እግዚአብሔርን አመስግኑ


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


#የሰባት_ቁጥር_ምስጢራት

➯በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ 7 ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን ዘንድም 7 ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ምሳሌ 24፡16 እግዚአብሔር ከሰኞ
እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት የነበሩት በ7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዘዳ 13፡21

➯ከዚህ ቀጥለንም ለቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የ7 ቁጥር ምስጢራትን ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፦

✅ሰባቱ አባቶች

፩. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
፪. የነፍስ አባት
፫. ወላጅ አባት
፬. የክርስትና አባት
፭. የጡት አባት
፮. የቆብ አባት
፯. የቀለም አባት

✅ሰባቱ ዲያቆናት

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ
፪. ቅዱስ ፊልጶስ
፫. ቅዱስ ጵሮክሮስ
፬. ቅዱስ ጢሞና
፭. ቅዱስ ኒቃሮና
፮. ቅዱስ ጳርሜና
፯. ቅዱስ ኒቆላዎስ

✅ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ

፩. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
፪. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
፫. እኔ የበጎች በር ነኝ
፬. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
፭. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
፮. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
፯. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

✅ሰባቱ ሰማያት

፩. ጽርሐ አርያም
፪. መንበረ መንግሥት
፫. ሰማይ ውዱድ
፬. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
፭. ኢዮር
፮. ራማ
፯. ኤረር

✅ሰባቱ ሊቃነ መላእክት

፩. ቅዱስ ሚካኤል
፪. ቅዱስ ገብርኤል
፫. ቅዱስ ሩፋኤል
፬. ቅዱስ ራጉኤል
፭. ቅዱስ ዑራኤል
፮. ቅዱስ ፋኑኤል
፯. ቅዱስ ሳቁኤል

✅ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት

፩. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
፪. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
፫. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
፬. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
፭. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
፮. የፊልድልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
፯. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

✅ሰባቱ ተዐምራት ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

፩. ፀሐይ ጨልሟል
፪. ጨረቃ ደም ሆነ
፫. ከዋክብት ረገፉ
፬. ዐለቶች ተሠነጠቁ
፭. መቃብራት ተከፈቱ
፮. ሙታን ተነሡ
፯. የቤተ መቅደስም መጋረጃ

✅ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

፩. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
፪. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
፫. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
፬. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
፭. ተጠማሁ
፮. ተፈጸመ
፯. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

✅ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን

፩. ምሥጢረ ጥምቀት
፪. ምሥጢረ ሜሮን
፫. ምሥጢረ ቁርባን
፬. ምሥጢረ ክህነት
፭. ምሥጢረ ተክሊል
፮. ምሥጢረ ንስሐ
፯. ምሥጢረ ቀንዲል

✅ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት

፩. ዐቢይ ጾም
፪. የሐዋርያት ጾም
፫. የፍልሰታ ጾም
፬. ጾመ ነቢያት
፭. ጾመ ገሀድ
፮. ጾመ ነነዌ
፯. ጾመ ድኅነት

✅ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

፩. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ 16፡6-19
፪. ሃሰተኛ ምላስ
፫. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
፬. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
፭. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
፮. የሐሰት ምስክርነት
፯. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

✅ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት

፩. ነግህ የጠዋት ጸሎት
፪. ሠለስት (የ3 ሰዓት ጸሎት)
፫. ቀትር (የ6 ሰዓት ጸሎት)
፬. ተሰአቱ (የ9 ሰዓት ጸሎት)
፭. ሰርክ (የ11 ሰዓት ጸሎት)
፮. ነዋም (የምኝታ ጸሎት)
፯. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)


"ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም"

ኢሳ፶፫፥፯

✞አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል✞

አማኑኤል/ፍቅርህ ይማርካል/(፪)
በመስቀል ተሰቅለህ መድኃኒት ሆነሃል
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል

ሳታቆስል በፍቅርህ ማረክኸን
ከፊት ቀድመህ በድል አስከተልከን
በደለኞች እኛ ሆነን ሳለ
አንተ ከፍለህ ክሳችን ተጣለ
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን(፪)
አዝ= = = = =
እንደሰማን እንዲሁ አይተናል
ማዳንህን ቀምሰን መስክረናል
የእግዚአብሔር በግ ቆስለህ የፈወስከን
ወደ ድንቁ ብርሃን ያሻገርከን
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን(፪)
አዝ= = = = =
አጽናንተኸን ሞትን አስተከዝከው
ወደ ጥልቁ እንዲወርድ አዘዝከው
በአንተ ፍቅር ምርኮ በዝቶልናል
ማማ ሆነህ ከፍ ከፍ ብለናል
ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን(፪)
አዝ= = = = =
ስንሸሽህ እየተከተልከን
ልጆች አርገህ በክብር አስጌጥከን
ተቅበዝባዡን ሰብስበሃልና
ከማደሪያህ ይፈልቃል ምስጋና
ኪርያላይሶን ኪርያላሶን(፪)

