ለመረዳት አዳምጥ!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
አልተግባባችሁም፣ መሃከላችሁ ልዩነት አለ፣ የማያስማማችሁ ነገር አለ። ነገር ግን በጉዳዩ መስማማት ባትችሉም፣ ወደ አንድ መምጣት ቢሳናችሁ እንኳን ባለመስማማት መስማማት እንደሚቻል መረዳት ተገቢ ነው። ለሁሉም ማዳመጥ፣ ከልብ ሆኖ መስማት የተሻለ ነው። ማንም ሰሚ በሌለበት፣ አዳማጭ በሌለበት ቦታ ቢያወራ ከድካም ውጪ ትርፍ አይኖረው። የምትሰማውም ለመልስ ሳይሆን ለመረዳት ነው፤ ጉዳዩን ለማወቅ ነው፤ ከልብ ለመገንዘብ ነው። ለምላሽ ማዳመጥ ልዩነቱን ከማስፋት ውጪ የሚያተርፈው ነገር አይኖርም። ተናግሮ ለማናገር፣ ተንኩሶ ነገሩን ለማባባስ ሳይሆን በእርግጥም ፈልጎ ልዩነትን ለማጥበብ ተናገር። ምላሽህ ምንም ሊሆን ይችላል፤ ጉዳዩ ላይመችህና ላያስማማህ ይችላል፣ ከተናጋሪው ላይ ቁርሾ ሊኖርብህ ይችላል ነገር ግን ከሁሉም በፊት ማዳመጥ ይቀድማልና ከልብህ አዳምጥ።
አዎ! ጀግናዬ..! መልስ ለመስጠት፣ ለመቃወም፣ ለማጣጣል፣ ለማንቋሸሽ ሳይሆን ለመረዳት አዳምጥ፤ ለመገንዘብ፣ ለማወቅ ስማ። ማንም የፈለገውን ሊያወራ ይችላል፤ እንደፈለገው ሊያወራ ይችላል፤ አለመስማማትም መብትህ ነው። ማንም በተመቸው መንገድ ሊጓዝ ይችላል አለመውደደና አለመቀበልም መብትህ ነው፤ ነገር ግን ማንም ሲያወራ መልስ ከመስጠትህ በፊት ከልብህ አዳምጥ፤ መጥፎ ስም ከመስጠት ይልቅ በበጎ ለመረዳት ሞክር። ያልተመቸህን እንደተመቸህ ሳይሆን አለመመቸቱንም ቢሆን በጭፍን ጥላቻ ሳይሆን ስረዓትና አግባብ ባለው መልክ ግለፅ። አንተ ያልከው ብቻ ልክ አይደለም፤ ሌሎችም የሚናገሩት ብቻም ልክ አይደለም።
አዎ! እንድትስማማ፣ እንድትረዳ፣ ሙሉ በሙሉ እንድትቀበል የሚያስገድድህ አካል የለም። ሁሌም ልትቀበል የምትችለው ከእራስህ አረዳድ፣ እውቀትና ግንዛቤ አንፃር ነው። ያንተ ምቾት ሌላውን የሚጎረብጥበት ሁኔታ ይኖራል፤ የሌላው ምቾትና ከፍታም አንተ ትክክል በምትለው መንገድ የመጣ ስላልሆነ ላይመችህ ይችላል። ለማዳመጥ ግን ምቾት ወይም ተናጋሪውን መውደድ አይጠበቅብህም። እውነታውን ለመረዳት ማዳመጥ ባትችል እንኳን ባለመስማማት ለመስማማትም ማዳመጥ ግድ ይልሃል። ምላሽህን አቆይተህ፣ ለመረዳት ብቻ የምታዳምጥ ከሆነ ክፍተቶችህን በስምምነት፣ ጭፍን ጥላቻህንም ወደጎን በመተው በማዳመጥና ትኩረት በመስጠት የትኛውንም ግንኙነትህን ማስተካከል እንደምትችል እወቅ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