Mesay Mekonnen/መሳይ መኮንን


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ኢትዮጵያ ለዘላልም ትኑር🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የአብይ ሰራዊት በተለያዩ አከባቢዎች የአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት ከፍቷል። ሰላማዊ ዜጎችን እየገደለ ነው። ይህኛው ዙር ጥቃቱ መጠነ ሰፊ ነው። ቁጥር ስፍር የሌለው ጦርና ከባድ መሳሪያ አስገብቷል። ይፋዊ ጦርነት እያካሄደ ነው። የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቅ መደረግ አለበት። ይህ ግልፅ ጦርነት ነው። የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብም ምን እየተደረገ እንዳለ ማወቅና ከአማራው ጎን መቆም ይገባዋል። አደገኛ የታሪክ እጥፋት ላይ ነን። አብይ በህግ ማስከበር ስም የእማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ በዝምታ እየጨፈጨፈ ነው። ዓለም ይወቀው!!

መልዕክቴን ሼር በማድረግ ተባበሩኛ🙏
የቴሌግራም ቻናሉንም ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/mesaymekonnenet
https://t.me/mesaymekonnenet


ግራ የሚገባ ነገር እኮ ነው። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሀገር እያመሰ፡ ከተማ እያተራመሰ፡ እየዘረፈና እየገደለ የጋራ ግብረሃይል የሚባለው ቡድን ትንፋሹም አይሰማም። 500ኪሎሜትር በርቀት በሰፈሩ በሰላም የተቀመጠውን ፋኖ ካላጠፋሁ ብሎ ሰራዊት ያዘመታል። እንዴት ያለ ጥልቅ አደጋ ውስጥ ነን ጎበዝ? ድንዛዜው እጅግ ያስፈራል። ምን ዓይነት አዚም፡ መተት በሉት የጥንቆላ ትብታብ በተለይ መሀል ሀገርን እንዲህ ያደነዘዘው ምንድን ነው?

መንግስት ሁለት ጃኬት አለው። አንዱ የቤተመንግስቱ ጃኬት ነው። ሁለተኛውን ያጠልቅና ''ሸኔ'' በሚል የብዕር ስም ሀገር ያተራምሳል። አዲስ አበባ አፍንጫ ስር የማፊያ ተግባር ያከናውናል። ኮሽ አለ ብሎ የመግለጫ ጋጋታ፡ የማስፈራርያ ክምር የሚቆልለው የጋራ ግብረሃይል የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ግስጋሴን 'የእኛው ልጆች ናቸው' በሚል ሂሳብ ጉዳዬም አላላቸውም። እነዚህኞቹ ባለአንደኛው ጃኬቶች ህገመንግስት የሚንዱ አይደሉም። ህገመንግስታዊ ስርዓቱን የሚገለብጡም አይደሉም። የቤት ልጅ ናቸው። የስለት ልጅ። እንዳሻቸው ይፈንጩ። ይዝረፉ። ህዝብ ያስለቅሱ። የሚገድሉትን ሰዎች 'ህጋዊ ሟቾች'' የሚል ስም ለጥፎላቸው መግለጫ የሚሰጥ ሌላኛውን ጃኬት ያጠለቀ የመንግስት ባለስልጣን ይመጣል።

ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። በወንበዴ፡ ወረበላ፡ ዘረኛ፡ዘራፊ፡ ቀጣፊ፡ መንደርተኛ፡ አቅመ ቢስ፡ ደካማ፡ ልፍስፍስ፡ ጠባብ ቡድን እጅ ላይ ወደቃለች። ሸኔ እየገደለ እየዘረፈ ይሸለማል። ፋኖ ሀገር እያዳነ ይታደናል። ፋኖ የእንጀራ ልጅ ነውና። ዓለም ቲያትር ናት ያለው ማን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ አሰቃቂና ዘግናኝ ትራጄዲ ሆናለች።

