የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ ማሽን አዲስ ቤት ገንብቶ ዛሬ አስመርቋል። የትኛውም ህንጻ ሰማይ ጠቀስ ቢሆን፡ በውብ ዲዛይን ቢሰራ፡ ቴክኖሎጂ ያፈራው መሳሪያ ቢገጠምለት ትርጉም የሚኖረው በሚያመርተው የሚዲያ ውጤቶች የህዝብ ድምጽ መሆኑን ሲያረጋግጥ ነው። የአምባገነኖች ስክሪን ሴቨር ለመሆንና ዲስኩራቸውን ለማንደቅደቅ ይህ ሁሉ ህንጻና ማሽን አስፈላጊ አይደለም። ሰላም በሌለበት ሀገር የሚገነባ ህንጻ ምሽግ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ጠ/ሚሩ ደግሞ ትርክታችንን የምናሳልጥበት ተቋም እናደርገዋለን ብለዋል። ትርክታቸው ምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። ኢቢሲ የዚህ ትርክት መፈልፈያ ማሽን እንደሚሆን ይጠበቃል። የባለስልጣናትን የቀን ውሎ ለመተንተን ይህ ሁሉ ህንጻ አያስፈልግም። በሀሳብ ድርቅ የተመታን ተቋም በአብረቅራቂ፡ ዘመናዊ ህንጻ ቢያሽሞነሙኑት፡እርባና ቢስ እቃን በውድ መጠቅለያ ከመሸፈን ያለፈ ትርጉም የለውም።
https://t.me/mesaymekonnenet
https://t.me/mesaymekonnenet