ራሳችሁን ውቀሱ!
፨፨፨////////፨፨፨
ምን አሰራችሁ? ምን ወደኋላ አስቀራችሁ? ምንስ አቅማችሁን እንዳታወጡ አደረጋችሁ? ሲበዛ ሌላውን ወቃሽ ናችሁ፤ በህይወታችሁ ለተፈጠረው የትኛውም ነገር ሰዎች ላይ ጣታችሁን ትቀስራላችሁ፣ ጥፋታችሁን አምኖ የመቀበል ችግር አለባችሁ። ማንም ወደ ህይወታችሁ ገብቶ የፈለገውን አድርጎ እንዲወጣ በራችሁን ከፍታችሁ ካስገባችሁ ቦሃላ፣ ክብራችሁን አሳልፋችሁ ከሰጣችሁት ቦሃላ፣ ለራሳችሁ ምንም ሳትጠነቀቁ ሁሉ ነገራችሁን ካጋራችሁት ቦሃላ ጥሏችሁ ሲሔድ እርሱን ለመውቀስና ለመኮነን ትፈልጋላችሁ። ነገር ግን በቅድሚያ መወቅስና መኮነን ያለባችሁ እናንተ ናችሁ። ቦሃላ ምን ሊመጣ እንደሚችል ሳታውቁ ያለምንም ጥንቃቄና ዝግጅት ሰውን ወደ ህይወታችሁ አስገባችሁ፣ ከዛም መሰጠት የሌለበትን ነገር አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፣ በእናንተ ላይ እንዲያዝና እንደ ፈለገው እንዲነዳችሁ ፈቀዳችሁለት። "ወደ ህይወታችሁ ካልገባው ሞቼ እገኛለሁ" አላላችሁም፤ "ከእናንተ ጋር ካልሰራው እከስራለሁ" አላላችሁም፤ "ያለ እናንተ መኖር አልችልም" አላላችሁም፤ "ክብራችሁን ካልነካው የእኔ ክብር አይጨምርም" አላላችሁም። እያንዳንዱ ያደረጋችሁት ነገር በፍቃዳችሁ ነው።
አዎ! ራሳችሁን ውቀሱ! ለደረሰባችሁ በደል፣ ላጣችሁት ነገር፣ ለኪሳራችሁ፣ ለስህተታችሁ፣ ለውድቀታችሁ ሰዎችን መውቀስ አቁሙ። ድክመትና ስንፍናችሁን ሰዎችን በመውቀስ ለመሸፈን አትሞክሩ። ምንም ነገር በህይወታችሁ ይከሰት ዘንድ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የእናንተ ፍቃድ ወይም ይሁንታ እንደሆነ አስተውሉ። በራችሁን ከዘጋችሁ ማንም በሩን ሰብሮ አይገባም። ወቀሳችሁ ምን እንዳሳጣችሁ አስታውሱ። በገዛ ፍቃዳችሁ ተከናውኖ ለሚመጣው ውጤት ሁሌም ሌላውን አካል እየወቀሳችሁ ከሆነ መቼም ከተመሳሳይ አዙሪት ልትወጡ አትችሉም። ብዙዎች ሌላውን መውቀስ እነርሱን ነፃ የሚያወጣ ይመስላቸዋል፣ ብዙዎች ለገዛ ህይወታቸው መበላሸት ሌሎችን ተጠያቂ ማድረግ የእነርሱን ጥፋት የሚሸፍን ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ሰዎችን ወቀሱም አልወቀሱም፣ ሃላፊነቱን ሰዎች ላይ ጣሉም አልጣሉም ለሆነባቸው የትኛውም ነገር ግንባር ቀደም ተጠያቂዎቹ ራሳቸው መሆናቸው ነው።
አዎ! ጀግናዬ..! ላንተ ጥፋት ማን ሃላፊነት ሊወስድ የሚመጣ ይመስልሃል? ማን ላንተ ስህተት ሽንጡን ገትሮ የሚከራከር ይመስልሃል? ማን ላንተ ኪሳራ ተጠያቂ የሚሆን ይመስልሃል? ከራስህ በቀር ማንም ፊትለፊት ቆሞ የሚጋፈጥልህ ሰው የለም። ያገኘሀውን ሁሉ አብረሀው ስታጠፋ የነበረው ጓደኛህ፣ ከፍታኛ ድርሻን የሚጋራህ የስራ ባልደረባህ፣ ከዛም በላይ ከልብ የምትወዳቸው የሚወዱህ ቤተሰቦችህ፣ ፍቅረኛህ ወይም የትዳር አጋርህ በሙሉ ያንተን የግል ሸክም ሊሸከሙልህ አይችሉም። ህይወት የማንንም ሃላፊነት አሸጋሽጋ ለሌላው አትሰጥም። ከራስህ ጀምሮ ያንተ የሆነው ነገር በሙሉ ያንተ ሃላፊነት ነው። ሁሌም ሰዎችን ወይም ሌላውን አካል መውቀስ የደካሞች እንጂ የጠንካሮች መገለጫ አይደለም። ሰውን መውቀስህን በቀጠልክ ቁጥር የራስህን አቅምና ተነሳሽነት እየገደልከው ትመጣለህ። ሰበብ መደርደር፣ በሆነው ባልሆነው ራስን ከተጠያቂነት ለማንፃት መሞከር፣ ጥፋት በተከሰተ ቁጥር ሰዎች ላይ ጣትን መቀሰር እንዴትም ሊጠቅምህ አይችልም። ለራስህ ህይወት ሃላፊነት ውሰድ፣ ሰውን ከመውቀስ በላይ ራስህን ውቀስ፣ ከተጠያቂነትም ራስህን አድን።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