይ ድምጿን አጎርንና የምትናገረው ሀዋ በሩን አንኳኩታ ትገባለች። ያኔ በቦርሳዋ ውስጥ እሱን ለማየት ሰበብ እንዲሆናት ብቻ ጨው ይዛለት ብዙ ኪሎ ሜትር አቆራርጣ ትመጣለች። ታድያ ይሄን ካደረጉ በኋላ አብራው ትቆያለች አብራው ስራውን ታሰራዋለች። ግን ለሰሚርም ጭምር የሚገርመው አብራው ከቆየችና አብራው ከዋለች በኋላ ከስራው መውጫ ጥቂት ሰአታት ሲቀሩ ደሞ ጥላው ወደ ቤት ብርር... ብላ ትሄዳለች። አብረው መቆየት አብረው መዋል አብሮ መሆን ካለ አብረው ወደ እቤት መሄድ እየቻሉ ቀድማው የምትሄድበት ብቸኛ ምክንያት እቤት ሲገባ ልክ እንደ አዲስ ሰው አመታት እንደተነፋፈቀ አይነት ሰው ቁንጅትጅት ብላ ደሞ በአዲስ ስሜት ትቀበለዋለች። ይሄን ውድ እና ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ በእዝነ ህሊናቸው እያመላለሱ ያሉት እትዬ መርየም ድንገት የጊቢው በር ሲንኳኳ ከሀሳባቸው ነቃ አሉ።
ኻሊድ የተንኳኳውን በር ለመክፈት ከሁሉም ቀድሞ በሩጫ ሄደ። ነገር ግን በሩን ሲከፍተው ደንግጦ ቀረ። ያንኳኳው ይህን ጉዳይ በምርመራ የያዘው ኢንስፔክተር ግርማ ነው። ከውስጥ ደሞ ሰሚር ተቀምጧል። ሰሚር ባለበት ሁኔታ ኢንስፔክተር ቢገባ ጉዳዩ እዚ ይፈርጣልና ....ኻሊድ ድንገት ተቅለብልቦ ብሎ መለሰ።ግርማም ብዙ አላንገራገረም በማለት ጥያቄ አቀረበ። ኻሊድም ግርማ ብዙ አላንገራገረም በማለት ቀለል ባለ አማርኛ ተሰናበተው። ኻሊድም በሀይል እየተነፈሰ በሩን ዘጋ። ነገር ግን ድንገት በሩን ዘግቶ ሲቆም ከኋላው ሰሚር ቆሟል። ጠየቀው ኻሊድ ድንጋጤ ላይ ነበርና ያለውን እንኳን ሳያውቀው ድንገት ከአፉ አምልጦ >ብሎ ተነፈሰ።
ይቀጥላል.......
Https://t.me/halal_couples