ኪርላይሶን ኪርያላይሶን
ኪርላይሶን ኪርያላይሶን

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን
ቴዎድሮስ ዮሴፍ


✝️ቅዱስ_አማኑኤል✝️🌹🌹🌹

🌺አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው
🌺ዘወትር እግዚአብሔ ከሁላችን ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን አሜን

🌺አማኑኤል ማለት አማኑ ኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው።
🌺«አማነ»እና «ኤል» ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛጋ ማለት ነው።

🌺«ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ»

🌺«ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡» ( ኢሳ 7፥14)

❤️ክብር ፣ኃይልና ምስጋና ለአምካችን ለአማኑኤል ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
💚ወስብሓት ለእግዚአብሔር
💛ወለወላዲቱ ድንግል
❤️ወለመስቀሉ ክብር አሜን
https://t.me/egeziabhern


✞ምስጉን ነው✞

ምስጉን ነው የተመሰገነ
ባሪያውን እኔን ይቅር ያለ
ይመስገን ይመስገንልኝ
ጎጆዬን አምላክ ሞላልኝ

እጅህ ሰፊ እንደሆነ አውቃለሁ ጌታዬ
የጎደለው ሞልቷል ይድረስ ምስጋናዬ
ያጣሁትን ካንተ አግኝቻለሁ
ሁሉን ነገር ለበጎ ብያለሁ(፪)
አዝ= = = = =
ማቄን የቀደደው ደስታ አስታጠቀኝ
ባዶ የነበርኩኝ ደስታ ተሰጠኝ
ሰጪም ነሺም እግዚአብሔር ብቻ ነው
የሰው ድርሻ በር ማንኳኳት ነው(፪)
አዝ= = = = =
እገፋለሁ እንጂ እኔ አልጨነቅም
መሠረቴ አንተ ነህ ከቶ አልናወጥም
ስትሰጠኝ የሚታየውን
እንዳትነሳኝ የዘላለሙን(፪)
አዝ= = = = =
ቢሰጥ አያልቅበት ለጋስ ክቡር ጌታ
ሁሉን ከወነልኝ በልዩ ችሮታ
ድሆች ስንሆን ሁሉ አለንና
አማላካችን ይድረሰው ምስጋና(፪)


Репост из: እግዚአብሔርን አመስግኑ
#የወደደኝ_ጌታ

የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው
ብዘምርለትም ያንስበታል ይኽው
ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝኸኝ
ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ

በኢያሪኮ መንገድ ስለምን ቁጭ ብዬ
ብርሃን እጅግ ናፍቆኝ ከሰው ተገልዬ
የብርሃን ጌታ ወደ እኔ መጣና
ዓይኔን አበራልኝ በእጁ ዳሰሰና
#አዝ
ለብዙ ዘመናት አልጋ ላይ ተኝቼ
የሚረዳኝ አጣሁ ጠሉኝ ዘመዶቼ
የእኔ ጌታ አምላኬ ወደእኔ መጣና
አልጋህን ተሸከም አለኝ ፈወሰና
#አዝ
አሥራ ሁለት ዓመት ደም እየፈሰሰኝ
ምራቅ እየተፉ ሁሉም ሲያንቋሽሹኝ
የጌታዬ ልብሱን ጫፉን ብዳስሰው
ኃይል ከእርሱ ወጣ ደሜን ቀጥ አረገው
#አዝ
ሰካራም ዘማዊ ወንበዴ ነበርኩኝ
ያመፀኞች መሪ ደምን ያፈሰስኩኝ
ዛሬ ግን ታሪኬን ጌታ ቀይሮታል
ለኃያሉ ጌታ ምስጋና ይገባል

https://t.me/egeziabhern


አሜን አሜን አሜን 😍


❤#እንኳን_ለቸሩ_መድኃኔዓለም_መታሰቢያ
#አደረሰን_አደረሳችሁ
💖ቸሩ መድኃኔዓለም በምህረቱ ይመልከተን🙏


🌹🙏የእኔ መድኃኔዓለም🙏🌹

🌹አንተን ይዤ ሽንፈትን አላውቀውም ድሌ ነህና🙏
🌹ውድቀትን አላውቀውም ሀይሌ ጉልበቴ ነህና🙏
🌹ሞትን አላውቀውም ሕይወቴ ነህና🙏
🌹ሕመሜን አላስታውሰውም ፈውሴ ነህና🙏
🌹ሐዘኔን አላውቀውም ሐሴቴ ነህና🙏
🌹ብቸኝነትን አላውቀውም ፅኑ ወዳጄ ነህና🙏
🌹ጉድለትን አላውቀውም ሙላቴ ነህና🙏

