የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ።
ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በተረጋጋ ሁኔታ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናዎችን ይወስዱ ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ይወጣ!
በያዝነው ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ኩረጃን እና የፈተና ስርቆትን ለመከላከል መንግሥት የወሰደውን እርምጃ በአድናቆት ይመለከተዋል።
ኩረጃና የፈተና ስርቆት የታታሪ ተማሪዎችን ድካም ዋጋ የሚያሳጣ እኩይ ድርጊት ከመሆኑም ባሻገር ለሀገራችን እድገት እንቅፋት ነው ብሎ አብን ያምናል። ስለሆነም የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱን ለማዘመን የሚደረጉ ጥረቶች አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጎን ለጎን ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።
ይሁን እንጂ በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች የታዩት ክስተቶች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን አሳስበውታል። ትላንት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አሳዛኝ ድንገተኛ አደጋ የፈጠረው መረበሽ ሳይበቃ ዛሬ በደብረታቦርና ደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ የተፈጠረው አለመረጋጋት መፈጠር ያልነበረበት ነው በለን እናምናለን:: በምንም ሁኔታ ውስጥም ቢሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል። ፈተናን ሳይፈተኑ አቋርጦ መውጣት የታዳጊ ተማሪዎችን የነገ ተስፋ የሚያጨልም በመሆኑ መታረም ይኖርበታል።
የሚመለከታችሁ የተፈታኝ ተማሪ ወላጆች፣ መምህራን፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተፈታኞች በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆነው ፈተናዎችን እንዲሰሩ የሚጠበቅባችሁን እንድትወጡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።
በዚህ አጋጣሚ አንቂዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች የተፈታኝ ተማሪዎችን ስሜት የሚረብሹ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ እንድትቆጠቡ አብን ጥሪውን ያስተላልፋል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
አዲስ አበባ፣
ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.
@Addis_News