Репост из: የሠለፍዮች የግጥም ብቻofficial channel
✒️ ነቃ => በል 📖
ነቃ በል ወንድሜ ይብቃህ ማንቀላፋት
ራስክ አዘጋጅ ዲንህ ለመረዳት
እምነትህ ለማወቅ አውቀህም ለመስራት
ራስክን ጠይቅ ነፍስያክ ፈትሻት
ያለችበትን ሀል ትንገርክ መርምራት።
ለትልቅ አላማ ነው የተፈጠርከው
ጌታህን አውቀኸው እንድትገዛው ነው
ምንም ሳታጋራ እጅ እግር ልትሰጥ ነው
ካላወከው እወቅ ካወቅክ ግን መስራት ነው።
በዚህ መልኩ ከሄድክ አለክ ትልቅ ፀጋ
አምፀክ ከሄድክ ግን ፍራ ልብህ ይስጋ
ስለ ሚጠብቅክ ማትችለው አደጋ ።
ዛሬ አይሸንግልክ የዱንያ ውበት
ሞልቶ ላይሞላልክ መቼም ላትረካበት
ቢሞላልክ እንኳ ላትሰነብትበት
ቢያምር ቢጣፍጥ ተወው አትስጠው ትኩረት።
አይቀርም መሄድክ ጥለከው ለሌላ
አንተ አፈር ሆነክ ቁጭ ብሎ ሊበላ።
እወቀው ዱንያ ውለታ አያቅም
ለሱ ብለክ ብትሞትም ዞር ብሎ አያይም
ከውለታ ቢስ ጋ አትልፋ አትድከም።
ባይሆን ግን ንቃበት አትታለልለት
ቢሳካ ባይሳካም አትጨነቅለት
ሚጠቅምክን ይዘክ ቀሪውን ተውለት
ያገኘከው ይብቃክ ተጠቃቀምበት
አስቀምጠው በቦታው እንዳትቆጥብበት
ያለ ቦታም አውለክ እንዳይመጣ ብክነት
ነገም በአኼራ እንዳትቆጭበት።
https://t.me/joinchat/WPo67AKOkKlXgCd1
ነቃ በል ወንድሜ ይብቃህ ማንቀላፋት
ራስክ አዘጋጅ ዲንህ ለመረዳት
እምነትህ ለማወቅ አውቀህም ለመስራት
ራስክን ጠይቅ ነፍስያክ ፈትሻት
ያለችበትን ሀል ትንገርክ መርምራት።
ለትልቅ አላማ ነው የተፈጠርከው
ጌታህን አውቀኸው እንድትገዛው ነው
ምንም ሳታጋራ እጅ እግር ልትሰጥ ነው
ካላወከው እወቅ ካወቅክ ግን መስራት ነው።
በዚህ መልኩ ከሄድክ አለክ ትልቅ ፀጋ
አምፀክ ከሄድክ ግን ፍራ ልብህ ይስጋ
ስለ ሚጠብቅክ ማትችለው አደጋ ።
ዛሬ አይሸንግልክ የዱንያ ውበት
ሞልቶ ላይሞላልክ መቼም ላትረካበት
ቢሞላልክ እንኳ ላትሰነብትበት
ቢያምር ቢጣፍጥ ተወው አትስጠው ትኩረት።
አይቀርም መሄድክ ጥለከው ለሌላ
አንተ አፈር ሆነክ ቁጭ ብሎ ሊበላ።
እወቀው ዱንያ ውለታ አያቅም
ለሱ ብለክ ብትሞትም ዞር ብሎ አያይም
ከውለታ ቢስ ጋ አትልፋ አትድከም።
ባይሆን ግን ንቃበት አትታለልለት
ቢሳካ ባይሳካም አትጨነቅለት
ሚጠቅምክን ይዘክ ቀሪውን ተውለት
ያገኘከው ይብቃክ ተጠቃቀምበት
አስቀምጠው በቦታው እንዳትቆጥብበት
ያለ ቦታም አውለክ እንዳይመጣ ብክነት
ነገም በአኼራ እንዳትቆጭበት።
https://t.me/joinchat/WPo67AKOkKlXgCd1