❤️የእኔ መድኃኔዓለም አንተ እድል ፋንታዬ ነህ ዘመንና ጊዜ ወረት የማይቀይርህ የሰው ልጆች ሁሉ ፅኑ ወዳጅ🌹🌹🌹


Репост из: ፈላስፋዋ ድመት 😊
❤️የጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርልን
🌿💚💛❤️🌿💚💛❤️🌿💚💛❤️🌿


✞አቡነ ሐብተማርያም✞

ጽኑ ቃልኪዳን ነው ለሱ የተሰጠው
አቡነ ሐብተማርያም ለጽድቅ የመነነው
ክብሩ ታላቅ ነው ጸጋው ልዩ ነው

የጸሎቱ ዕጣን ድውዩን አድኗል
የታወረው በርቶ ሽባውን ተርትሯል
/ዛሬም ለአለማችን ጽኑ መዳኛ ነው
አባ ሐብተማርያም ኪዳኑ ልዩ ነው/(፪)
አዝ= = = = =
ረሃብ ቸነፈር ምድር ላይ ቢበዛ
የማዕጠንቱ ጸሎት ፈውሱን አበዛ
/በውስጥም በውጭም በጥላው ላላሉቱ
ዛሬም መድኃኒት ነው አቡነ እምነቱ/(፪)
አዝ= = = = =
ለሚያምን ይቻላል ተብሎ እንደተጻፈ
በሐብተማርያም ጸሎት ጽኑ ሞት አለፈ
/ከድቅድቅ ጨለማ መውጣት ከአማራችሁ
ሐብተማርያም በሉ ትፈወሳላችሁ/(፪)
አዝ= = = = =
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በስራዋ ብዙ ፈውስን ትሰጣለች
/ይደርብን በእኛ የቅዱሳን ጸጋ
ምልጃ ጥባቄአቸው እንዲሆን ከእኛጋ/

መዝሙር
ብርሃኑ ተረፈ

"የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
ያዕ፭፥፲፮


ቸሩ መድሀኒአለም ስሙ የተመሰገን ይሁን🤲
እንዴት አመሻችሁ🙏🙏🙏


🙏ሠላም የተዋሕዶ ልጆች🙏

❤️እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሠላም አደረሳችሁ🙏


❤️የክርስቶስ መሆን ክርስቲያን መሆንኮ መታደል ነው።
በቃላት የማይገለፅ ደስታ። ክርስቲያናዊነት ውበት ነው። የማይደበዝዝ ውበት! የድንግል ማርያም ልጅ የክርስቶስ እንደ መሆን ኦርቶዶክስ እንደ መሆን ምን ልዩ ደስታ ሊኖር ይችላል። ።ክርስቲያን ያደረገን አምላክ ይመስገን።
ውበታችን እምነታችን ነው
የትም ተወለድ በተዋሕዶ ቤት እደግ♥️

ሠናይ ሰንበት ❤️❤️❤️
━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


❤️እንኳን ለታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ
ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሠላም አደረሳችሁ🙏
የቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት በረከቱ ይደርብን፤ጸሎቱ ይጠብቀን፤ለመንግሥተ ሰማይ መሪ በትር ይሁነን🤲🤲
🙏💚💛❤️🙏💚💛❤️🙏💚💛❤️🙏
https://t.me/egeziabhern


1⃣እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ የተባሉት ምን ምን ናቸው? ከሦስቱ የትኛው ይበልጣል? ምዕራፍና ቁጥሩስ?




#ተክለሃይማኖት

ተክለሃይማኖት ተክለ አብ
ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
አባታችን አማልደን አስታርቀን
ከፈጣሪ ጋር አምላካችን

በሦስት ቀን ሥላሴን ያመሰገንክ
ከጭንጫ ድንጋይ ውኃ ያፈለቅክ
አባታችን ተክለ ሃይማኖት አማልደን
በኃጢአት እንዳንሞት
አኸ… አባታችን ተክለ ሃይማኖት አማልደን
በኃጢአት እንዳንሞት
#አዝ
እንደ መላእክት ክንፍ የተሰጠህ
ሰማዕት ነቢይ አንድም ካህን ነህ
መምህራችን ሃዲስ ሐዋርያ
አስተምረን የፍቅር ባለሞያ
አኸ… መምህራችን ሃዲስ ሐዋርያ
አስተምረን የፍቅር ባለሞያ
#አዝ
እንደ ሱራፌል በሰማይ ሲያጥን
በምድርም ነቢይ ሆኖ ማገልገሉን
በተሰጠው ፀጋ ሲያስነሳ ሙታን
ክህነትህ ካንተ ዘንድ ናት
አባታችን ፍታን ከኃጢአት
አኸ… ክህነት ካንተ ዘንድ ናት
አባታችን ፍታን ከኃጢአት