https://t.me/mesaymekonnenet


''በዚህ ሁሉ መዓት፡ ሚሊዮኖች ተፈናቅለው፡ ሚሊዮኖች ተርበው፡ ግሽበት ሀገሪቱን እግሯን እያሽመደመደ፡ በየቦታው ግጭትና ዘረፋ በርክቶ አንድ መሪ ቤተመንግስት ልገንባ ካለ ይህ ጥልቅ የሆነ የስነአእምሮ ህመም ነው። ይህ ሰው በጣም ታሟል። '' ከሰሞኑ የአንከር እንግዳ ሆነው የሚቀርቡ የስነልቦና ባለሙያ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደ ነው። ወዳጄ ጋዜጠኛ ዘሪሁን ተስፋዬ ስለሰውዬው ሲገልጽ የኡጋንዳውን ሰው በላ መሪ ያስታወሳል። ኤዲያሚን ዳዳ ድንገት የክብር ጠባቂ ጦሩን ይጠራና ታንክ ይዞ ካምፓላ አጠገብ የሚገኝ ተራራ ላይ ይወጣል። ከዚያም ሚዲያዎቹን ጠርቶ 'የጎላን ኮረብታን ተቆጣጥረናል' ሲል ዜና ያስነግራል። አብይ ማለት ኤዲያሚን ዳዳን ቁርጥ ነው። የደቀቀችና የረሃብ ጉንፋን የምታስል ሀገር አናት ላይ ጉብ ብሎ፥ ፓርላማውን ጠርቶ 'ብልጽግናን ጨብጠናል' የሚል ወፈፌ!

https://t.me/mesaymekonnenet


የአገዛዙ የፕሮፖጋንዳ ማሽን አዲስ ቤት ገንብቶ ዛሬ አስመርቋል። የትኛውም ህንጻ ሰማይ ጠቀስ ቢሆን፡ በውብ ዲዛይን ቢሰራ፡ ቴክኖሎጂ ያፈራው መሳሪያ ቢገጠምለት ትርጉም የሚኖረው በሚያመርተው የሚዲያ ውጤቶች የህዝብ ድምጽ መሆኑን ሲያረጋግጥ ነው። የአምባገነኖች ስክሪን ሴቨር ለመሆንና ዲስኩራቸውን ለማንደቅደቅ ይህ ሁሉ ህንጻና ማሽን አስፈላጊ አይደለም። ሰላም በሌለበት ሀገር የሚገነባ ህንጻ ምሽግ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው። ጠ/ሚሩ ደግሞ ትርክታችንን የምናሳልጥበት ተቋም እናደርገዋለን ብለዋል። ትርክታቸው ምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። ኢቢሲ የዚህ ትርክት መፈልፈያ ማሽን እንደሚሆን ይጠበቃል። የባለስልጣናትን የቀን ውሎ ለመተንተን ይህ ሁሉ ህንጻ አያስፈልግም። በሀሳብ ድርቅ የተመታን ተቋም በአብረቅራቂ፡ ዘመናዊ ህንጻ ቢያሽሞነሙኑት፡እርባና ቢስ እቃን በውድ መጠቅለያ ከመሸፈን ያለፈ ትርጉም የለውም።

https://t.me/mesaymekonnenet


በመጨረሻም አባቶቹ እግዚያብሄርን ትተው ፖለቲከኞቹን ተከተሏቸው። የፈጣሪ ቃል ተሸሮ የባለስልጣን ትዕዛዝ ተፈጻሚ ሆነ። የኦነጉ የፖለቲካ ኦፌሰር ኮ/ል ገመቹ አያና ሰሞኑን በ50ኛ ዓመት በዓላቸው ላይ ቤተክርስቲያን ፈርሳለች አሉ በግልጽ። የዛሬውን ውሳኔ ቀድመው አውቀውት የተናገሩት ይሆን? እነ አቡነ ጴጥሮስና አቡነ አብረሃም ምን መግለጫ ሊሰጡ ይመጣሉ? በጉጉት የሚጠበቅ ነው። የዛሬው ውሳኔ በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እጅግ አሳፋሪ ነው። የቤተክርስቲያኒቱንም አንድነት የሚያናጋ ነው።

https://t.me/mesaymekonnenet

Показано 5 последних публикаций.

2

подписчиков
Статистика канала