❤️ሠላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች 🙏

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን
የፃድቁ ተክለ ሃይማኖት በረከታቸዉ
ጥበቃቸዉ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏🙏


Репост из: ፈላስፋዋ ድመት 😊
❤️ቅዱስ ጊዮርጊስ: ሆይ ፡ ፈጥነህ ድረስልን አማልደን የመከራን ልክ ታውቃለ ህና ከመከራ ሰውረን “ከወርቅና ከብር ይልቅ ሞገሱ የሚበልጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረሱ እኛን ለመርዳት ይምጣ፤ ይመላለስም

♱ስብሐተ ፍቁር ዘጊዮርጊስ♱
━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


Репост из: ፈላስፋዋ ድመት 😊
"ፍቅር ማነው⁉

❤ሼር ሳታድርጉ አትለፍ💝
...................
እስኪ አንድ ታሪክ ልንገራችሁ።
አንድ የዋህ አባት ባንድ ሀገር ይኖሩ ነበር። የዋህነታቸውን የተመለከቱ አስራ ሶስት ሽፍቶች ጩቤ፤ሳንጃ፣ጎራዴ በልብሳቸው ውስጥ ደብቀው የኛን የዋህ ሰው ቤት አንኳኩ።
እኛም የዋህ አባት የዘመኑ አብረሃም ይባሉ ነበርና እንግዶቹን በደስታ ተቀብለው ወደ ቤት አስገቧቸው። እንግዶቹን ሲቆጥሯቸው አስራ ሶስት ናቸው ውይ ጌታ ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር ወደ ቤቴ መጣልኝ ብለው ደስ አላቸው።
ከዚያም ጌታ የቱ ነው፤ ጴጥሮስ የቱ ነው፤ ዮሐንስ የቱ ነው እያሉ መጠየቅ ጀመሩና እግራቸውን አጥበው፤ ምግብ አቅርበው፤ በታላቅ ፍቅር አስተናገዷቸው። ሽፍቶቹ ይህን ሁሉ ደግነት አዩና ልባቸው እራራ ሊገድሏቸው መተው በፍቅራቸው ተማረኩ፤በእግራቸው ሰር ተንበረከኩ፤ ሀያላን ጉልበተኛ ቢሆንም በፍቅር ተሸነፈ። በሽፍትነት የዋኙባትን ይችን አለም ንቀው በቅድስና ህይወት መኖር ጀመሩ።

"ፍቅር ማነው"?

#ፍቅር ሀያል ነው ጉልበተኛውን ያንበረክካል።
#ፍቅር ጉልበተኛ ነው ትዕቢተኛውን ትሁት ያደርጋል።
#ፍቅር ጠቢበኛ ነው በጥላቻ አይኑ የታወረውን ያበራልና።
#ፍቅር ታጋሽ ነው እልኸኛውን ያረጋጋል።
#ፍቅር ታጋሽ ነው የበደለን ያጽናናል።
#ፍቅር ጥበበኛ ነው ተሳዳቢው ይምራል።
#ፍቅር መካሪ ነው ስሜታውዩን ይገስጻል።
#ፍቅር እሩህሩህ ነው የካደውን ደግሞ ይወዳል።
#ፍቅር ጤና ነው የህሊና ሰላም ይሰጣል።
#ፍቅር ቸር ነው የበደሉትን አይበድልም።
#ፍቅር እርግብ ነው ቂም አይዝም።
#ፍቅር መልካም ነው አይመቀኝም።
#ፍቅር የተረጋጋ ነው በቶሎ አይቆጣም።
#ፍቅር የዋህ ነው በደልን አይቆጥርም።

"ታዲያ ፍቅር ማነው"!!!
ፍቅርማ! እንደ እረጅም ፈትል ከዙፋኑ የወረደው፤ዝቅ ዝቅ ብሎ የፈጠረውን የፍጡሩን እግር ያጠበው ነው።
ፍቅርማ! እንደሚታረዱ በጎች አንገቱን ለሸላቾች የሰጠው ነው።
ፍቅርማ! በመስቀል ላይ እጁን የዘረጋው የድንግል ማርያም ልጅ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ፍቅርማ! መራራ ሀሞት እየጠጣ ጣፋጭ ደሙን የሰጠን አምላካችን ክርስቶስ ነው።
ፍቅርማ! ወደ ድቅድቅ ጨለማ ወርዶ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ያወጣን አምላካችን ነው።
በእውነት ክርስቶስ ፍቅር ነው!!!

እግዚአብሔር ። ፍቅር አብዝቶ ይስጠን።

Показано 20 последних публикаций.

189

подписчиков
Статистика канала